ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.58K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
"መሸበርና መፍራት የነገን ችግር አያስወግድልንም ይልቁኑስ የዛሬን ደስታ ያሳጣናል ።

... ሕይወት፣ የመዘጋጃና የመኖሪያ ዕድሜ የሌላት፣ ከአፈር ለተሠራ ሰው የተሰጠች ስጦታ ነች ፡፡ የሰው ልጅም ከተፈጠረ ጀምሮ ሕይወትን በውስጡ ለማሰንበት በትግል የሚኖር፣ ሲያጣትም እጅግ ጠሊቅ ሐዘን ውስጥ የሚገባ ፍጡር ነው፡፡ ሰዉ የራሱንና የሚወዳቸውን እስትንፋስ ለማቈየት፣ ከሰከንድ እስከ ሰዓታት ከዛሬው እየተበደረ ለማያውቀው ነገ ሲገብር፣ ለማያውቀው ነገ ደስታ ዛሬ ሲያለቅስ፣ ለማያውቀው ነገ ጥጋብ ዛሬ ሲራብ ሲታረዝ፣ ከማያውቀው ነገ ተበድሮ ዛሬ ሲጨነቅ የሚኖርና መኖሩን ሳያውቅ የሚሞት ፍጡር…፡፡"

*
ሜሎሪና ገጽ 9
#እኔነትን ጥላችሁ የሁለተናው አካል መሆናችሁን ከተረዳችሁ ሞት የሚባል ነገር የለም፤ ሞት ልክ አሮጌ ልብሳችሁን ጥላችሁ አዲስ ልብስ እንደ መልበስ ይመሰላል።
በእናታችው ማህፀን ለዘጠኝ ወር ቆይታችው ትወለዳላችሁ ለዚህ ምድር ውልደት ሲሆን በእናታችው ማህፀን ለነበረው ህይወታችሁ ግን መወለድ መሞት ነው።
:
#ኦሾ/Osho
"እውነትን ገድዬ እኔ ነፃ ከምሆን እኔ ሞቼ ሕግ ነፃ ትሁን !"
/ሶቅራጠስ/
"ፕሌቶን ከቀደምት የግሪክ ፈላስፋዎች ለየት የሚያደርገው በፊት የነበሩት የግርክ ፍልስፍናዎች በተወሰነ መልኩ በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ የሚያጠነጥኑ ሲሆኑ ፕሌቶ ግን በሁሉም የእውቀት ዘርፎች ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ መስጠት መቻሉ ነበር፡፡ ደህና ደረጃ ከነበራቸው ቤተሰቦቹ ከክርስቶስ ልደት በፊት 427 ም.አ በአቴንስ የተወለደው ፕሌቶ በምዕራባዉያን ፍልስፍና ታሪክ እጅግ በጣም ጎላ ያለ ቦታ የሚሰጠውና ከሶቅራጥስ ተማሪዎች አንዱ በመሆን ጎልቶ መውጣት የቻለ ፈላስፋ ነው፡፡ ፕሌቶ በኖረበት ዘመን አቴናዉያን ዴሞክራሲ እየተዳከመ የመጣበት ዘመን በመሆኑና እንደ መሲህ የሚያየው የቀለም አባቱ ሰቆራጥስ በአቴናዉያን ፊት ለፊቱ በመርዝ ሲደፋ በማየቱ ለአቴናውያን የነበረው አስተሳሰብ በአሉታዊ ገጽታ የሚቀምጥ ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ ፕሌቶ እየዘመመ የመጣውን የአቴናዉያን ዴሞክራሲን እንዲንሰራራ ለማድረግ የተለያዩ የፖለቲካ አስተሳሰቦችን ለመቀመር መነሳሳት ጀመረ፡፡ በ387 ም.አ ገደማ በአዉሮፓ ከቀደምት ጥንታዊ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ ሊባል የሚችለውንና ለብዙ ተማሪዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ትምህርት የሚሰጥበትን አካዳሚ መስርቶ በመምህርነት እና ፍልስፍ በመፃፍ ከ40 አመት በኋላ ያለውን እድሜውን አሳልፏል፡፡ የፕሌቶ ስራዎች በርካታ ሲሆኑ አብዛኞቹ አስተማሪው ከነበረው የሶቅራጥስ ትምህርቶችን የያዙ ነበሩ፡፡
:
ታላቁ የፍልስፍና ሰው ሶቅራጦስ ከመገደሉ አንድ ቀን በፊት የእሱ ደቀመዝሙር የነበረው ፕሌቶ ገንዘብ ሰብስቦ ለጠባቂዎች ጉቦ በመስጠት እሱን ለማስመለጥ እየሞከረ መሆኑን ነገረው ። ሶቅራጦስም ፦ "በዘመኔ ሁሉ ለሕግ እንደኖርኩ አሁንም ለእሷ ለመሞት እንደተዘጋጀሁ ታውቃለህ ፤ እውነትን ገድዬ እኔ ነፃ ከምሆን እኔ ሞቼ ሕግ ነፃ ትሁን !" በማለት የፕሌቶን ሀሳብ ሳይቀበል ቀረ ። ለዚህም ነው የሶቅራጦስ አድናቂዎች ፦ " ማሰብ ሳይችሉ እንደ ካሊባን ዙፋን ላይ ከመቀመጥ በወህኒ ቤት እንደ ሶቅራጦስ እያሰቡ መኖር ይሻላል!" የሚሉት ። እኔ ደሞ እንዲህ አልኩ በንባብ የሀሳብ አድማሳችንን እናስፉ።
:
ጥበብ ከጲላጦስ ቁ1/ኃይለጊዮጊስ ማሞ
ሰው ላይ እንድትፈርድ የሚያስቸኩልህ ባህሪ የሚያሳየው ሁሉንም ሰው ከአንተ በታች ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ነው።

