ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.59K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
የሌለህን ነገር ብቻ ካሰብክ ያለህንም ታጣዋለህ፡፡ ያለህን ነገር ካሰብክ ግን የሌለህንም ታገኘዋለህ፡፡
#ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)
ሰውዬው በሚስቱ ሞያ ይማረራል፡፡ ገና ወደ ቤቱ ለመምጣት ሲያስብ የሚበላው እንጀራና ወጥ ትዝ ሲለው ሐሞቱ ፍስስ ይላል፡፡ «እንግዲህ ለዚያ ሊጥ ልሂድለት» ብሎ ይመጣል፡፡ ይህ ነገር ሰለቸውና ከሚስቱ ጋር ተፋታ፡፡ ወደ ጓደኛውም ቤት ሄደ፡፡ ጓደኛው አልጋ አንጥፎ ተቀበለው፡፡
ማታ ራት ቀረበ፡፡ ምን የመሰለ ነጭ ጤፍ ላይ አልጫና ቀዩ ተጋድሞ ቀረበለት፡፡ በአንድ በኩል ቃሪያው፣ በአንድ በኩል ስልጆው፣ በአንድ በኩል ፍትፍቱ፣ በአንድ በኩል አተር ክኩ ተሰለፈ፡፡ «ወይ ሞያ እኔማ ኖርኩ አይባልምኮ» እያለ ያማርር ጀመር፡፡ «አንተማ ታድለህ» ይለዋል ጓደኛውን፡፡ «ይሁን እስኪ» ይላል ያኛውም፡፡ ጠላው ሲቀርብ ደግሞ እያደነቀ ጠጣ፡፡ «ከኖሩ ላይቀር እንዲህ ነው» ይል ጀመር፡፡ ያችንም ባለሞያ ሚስት በምስጋናና በአድናቆት አረሰረሳት፡፡

በልተው ሊያጠናቅቁ ሲሉ ጋባዡ ሊጠጣበት ያነሣው ብርጭቆ ተሰበረ፡፡ ደነገጠ፡፡ ሚስት ከጓዳ መጣች፡፡ «ምንድን ነው የተሰበረው?» አለች፡፡

«ያ የምትወጅው ብርጭቆ ተሰበረ፡፡» አላት ባልዋ በተስለመለመ ድምፅ፡፡ ተናደደችና አንዴ በጥፊ አላሰችው፡፡ ጓደኛው ደነገጠ፡፡ «እንዲህ ሰብረህ ሰብረህ የአባት የናቴን ስጦታ ጨረስከው፡፡ አንተ ምን ታደርግ ተንቀባርረህ ከነ ጓደኛህ ትልፋለህ» እያለች ቁም ስቅሉን ታሳየው ጀመር፡፡ ባልዬው ጠባይዋን ያውቃልና ዝም አለ፡፡ ያም ጓደኛው «ምን ለብርጭቆ ደግሞ ነገ ይገዛል፤ ዋናው ጤና ነው» አለ ነገር ያበረደ መስሎት፡፡ «አንተ ደግሞ አርፈህ ተቀመጥ፤ ሚስትህን እንደዚህ አማረሃት ይሆናል ይኼኔ፤ ቀላዋጭ» አለችና አቀመሰችው፡፡ ተፈታተነው ስሜቱ፡፡ ግን እንግድነቱ በልጦበት «ኧረ የኔዋስ እንዳንቺ» አለና ጀምሮ ተወው፡፡ ወደ ጓዳ ገባችና አንድ ፍልጥ ይዛ መጣች፡፡ እስኪ ጨርሰው አለቺው፡፡ ዓይኑ ተቁለጨለጨ፡፡ «እንዳንቺ የባሰባት አይደለችም» ሲላት ፍልጡን ይዛ መጣች፡፡

