ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.59K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
"የምትማሩት ትምህርት እናንተን ካልቀረፀ የምታዶለዱሙት እንጂ የምትቀርፁት ነገር አይኖራቹህም።"
#ኦሾ
የሰው ልጅ ከሌሎች እንሰሳት በማሰቡ አይደለም የሚለየው፥ በማሰቡ ያው እንሰሳ ነው፥ የሚለየው በምግባር ነው፥ 'Moral' የሚባል ጉዳይ ነው ሰውን ከእንሰሳ የሚለየው፥ ይሄ መሠመር አለበት።
*
በማሰብ ቢሆን ኖሮሞ እነ አሜሪካና እንግሊዝ ወራሪዎች ባልሆኑ ነበር።
*
'Moral' (ምግባር፣ ስነ-ምግባር፣ ግብረ-ገብ) የሠው ልጅ ተፈጥሮ ነው። በሂደት ያመጣው አይደለም፥ ሲፈጠር ጀምሮ ጥሩና መጥፎውን ያውቀዋል።
ያለ ባህል የተፈጠረ ህዝብ የለም። ባህል ደግሞ የ'Moral' (ምግባር፣ ስነ-ምግባር፣ ግብረ-ገብ) መስታወት ነው። እያንዳንዱ ባህል ጥሩና መጥፎ የሚልበት ሚዛን አለው።
*** *=* ***
ጸሐፊ መሐመድ አሊ/ቡርሃን አዲስ/
ተጓዡ ሰፊውን እና ሃሩሩን በረሃ እያቋረጠ ነበር ድንገት አንድ ትልቅ ዛፍ አጋጠመው እና እረፍት ለማድረግ ከዛፋ ስር ተቀመጠ ። ያለ እረፍት ረጅም ጉዞ ሲጓዝ ስለ ነበር የረሃብ ስሜት ተሰማው "ምናለ የሆነ የሚበላ ነገር ባገኝ" ብሎም አሰበ ዙሪያውን ሲያማትርም የሆነ ሳጥን ይመለከታል ሄዶ ሲከፍተውም ምግብ ሆኖ ያገኘውና እስኪጠግብ ይበላል።
ተመልሶ ዛፋ ስርም ይቀመጣል ሆድ ሲሞላ ጉሮሮ የሚጎነጭ ነገር ይጠይቃል እና አሁንም ይህ ቸጓዥ የሚጠጣ ነገር ቢገኝ ብሎ ተመኘ። አፍታም አልቆየም ከጎኑ ጠርሙስ ሙሉ ጣፋጭ ወይን ከጎኑ ተቀምጦ ይመለከታል እስኪበቃውም ይጎነጫል,,,,ሰው በሙሉ አእምሮው ማሰብ የሚጀምረው ረሃቡን ካስታገሰ ጥማቱን ካረካ በሃላ ነውና ተጓዡ የሆነውን ሁሉ መልሶ ሲያስበው ግራ መጋባት ይጀምራል "ምግብ ባገኝ ብዬ ተመኘሁ ምግብ በአቅራቢያዬም አገኘሁ ስለ ሚጠጣም ነገር ተመኘሁ ከጎኔም ጣፋጭ ወይንም አገኘሁ የተመኘሁትን ነገር በሙሉ በአንዴ ያገኘሁት ምናልባት ይህ አካባቢ የመናፍስት መኖሪያ ቢሆን ነዉ" ብሎ ገመተ ጥቂት እንደቆየም ብዙ መናፍስት ወደ እሱ እየበረሩ ሲመጡ ተመለከተ በፍርሀት እና በድንጋጤም ሆኖ " በቃ ዛሬ መሞቴ ነው ስጋዬን ቦጫጭቀው ሊገሉኝ ነው" ብሎ በተስፋ መቁረጥ ደመደመ መናፍስቶቹም ቦጫጭቀው ገደሉት።