አንድ ሰው ልእለ ሰብነት (ታላቅነት) ላይ ለመድረስ ታላቅ ንቃት ይጠይቃል። ከውስጣችሁ ካለው ተራራ ጫፍ ላይ መውጣትይጠበቅ ባችኋል። ይህ ደግሞ አስቸጋሪ ይመስላል።

ስለዚህ ቀላሉና ርካሹ መንገዱ ራሳችሁን የበላይ ለማድረግ ከመጣር ይልቅ ....ምንም ድካም እማያስፈልገው ሌሎችን የበታች አርጎ መቁጠር ነው።

ለዛ ነው ሰው ላይ ለመፍረድ የምትቸኩለው። ሌላው ላይ ለመፍረድ የምታደርገው ጥረት አንተ የተሻልክ እንደሆንክ ለማሳየት ያለህን ፍላጎት ያረጋግጣል። "ይህ ሰውየ እኮ ሌባ ነው፤ ይህ ሰውየ እኮ ሴት ተደፍሯል፤ ይህኮ የለየለት እብድ ነው.............."

ለሁሉም ሰው ልክ ታወጣና መጨረሻ አንተ ብቻ ንፁህ ሆነህ ትቀራለህ። ግን ሰው ላይ መፍረድ የዝቅተኛ ሰው መለያ ነው።
ኦሾ
"የተነገራችሁን ሁሉ ቀጥታ እንደወረደ አምናችሁ አትቀበሉ ከዚያ ይልቅ እውነትን በብልሃትና በንቃት ለማግኘት ሞክሩ።
እውነት ሁልጊዜ ተሞክሮ ነው። የእኔ እውነት የእናንተ ሊሆን አይችልም ፤ ያለማወላወል የእኔ ብቻ ነው። እውነትን ልንጋራው አንችልም።እኔ የምሰጣችሁ ግንዛቤ ብቻ ነው። ከዚያ በተረፈ እያንዳንዱ ሰው እውነትን ደጋግሞ በራሱ ማግኝት አለበት ። ስለሆነም ለመመራመር ፣ ለመጠየቅ፣ ለመሞከር ለመተግበር ትጉ።"
#ኦሾ
#ለፈገግታ ያህል ከሙጋቤ ንግግሮች አንዱን
============
የ CNN ጋዜጠኛ የዚምባቡዌ ፕሬዝደንት ሙጋቤን እየጠየቃቸው ነው፡-
ጋዜጠኛ፡- ሩሲያ ወደ ጠፈር ለመሄድ የመጀመሪያዋ አገር ነበረች፡፡ አሜሪካ ደግሞ ጨረቃ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በማረፍ ታሪክ አስመዝግባለች፡፡ አፍሪካስ ምን ዓይነት ታሪክ በመስራት አለምን ታስደንቅ ይሆናል ብለው ያስባሉ?
ሙጋቤ፡- እኛ ፀሃይ ላይ በማረፍ የመጀመሪያውን ታሪክ እንሰራለን፡፡
ጋዜጠኛ፡- ግን ፀሃይ በጣም የሚያቃጥል ነገር ነው፡፡
ፀሃይ ላይ ማረፍ አይቻልም፡፡
ሙጋቤ፡- እኛ ጅል መሰልንህ እንዴ ፣ ሲመሽ ነው ወደ ፀሃይ የምንሄደው፡፡