ይህንን ሲያይ ባልዬው «ቀስ ብለህ አምልጥ» አለው፡፡
በዚያ ሌሊት እየገሠገሠ የሚስቱ እናት ጋ ሄደ፡፡

እናቲቱም «ምነው ልጄ» አሉት
«እማማ፤ ከሌሊት ፍልጥ፣ የቀን ሊጥ ይሻለኛል ብዬ መጣሁ፡፡ አላቸው ይባላል፡፡
ወዳጄ ያለህን ካላሰብከው የባሰው ላይ ትወድቃለህ ያልኩ ለዚህ ነው፡፡
እስኪ ወዳጄ ያለህን ዕወቀው፤ አክብረው፤ አሟጠህ በሚገባ ተጠቀምበት፤ በዚያ ኑርበት፤ አጊጥበት፡፡ ከዚያ ሌላውን ለመያዝ ፈልግ፡፡ ባለህ የማትረካ ከሆንክ ግን ሩጫህ የተሻለ ነገር ፍለጋ ሳይሆን ሌላ ነገር ፍለጋ ብቻ ይሆናል፡፡
:
#ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)
የስብሃት ለአብ ትውስታዎች!!
* * *
"ሠይጣን ወደ ኢትዮጵያ ቢመጣ ስራ የለውም ምክንያቱም የሰው ልጅ እሱ የሚሰራውን ሥራ ቀድሞ ሠርቶ ጨርሶቷል።ምን ሊሰራ ይመጣል?"የሚል ሀሳብ ያዘለ ጽሑፍ ጋዜጣ ላይ ጻፍኩ።
ታድያ ጹሑፉን ያነበቡ ጓደኞቼ...
"ጋሽ ስብሐት ህዝቡ በፅሑፉ ቅር ተሰኝቷል÷ የሰው ልጅ ለመልካም ሥራ እንዲነሳሳ በተቃራኒው ብትጽፈውስ?" አሉኝ።
በሳምንቱ...
"መልዓክ ወደ ወደ ኢትዮጵያ ቢመጣ ቦታ የለውም÷ ምክንያቱም የሰው ልጅ የሱን ተግባር ቀድሞ ሠርቶ ጨርሶቷል።ምን ሊሰራ ይመጣል?"
በማለት ጻፍኩ::
ነገር ግን ይሄ የባሰ የቁጣ ማዕበል አስነሳ!"
ሲል ፅፏል፡፡
* * *
#እንዲህ ነን እኛ!!
አንድ ሀብታም ሰው ዘመናዊ መኪናውን አቁሞ ለጉዳዩ ገባ ይላል ጉዳዩን ጨርሶ ወደ መኪናው ሲመለስ የአንዱ ጎማው 4 ብሎኖች ተፈተው ተወስዶበት ያያል፡፡ ይህኔ ይበሳጭ እና አከባቢው ላይ ዞር ዞር ብሎ ብሎን ፈልጎ ያጣል፡፡
ያኔ መኪናውን ተደግፎ በጭንቀት ቆዝሞ ሳለ አከባቢው ላይ ያለ አንድ እብድ ነገሩን ተከታትሎ ኖራልና "ምን ሆነህ ነው?" ይለዋል፡፡ሰውየውም በንቀት አይን አየት እያደረገው "የጎማዬ ብሎኖች ተፈተው ተወስዶብኝ ነው እንዳልገዛ አከባቢው ላይ የለም" ይለዋል በብስጭት ስሜት ውስጥ ሆኖ፡፡
ይህኔ እብዱ "ነው እንዴ? ታዲያ ለምን ከ3 ጎማዎች አንድ አንድ ብሎን ፈተህ አራተኛውን ጎማ አታስርም" አለው፡፡
ሰውየውም በመገረም ሀሳቡ በጣም አስደሰተውና አንዳለውም አደረገ፡፡
"ቆይ አንተ እብድ አይደለህ እንዴ! አንዴት ይህ ሀሳብ ሊመጣልህ ቻለ?" ብሎ ጠየቀው፡፡
እብዱም ቀበል አድርጎ "ታዲያ እኔ እብድ ነኝ እንጂ ደደብ አይደለሁም" ብሎ ይመልስለታል፡፡
"ዝቅ በል፤ ዝቅ ስትል ከፍ ትላለህ፤ ተናነስ፤ ራስህን አትቆልል፤ ሁሌም እኔ አዋቂነኝ አትበል"
"ዲ/ን ዳንኤል ክብረት"
ሁሉንም ልምዶች እቃወማለሁ!!!

እኔ ሁሉንም ልምዶች እቃወማለሁ። ጥሩና መጥፎ ብየ አልከፋፍላቸውም። ምክንያቱም ጥሩም ሆነ መጥፎ የሚባል ልምድ ስለሌኝ ነው። ልምዶች ሁሉ ጎጂ ናቸው። ምክንያቱም ልማድ ማለት አንድ ያለንቃት የምናደርገው ተደጋጋሚ የሆነ ነገር በህይወታችን ላይ እእጅግ ወሳኝና የበላይ ሆኖ እየተቆጣጠረን ሲመጣ የሚፈጠር ሁኔታ ማለት ነው። ያኔ አንተ በህይወትህ ላይ የበላይነትህ ያበቃለታል። ለነገሮች ያለህ ምላሽ ከንቃት የመነጨ ሳይሆን ካለፈው ግዜ ከተማርካቸው መዋቅራዊ ከሆኑ ተግባሮች ነው።