ይህ ሁሉ ሲሆን ይህ ምስኪን ተጓዥ ያልተረዳው ነገር ቢኖር የተቀመጠበት ዛፍ ያሰቡትን እና የተመኙትን እንደወረደ የሚፈፅም መሆኑን ነበር ....ልብህ ደም እየረጨ መሆኑን ብትረሳ ችግር የለውም ልብህ ስራውን አያቆምም እያሰብክ መሆኑን ከረሳህ ግን ዋጋ ያስከፍላል ምክንያቱም እያንዳንዱ ሀሳብህ እና ምኞትህ እጣ ፋንታህን የመወሰን አቅም አለውና።
ምንጭ፡ ከዜን አስተምህሮት መፅሀፍ ተተርጉሞ የቀረበተጓዡ ሰፊውን እና ሃሩሩን በረሃ እያቋረጠ ነበር ድንገት አንድ ትልቅ ዛፍ አጋጠመው እና እረፍት ለማድረግ ከዛፋ ስር ተቀመጠ ። ያለ እረፍት ረጅም ጉዞ ሲጓዝ ስለ ነበር የረሃብ ስሜት ተሰማው "ምናለ የሆነ የሚበላ ነገር ባገኝ" ብሎም አሰበ ዙሪያውን ሲያማትርም የሆነ ሳጥን ይመለከታል ሄዶ ሲከፍተውም ምግብ ሆኖ ያገኘውና እስኪጠግብ ይበላል።
ተመልሶ ዛፋ ስርም ይቀመጣል ሆድ ሲሞላ ጉሮሮ የሚጎነጭ ነገር ይጠይቃል እና አሁንም ይህ ቸጓዥ የሚጠጣ ነገር ቢገኝ ብሎ ተመኘ። አፍታም አልቆየም ከጎኑ ጠርሙስ ሙሉ ጣፋጭ ወይን ከጎኑ ተቀምጦ ይመለከታል እስኪበቃውም ይጎነጫል,,,,ሰው በሙሉ አእምሮው ማሰብ የሚጀምረው ረሃቡን ካስታገሰ ጥማቱን ካረካ በሃላ ነውና ተጓዡ የሆነውን ሁሉ መልሶ ሲያስበው ግራ መጋባት ይጀምራል "ምግብ ባገኝ ብዬ ተመኘሁ ምግብ በአቅራቢያዬም አገኘሁ ስለ ሚጠጣም ነገር ተመኘሁ ከጎኔም ጣፋጭ ወይንም አገኘሁ የተመኘሁትን ነገር በሙሉ በአንዴ ያገኘሁት ምናልባት ይህ አካባቢ የመናፍስት መኖሪያ ቢሆን ነዉ" ብሎ ገመተ ጥቂት እንደቆየም ብዙ መናፍስት ወደ እሱ እየበረሩ ሲመጡ ተመለከተ በፍርሀት እና በድንጋጤም ሆኖ " በቃ ዛሬ መሞቴ ነው ስጋዬን ቦጫጭቀው ሊገሉኝ ነው" ብሎ በተስፋ መቁረጥ ደመደመ መናፍስቶቹም ቦጫጭቀው ገደሉት።
ይህ ሁሉ ሲሆን ይህ ምስኪን ተጓዥ ያልተረዳው ነገር ቢኖር የተቀመጠበት ዛፍ ያሰቡትን እና የተመኙትን እንደወረደ የሚፈፅም መሆኑን ነበር ....ልብህ ደም እየረጨ መሆኑን ብትረሳ ችግር የለውም ልብህ ስራውን አያቆምም እያሰብክ መሆኑን ከረሳህ ግን ዋጋ ያስከፍላል ምክንያቱም እያንዳንዱ ሀሳብህ እና ምኞትህ እጣ ፋንታህን የመወሰን አቅም አለውና።
ምንጭ፡ ከዜን አስተምህሮት መፅሀፍ ተተርጉሞ የቀረበ
በአንድ ሀገር ውስጥ በጣም የታዋቀ አንድ ዐዋቂ ሰው ነበረ አሉ።ያንን ሀገር የሚገዛም ደግሞ በጣም ክፉ ንጉሥ ነበር አሉ።ህዝብ ወደዚህ አዋቂ ዘንድ ይሄድና ፤ "እባክህ እንደው ከፈጣሪ አማልደህ ይኼንን ክፉ ንጉሥ አስወግድልን" አሉት።
"ለምን ?"ብሎ ሲጠይቃቸው።