ሞሀንዳስ ካራምቻንድ ጋንዲ (ማህተመ ጋንዲ) የሚከተሉትን ተግባራት በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ሀጢያቶች (sins against humanity) ናቸው ብሎ ያምናል ።

1. Wealth without work -
ያለሥራ የተገኘ ሀብት

2. Enjoyment without work conscience -ሕሊና የማይቀበለው ደስታ

3.knowledge without character -
ምግባር ያልታከለበት እውቀት

4.Business without Morality -
ግብረገብነት የጎደለው ንግድ

5.science without Humanity -
ሰብአዊነት የሌለበት ሳይንስ

6.Religion without compassion
ሀይማኖት ያለ ከፍተኛ ርህራሔ

7.Politics without principle
- መርህ የሌለው ፖለቲካ

8.Rights with out Responsibility
ሀላፊነት ያልታከለበት መብት

9.Power without Accountability -
ተጠያቂነት የሌለበት ሥልጣን

10.Development Without Sustainability -ቀጣይነት የሌለው ልማት
የሌለህን ነገር ብቻ ካሰብክ ያለህንም ታጣዋለህ፡፡ ያለህን ነገር ካሰብክ ግን የሌለህንም ታገኘዋለህ፡፡
#ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)
ሰውዬው በሚስቱ ሞያ ይማረራል፡፡ ገና ወደ ቤቱ ለመምጣት ሲያስብ የሚበላው እንጀራና ወጥ ትዝ ሲለው ሐሞቱ ፍስስ ይላል፡፡ «እንግዲህ ለዚያ ሊጥ ልሂድለት» ብሎ ይመጣል፡፡ ይህ ነገር ሰለቸውና ከሚስቱ ጋር ተፋታ፡፡ ወደ ጓደኛውም ቤት ሄደ፡፡ ጓደኛው አልጋ አንጥፎ ተቀበለው፡፡
ማታ ራት ቀረበ፡፡ ምን የመሰለ ነጭ ጤፍ ላይ አልጫና ቀዩ ተጋድሞ ቀረበለት፡፡ በአንድ በኩል ቃሪያው፣ በአንድ በኩል ስልጆው፣ በአንድ በኩል ፍትፍቱ፣ በአንድ በኩል አተር ክኩ ተሰለፈ፡፡ «ወይ ሞያ እኔማ ኖርኩ አይባልምኮ» እያለ ያማርር ጀመር፡፡ «አንተማ ታድለህ» ይለዋል ጓደኛውን፡፡ «ይሁን እስኪ» ይላል ያኛውም፡፡ ጠላው ሲቀርብ ደግሞ እያደነቀ ጠጣ፡፡ «ከኖሩ ላይቀር እንዲህ ነው» ይል ጀመር፡፡ ያችንም ባለሞያ ሚስት በምስጋናና በአድናቆት አረሰረሳት፡፡