ኦሾ/osho
"ህፃናት ሕይወት በሰው ልጆች ተስፋ እንዳልቆረጠ የሚገልፁ ህያው ስጦታዎች ናቸው"
*
ካህሊል ጂብራን
ራሱን የሚያፈቅር ሠው ወደ እውነተኛው ፍቅር ለመድረስ የመጀመሪያውን እርምጃ ተራምዷል፡፡
.
ኦሾ
#መልካም ቅዳሜ

****
"በህሊና ዳኝነት ህይወቱን የሚመራ ሰው ታላቅና ንፁህ ነፍስ ያለው ሰው ነው''
******
/ምንዱባን/
"ለሕይወት የከበሬታ ስሜት ካልፈጠረ እና ክብር ካልሰጠ በስተቀረ ፣ ማንም የሰው ልጅ የህይወት መሠረታዊ መብትን የመጎናጸፍ አላማን አይረዳውም።"
Osho/ኦሾ
ብቸኛው ጊዜ አሁን ነው ! ብቸኛው ቦታ እዚህ
የእውነታን ሙሉዕነት የያዘው ይህ ይቅጽበት ነው!"
:
#ኦሾ/Osho
#ተጨልፎ ከማያልቀው ከኦሾ እይታዎች የተወሰነ ስለፍቅር ከተናገረው ወደናንተ እንበትን ዘንድ የተገባ ሆኖ አገኝነው

" ፍቅር ማለት በምትወደው ሰው ነፍስ ውስጥ ራስህን መግደል ነው። ፍቅር ማለት ሞት ነው ፤ የሚቻልህን ያህል ጥልቅ በሆነ ሞት ውስጥ ትገባለህ ፤ የምትሞተውም በምትወዳት ሴት ነፍስ ውስጥ ነው ። ዕለት ዕለት ወደ ጥልቅ የነፍሷም ቦታ ትወሰዳለህ ፤ ፍቅር ወደምታፈቅራት ሴት የነፍስ ቦታ የምታደርገው ዘላለማዊ ጉዞ ነው ። ጉዞውም ማቆሚያ የለውም ። አንዲትን ሴት ስታፈቅራት በአንተ ሕይወት ውስጥ ከአንተ በላይ ዋጋ አላት ። ፍቅር ማለት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መማረክ ማለት ነው ። ምክንያቱም አንዳች ቅድመ ሁኔታ የምታስቀምጥለት ከሆነ ከምታፈቅረው ሰው በላይ ለራስህ ዋጋ ሰጥተሃል ማለት ነው ። ራስህን ዋነኛው ጉዳይ አድርገህ በፍቅር ውስጥ ስትመለከት ተፈቃሪዋ መጠቀሚያህ ሆነች ፤ የፍላጎትህ ማርኪያ አደረግሃት፤ በሌሎች ዘንድ መደነቂያህ ሆነች...መነሻውም መድረሻውም አንተ ሆነሃል ።
#OSHO/ኦሾ/
#ከእለታት አንድ ቀን አንድ የፐርሺያ ንጉሥ ሁለት ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ ፈረደባቸው፡፡
በመጨረሻም፤ “የሞት ፍርዱ ከመፈፀሙ በፊት የፈለጋችሁትን ተናገሩ” ሲል እድል ይሰጣቸዋል፡፡
አንደኛው፤ “ምንም የምናገረው የለኝም” አለ ሁለተኛው፤
ንጉሡ ምን ያህል ፈረሳቸውን እንደሚወዱት ስለሚያውቅ፤“ንጉሥ ሆይ፤ የአንድ ዓመት ጊዜ ከሰጡኝ ፈረስዎ ወደ ሰማይ እየከነፈ እንዲሄድ ላስተምረው እችላለሁ” አላቸው፡፡ንጉሡ በሰማይ ላይ የሚከንፍ ፈረስ እየጋለቡ ሲሄዱ ታያቸው፡፡ ካሁኑ ነሸጣቸውና ይቁነጠነጡ ጀመር፡፡“ይሁን አንድ ዓመት ሰጥተንሃል፡፡ ፈረሱን አምጥተው እንዲያስረክቡህ አደርጋለሁ” አሉ፡፡
የመጀመሪያው እሥረኛ በምንም አይነት ፈረስ እንደማይበር ስለሚያውቅ ፈረስ አስተማሪውን እሥረኛ ጓደኛውን እንዲህ ሲል ጠየቀው፤“ወዳጄ፤ ፈረስ በሰማይ እንደማይበር አሳምረህ ታውቃለህ፡፡ እንዲህ ያለ የዕብድ ሀሳብ ከየት አምጥተህ ነው ቃል የገባኸው፡፡ የመሞቻችንን ጊዜ ከማራዘም በስተቀር ምን ይፈይድልሃል?”
ፈረስ አስተማሪውም፤“አይምሰልህ ወዳጄ፤ ነፃነቴን የማገኝባቸውን አራት ዕድሎች ራሴ መስጠቴ ነው”አለ
አንደኛው እሥረኛም፤
“አራቱ ዕድሎች ምን ምን ናቸው?” ሲል በመጓጓት ጠየቀው፡፡
ፈረስ አስተማሪው፤ እንዲህ ሲል ዘረዘረለት፡-
1ኛ ወይ በዚህ ዓመት ውስጥ ንጉሡ ሊሞቱ ይችላሉ
2ኛ እኔም ልሞት እችላለሁ
3ኛ ወይ ደሞ ፈረሱም ሊሞት ይችላል
4ኛ ደሞስ ማን ያውቃል እኔ ፈረሱ በሰማይ እንዲበር ላስተምረው እችል ይሆናል አለው ይባላል።
* * *
እና ምን ልልህ ፈልጌ መሰለህ በችግሮች ተሸንፈህ ቀድመህ እጅ አትስጥ ጣር ሞክር ልፋ ታገል በነገሮች ተስፋ አድርግ እንጂ ተስፋ አትጣ።ህይወት አንድ ሺህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ አንድ ሺህ ጊዜ ተስፋ የምታደርግባት የግብግብ መድረክ ናት።
"ተስፋ በሌለበት እንኳ ተስፍ አድርግ ያለው ጸሐፊው በምክንያት ነው።አይህ ወዳጄ ከመሰንበት መላ አይጠፋምና።
#መልካም ቀን ተመኘው
"ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ የተወሰዱ ምክሮችና እውነታዎች

#ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡

#በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መኾን ባትችል ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትኹን፡፡

#በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ኹሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡

#ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡

#ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡

#በሕይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡
.." አንድ ካሬ ሜትር መርካቶ ውስጥ 350 ሺ ብር ካወጣና አንድ ፕሮፌሰር አርባ አመት ደክሞ በወር የሚያገኛት የአንዲት ካሬ ሜትር ዋጋ የምትመዝን ካልሆነች ሰው ተፈጥሮን አላሸነፈውም ማለት ነው፣ ሰው ከተፈጥሮ አልበለጠም ማለት ነው። መሬት ተፈጥሯዊ ነች፣ ለምንድነው ትንሿ መሬት ይህቺን ያህል ስትወደድ ለምንድነው እኛ ይሄን ያህል አመት የተማርን ሰዎች ልንወደድ ያልቻልነው? ምክንያቱም በምንፈታው ችግር ልክ ነው እኛ ልንወደድ የምንችለው!! መሬቷ 30 ፎቅ ስለሚሰራባት 30 ፎቅ ልትከራይ ነው። የዚያች ቁራሽ መሬት ዋጋ ወደ ላይ 30 ፎቅ ሲያሰራ፣ እኛ ግን አንዲት ክፍል ውስጥ ገብተን ነው የምናስተምረው!!....የእኛ 30 እና 40 አመት የተማርንበት ዋጋ ግን ለብዙ ትውልድ መትረፍ አልቻለም። መብራት አልሰራም፣ አውሮፕላን አልሰራም፣ መርከብ አልሰራም፣ ባቡር አልሰራም። ሲንጋፖር ዕኮ መሬት የላትም! የምትሸጠው ዕኮ የአዕምሮዋን ውጤት ነው። የአዕምሮዋ ውጤት ደግሞ በአመት 540 ቢሊዮን ዶላር$ ኤክስፖርት ወደውጪ ይደረጋል። የእኛ የተፈጥሮ የሆነች ነገር ደግሞ 100 ሚሊየን ሕዝብ ይዘን የምታመጣልን 3 ቢሊየን ያልሞላ ኤክስፖርት እናደርጋለን። ሲንጋፖር 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ሕዝብ የያዘች ትንሽ ሀገር ናት። ስለዚህ አዕምሮ መስራት ካልቻለ የተፈጥሮ መሬት የበለጠ እየተወደደች ትሄዳለች። እናም መማር ችግር ፈቺነትን ካላሳደገ፣ አዕምሯችን የተሻለ ነገር መፍጠር ካልቻለ፣ መሬት ላይ ቤት ሰርቶ፣ አከራይቶ፣ ሽጦና ለውጦ የተፈጥሮን ነገር ብቻ ሙጥኝ ብሎ መገላበጡ ይቀጥላል።