"በቃ አንፈልገውም ይወገድልን"አሉት።ዐዋቂም እሺ አለ።ክፉ ንጉሥም ተወገደ።ሌላ ንጉሥም መጣ።የመጣው ንጉሥም ደግሞ የባሰ ሆነ።ለውጡ ከጅራፍ ወደ ጊንጥ ሆነ።ሕዝብ አዲስ የመጣውን ንጉሥ ትንሽ ጊዜ ካየው በኃላ ወደ ዐዋቂው ዘንድ ሄዶ "ይኸንንም ንጉሥ አስወግድልን አለ።
ለውጡ ከጊንጥ ወደ እፍኝት ሆነ።ሁለተኛውም እንዲወገድ ሆኖ ሌላ ንጉሥ መጣ። ሦስተኛ የመጣው ንጉሥም ከመጀመርያው ከሁለኛውም ንጉሦች የባሰ ሆነ። ወዲያው ሕዝብ ዝም አለ።ንጉሡ ቢያደምጥ ዐዋቂው ቢያደምጥ፣ምንም ድምጽ ጠፉ።ሕዝቡ ዝም አለ። ወደ ንጉሡ የሚሄድ የለም ወደ ዐዋቂው የሚሄድ የለም።በዚህ ጊዜ ንጉሡ ወደ ዐዋቂው ዘንድ መልዕክተኛ ላከ። ወደ አንተ ጋ ሕዝብ መጥቶ ያውቃል?"
አዋቂው "አልመጣም ሲል መለሰ።
"ንጉሡ ዕድሜው ይርዘም ብሎስ ያውቃል?"
"አያውቅም"
ዕድሜው ይጠርስ ብሎ ያውቃል?"
"አያውቅም"
አሁን አደጋ ላይ ነን ፤አሁን ነው ህዝብን ማድመጥ"አለ ይባላል ንጉሡ።
፦"እናም ሕዝብ ዐውቆ ዝም ሲል ዝምታውን ማድመጥ ያሰፈልጋል ዝምታው ሌላ ወጀብ ይዞ ሳይነሳ።"
:
*ብቻዬን እቆማለሁ እና ሌሎች
@ዳንኤል ክብረት ጥር /2012ዓ.ም/
የተመዘዘ
አንተ የምትለውን ነገር ሰዎች ስላልተረዱህ
አንተ ትክክል አይደለህም ማለት አይደለም፤ ለምን ካልከኝ ያንተ እውነት እውነትነቱ ላንተ እንጂ ለሌሎች አይደለማ!!!
#
#ማንነት የህልውና ከፍተኛው የመገለጫ ደረጃ ነው ። #ማንነታችሁ ደግሞ በፍፁማዊ አርነት ካልተሞላ #የህልውናችሁ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የገባ ይሆናል ።

#ኦሾ
#ሜንሲየስ ፦ የቻይናው ፈላስፋ

አንድ ቀን ንጉስ ሱአን ወደ ቤተመንግስቱ አስጠራውና ጥያቄ አቀረበለት ፦ << ለሕዝቤ ጠቃሚ የምሆንበትን መንገድ አስተምረኝ ..>> አለው ።
#ሜንሲየስም ፦ "ጠቃሚ ከመሆን በፊት ሰብዓዊነትና ፅድቅን ተማር ። ንጉስ ሆይ !ለአገር የሚጠቅም ነገር እንድነግርህ የምትሻ ከሆነ ይህንን ስማ ....#ታላላቅ ባለስልጣኖችህ ለቤተሰቦቻቸው የሚጠቅም ነገር እንድታደርግላቸው ከጠየቁህ ....#ታናናሽ ባለስልጣኖችና ህዝብህ ደግሞ ለራሳቸው የሚጠቅም ነገር እንድታደርግላቸው ከጠየቁህ ...ያን ጊዜ #የአገርህ_መውደቅያ እየተቃረበ መሆኑን ተረዳ "አለው ። ታላቁ ፈላስፋ ሜንሲየስ

ምንጭ ጥበብ ከጲላጦስ
"የሆነ ሰውን ለመሆን መጣር እራስህን የምታባክንበት መንገድ እንጂ የምታገኝበት አይሆንም!!