በልተው ሊያጠናቅቁ ሲሉ ጋባዡ ሊጠጣበት ያነሣው ብርጭቆ ተሰበረ፡፡ ደነገጠ፡፡ ሚስት ከጓዳ መጣች፡፡ «ምንድን ነው የተሰበረው?» አለች፡፡

«ያ የምትወጅው ብርጭቆ ተሰበረ፡፡» አላት ባልዋ በተስለመለመ ድምፅ፡፡ ተናደደችና አንዴ በጥፊ አላሰችው፡፡ ጓደኛው ደነገጠ፡፡ «እንዲህ ሰብረህ ሰብረህ የአባት የናቴን ስጦታ ጨረስከው፡፡ አንተ ምን ታደርግ ተንቀባርረህ ከነ ጓደኛህ ትልፋለህ» እያለች ቁም ስቅሉን ታሳየው ጀመር፡፡ ባልዬው ጠባይዋን ያውቃልና ዝም አለ፡፡ ያም ጓደኛው «ምን ለብርጭቆ ደግሞ ነገ ይገዛል፤ ዋናው ጤና ነው» አለ ነገር ያበረደ መስሎት፡፡ «አንተ ደግሞ አርፈህ ተቀመጥ፤ ሚስትህን እንደዚህ አማረሃት ይሆናል ይኼኔ፤ ቀላዋጭ» አለችና አቀመሰችው፡፡ ተፈታተነው ስሜቱ፡፡ ግን እንግድነቱ በልጦበት «ኧረ የኔዋስ እንዳንቺ» አለና ጀምሮ ተወው፡፡ ወደ ጓዳ ገባችና አንድ ፍልጥ ይዛ መጣች፡፡ እስኪ ጨርሰው አለቺው፡፡ ዓይኑ ተቁለጨለጨ፡፡ «እንዳንቺ የባሰባት አይደለችም» ሲላት ፍልጡን ይዛ መጣች፡፡