ዶር ምህረት ደበበ
በአንድ ሀገር ውስጥ በጣም የታዋቀ አንድ ዐዋቂ ሰው ነበረ አሉ።ያንን ሀገር የሚገዛም ደግሞ በጣም ክፉ ንጉሥ ነበር አሉ።ህዝብ ወደዚህ አዋቂ ዘንድ ይሄድና ፤ "እባክህ እንደው ከፈጣሪ አማልደህ ይኼንን ክፉ ንጉሥ አስወግድልን" አሉት።
"ለምን ?"ብሎ ሲጠይቃቸው።
"በቃ አንፈልገውም ይወገድልን"አሉት።ዐዋቂም እሺ አለ።ክፉ ንጉሥም ተወገደ።ሌላ ንጉሥም መጣ።የመጣው ንጉሥም ደግሞ የባሰ ሆነ።ለውጡ ከጅራፍ ወደ ጊንጥ ሆነ።ሕዝብ አዲስ የመጣውን ንጉሥ ትንሽ ጊዜ ካየው በኃላ ወደ ዐዋቂው ዘንድ ሄዶ "ይኸንንም ንጉሥ አስወግድልን አለ።
ለውጡ ከጊንጥ ወደ እፍኝት ሆነ።ሁለተኛውም እንዲወገድ ሆኖ ሌላ ንጉሥ መጣ። ሦስተኛ የመጣው ንጉሥም ከመጀመርያው ከሁለኛውም ንጉሦች የባሰ ሆነ። ወዲያው ሕዝብ ዝም አለ።ንጉሡ ቢያደምጥ ዐዋቂው ቢያደምጥ፣ምንም ድምጽ ጠፉ።ሕዝቡ ዝም አለ። ወደ ንጉሡ የሚሄድ የለም ወደ ዐዋቂው የሚሄድ የለም።በዚህ ጊዜ ንጉሡ ወደ ዐዋቂው ዘንድ መልዕክተኛ ላከ። ወደ አንተ ጋ ሕዝብ መጥቶ ያውቃል?"
አዋቂው "አልመጣም ሲል መለሰ።
"ንጉሡ ዕድሜው ይርዘም ብሎስ ያውቃል?"
"አያውቅም"
ዕድሜው ይጠርስ ብሎ ያውቃል?"
"አያውቅም"
አሁን አደጋ ላይ ነን ፤አሁን ነው ህዝብን ማድመጥ"አለ ይባላል ንጉሡ።
፦"እናም ሕዝብ ዐውቆ ዝም ሲል ዝምታውን ማድመጥ ያሰፈልጋል ዝምታው ሌላ ወጀብ ይዞ ሳይነሳ።"
:
***ብቻዬን እቆማለው እና ሌሎች ****
@ዳንኤል ክብረት/2012ዓ.ም/
ገጽ 12-14 የተመዘዘ
የመገደድ ስሜት

ውስጥህ ካለማቋረጥ ይናገርሃል፡፡ ውስጥህን ማድመጥ ግን የአንተ ሃላፊነት ነው፡፡ ስህተት ስትሰራ ህሊናህ እንደሚናገርህና እንዲሁም ሲያምህ፣ ሲርብህና ሲጠማህ አካልህ እንደሚናገርህ ሁሉ ውስጥህ ከሚነግርህ በርካታ ጠቃሚ ነገሮች አንዱ በሰዎች የመገደድን ስሜትህን ነው፡፡

በሰዎች የመገደድን ስሜት ማድመጥ ማለት ከማንነታችን የሚያወጣንን የሰዎች ግፊት መለየት ማለት ነው፡፡ በአካባቢያችን የሚገኙ ሰዎች የማናምንበትን ነገር እንድናደርግ፣ የማንፈልገውን ውሳኔ እንድንወስንና ምቾት ወደማይሰማን የሕይወት ቀጠና ውስጥ እንድንገባ ካለማቋረጥ ግፊት ያደርጉብናል፡፡

አንዳንድ ሰዎች የሚጫኑንና የሚያስገድዱን ለእኛ መልካም የሰሩ እየመሰላቸው ሲሆን፣ ሌሎች ግን እኛን የመቆጣጠር ዝንባሌ ስላላቸው ነው፡፡ በዚህች አለም ላይ ስትኖር ራስህን ከአስገዳጅና ከተቆጣጣሪ ሰዎች ነጻ ማውጣት ከቻልክ የድሎችን ሁሉ ድሎች ተጎናጽፈሃል፡፡ ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜህን ካባከንክ በኋላ የባነንክባቸውን ሁኔታዎች መለስ ብለህ ብታጤናቸው በሰዎች ግፊት ምክንያት ካደረካቸው ወይም ከማድረግ ከተቆጠብክባቸው ሁኔታዎች ጋር ተዛምደው ታገኛቸዋለህ፡፡

ከዚህ ሁኔታ ለመዳን ከፈለክ፣ ምንም አሰብክ ምንም ሃሳቡ ከውስጥህ የወጣ ወይም ውስጥህ ያመነበት መሆን አለበት፡፡ ስለዚህም፣ በሰዎች ከመገደድ አዙሪት ነጻ ለመውጣት መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች አሉ፡፡

