ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.58K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
ከጅምሩ እራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ ማወዳደር ትልቅ በሽታ ነው ፤ እንደ ካንሰር ነው ነፍስህን እያጠፋ ይሄዳል? ምክንያቱም እያንዳንዱ ግለሰብ ልዩ ነው ፣ እና ማወዳደር አይቻልም። እኔ እኔ ነኝ አንተም አንተ ነህ ፡፡ በዓለም ላይ አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለምና ፡፡
* ኦሾ *
#አለማችን በጣም እየተጎዳች ያለችው በመጥፎ ሰዎች ክፋት ብቻ ሳይሆን በጥሩ ሰዎች ዝምታ ነው። "
/ናፓሊዮን/
#ለምታገኘው ደስታም ሆነ ለሚደርስብህ ችግር ተጠያቂው አንተና አንተ ብቻ ነህ ማንም ላንተ ህይወት ሃላፊነቱን አይወስድም...የራስህን ገነት የምትገነባውም ሆነ እራስህን በገሃነም እሳት የምትጥለው አንተ እና አንተ ብቻ ነህ ።

ኦሾ /Osho
የበታችነት ስሜት በሽታ ነው፤ ይህን የበታችነት ስሜት ለመደበቅ የሚመጣው የበላይነት ስሜት ደግሞ የባሰ በሽታ ነው። አብዛኛውን ጊዜ መድሀኒቱ ከበሽታው ይልቅ አደገኛ ነው። አንድ ሰው ተፈጥሯዊ ሚዛኑን መጠበቅ የሚችለው ከበታችነትም ሆነ ከበላይነት ስሜት ነፃ ሲሆን ነው።

ኦሾ/osho
ራሱን የሚያፈቅር ሠው ወደ እውነተኛው ፍቅር ለመድረስ የመጀመሪያውን እርምጃ ተራምዷል፡፡ ››
"ምክንያት ለሰው ልጅ ወሳኝ ባይሆን ኖሮ አእምሮ ባልተፈጠረ ነበር "
/ዘርያቆብ/
መላው አለም ከኔ በተቃራኒው ቢቆም እንኳን በውስጤ አንድም ጥርጣሬ አይፈጠርም ምክንያቱም የማውቀውን አውቃለሁ የሆንኩትን ሆኛለሁ። እናተም እራሳችሁን ሁን!!!
ቅናት የሚፈለፈለው ከማወዳደር ነው፡፡ ማንም ከማንም አይበላለጥም፡፡ ሁሉም ሰው በራሱ ሙሉዕ ነው፡፡ አንዱ በሆነ መስክ ከሌሎች ሊሻል ይችላል፤ ሌላው ደግሞ በሌላ መስክ ልቆ ይገኛል፡፡ ይሄ ደግሞ ሰዎች የተለያየን መሆናችንን ነው የሚያሳየው - ውድድር እዚህ ውስጥ ፈጽሞ አይገባም፡፡ "
"አገርን የሚጎዱት አስበው መናገር ሲገባቸው ተናግረው በሚያስቡት ነው!"
«አንተ በፈጣሪ ቁጥጥር ስር ከሆንክ ተፈጥሮን በቁጥጥርህ ሥር ማድረግ ትችላለህ!»
*
#መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
መልካምነት የተደረገልህን ሳይሆን ያልተደረገልህን የመክፈል ብቃት ነው"
/ኮንፊሺየስ/
በአንድ ነገር የወደደህ ሰው በአንድ ነገር ይጠላሃል። ነገር ግን ያለምክንያት የሚወድህ ግን ሁሌም ሲወድህ ይኖራል።
ሕይወትን እንድትቃወሙ ፣ደስታና ፈንጠዚያን እንድታወግዙ የሚመክራችሁ ማንኛውም ሃይማኖት የተመረዘ ነው ተግባሩ ከሕይወት ተፃራሪ ነው ፤ የሞት አገልጋይ ነው። እኔ ግን በፍቅር በዜማ ፣ በሃሴት የተሞላ ስብዕና ፈላጊ ነኝ።
Osho
እምነትን ማዕከል አድርጎ የሚኖር ህዝብ በውድቀቱም ሆነ በስኬቱ ራሱን ኃላፊ አያደርግም።
ሁሉን ለሚያመልከው መለኮተ-ኃይል ይሰጠል።
::::::*::::***:::::***:*:*: : :*:*:*:*
# መሀመድ ዓሊ
#የዘር ካርድ
""ራሳችሁን ሆናችሁ ተፈጥራችሁ እስከመቼ የካርቦን ቅጂ ሆናችሁ ትኖራላችሁ። ማንም ከራሱ በስተቀር ሌሎችን መሆን የለበትም።"
*
📍
ኦሾ/Osho
#ፍልስፍና የአእምሮ ጂምናስቲክ ነው!
