ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.58K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
ከሰው ጋር አትወዳደር። አለም ላይ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ስላሉ በውድድሩ እግሮችህ ተጠላልፈው ትወድቃለህ። ውድድርህን ከራህ ጋር አድርግ።" ዛሬህን ከትናንትናህ ጋር እያወዳደርክ ለነገም እያቀድክ መኖር!

#ከእሳት የወጣች ነፍስ
የኦሾ እይታዎች።።።።።።።።።
#ሀይማኖትና #ፖለቲካ ተመሳሳይ እብዶች ናቸዉ:: ሁለቱም አንተ ባልፈፀምካቸዉ ስህተቶች ተጠያቂ ያደርጉሃል::ገና አንተ ይችን አለም ከመቀላቀልህ በፊት የአንተ የዘር ሀረግ የሚመዘዝበት ትዉልድ ስህተት ስለ ሰራ አንተም የእሱ ዘር ነህና ወንጀለኛ ነህ ይሉሃል:: #ኦሾ /ቻንድራ ሞሃንጄ/
ተራ ዕውቀት (knowledge) ተግባራዊ አይደለም፡፡ በልምድ የካበት ጥበብ (wisdom) ግን ተግባራዊ እና ተጨባጭ ነው፡፡

ዕውቀት ተጨባጭነት ይጎድለዋል፡፡ ጥበብ ወይም ብልህነት ግን ወደ መሬት የወረደ እና ተጨባጭ ነው፡፡

ዕውቀት ተራ የቃላት ጨዋታ ነው፤ ጥበብ እና ብልህነት ግን ከሕይወት ልምድ የተጨለፉ ናቸው፡፡
Osho/ኦሾ
የትኛውም መሻትና ፍላጎትህ ወይም ውድቀትህና ስኬትህ በአንተ ማንነት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚገለጥ እውነት ነው::
ስለዚህ አንተ ከምታውቀውና ከምታምነው በላይ ሌላ ማንነት አለህና እሱን ፈልገህ አግኝ::''
።።።።
#ተዓምራት እና ጣዖታት
ማንበብ ፊደልና ቁጥር መለየት አይደለም!
መማር ጥቁር ጋዋን እና መነሳነስ ማድረግ አይደለም!
ንቃተህሊና የምስክር ወረቀት መያዝ አይደለም!

ማወቅ አራቱን የሂሳብ ስሌቶችን ወይም የካልኩለስ ጥበብን መረዳት አይደለም። እውቀት ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ወይም ረዣዥም ድልድዮች መገንባት አይደለም። መለወጥ እጅግ ፈጣን የሆኑ ማይክሮቺፖችን መፈልሰፍ አይደለም። ወይም ከድምፅ ፍጥነት የፈጠኑ ኮንኮርድ አውሮፕላኖች መፈብረክ አይደለም። መሰልጠን ትላልቅ ከተማዎችን፣ ቅንጡ ተሽከርካሪዎችን መስራት አይደለም።

ማንበብ መንገድ ነው። መድረሻው የብርሃን ልብ፣ አስተዋይ አእምሮ ነው። መማርህ እንዲህ ካላደረገህ ተወው ይቅርብህ። ማወቅህ ለክፋትህ መሳሪያ ከሆነ አትጠጋው። የአእምሮ እውቀት በልብ ጥበብ ካልተገራ ሁሉም ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ ነው። አእምሮ መሳሪያ ልብ ደግሞ ባለቤት ነው። ልባችን በሚመራን በዚያ መንገድ አእምሮአችን ያድርሰን። እውቀት በጥበብ ልጓም ካልተበጀለት ግን በዚያ ከፍተኛ አደጋ አለ! ሁሌም ቢሆን አለም የምትታመሰው ልባቸውን፣ ሰብአዊነታቸውን ችላ ብለው አእምሮአቸውን ብቻ ባሰለጠኑ ክፉ ሰዎች ነው። ታሪኩ ትላንትም፣ ዛሬም፣ ነገም ይኼው ነው። እራሳችንን ሳንለውጥ አለምን ብንለውጥ ድካማችን ሁሉ ረብ ቢስ ነው። መለወጥ ከራስ ይጀምራል።
በእውነት ጎዳና ለመሄድ መወሰን በእሳት ላይ የመራመድ ያህል ነው ። እሳቱ ይፈጃችኋል።
ከእሳቱ የሚተርፈው ትንሽ አካላችሁ የእናንተ እውነተኛ ማንነት ነው።
እሳቱ የሚበላው በሙሉ ግን ዋጋ ቢስ እና በሌሎች የተጫነባችሁ ማንነታችሁ ነው ። ማንም እውነትን ሊያቃጥልም ሆነ ሊያጠፉ አይቻለውም ።
እውነትን ለማግኘት የግድ ሸክማችሁን ማራገፍ ይኖርባችኃል።