1. የሕይወት መመሪያ ይኑርህ
የሕይወትህን መመሪያ በመለየትና በማወቅ ያንን ማዳበርና በዚያ እውቀት መደላደል አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ ራስህን ካልመራህ የመጣው ሰውና ገጠመኝ ይመራሃል፡፡ ራስህን ስትመራ ግን ሁሉን የምትመዝን ትሆናለህ፡፡

2. ገደብህን እወቅ
ለሰዎች ብለህ የት ድረስ መሄድ እንዳለብህ ለይተህ እወቅ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ ማድመትም ሆነ ለሰዎች ስትል ዋጋ መክፈል ታላቅ ብስለትና ጨዋት የመሆኑ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ያንን ማድረግ ያለብህ ግን በመገደድ ስሜት ሳይሆን ውስጥህ ስላመነበትና ያንን ለማድረግ ስለወሰንክ መሆን አለበት፡፡

3. ለሰዎች ገደብን አብጅላቸው
ያላመንክበትን ነገር ካለምንም የጥፋተኝነት ስሜት እምቢ ማለትን መልመድ መልካም ልማድ ነው፡፡ የሰው ስሜት ላለመጉዳትና ክፉ መስሎ ላለመታየት ለሁሉም ነገር እሺ ማለት ማንነትህን እንደሚሸረሽረውና ዘመንህን በከንቱ እንደሚበላው አትርሳ፡፡

ከፈዘዝክበትና ከደነዘዝክበት ሁኔታ ተነሳና ውጣ! ለማን ሰውና ለምን አይነት ሁኔታ እሺ እንደምትል ለይተህ እወቅ! የራስህ ጉዞ ከሰዎች እጅ አውጣና ወደራስህ እጅ አስገባ!
ፍቅር ማለት በዚህ በምትመለከተው ጨለማ ውስጥ ከሚብለጨለጩት ቁጥር ስፍር የሌላቸው አምፓሎች መሀል ፣ነፍስ አንዷን መርጣ በብርሃኗ ስትደምቅ ነው።ብርሀን ሁሉ የነፍስን ጨለማ አይገፍም ቢበዛ የራስህን ብርሃን ትፈልግ ዘንድ ያግዝህ ይሆናል።ሰው የቱንም ያህል በደማቅ ብርሀን ቢከበብ፣እውነተኛውን የራሱን ብርሃን እስካላገኘ ድረስ ነፍሱ ጨለማ ውስጥ ናት።ፍቅርና ዝምታ መለኮታዊ ኃይሎች ናቸው።ፈጣሪን የምንፈራው ከተከታዮቹ ብዙ ጩኸት ይልቅ በጥልቅ ዝምታው ሳይሆን አይቀርም እናም በዝምታ ግርማ ሞገስ ውስጥ ባለ እውነተኛ ፍቅሩ።ዝምታን የሚያሸንፍ ጬኸት ፍቅርን የሚያንበረክክ ብልጣ ብልጥነት የለም።