* * *
አንድ የመጠጥ ባለሙያ መጠጥ ቤት ውስጥ አይኑ ተሸፍኖ ማንኛውንም አይነት መጠጥ ቢቀምስ በቀላሉ መለየት እንደሚችል ፣ መለየትምን ብቻም ሳይሆን የትኛው ኩባንያ እንደስራው መናገር እንደሚችል ይወራራዳል።የመጠጥ አስተናጋጁም ውርርዱን ይቀበላል።የውርርዱን ሁኔታ ለማየት ብዙ ሰዎች በሁሉቱ ዙሪያ ይሰበሰባሉ።በመቀጠልም ባለሙያው አይኑን ታስሮ የመጀመርያውን ቅምሻ አደረገና ወዲያው "ለፎርቹን ሮዝስ በፍራንክፈርት ኤፈርት ጠማቂዎች የቀረበ"ብሎ ይመልሳል።
"ትክክል"መለሰ አለ አስተናጋጁ ።እንደገናም ለመሞከር ይወራረዳል።በሁለተኛው ሙከራው አሁንም አንድ ቅምሻ ወሰደና "ካናዲያን ክለብ- በሂራም ዎከር የቀረበ" ብሎ ይመልሳል።ትክክል"መለሰ አለ አስተናጋጁ በድጋሚ።ባለሞያው እስቲ አንዴ ድጋሚ ልሞክር" አለ።
በዚህ ጊዜ የተሰበሰቡት ሰዎችና አስተናጋጁ ተመካከሩና ጠርሙሱን በሽንት ሞሉት።
ሰውዬው ሲቀምሰው በመጮህ "እንዴ!ይህ ሽንት ነው!አለ" ትክክል ነህ"አለው አስተናጋጁ በመስማማት ፣ግን የማን ሽንት ነው? እያለ እያለ ይቀጥላል....ፍልስፍና እንዲህ ነው።
#*****,
#ፍልስፍና አላስፈላጊ ጉጉት ነው።ነጥብ የለሽ ጉጉት።ልታወሩ አሁንም ልታወሩ ትችላላችሁ ...... ግን መጨረሻው ማጥወልወል ነው ።አስወግዱት !ፍልስፍና ብዙ ሰዎችን አጥምዶ ህይወታቸውን አበላሽቷል።
#ፍልስፍና የአእምሮ ጂምናስቲክ ነው።ፀጉር ስንጠቃ ነው። አንዱ በጣም በጥልቀት ሊገባበት ይችላል። በጣም ማራኪ ነገር ነው።ምክንያቱም አንድ ጥያቄ ውስጥ አስር ጥያቄዎች ይመራችኃልና። አስሩ ወደ ሌላ አስር ጥያቄዎች ግን...... የአዕምሮ ጉዞ ውስጥ ናችሁ ያላችሁት። ከህይወት እየራቀ እየራቀ ይመራችኃል።ከህይወት እወነተኛ ችግሮችም ያርቃችኃል።ከመፈጠር ያርቃችኃላ። በግምቶች ትብሰለሰሉና መኖርን ትረሱታላችሁ።ለዚህ ነው ጥበብ የተሻለ ነው የምለው። ምክንያቱም በጣም ዓለማዊ ነውና።ፍልስፍና ረቂቅ ነው። ረቂቅነትን አስወግዱ ።በረቂቅነት ውስጥ ወደ እውነታው በፍፁም አትመጡም። ወደ እወነታው መምጣት አለባችሁ ።ምክንያቱም የዳቦን ፍልስፍናዊ ሃሳብ ሳይሆን እውነተኛውን ዳቦ ነው የምትመገቡት ፍልስፍና ሁሌም "ስለ"እና"ስለ"ነው:ዙሪያ ጥምጥም እንደተሽከረከረ ነው......የትም ቦታ አይደርስም።
Osho/ኦሾ/
የሰው ልጅ ከሌሎች እንሰሳት በማሰቡ አይደለም የሚለየው፥ በማሰቡ ያው እንሰሳ ነው፥ የሚለየው በምግባር ነው፥ 'Moral' የሚባል ጉዳይ ነው ሰውን ከእንሰሳ የሚለየው፥ ይሄ መሠመር አለበት።
*
በማሰብ ቢሆን ኖሮሞ እነ አሜሪካና እንግሊዝ ወራሪዎች ባልሆኑ ነበር።
*
