ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.59K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
አንተ የምትለውን ነገር ሰዎች ስላልተረዱህ
አንተ ትክክል አይደለህም ማለት አይደለም፤ ለምን ካልከኝ ያንተ እውነት እውነትነቱ ላንተ እንጂ ለሌሎች አይደለማ!!!
#
#ማንነት የህልውና ከፍተኛው የመገለጫ ደረጃ ነው ። #ማንነታችሁ ደግሞ በፍፁማዊ አርነት ካልተሞላ #የህልውናችሁ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የገባ ይሆናል ።

#ኦሾ
#ሜንሲየስ ፦ የቻይናው ፈላስፋ

አንድ ቀን ንጉስ ሱአን ወደ ቤተመንግስቱ አስጠራውና ጥያቄ አቀረበለት ፦ << ለሕዝቤ ጠቃሚ የምሆንበትን መንገድ አስተምረኝ ..>> አለው ።
#ሜንሲየስም ፦ "ጠቃሚ ከመሆን በፊት ሰብዓዊነትና ፅድቅን ተማር ። ንጉስ ሆይ !ለአገር የሚጠቅም ነገር እንድነግርህ የምትሻ ከሆነ ይህንን ስማ ....#ታላላቅ ባለስልጣኖችህ ለቤተሰቦቻቸው የሚጠቅም ነገር እንድታደርግላቸው ከጠየቁህ ....#ታናናሽ ባለስልጣኖችና ህዝብህ ደግሞ ለራሳቸው የሚጠቅም ነገር እንድታደርግላቸው ከጠየቁህ ...ያን ጊዜ #የአገርህ_መውደቅያ እየተቃረበ መሆኑን ተረዳ "አለው ። ታላቁ ፈላስፋ ሜንሲየስ

ምንጭ ጥበብ ከጲላጦስ
"የሆነ ሰውን ለመሆን መጣር እራስህን የምታባክንበት መንገድ እንጂ የምታገኝበት አይሆንም!!

ኦሾ/Osho
"ጥሩ ሰው ከምትፈልግ አንተ እራስህ መጀመርያ ጥሩ ሰው ሆነህ ተገኝ!"
‹‹ዘመን እኮ ንፋስ ወይንም በፊኛ የተሞላ አየር አይደለም፡፡ እያንዳንዱን ዘመን የምንፈጥረው እኛው ነን፡፡ ጀግና ከሆንን የታታሪነት ዘመን እንፈጥራለን፡፡ ነቀዞች ከሆንን የንቅዘት ዘመን እንፈጥራለን፡፡ የውሻ ዘመን ጩኸትና ጭራ መቁላት ይበዛበታል፡፡ የጅብ ዘመን ሆዳም ይበዛበታል፡፡ የአህያ ዘመን ሸክም ይበዛበታል፡፡ የድመት ዘመን ቡጭሪያ ይበዛበታል፡፡ የጥንቸል ዘመን ፍርጠጣ ይበዛበታል፡፡ የጦጣ ዘመን ብልጠት ይበዛበታል፡፡ ዘመኑ ምን አደረገን?! እያንዳንዱን ዘመን የምንፈጥረው እኛው ራሳችን ነን፡፡ ውስጣችንን መፈተሽ ሲያቅተን፣ ራሳችንን መግዛት ሲሳነን፣ ፀባያችንን ማረቅ ሲያስቸግረን በዘመን እናላክካለን፡፡ ዘመንን እናማርራለን፡፡››

➦ሲሳይ ንጉሱ
➦ረቂቅ አሻራ
".በአንድ ልብ ውስጥ ፍቅር እና ጥላቻ በጋራ ሊኖሩ አይችሉም። እነዚህ ሁለት ነገሮች እንደ ሞትና ህይወት ተቃራኒዎች ናቸው። በአንድ ልብ ውስጥ በጋራ ሊኖሩ አይቻላቸውም። ታዲያ "ፍቅር" ብለን የምንጠራው ነገር ምንድነው?"

"አነስተኛ ጥላቻ በውስጣችን ሲኖር "ፍቅር" እንለዋለን፤ መጠኑ ከፍ ያለ ጥላቻን ደግሞ "ጥላቻ" ብለን እንጠረዋለን። ሁለቱም አነስተኛና ከፍተኛ የጥላቻ መጠኖች ናቸው። በዚህ ሁነት ውስጥ ባለ ልብ ውስጥ ፍቅር ከነጭራሹ የለም። ስህተቱ የሚፈጠረው በጥላቻው መጠኖች ሳቢያ ነው። ከመጠን ጋር በተያያዘ ቅዝቃዜና ሙቀት ሁለት የተለያዩ ነገሮች እንደሆኑ ታስቡ ይሆናል። ሁለት የተለያዩ ነገሮች አይደሉም። ሙቀትና ቅዝቃዜ የአንድን ነገር ደረጃዎች የሚያሳዩ ናቸው። የሙቀት መጠን ሲያንስ ቅዝቃዜ መሰማት ይጀምራል። የሙቀት መጠን ሲበዛ ደግሞ ሙቀት መሰማት ይጀምራል......"