#ከዕለታት ግማሽ ቀን #ከአሌክስ አብርሀም
አልወለድም - አቤ ጉበኛ
=============
እውነት በሌለበት በዚህ ውሸት አለም፣
እኔ አልወለድም ይቅርብኝ ግዴለም፣
ሠው በሰውነቱ እኩል ካልተዳኘ፣
ወፍራም በውፍረቱ ዳኝነት ካገኘ፣
ድህነት እርሀብን ችግርና ስቃይን ፣
ለማየት አልሻም ቅጡ ያጣ ፍርድን፣
አልወለድም፣
እቢ አልወለድም እኔ በዚህ ዓለም፣
ለህይወት የሚያጓጓ አንድ ነገር የለም፣
ለኗሪ አኗኗሪ ሆኘ ከምገፋው፣
ህይወት ተብሎ ስቃይን ከምጎናፀፈው፣
ሳልወለድ ልሙት እዚሁ ግደሉኝ፣
ከእናቴ ማህፀን ቀጥታ ቅበሩኝ፣
አልወለድም
ሳልፈልግ በወላጆች ስራ ፈጥራችሁኝ ሳለ፣
ብየ ስጠይቃችሁ በዓለም ምንድን አለ?
ለእኔ መኖሪያ ሚሆን ፣
ሀብት አለ?..........የለም፣
ነፃነት አለ?..........የለም፣
ፍትህ?..........የለም፣
ታዲያ ይሁ ነገር ከሌለ በምድር፣
ኧረ አልወለድም ውሀ ሁኘ ልቅር፣
አልወለድም፣
በዳይ እና ተበዳይ ገዢና ተገዢ፣
የሚል መደብ ካለ ስበብ ሳታበዢ፣
ዐለም አልሻሽም አትሽኝ እኔንም፣
ከአንቺጋ ለመኖር እኔ አልወለድም፣
አልወለድም፣
የዋሁ ደሀ ህዝብ ጉልበቱን በዝብዞ፣
ሀብታሙ ካለልክ ሁሉን አግበስብሶ
የሚወስድበት ዓለም፣
ባለስልጣን እንደጌታ እራሡን ኮፍሶ፣
ሁሉን የሚያሸክም የሚቀማም ነክሶ፣
በሆነበት ዓለም ለመኖር አልመጣም፣
እንዲህ ያለ ህይወት ልኖር እኔ አልወጣም፣
አልወለድም፣
ተወለድ ካላችሁ
ሠው በሠውነቱ እኩል ከተዳኘ፣
በሚሠራው ስራ ፍትህን ካገኘ፣
ጥቅምም ሆነ ጉዳት እንደሠራው ሁሉ
እኩል ክፍፍልን ካደረግን እዉን
የዛኔ ልወለድ ዐለም እኩል ስታይ
ሠውን ላይ ታች አድርጋ ከፍላ ሳትለያይ፡፡
ለአንተ ፍቅር ብቻ ነው ነፃነትን ሊያቀዳጅህ የሚችለው። ፍቅርን ደግሞ ነፃነትን የሚያጎናጽፍህ ለማፍቅር ዝጉጁ ስትሆን ብቻ ነው።ካፈቀርክና አንተም በምላሹ መፈቀርን ካገኘህ ፍቅር ዘውድህ ይሆናል።የገዛ ራስህም ንጉሰ ነገስት ያደርግሃል።
በአንተ ላይ ፍቅር ካልሰፈረብህ ፤ ፍቅርን በውስጥትህ ካላበበ ፤ እንደምን የተዋብክ ትሆናለህ አስቀያሚ ነው የምትሆነው።ዝግ የሆነ ነገር ትሆናለህ። ስስታም ሰዎች ፈሪ ናቸው።ም/ቱም ሁሉም ብሩን የሚጋራቸው መስሎ ስለሚታያቸው ከሰዎች ጋር መቀራረብ አይፈልጉም ።ቁሳቁሶችን የሚያፈቅሩ ሰዎች ራሳቸው ቁሳቁሶች ይሆናሉ።ሙት ዝግ በውስጣቸው ምንም የሚነዝር ፤ ደስ የሚያሰኝ እርካታ የላቸውም።ልብ ምቶቻቸውን አጥተዋል።የሚኖሩት ኑሮ መካኒካዊ ይሆናል።ፍቅርን እንደ ጦር የሚፈሩት ሰዎች ፤ ገንዘብን የተመለከተ ራስ ወዳድ(ሁሉም ነገር የኔ ነው ባይነት ) ስሜት ያድርባቸዋል።
Osho
👉 ራስን ማወቅ 👈
ሁሉን ነገር ማወቅ ብትችሉ ራሳችሁን ለማወቅ ግን አትችሉም
ራሰን አለማወቅ ይጎዳል በገላ ላይ እንዳለ ቁስልም ያማል
ራስን አለማወቅ ህይወትን በሙሉ ትርጉም አልባ ያደርጋታል
ሁሉን ነገር ልታውቁ ብትችሉም ራሳችሁን ግን አታውቁም የሚገርመው ግን ከእውቀታችሁ በፊት ልታውቁት የሚገባው ራሳችሁን ነበር
ለዚህም ነው በተቻለ መጠን በቃል ጥያቄና መልስ ከመጠመድ ራሳችሁን አርቁ የምለው እኔ ማን ነኝ በሚል ጥያቄ አትጃጃሉ
ምክንያቱም ከጥያቄው በፊት የጥያቄው መልሶች እናንተ አላችሁ እኮ ከጥንት ጀምሮ የማንነት የማንነት ጥያቄ እንደ ቃል አልባ ጥም ( non - verbal thirst ) ምላሽ የማይገኝለት ነው
( ኦሾ )
የመገደድ ስሜት

ውስጥህ ካለማቋረጥ ይናገርሃል፡፡ ውስጥህን ማድመጥ ግን የአንተ ሃላፊነት ነው፡፡ ስህተት ስትሰራ ህሊናህ እንደሚናገርህና እንዲሁም ሲያምህ፣ ሲርብህና ሲጠማህ አካልህ እንደሚናገርህ ሁሉ ውስጥህ ከሚነግርህ በርካታ ጠቃሚ ነገሮች አንዱ በሰዎች የመገደድን ስሜትህን ነው፡፡