ይህንን ሲያይ ባልዬው «ቀስ ብለህ አምልጥ» አለው፡፡
በዚያ ሌሊት እየገሠገሠ የሚስቱ እናት ጋ ሄደ፡፡

እናቲቱም «ምነው ልጄ» አሉት
«እማማ፤ ከሌሊት ፍልጥ፣ የቀን ሊጥ ይሻለኛል ብዬ መጣሁ፡፡ አላቸው ይባላል፡፡
ወዳጄ ያለህን ካላሰብከው የባሰው ላይ ትወድቃለህ ያልኩ ለዚህ ነው፡፡
እስኪ ወዳጄ ያለህን ዕወቀው፤ አክብረው፤ አሟጠህ በሚገባ ተጠቀምበት፤ በዚያ ኑርበት፤ አጊጥበት፡፡ ከዚያ ሌላውን ለመያዝ ፈልግ፡፡ ባለህ የማትረካ ከሆንክ ግን ሩጫህ የተሻለ ነገር ፍለጋ ሳይሆን ሌላ ነገር ፍለጋ ብቻ ይሆናል፡፡
:
#ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)
የስብሃት ለአብ ትውስታዎች!!
* * *
"ሠይጣን ወደ ኢትዮጵያ ቢመጣ ስራ የለውም ምክንያቱም የሰው ልጅ እሱ የሚሰራውን ሥራ ቀድሞ ሠርቶ ጨርሶቷል።ምን ሊሰራ ይመጣል?"የሚል ሀሳብ ያዘለ ጽሑፍ ጋዜጣ ላይ ጻፍኩ።
ታድያ ጹሑፉን ያነበቡ ጓደኞቼ...
"ጋሽ ስብሐት ህዝቡ በፅሑፉ ቅር ተሰኝቷል÷ የሰው ልጅ ለመልካም ሥራ እንዲነሳሳ በተቃራኒው ብትጽፈውስ?" አሉኝ።
በሳምንቱ...
"መልዓክ ወደ ወደ ኢትዮጵያ ቢመጣ ቦታ የለውም÷ ምክንያቱም የሰው ልጅ የሱን ተግባር ቀድሞ ሠርቶ ጨርሶቷል።ምን ሊሰራ ይመጣል?"
በማለት ጻፍኩ::
ነገር ግን ይሄ የባሰ የቁጣ ማዕበል አስነሳ!"
ሲል ፅፏል፡፡
* * *
#እንዲህ ነን እኛ!!
አንድ ሀብታም ሰው ዘመናዊ መኪናውን አቁሞ ለጉዳዩ ገባ ይላል ጉዳዩን ጨርሶ ወደ መኪናው ሲመለስ የአንዱ ጎማው 4 ብሎኖች ተፈተው ተወስዶበት ያያል፡፡ ይህኔ ይበሳጭ እና አከባቢው ላይ ዞር ዞር ብሎ ብሎን ፈልጎ ያጣል፡፡
ያኔ መኪናውን ተደግፎ በጭንቀት ቆዝሞ ሳለ አከባቢው ላይ ያለ አንድ እብድ ነገሩን ተከታትሎ ኖራልና "ምን ሆነህ ነው?" ይለዋል፡፡ሰውየውም በንቀት አይን አየት እያደረገው "የጎማዬ ብሎኖች ተፈተው ተወስዶብኝ ነው እንዳልገዛ አከባቢው ላይ የለም" ይለዋል በብስጭት ስሜት ውስጥ ሆኖ፡፡
ይህኔ እብዱ "ነው እንዴ? ታዲያ ለምን ከ3 ጎማዎች አንድ አንድ ብሎን ፈተህ አራተኛውን ጎማ አታስርም" አለው፡፡
ሰውየውም በመገረም ሀሳቡ በጣም አስደሰተውና አንዳለውም አደረገ፡፡
"ቆይ አንተ እብድ አይደለህ እንዴ! አንዴት ይህ ሀሳብ ሊመጣልህ ቻለ?" ብሎ ጠየቀው፡፡
እብዱም ቀበል አድርጎ "ታዲያ እኔ እብድ ነኝ እንጂ ደደብ አይደለሁም" ብሎ ይመልስለታል፡፡
"ዝቅ በል፤ ዝቅ ስትል ከፍ ትላለህ፤ ተናነስ፤ ራስህን አትቆልል፤ ሁሌም እኔ አዋቂነኝ አትበል"
"ዲ/ን ዳንኤል ክብረት"
ሁሉንም ልምዶች እቃወማለሁ!!!

እኔ ሁሉንም ልምዶች እቃወማለሁ። ጥሩና መጥፎ ብየ አልከፋፍላቸውም። ምክንያቱም ጥሩም ሆነ መጥፎ የሚባል ልምድ ስለሌኝ ነው። ልምዶች ሁሉ ጎጂ ናቸው። ምክንያቱም ልማድ ማለት አንድ ያለንቃት የምናደርገው ተደጋጋሚ የሆነ ነገር በህይወታችን ላይ እእጅግ ወሳኝና የበላይ ሆኖ እየተቆጣጠረን ሲመጣ የሚፈጠር ሁኔታ ማለት ነው። ያኔ አንተ በህይወትህ ላይ የበላይነትህ ያበቃለታል። ለነገሮች ያለህ ምላሽ ከንቃት የመነጨ ሳይሆን ካለፈው ግዜ ከተማርካቸው መዋቅራዊ ከሆኑ ተግባሮች ነው።

ኦሾ/osho
"ህፃናት ሕይወት በሰው ልጆች ተስፋ እንዳልቆረጠ የሚገልፁ ህያው ስጦታዎች ናቸው"
*
ካህሊል ጂብራን
ራሱን የሚያፈቅር ሠው ወደ እውነተኛው ፍቅር ለመድረስ የመጀመሪያውን እርምጃ ተራምዷል፡፡
.
ኦሾ
#መልካም ቅዳሜ