#Osho/ኦሾ

#እውነት፥እምነትና ሕይወት
ከማያውቀው ነገ ተበድሮ ዛሬ ሲጨነቅ የሚኖርና መኖሩን ሳያውቅ የሚሞት ፍጡር ሰው!!
* * *
በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡
* * *
#ሜሎሪና
#በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)
ወደ ኋላ ቀርታችሁ አልዘገያችሁም
ወደ ፊትም ሄዳችሁ አልፈጠናችሁም
የኒውዮርክ የሰዓት አቆጣጠር ከካሊፎርኒያ በ3 ሰዓት ይቀድማል፡፡ ይህ ማለት ግን ካሊፎርኒያ ቀርፋፋ ናት ማለት ግን አይደለም።
አንዳንዶቹ በ22 አመታቸው ትምህርታቸውን ጨርሰው ይመረቃሉ ግን ትክክለኛውን ስራ እስከሚያገኙ ድረስ 5 አመት ሊጠብቁ ይችላሉ..
አንዳንዱ በ25 አመቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ ግን በ50 አመቱ ሊሞት ይችላል። አንዳንዱ ደግሞ በ50 አመቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ ነገር ግን በ90 አመቱ ሊሞት ይችላል።
አንዱ ወንደላጤ ሲሆን እኩያው አግብቶ ሊሆን ይችላል።
ኦባማ በ55 አመቱ ከፕሬዜዳንትነት ጡረታ ቢወጣም ትራምፕ ግን ይህንን ስራ አሃዱ ብሎ የጀመረው በ70 አመቱ ነው።
ሁሉም እዚህ አለም ላይ እየኖረ ያለው በራሱ የጊዜ ኡደት ውስጥ ነው።
አጠገብህን የከበቡት ሰዎች ገሚሱ የቀደመህ ሊመስልህ ይችላል ገሚሱ ደግሞ ከኋላህ ሊመስልህ ይችላሉ ነገር ግን ሁሉም የራሱን ሩጫ በራሳቸው ጊዜ እየሮጡ ነው..ስለዚህ በዙሪያ ያሉትን ሰዎች አትመቀኝባችው እንዲሁም አትሳቅባቸው!
ሁሉም በራሱ የጊዜ ኡደት ውስጥ በመሆኑ ከራስህ ጊዜ ጋር አታነፃፅራቸው።
ህይወት ማለት ትክክለኛውን ነገር በትክክለኛው ጊዜ ማድረግ ማለት ነው!!
#ዶ/ር ምህረት ደበበ
እኛው ነን
(ጌትነት እንየው )

እኛው ነን የገፋን እኛው ነን የከፋን
እኛው ነን ያጠፋን እኛው ነን የጠፋን
ከዘመን ጋር አብሮ መዘመን ተስኖን
ሰፊ ሀገር ይዘን በሀሳብ የጠበብን
በፍቅር ተሳስቦ አብሮ መራመድ አቀበት የሆነብን
ቂም እየቆጠርን ቂም እየመነዘርን
በዛሬ መንጋጋ የትላንት ድርቆሽ የምናመነዥክ
በዛሬ ምድጃ የትላንቱን አመድ ታቅፈን የምንሞቅ
በአንድ ላይ ከመጓዝ በየፊና ሩጫ አረፋ የምንደፍቅ