በሰዎች የመገደድን ስሜት ማድመጥ ማለት ከማንነታችን የሚያወጣንን የሰዎች ግፊት መለየት ማለት ነው፡፡ በአካባቢያችን የሚገኙ ሰዎች የማናምንበትን ነገር እንድናደርግ፣ የማንፈልገውን ውሳኔ እንድንወስንና ምቾት ወደማይሰማን የሕይወት ቀጠና ውስጥ እንድንገባ ካለማቋረጥ ግፊት ያደርጉብናል፡፡

አንዳንድ ሰዎች የሚጫኑንና የሚያስገድዱን ለእኛ መልካም የሰሩ እየመሰላቸው ሲሆን፣ ሌሎች ግን እኛን የመቆጣጠር ዝንባሌ ስላላቸው ነው፡፡ በዚህች አለም ላይ ስትኖር ራስህን ከአስገዳጅና ከተቆጣጣሪ ሰዎች ነጻ ማውጣት ከቻልክ የድሎችን ሁሉ ድሎች ተጎናጽፈሃል፡፡ ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜህን ካባከንክ በኋላ የባነንክባቸውን ሁኔታዎች መለስ ብለህ ብታጤናቸው በሰዎች ግፊት ምክንያት ካደረካቸው ወይም ከማድረግ ከተቆጠብክባቸው ሁኔታዎች ጋር ተዛምደው ታገኛቸዋለህ፡፡

ከዚህ ሁኔታ ለመዳን ከፈለክ፣ ምንም አሰብክ ምንም ሃሳቡ ከውስጥህ የወጣ ወይም ውስጥህ ያመነበት መሆን አለበት፡፡ ስለዚህም፣ በሰዎች ከመገደድ አዙሪት ነጻ ለመውጣት መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች አሉ፡፡

1. የሕይወት መመሪያ ይኑርህ
የሕይወትህን መመሪያ በመለየትና በማወቅ ያንን ማዳበርና በዚያ እውቀት መደላደል አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ ራስህን ካልመራህ የመጣው ሰውና ገጠመኝ ይመራሃል፡፡ ራስህን ስትመራ ግን ሁሉን የምትመዝን ትሆናለህ፡፡

2. ገደብህን እወቅ
ለሰዎች ብለህ የት ድረስ መሄድ እንዳለብህ ለይተህ እወቅ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ ማድመትም ሆነ ለሰዎች ስትል ዋጋ መክፈል ታላቅ ብስለትና ጨዋት የመሆኑ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ያንን ማድረግ ያለብህ ግን በመገደድ ስሜት ሳይሆን ውስጥህ ስላመነበትና ያንን ለማድረግ ስለወሰንክ መሆን አለበት፡፡

3. ለሰዎች ገደብን አብጅላቸው
ያላመንክበትን ነገር ካለምንም የጥፋተኝነት ስሜት እምቢ ማለትን መልመድ መልካም ልማድ ነው፡፡ የሰው ስሜት ላለመጉዳትና ክፉ መስሎ ላለመታየት ለሁሉም ነገር እሺ ማለት ማንነትህን እንደሚሸረሽረውና ዘመንህን በከንቱ እንደሚበላው አትርሳ፡፡

ከፈዘዝክበትና ከደነዘዝክበት ሁኔታ ተነሳና ውጣ! ለማን ሰውና ለምን አይነት ሁኔታ እሺ እንደምትል ለይተህ እወቅ! የራስህ ጉዞ ከሰዎች እጅ አውጣና ወደራስህ እጅ አስገባ!
ፍቅር ማለት በዚህ በምትመለከተው ጨለማ ውስጥ ከሚብለጨለጩት ቁጥር ስፍር የሌላቸው አምፓሎች መሀል ፣ነፍስ አንዷን መርጣ በብርሃኗ ስትደምቅ ነው።ብርሀን ሁሉ የነፍስን ጨለማ አይገፍም ቢበዛ የራስህን ብርሃን ትፈልግ ዘንድ ያግዝህ ይሆናል።ሰው የቱንም ያህል በደማቅ ብርሀን ቢከበብ፣እውነተኛውን የራሱን ብርሃን እስካላገኘ ድረስ ነፍሱ ጨለማ ውስጥ ናት።ፍቅርና ዝምታ መለኮታዊ ኃይሎች ናቸው።ፈጣሪን የምንፈራው ከተከታዮቹ ብዙ ጩኸት ይልቅ በጥልቅ ዝምታው ሳይሆን አይቀርም እናም በዝምታ ግርማ ሞገስ ውስጥ ባለ እውነተኛ ፍቅሩ።ዝምታን የሚያሸንፍ ጬኸት ፍቅርን የሚያንበረክክ ብልጣ ብልጥነት የለም።

#ከዕለታት ግማሽ ቀን #ከአሌክስ አብርሀም