****
"በህሊና ዳኝነት ህይወቱን የሚመራ ሰው ታላቅና ንፁህ ነፍስ ያለው ሰው ነው''
******
/ምንዱባን/
"ለሕይወት የከበሬታ ስሜት ካልፈጠረ እና ክብር ካልሰጠ በስተቀረ ፣ ማንም የሰው ልጅ የህይወት መሠረታዊ መብትን የመጎናጸፍ አላማን አይረዳውም።"
Osho/ኦሾ
ብቸኛው ጊዜ አሁን ነው ! ብቸኛው ቦታ እዚህ
የእውነታን ሙሉዕነት የያዘው ይህ ይቅጽበት ነው!"
:
#ኦሾ/Osho
#ተጨልፎ ከማያልቀው ከኦሾ እይታዎች የተወሰነ ስለፍቅር ከተናገረው ወደናንተ እንበትን ዘንድ የተገባ ሆኖ አገኝነው

" ፍቅር ማለት በምትወደው ሰው ነፍስ ውስጥ ራስህን መግደል ነው። ፍቅር ማለት ሞት ነው ፤ የሚቻልህን ያህል ጥልቅ በሆነ ሞት ውስጥ ትገባለህ ፤ የምትሞተውም በምትወዳት ሴት ነፍስ ውስጥ ነው ። ዕለት ዕለት ወደ ጥልቅ የነፍሷም ቦታ ትወሰዳለህ ፤ ፍቅር ወደምታፈቅራት ሴት የነፍስ ቦታ የምታደርገው ዘላለማዊ ጉዞ ነው ። ጉዞውም ማቆሚያ የለውም ። አንዲትን ሴት ስታፈቅራት በአንተ ሕይወት ውስጥ ከአንተ በላይ ዋጋ አላት ። ፍቅር ማለት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መማረክ ማለት ነው ። ምክንያቱም አንዳች ቅድመ ሁኔታ የምታስቀምጥለት ከሆነ ከምታፈቅረው ሰው በላይ ለራስህ ዋጋ ሰጥተሃል ማለት ነው ። ራስህን ዋነኛው ጉዳይ አድርገህ በፍቅር ውስጥ ስትመለከት ተፈቃሪዋ መጠቀሚያህ ሆነች ፤ የፍላጎትህ ማርኪያ አደረግሃት፤ በሌሎች ዘንድ መደነቂያህ ሆነች...መነሻውም መድረሻውም አንተ ሆነሃል ።
#OSHO/ኦሾ/
#ከእለታት አንድ ቀን አንድ የፐርሺያ ንጉሥ ሁለት ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ ፈረደባቸው፡፡
በመጨረሻም፤ “የሞት ፍርዱ ከመፈፀሙ በፊት የፈለጋችሁትን ተናገሩ” ሲል እድል ይሰጣቸዋል፡፡
አንደኛው፤ “ምንም የምናገረው የለኝም” አለ ሁለተኛው፤
ንጉሡ ምን ያህል ፈረሳቸውን እንደሚወዱት ስለሚያውቅ፤“ንጉሥ ሆይ፤ የአንድ ዓመት ጊዜ ከሰጡኝ ፈረስዎ ወደ ሰማይ እየከነፈ እንዲሄድ ላስተምረው እችላለሁ” አላቸው፡፡ንጉሡ በሰማይ ላይ የሚከንፍ ፈረስ እየጋለቡ ሲሄዱ ታያቸው፡፡ ካሁኑ ነሸጣቸውና ይቁነጠነጡ ጀመር፡፡“ይሁን አንድ ዓመት ሰጥተንሃል፡፡ ፈረሱን አምጥተው እንዲያስረክቡህ አደርጋለሁ” አሉ፡፡
የመጀመሪያው እሥረኛ በምንም አይነት ፈረስ እንደማይበር ስለሚያውቅ ፈረስ አስተማሪውን እሥረኛ ጓደኛውን እንዲህ ሲል ጠየቀው፤“ወዳጄ፤ ፈረስ በሰማይ እንደማይበር አሳምረህ ታውቃለህ፡፡ እንዲህ ያለ የዕብድ ሀሳብ ከየት አምጥተህ ነው ቃል የገባኸው፡፡ የመሞቻችንን ጊዜ ከማራዘም በስተቀር ምን ይፈይድልሃል?”
ፈረስ አስተማሪውም፤“አይምሰልህ ወዳጄ፤ ነፃነቴን የማገኝባቸውን አራት ዕድሎች ራሴ መስጠቴ ነው”አለ
አንደኛው እሥረኛም፤
“አራቱ ዕድሎች ምን ምን ናቸው?” ሲል በመጓጓት ጠየቀው፡፡
ፈረስ አስተማሪው፤ እንዲህ ሲል ዘረዘረለት፡-
1ኛ ወይ በዚህ ዓመት ውስጥ ንጉሡ ሊሞቱ ይችላሉ
2ኛ እኔም ልሞት እችላለሁ
3ኛ ወይ ደሞ ፈረሱም ሊሞት ይችላል
4ኛ ደሞስ ማን ያውቃል እኔ ፈረሱ በሰማይ እንዲበር ላስተምረው እችል ይሆናል አለው ይባላል።
* * *
እና ምን ልልህ ፈልጌ መሰለህ በችግሮች ተሸንፈህ ቀድመህ እጅ አትስጥ ጣር ሞክር ልፋ ታገል በነገሮች ተስፋ አድርግ እንጂ ተስፋ አትጣ።ህይወት አንድ ሺህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ አንድ ሺህ ጊዜ ተስፋ የምታደርግባት የግብግብ መድረክ ናት።
"ተስፋ በሌለበት እንኳ ተስፍ አድርግ ያለው ጸሐፊው በምክንያት ነው።አይህ ወዳጄ ከመሰንበት መላ አይጠፋምና።
#መልካም ቀን ተመኘው
"ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ የተወሰዱ ምክሮችና እውነታዎች

#ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡

#በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መኾን ባትችል ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትኹን፡፡

#በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ኹሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡

#ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡

#ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡

#በሕይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡
.." አንድ ካሬ ሜትር መርካቶ ውስጥ 350 ሺ ብር ካወጣና አንድ ፕሮፌሰር አርባ አመት ደክሞ በወር የሚያገኛት የአንዲት ካሬ ሜትር ዋጋ የምትመዝን ካልሆነች ሰው ተፈጥሮን አላሸነፈውም ማለት ነው፣ ሰው ከተፈጥሮ አልበለጠም ማለት ነው። መሬት ተፈጥሯዊ ነች፣ ለምንድነው ትንሿ መሬት ይህቺን ያህል ስትወደድ ለምንድነው እኛ ይሄን ያህል አመት የተማርን ሰዎች ልንወደድ ያልቻልነው? ምክንያቱም በምንፈታው ችግር ልክ ነው እኛ ልንወደድ የምንችለው!! መሬቷ 30 ፎቅ ስለሚሰራባት 30 ፎቅ ልትከራይ ነው። የዚያች ቁራሽ መሬት ዋጋ ወደ ላይ 30 ፎቅ ሲያሰራ፣ እኛ ግን አንዲት ክፍል ውስጥ ገብተን ነው የምናስተምረው!!....የእኛ 30 እና 40 አመት የተማርንበት ዋጋ ግን ለብዙ ትውልድ መትረፍ አልቻለም። መብራት አልሰራም፣ አውሮፕላን አልሰራም፣ መርከብ አልሰራም፣ ባቡር አልሰራም። ሲንጋፖር ዕኮ መሬት የላትም! የምትሸጠው ዕኮ የአዕምሮዋን ውጤት ነው። የአዕምሮዋ ውጤት ደግሞ በአመት 540 ቢሊዮን ዶላር$ ኤክስፖርት ወደውጪ ይደረጋል። የእኛ የተፈጥሮ የሆነች ነገር ደግሞ 100 ሚሊየን ሕዝብ ይዘን የምታመጣልን 3 ቢሊየን ያልሞላ ኤክስፖርት እናደርጋለን። ሲንጋፖር 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ሕዝብ የያዘች ትንሽ ሀገር ናት። ስለዚህ አዕምሮ መስራት ካልቻለ የተፈጥሮ መሬት የበለጠ እየተወደደች ትሄዳለች። እናም መማር ችግር ፈቺነትን ካላሳደገ፣ አዕምሯችን የተሻለ ነገር መፍጠር ካልቻለ፣ መሬት ላይ ቤት ሰርቶ፣ አከራይቶ፣ ሽጦና ለውጦ የተፈጥሮን ነገር ብቻ ሙጥኝ ብሎ መገላበጡ ይቀጥላል።