እኛው ነን እኛው ነን
ከእምነት የተፋታን ከፈጣሪ የራቅን
እኛው ተጋፊዎች እኛው ተገፊዎች
እኛው አሳዳጆች እኛው ተሳዳጆች
ካሳለፍነው ህይወት ካሳለፍነው መከራ መማር የተሳነን ደመና ወራሾች
እኛው ነን እኛው ነን እኛው የዛሬዎች
የነገ የታሪክ የሀገር ባለዳዎች

እኛው ነን

በንፍገት ፣ በስስት ፣ በስግብግብ መዳፍ
ከድሆች ጉሮሮ ካ'ፋቸው መንጭቀን
ሌሎችን እረግጠን ሌሎችን ጨፍልቀን
በሌሎቹ ጀርባ በሌሎች ጫንቃ ላይ
ወደላይ መሳቡ ቅንጣት የማይጨንቀን
በማስመሰል ጥበብ በአድርባይ አንደበት በሸፍጥ የሰለጠንን
ከብዞዎች ድርሻ ተሻምተን ተናጥቀን
ለአንድ ለእራሳችን በወርቅ ላይ አልማዝ በህንፃ ላይ ህንፃ
ስንቆልል ስንከምር የማይሰቀጥጠን
የመንፈስ ድዊዎች የንዋይ ምርኮኞች
የወንበር ሱሰኞች የሆድ አምላኪዎች
ከሰውነት ወርደን በነፍስ የኮሰመንን የስጋ ቡኩኖች
የራሳችን ኃጢያት የራሳችንን ሲኦል እኛው ነን መርገምቶች

እኛው ነን!
እስቲ አፍቅሩ !
(አሌክስ አብርሃም )