'Moral' (ምግባር፣ ስነ-ምግባር፣ ግብረ-ገብ) የሠው ልጅ ተፈጥሮ ነው። በሂደት ያመጣው አይደለም፥ ሲፈጠር ጀምሮ ጥሩና መጥፎውን ያውቀዋል።
ያለ ባህል የተፈጠረ ህዝብ የለም። ባህል ደግሞ የ'Moral' (ምግባር፣ ስነ-ምግባር፣ ግብረ-ገብ) መስታወት ነው። እያንዳንዱ ባህል ጥሩና መጥፎ የሚልበት ሚዛን አለው።
*** *=* ***
ጸሐፊ መሐመድ አሊ/ቡርሃን አዲስ/
"... የተፈጠረው ሰውም የፈጠረው አምላክም አያልቅባቸውም። ምናልባት ሰውን ከሁሉ ሌላ ፍጡር የተለየ ብቸኛ የሚያደርገው፣ ከመልአክ እኩል ደግና በጎ አድራጊ ለመሆን መቻሉ፣ እና በዚያም መጠን ከሰይጣን እኩል ከይሲ እርኩስ ስራዎችን እንደ ቅዱስ ተግባር እያመለካቸውና እየታዘዛቸው መፈፀሙ ነው። ሂትለር ብዙ ሚሊዮን የሚኖሩባትን ሀገር አፀዳታለሁ፣ አይሁድ የሚባለውን ቆሻሻ ከኛ ከንፁሀን ነጮች አገር እየጠረግኩም፣ እያቃጠልኩም አስወጣዋለሁ ብሎ ተነስቶ ዛቻውን ፈፀመ።.. ሂትለር ሰው አይደለም አንልም መቸስ። ግን ሂትለር ሰው ከሆነ_ "ሰው ሰይጣን ነው፣ ሰይጣን ሰው ነው"_ አንዳንዴ።.. የሰው ልጅ ምድርን እስኪያጣብባት መብዛቱ እነ ሂትለርን በይህ በኩል፣ እነ ማህታማ ጋንድሂን በያ በኩል ማስገኘት ምን ያቅተዋል ?"
*
👉 ስብሀት ገብረ እግዚአብሄር
("ሰውና ማስመሰል".. ከተሰኘው መጣጥፉ የተቀነጨበ)
#ሞትን ሸሽተህ አታመልጣትም።
የባግዳድ ነዋሪ የነበረ አንድ ባለጸጋ በጣም የሚወደው ባሪያውን ወደ ገበያ ይልከዋል፡፡ የተላከው ባሪያ ብዙም ሳይቆይ ላብ በላብ ሆኖ በፍርሀት እየተንቀጠቀጠ ይመለሳል፡፡
ጌታውም ምን እንደሆነ ሲጠይቀው ፦ “አንዲት ሴት በገበያው መሀከል ስትዘዋወር አየሁ፡፡ ቀረብ ብዬ ሳስተውላት ሞት ናት፡፡ እሷም ልክ እንዳዬችኝ በጣቷ የዛቻ ምልክት አሳየችኝ፡፡ ጌታዬ ሆይ፦ እባክህ ፈረስህን ስጠኝና ወደ ሳማራ ከተማ ሸሽቼ ሞትን ላምልጣት፡" አለው።
ባለፀጋውም ለባሪያው ፈረሱን ሰጠው፡፡
ባሪያውም ሞትን ሽሽት ወዲያውኑ ፈረሱ ላይ ወጥቶ ሽምጥ እየጋለበ ወደ ሳማራ ከተማ ገሰገሰ።
ባለፀጋውም የሚያስፈልገውን ነገር ራሱ ለመገብዬት ከጥቂት ከቆይታ በኋላ ወደ ገበያ ሄዶ ሲዘዋወር ሞትን አገኛት፡፡ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላም፦ “ቅድም ባሪያዬ ስታይው ስለምን አስፈራራሽው?” ሲል ጠየቃት፡፡ ሞትም ፈገግ ብላ፦ “እያስፈራራኹትኮ አይደለም። ዛሬ ማታ ሳማራ ከተማ ላይ ቀጠሮ ስላለን፣ እዚህ ሳየው ተገርሜ ነው” አለችው።

ፈጣሪ የቀጠራት ቀን ከደረሰች ሞትን ሸሽተህ አታመልጣትም።ከባግዳድ አመለጥኳት ያልካት ሞት- ቀድሞ ሳማራ ገብታ ትጠብቅሀለች።
"ሰብአዊነት ሊወለድ የሚችለው ከፍቅር ልብ ነው!"