ዶር ምህረት ደበበ
በአንድ ሀገር ውስጥ በጣም የታዋቀ አንድ ዐዋቂ ሰው ነበረ አሉ።ያንን ሀገር የሚገዛም ደግሞ በጣም ክፉ ንጉሥ ነበር አሉ።ህዝብ ወደዚህ አዋቂ ዘንድ ይሄድና ፤ "እባክህ እንደው ከፈጣሪ አማልደህ ይኼንን ክፉ ንጉሥ አስወግድልን" አሉት።
"ለምን ?"ብሎ ሲጠይቃቸው።
"በቃ አንፈልገውም ይወገድልን"አሉት።ዐዋቂም እሺ አለ።ክፉ ንጉሥም ተወገደ።ሌላ ንጉሥም መጣ።የመጣው ንጉሥም ደግሞ የባሰ ሆነ።ለውጡ ከጅራፍ ወደ ጊንጥ ሆነ።ሕዝብ አዲስ የመጣውን ንጉሥ ትንሽ ጊዜ ካየው በኃላ ወደ ዐዋቂው ዘንድ ሄዶ "ይኸንንም ንጉሥ አስወግድልን አለ።
ለውጡ ከጊንጥ ወደ እፍኝት ሆነ።ሁለተኛውም እንዲወገድ ሆኖ ሌላ ንጉሥ መጣ። ሦስተኛ የመጣው ንጉሥም ከመጀመርያው ከሁለኛውም ንጉሦች የባሰ ሆነ። ወዲያው ሕዝብ ዝም አለ።ንጉሡ ቢያደምጥ ዐዋቂው ቢያደምጥ፣ምንም ድምጽ ጠፉ።ሕዝቡ ዝም አለ። ወደ ንጉሡ የሚሄድ የለም ወደ ዐዋቂው የሚሄድ የለም።በዚህ ጊዜ ንጉሡ ወደ ዐዋቂው ዘንድ መልዕክተኛ ላከ። ወደ አንተ ጋ ሕዝብ መጥቶ ያውቃል?"
አዋቂው "አልመጣም ሲል መለሰ።
"ንጉሡ ዕድሜው ይርዘም ብሎስ ያውቃል?"
"አያውቅም"
ዕድሜው ይጠርስ ብሎ ያውቃል?"
"አያውቅም"
አሁን አደጋ ላይ ነን ፤አሁን ነው ህዝብን ማድመጥ"አለ ይባላል ንጉሡ።
፦"እናም ሕዝብ ዐውቆ ዝም ሲል ዝምታውን ማድመጥ ያሰፈልጋል ዝምታው ሌላ ወጀብ ይዞ ሳይነሳ።"
:
***ብቻዬን እቆማለው እና ሌሎች ****
@ዳንኤል ክብረት/2012ዓ.ም/
ገጽ 12-14 የተመዘዘ