ኦሾ/Osho
"ጥሩ ሰው ከምትፈልግ አንተ እራስህ መጀመርያ ጥሩ ሰው ሆነህ ተገኝ!"
‹‹ዘመን እኮ ንፋስ ወይንም በፊኛ የተሞላ አየር አይደለም፡፡ እያንዳንዱን ዘመን የምንፈጥረው እኛው ነን፡፡ ጀግና ከሆንን የታታሪነት ዘመን እንፈጥራለን፡፡ ነቀዞች ከሆንን የንቅዘት ዘመን እንፈጥራለን፡፡ የውሻ ዘመን ጩኸትና ጭራ መቁላት ይበዛበታል፡፡ የጅብ ዘመን ሆዳም ይበዛበታል፡፡ የአህያ ዘመን ሸክም ይበዛበታል፡፡ የድመት ዘመን ቡጭሪያ ይበዛበታል፡፡ የጥንቸል ዘመን ፍርጠጣ ይበዛበታል፡፡ የጦጣ ዘመን ብልጠት ይበዛበታል፡፡ ዘመኑ ምን አደረገን?! እያንዳንዱን ዘመን የምንፈጥረው እኛው ራሳችን ነን፡፡ ውስጣችንን መፈተሽ ሲያቅተን፣ ራሳችንን መግዛት ሲሳነን፣ ፀባያችንን ማረቅ ሲያስቸግረን በዘመን እናላክካለን፡፡ ዘመንን እናማርራለን፡፡››

➦ሲሳይ ንጉሱ
➦ረቂቅ አሻራ
".በአንድ ልብ ውስጥ ፍቅር እና ጥላቻ በጋራ ሊኖሩ አይችሉም። እነዚህ ሁለት ነገሮች እንደ ሞትና ህይወት ተቃራኒዎች ናቸው። በአንድ ልብ ውስጥ በጋራ ሊኖሩ አይቻላቸውም። ታዲያ "ፍቅር" ብለን የምንጠራው ነገር ምንድነው?"

"አነስተኛ ጥላቻ በውስጣችን ሲኖር "ፍቅር" እንለዋለን፤ መጠኑ ከፍ ያለ ጥላቻን ደግሞ "ጥላቻ" ብለን እንጠረዋለን። ሁለቱም አነስተኛና ከፍተኛ የጥላቻ መጠኖች ናቸው። በዚህ ሁነት ውስጥ ባለ ልብ ውስጥ ፍቅር ከነጭራሹ የለም። ስህተቱ የሚፈጠረው በጥላቻው መጠኖች ሳቢያ ነው። ከመጠን ጋር በተያያዘ ቅዝቃዜና ሙቀት ሁለት የተለያዩ ነገሮች እንደሆኑ ታስቡ ይሆናል። ሁለት የተለያዩ ነገሮች አይደሉም። ሙቀትና ቅዝቃዜ የአንድን ነገር ደረጃዎች የሚያሳዩ ናቸው። የሙቀት መጠን ሲያንስ ቅዝቃዜ መሰማት ይጀምራል። የሙቀት መጠን ሲበዛ ደግሞ ሙቀት መሰማት ይጀምራል......"