በምድር ላይ ያልባከነ ምርጥ ጊዜ ማለት በፍቅር ያሳለፋችኋቸው ደይቃዎች ናቸው … እስቲ አፍቅሩ …መልካችሁ ምንም ይሁን አፍቅሩ …እድሚያችሁ ምንም ይሁን አፍቅሩ … ኑሮ ቢከብዳችሁ ራሱ ኑሮ ከከበደው ጋር ተፋቀሩ …ፍቅር ተያይዞ ማደግ ብቻ አይደለም ተያይዞ መውደቅም ነው ! በጥላቻና በድርቅና ከመቆም ለፍቅር መውደቅ ተለማመዱ !
💗
``አገር፣ህዝብ ፣ፖለቲካ በሚል ግዙፍ ነገር ውስጥ እየዳከራችሁ የጤፍ ቅንጣት አክላችሁ አትሙቱ … ፍቅር የሚባል እጅግ ረቂቅ አየር ወደውስጥ ሳቡና አገር አክሉ ! የማታፈቅሩበት አገር ምን ያደርግላችኋል? ገብስ ልታመርቱበት ነው? …የማታፈቀሩበት ህዝብ ምን ያደርግላችኋል ቀብራችሁን እንዲያደምቅ ነው …?የማታፈቅሩበት ፖለቲካ ምን ያደርግላችኋል? ፓርላማ ልተሰየሙበት ነው? …የማታፈቅሩበት ህገ መንግስት ምን ያደርግላችኋል ሲጀመር ይልተጣመራችሁትን መገንጠል እንዲፈቅድላችሁ ነው? …
:
ተያዩ ተነጋገሩ ትዝብት ጥርጣሬ ፍርሃትን ወደዛ ጣሉና በፈገግታ በተሞላ ፊታችሁ የወደዳችኋትን ወደእናተ ሳቡ የወደድሽውን ወደራስሽ ጋብዥ ! ተቃቀፉ …አብራችሁ ቡና ጠጡ … ተደዋወሉ ‹ቴክስት› ተላላኩ ! በሚወዷችሁ ሰዎች እቅፍ ውስጥ ስጋችሁ ይድላው !ነፍሳችሁም ደስ ይበለው !ተሳሳሙ …ለመጨረሻ ጊዜ በፍቅር ከተሳማችሁ ስንት ቀን ስንት ወር ስንት ዓመት ሆናችሁ … ኪሳራ !
:
ህግ ስርዓትና አሉባልታ አትፍሩ …ደግሞ አትንቀዠቀዡ! ብቻ ማፍቀርም መፈቀርም ፈልጉ ..ራሳችሁን ብቻ ቀለል አድርጉት አየሩ ራሱ ወደየት እንደሚወስዳችሁ ያውቃል !…ለምርጫችሁ ብዙ መስፈርት አታስቀምጡለት ….ፈልጉ ተፈላለጉ ያለምንም ወሰን በነፍስም በስጋም ወደፍቅር ድንበር ቅረቡ ….ፀብ አትፍሩ መለያየት አያስጨንቃችሁ …ዘላለማዊ ጥላቻም ሆነ ጊዚያዊ ፍቅር ብሎ ነገር የለም ! አልፎ ሂያጅ ፍቅር የሚባል ነገር የለም ፍቅር ወደየትም አያልፍም …ፍቅር ራሱ መንገዱ ነው ! ተራመዱበት ፍጠኑበት …ብቻ አትቁሙ ! መንገድ ላይ በቆማችሁ ቁጥር ለሌላው እንቅፋት ትሆናላችሁ !
:
ማህበረሰቡ የሰከነ... ረጋ ያለ... ቁም ነገር …ሁነኛ ሰው… የማይሆን ሰው…የሚሆን ሰው… እያለ ከጫነባችሁ የጉልት ሂሳብ ውጡና እብደታችሁ በሰፈረላችሁ ልክ ከዚህ ነዝናዛ አዕምሮ ተላቃችሁ በልባችሁ ደስታ ኑሩ ! ካለፈ ታሪካችሁ ውጡ …ካለፈ ህመማችሁ አገግሙ … በዘፈን ስም ሙሾ ከሚያስወርዱ ሙዚቃዎች ራቁ ….እንዴ…! …እንዳሰባችሁና እንደተመኛችሁ እስከመቸ ትኖራላችሁ ?! ባለፈ ጥላቻችሁ ከሬዲዮና ከምናምን በተለቃቀመ የመካካድና ተጎዳሁ ተሰበርኩ ታሪክ (ያውም እንደዛም ብለው ማፍቀር ላያቆሙ) በፍርሃት ተሸማቃችሀ ትኖራላችሁ እንዴ ?!
:
አንዳንዴማ ልብሳችሁን ጣሉ …እራቁታችሁን መኖር ተለማመዱ …እራቁታችሁን ከሆናችሁ ልብስ አይኖራችሁም… ልብስ ከሌላችሁ ኪስ አይኖራችሁም ….ኪስ ከሌላችሁ በኪስ ከሚያዙ ነገሮች ሁሉ ነፃ ናችሁ … ምንም ነገር ልትይዙ የምትችሉት ብቸኛ ነገር ልባችሁ ብቻ ይሆናል … እንደልባችሁ ኑሩ ! የነፍሶቻችሁ ባሉን ላይ የተቋጠሩ ክሮችን ከራሳችሁ የፍርሃት እጅም ይሁን ከሌሎች ሰዎች የቁጥጥር እጅ ላይ አላቁና ወደሰፊው ህዋ ልቀቋቸው በአየሩ ላይ ይንሳፈፉ !
👉አሌክስ አብርሃም 👌
#ሰው ከሰውነት ደረጃ ሊያልፍ ፣ ከመልአክትም ከፍ ሊል እንደሚችል ሁሉ ከእንስሳትም ያነሰ ይሆናል።"
/ኦሾ/Osho
#አንድ ሰዓሊ የሚስለው የሚወደውን ነገር ነው፣አንድ ደራሲ የፃፈው የወደደውን ነው፣እግዚሃብሔርም ስለሚወዳችሁ እናንተን ስሎዋል።ለዛም ነው !ህይወት የሰጣችሁ።ይህን ስታምኑ ራሳችሁን፤ወዳጃችሁን፤ልጆቻችሁን፤የትዳር
አጋራችሁን፤ትወዳላችሁ ።
/ኦሾ/OSHO/
#ህያውነት ቀጥር 3
"እንደ ሀገር ክፉ የተባለውን ነገር ሁሉንም ሞክረናል አሁን የሚቀረን እንደ ሰው መልካም ማድረግ ብቻ ነዉ''
:
#ዶ/ር አለማዬሁ ዋሴ
ጦቢያ ግጥም በጃዝ ላይ ቀርቦ ከተናገረው የተወሰደ
።።።///።።። ፍቅር።።።///።።።
#ፍቅር ፀረ-ህግ ነው ፣ ፍቅር ፀረ-ስበት ነው ፍቅር ፀረ-ሳይንስ ነው ፍቅር ከሁሉም ሎጂክ እና ህግ በተቃርኖ ውስጥ ነው።
///።።። ኦሾ።።።///
ሴትና ፈጣሪ★
💕
ከፈጣሪህ በላይ ውደደኝ አለችኝ
እሱን በመፈለግ ስደክም እያየችኝ።