በፍቅር በተሞላ ልብ መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው።የፍቅር አመለካከት ሁላችንም ውስጥ ሊኖር ይገባል።ሰብአዊነት ሊወለድ የሚችለው ከፍቅር ልብ ነው፤በፍቅር ልብ ውስጥ ጥልቅ የደስታ ስሜት ይኖራል።ትንሽ ፍቅር ለሰው ከለገሷችሁ በኃላ የሚሰማችሁ የሀሴት ስሜት አስተውላችሁ ታውቁታላችሁ?
መስፈርት በሌለው ፍቅር(unconditional love) ወስጥ ሆናችሁ የሚኖረውን ሰላም አስተውላችሁ ታውቃላችሁ?
ንፁህ ፍቅር ሊኖር የሚችለው በምክንያቶችና በመሥፈርቶች ካልታጀበ ብቻ ነው፤በሁኔታ የሚወሰን ፍቅር (conditional love) ፍቅር አይደለም የማታውቁትን ሰው መንገድ ላይ ፊት ለፊት ፈገግታውን ተመልክታችሁ የሚሰማችሁን ደስታ አስተውላችሁታል?
የወደቀን ስታነሱ የደከመን ስትረዱ የታመመን አበባ ስታበረክቱና ስጠይቁ የሚሰማችሁ የደስታ ስሜት ወሰን የለውም፤ ይህን የምታደርጉት አባታችሁ ወይም እናታችሁ ስለሆኑ አይደለም በሰውነት የምታበረክቱት ስጦታ ለእናንተ በተራው ታላቅ ደስታና እርካታና ስለሚያበረክት እንጂ።ለዚህም ነው ሰብአዊነት ሊወለድ የሚችለው ከፍቅር ልብ ነው የምላችሁ።
➦ኦሾ/Osho /
የሚሸነፍ ትግል የለም፤ የሚሸነፍ ሰው እንጂ”
:
ይገርምሃል ወንድሜ፤ በሕይወትህ ድል አድርገህ ዋንጫ ወሰድክ ማለት እዚያው የልዕልና ማማ ላይ እንደተሰቀልክ ትቀራለህ ማለት አይደለም።ብዙዎች‘ኮ ሲወጡ መውረድን ይረሱታል፡፡ለሚወጣ ሰው ግን መውረድ የጥላውን ያህል ቅርብ ነው፡፡ ‹እኖራለሁ ብለህ ሥራ፤ እሞታለሁ ብለህ ኑር› ሲባል አልሰማህም? መውረድን የረሳ ባለ ሥልጣን፣ ሕመምን የረሳ ጤነኛ፣ ድህነትን የረሳ ሀብታም፣ ሞትን የረሳ ነዋሪ፣ ድቀትን የረሳ ጻድቅ፣ ውርደትን የረሳ ክቡር፣ ወደረሳው ነገር ለመጓዝ እንዴት ይፈጥናል መሰለህ? ድቅድቁ ጨለማ ያለው ከሻማው ሥር ነው፡፡ወዳጄ በዚህ ዓለም ላይ የማይነጠቅ የተጨበጠ፣የማይንሸራተት የተረገጠ የለም፡፡ nothing for granted ይሉ የለም ። የጨበጥክበት እጅህ፣ የረገጥክበት እግርህ አንድ ቀን ይዝላል፡፡የትናንት አይበገሬነትህ፣ የትናንት ጀግንነትህ፣ የትናንት ክብርህ፣የትናንት አሸናፊነትህ፣ የትናንት ተፈሪነትህ በዛሬ ጥረት ካልታገዘ ታሪክና ቅርስ እንጂ ድልና ውጤት አይኖርህም፡፡ድል ማለት ጥረትና ዕድል የሚገናኙባት አጋጣሚ ናት› ይላሉ፡፡ አንተ ትታገላለህ፣ ትጥራለህ፣ ትለፋለህ፣ ትደክማለህ፣ ትወጣለህ፣ ትወርዳለህ፤ እንዲህ ባለማቋረጥ ስትታገል አንድ ቀን የአንተ የጥረትህ መንገድ ከዕድል መንገድ ጋር ይገናኝና ታቋርጠዋለህ፡፡ ያኔ አይወድቅም የተባለው ወድቆ፣ አይሸነፍም የተባለው ተሸንፎ፣ አይነቀነቅም የተባለው ተነቅንቆ፣አይፈርስም የተባለው ፈርሶ፣ አይነካም የተባለው ተነክቶ ቦታውን ሲለቅ ታየዋለህ፡፡አንተ ካልጣርክና ካልታገልክ፣ ካልሠራህና ካልሞከርክ ግን በዕድል ብቻ የሚሆን ነገር የለም። ዛሬ አላሸነፍክም? ተስፋ አትቁረጥ፤ ቢያንስ የማሸነፍ ሞራልና የማሸነፍ ተስፋ አለህና፡፡ የሚሸነፍ ትግል የለም፡፡ የሚሸነፍ ሰው እንጂ፡፡ ትግል ትግልን ይወልዳል፣ ጥረት ጥረትን ይተካል፣ ሙከራ ሙከራን ያመጣል፡፡ዛሬ አንድ አካፋ አፈር ከተራራው ላይ ስታነሣ ተራራውን አልናድከው ይሆናል፡፡ በርግጠኝነት ግን የተራራውን መልክ ቀይረኸዋል፡፡ በአካባቢው የሚያልፉ ሰዎች፣ ወይም አንተ ራስህ እንኳን የተራራው መልክ መቀየሩን ላታውቀው ትችላለህ፡፡ ተራራው ራሱ ግን ያውቀዋል፡፡ የመሬት መሸርሸር የሚባለው ግማሽ ተራራ ተሸርሽሮ አይደለም‘ኮ፡፡ ውኃ እያሳሳቀ አፈሩን በየጊዜው ሲወስደው ነው፡፡ ምናልባትም ምንም አታመጣም ብለው ሰዎች ይነግሩህ ይሆናል፡፡
ዳንኤል ክብረት
#ራስን ማወቅ ሌላውንም ማወቅ ይሆናል!!

"...የሰው ልጅ የተፈጥሮን ህግ ሊለውጥ አይችልም። ለምሳሌ ቀንና ጨለማን፣ ሞትና ህይወትን፣ ማደግና ማርጀትን፣ ማበብና መክሰምን ሊለውጥ አይችልም። የማይለወጡ የተፈጥሮ ህግጋት አሉ ማለት ነው። እነዚህን አሜን ብሎ መቀበል አንዱ የደስታ ምንጭ ማለት ነው። አሜን ብሎ ተቀብሎ ዝም ማለት ብቻ አይደለም።

የህይወት መጨረሻ ግቡ የሰው ልጅ በዚህች አለም ላይ በሚኖርበት አጭር ጊዜ ውስጥ ተፈጥሮውን አሟልቶና ተደስቶ ለመኖር ስለሆነ፤ እያንዳንዱ ሰው ተፈጥሮውን እንዳያሟላና እንዳይደሰት የሚያደርጉትን መጥፎ ነገሮች ሁሉ ከራሱ ልብ ውስጥም ሆነ ከአካባቢው ለማስወገድ መጣር አለበት። ይህን ለማድረግ... ልበ ሙሉ መሆን ያስፈልጋል። የሰው ልጅ ክብር ዋስትና መስዋዕትነት ነው። መስዋዕትነት ደግሞ ያለ ልበ ሙሉነት መች ይሆናል። ራሳቸው እየነደዱ አልቀው ለሌላው ብርሀን የሚሆኑ ልበ ሙሉዎች ብቻ ናቸው። መፅሀፉም'ኮ እሹ ታገኛላችሁ፣ አንኳኩ ይከፈትላችኋል ያለው ሌላ ሳይሆን የራሳችንን ልብ ነው። ራስን ማወቅ የመጨረሻ ጥበብ ነው።

ራስን ማወቅ ሌላውንም ማወቅ ይሆናል። ካወክ ዘንድ ለራስህ የምትሻውን ለሌላውም ትመኛለህ። ለራስህና ለሰው ልጅ ሁሉ በጎ ፈቃድና ፍቅር ይኖርሀል። ከዚህ ዕውቀት ደረጃ ላይ ስትደርስ ለምታደርገው ነገር ሁሉ ምስጋናም ሆነ ጥቅም ከሰው ዘንድ አትሻም። ልብህ ጥቅም ላይ ካተኮረ የተፈጥሮን በጎ ምግባር ትስታለህ።

#"ደራሲው" በዓሉ ግርማ