".....ከኢጎ በመነጨ ፍቅር ከተፈቀራችሁ ከትንሽ ጊዜያት በኋላ በአፍቃሪ እጆች እንደታቀፋችሁ ሳይሆን በብረት ሰንሰለት እንደተጠፈራችሁ ይሰማችኋል። ከትንሽ ጊዜያት በኋላ ውብ ንግግሮችን ሲናገር፣ ውብ ዘፈኖችን ሲዘፍንላችሁ የነበረው ፍቅር፣ በውብ ዘፈኖቹና ንግግሮቹ ውስጥ መርዝ ደብቆ እንደነበር ታውቃላችሁ። የአበቦችን መልክ ተላብሶ የሚመጣው ፍቅር ምንጩ ኢጎ ከሆነ አበቦችን በዳሰሳችሁ ጊዜ እጆቻችሁን የሚወጉ እሾሆችን ታገኛላችሁ......"
ኦሾOsho
#አውሮፓውያን አፍሪካን እንደ ቅርጫ ለመከፋፈል ሲቧደኑ ምስኪኗ ጣልያን የሞት ምድብ ነበር የደረሳት!!
#ኢትዮጵያ
#ዓድዋ ታላቅ ታሪካዊ ቀን!!
ጅማሪው መጀመር ያለበት ፍጹም ርግጠኛ በመሆን ሳይሆን ለመማር /ለመለወጥ/ ሙሉ በሙሉ ፍላጎት በመያዝ ነው። ስለራሳችሁ ለማወቅና የሕይወትን ምስጢራት ለመረዳት ከልባችሁ ቆርጣችሁ ከተነሳችሁ ይበቃል።"
OSHO/ኦሾ
#ህይወት ሁሌም ጥሬ ገንዘብ ነች። ህይወት ቃል ኪዳናዊ የገንዘብ ኖት አይደለችም። ህይወት ቃል አትገባላችሁም። ህይወት ወዲያዊ ነች። ህይወት እዚህ እና አሁን ነች።
#ኦሾ/Osho
#ሱፊዝም
" ራሱን የሚያፈቅር ሠው ወደ እውነተኛው ፍቅር ለመድረስ የመጀመሪያውን እርምጃ ተራምዷል፡፡ "
ኦሾ/Osho
"ፍቅር እያንዳንዱ ግለሰብ ይዞት የሚወለድው ውድ ሃብት ነው"

Osho/ኦሾ
አንድ ሰው የቅናት ስሜት እየተሰማው ነው ማለት በሌላ ቋንቋ እራሱን ወይንም ሌላ ነገሩን ከሌላ የሆነ አካል ጋር እያወዳደረ ነው ማለት ነው!!#
ኦሾ
#ብሩህ ነገ የሚባል ቀን የለም ። ማንም ቢሆን ነገን ኖሮ የሚያውቅ የለም ። ምክንያቱም ነገን ለመኖር ስንጀምር ዛሬ ተብሏል ። ብዙዎቻችን ግን ሁሌም ብሩህ ነገን ለመኖር ስንናፍቅ ብዙ ዛሬያችን ያልፈናል ። እናም ብሩህ የሚባል ቀን ሳይኖረን እናልፋለን ። ብሩህ ቀን በእጃችን ያለው ዛሬ ነው ። "
#ጠበኛ እውነቶች
"ተራ ፍቅር በፍላጎት የተሞላ ነው ፣ እውነተኛ ፍቅር ማጋራት ነው ሙሌቱ ፡፡ ፍላጎት ላይ የተንተራሰ ሳይሆን የመስጠት ደስታን ብቻ ያውቃል!!
*
#ኦሾ/osho
#እኔ ማንንም ከእኔ የበታች፣ማንንም ከእኔ የበላይ አድርጌ አስቤ አላዉቅም። ለነገሩ ማንንም ዝቅ አድርገህ የማታይ ከሆነ ማንንም ከፍ አድርገህ አታይም።ሁሉም ሰዉ ልዩ ነዉ አይወዳደርም ።
እኔ እኔ ነኝ -አንተ አንተ ነህ።
ኦሾ/osho/
‹ የተፈጥሮ የመገንዘብ አቅም ካልታከለበት የአዋቂነትት መሠረት በመማር ብቻ አይመሰረትም፡፡ ብዙ ተምረው ምንም የማያውቁ ልሂቃን አሉና ››
#ይስማዕከ ወርቁ
#ደህንነቱ