እኔን አምልክ አለኝ እሱም ተደብቆ
ሕይወቴ እንደጫማ በእሷ መንገድ አልቆ።

እናም ግራ ገባት ነፍሴ መሃል ሆና
አምላኬ ከሴት ጋር እየተቀናና።

ሴትና ፈጣሪ

#ከጲላጦስ (ኃይለጊዮርጊስ ማሞ)
#"ወደ ራሳችሁ ተመለሱ ራሳችሁን አድምጡ ውስጥን መከተል ፍፁም ወደ ሆነ ምልዐት መምጣት ነው።
ወደ ራሳችሁ ካልተመለሳችሁ ከውልደት እስከሞት ይዛችሁ የምትጓዙት የእናንተ ያልሆነ አርቲፊሻል ማንነትን ነው።"
:
ኦሾ/Osho
ከጅምሩ እራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ ማወዳደር ትልቅ በሽታ ነው ፤ እንደ ካንሰር ነው ነፍስህን እያጠፋ ይሄዳል? ምክንያቱም እያንዳንዱ ግለሰብ ልዩ ነው ፣ እና ማወዳደር አይቻልም። እኔ እኔ ነኝ አንተም አንተ ነህ ፡፡ በዓለም ላይ አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለምና ፡፡
* ኦሾ *
#አለማችን በጣም እየተጎዳች ያለችው በመጥፎ ሰዎች ክፋት ብቻ ሳይሆን በጥሩ ሰዎች ዝምታ ነው። "
/ናፓሊዮን/
#ለምታገኘው ደስታም ሆነ ለሚደርስብህ ችግር ተጠያቂው አንተና አንተ ብቻ ነህ ማንም ላንተ ህይወት ሃላፊነቱን አይወስድም...የራስህን ገነት የምትገነባውም ሆነ እራስህን በገሃነም እሳት የምትጥለው አንተ እና አንተ ብቻ ነህ ።

ኦሾ /Osho
የበታችነት ስሜት በሽታ ነው፤ ይህን የበታችነት ስሜት ለመደበቅ የሚመጣው የበላይነት ስሜት ደግሞ የባሰ በሽታ ነው። አብዛኛውን ጊዜ መድሀኒቱ ከበሽታው ይልቅ አደገኛ ነው። አንድ ሰው ተፈጥሯዊ ሚዛኑን መጠበቅ የሚችለው ከበታችነትም ሆነ ከበላይነት ስሜት ነፃ ሲሆን ነው።

ኦሾ/osho