".....ከኢጎ በመነጨ ፍቅር ከተፈቀራችሁ ከትንሽ ጊዜያት በኋላ በአፍቃሪ እጆች እንደታቀፋችሁ ሳይሆን በብረት ሰንሰለት እንደተጠፈራችሁ ይሰማችኋል። ከትንሽ ጊዜያት በኋላ ውብ ንግግሮችን ሲናገር፣ ውብ ዘፈኖችን ሲዘፍንላችሁ የነበረው ፍቅር፣ በውብ ዘፈኖቹና ንግግሮቹ ውስጥ መርዝ ደብቆ እንደነበር ታውቃላችሁ። የአበቦችን መልክ ተላብሶ የሚመጣው ፍቅር ምንጩ ኢጎ ከሆነ አበቦችን በዳሰሳችሁ ጊዜ እጆቻችሁን የሚወጉ እሾሆችን ታገኛላችሁ......"
ኦሾOsho
#አውሮፓውያን አፍሪካን እንደ ቅርጫ ለመከፋፈል ሲቧደኑ ምስኪኗ ጣልያን የሞት ምድብ ነበር የደረሳት!!
#ኢትዮጵያ
#ዓድዋ ታላቅ ታሪካዊ ቀን!!
ጅማሪው መጀመር ያለበት ፍጹም ርግጠኛ በመሆን ሳይሆን ለመማር /ለመለወጥ/ ሙሉ በሙሉ ፍላጎት በመያዝ ነው። ስለራሳችሁ ለማወቅና የሕይወትን ምስጢራት ለመረዳት ከልባችሁ ቆርጣችሁ ከተነሳችሁ ይበቃል።"
OSHO/ኦሾ
#ህይወት ሁሌም ጥሬ ገንዘብ ነች። ህይወት ቃል ኪዳናዊ የገንዘብ ኖት አይደለችም። ህይወት ቃል አትገባላችሁም። ህይወት ወዲያዊ ነች። ህይወት እዚህ እና አሁን ነች።
#ኦሾ/Osho
#ሱፊዝም
" ራሱን የሚያፈቅር ሠው ወደ እውነተኛው ፍቅር ለመድረስ የመጀመሪያውን እርምጃ ተራምዷል፡፡ "
ኦሾ/Osho
"ፍቅር እያንዳንዱ ግለሰብ ይዞት የሚወለድው ውድ ሃብት ነው"

Osho/ኦሾ
አንድ ሰው የቅናት ስሜት እየተሰማው ነው ማለት በሌላ ቋንቋ እራሱን ወይንም ሌላ ነገሩን ከሌላ የሆነ አካል ጋር እያወዳደረ ነው ማለት ነው!!#
ኦሾ
#ብሩህ ነገ የሚባል ቀን የለም ። ማንም ቢሆን ነገን ኖሮ የሚያውቅ የለም ። ምክንያቱም ነገን ለመኖር ስንጀምር ዛሬ ተብሏል ። ብዙዎቻችን ግን ሁሌም ብሩህ ነገን ለመኖር ስንናፍቅ ብዙ ዛሬያችን ያልፈናል ። እናም ብሩህ የሚባል ቀን ሳይኖረን እናልፋለን ። ብሩህ ቀን በእጃችን ያለው ዛሬ ነው ። "
#ጠበኛ እውነቶች
"ተራ ፍቅር በፍላጎት የተሞላ ነው ፣ እውነተኛ ፍቅር ማጋራት ነው ሙሌቱ ፡፡ ፍላጎት ላይ የተንተራሰ ሳይሆን የመስጠት ደስታን ብቻ ያውቃል!!
*
#ኦሾ/osho
#እኔ ማንንም ከእኔ የበታች፣ማንንም ከእኔ የበላይ አድርጌ አስቤ አላዉቅም። ለነገሩ ማንንም ዝቅ አድርገህ የማታይ ከሆነ ማንንም ከፍ አድርገህ አታይም።ሁሉም ሰዉ ልዩ ነዉ አይወዳደርም ።
እኔ እኔ ነኝ -አንተ አንተ ነህ።
ኦሾ/osho/
‹ የተፈጥሮ የመገንዘብ አቅም ካልታከለበት የአዋቂነትት መሠረት በመማር ብቻ አይመሰረትም፡፡ ብዙ ተምረው ምንም የማያውቁ ልሂቃን አሉና ››
#ይስማዕከ ወርቁ
#ደህንነቱ
"ባለው የማይረካ የሚመኘውን ቢያገኝም አይረካም!!
ህይወት ማጥፊያ በሌለው እርሳስ የሚሳል ስዕል ነው።/ጆን ጋርድነር/
ማንም እኩል አይደለም።
ይህ ነው ስነ- ልቦናዊ እውነታው።
በአካልም በአዕምሮም ፣ በዕውቀትም በተሰጥዖም ከማንም ጋር እኩል አይደላችሁም - ማንም ከማንም ጋር እኩል አይደለም። ሁሉም ሰው ልዩ ነው!!
*
#ኦሾ/Osho
"ብቸኝነት ሌላ ሰውን የምታጡበት ሁኔታ ሲሆን፣
ለብቻ መሆን ግን ራሳችሁን የምታገኙበት ሁኔታ ነው!"
:
ኦሾ/Osho