ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.58K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
"ማንም ሰው የበላይ አይደለም ማንም ሰው የበታች አይደለም እንዲሁም ማንም ሰው እኩል አይደለም። ሰዎች ሁሉ የተለያዩ ናቸው። አንዱ ከአንዱ አይወዳደሩም ፤ አይነፃፀሩም።
#አንተ አንተን ነህ። እኔ ደግሞ እኔን ነኝ። "
•••
#OSHO/ኦሾ
#የኦሾ እይታዎች
አንድ ግለሰብ ለመሆን ከሁሉ የላቀ ድፍረት የተሞላበት መሰረት ያስፈልጋል። "መላው አለም እኔን መቃወሙ አያስጨንቀኝም። ዋናው ነገር ተሞክሮዬ ተቀባይነት ማግኘቱ ነው። ምን ያህል ሰዎች ከእኔ ጋር እንደሆኑ ለማውቅ ቁጥራቸውን አልመለከትም። ትኩረት የማደርገው በተሞክሮዬ ተቀባይነት የሌላ ሰው ቃላትን እንደበቀቀን እየደገምኩ መሆን አለመሆኔ ወይም የምናገራችው ነገሮች ከገዛ ራሴ ተሞክሮ የመነጨ መሆን አለመሆናቸው ላይ ነው።
ንግግሬ በገዛ ራሴ ተመክሮ ውስጥ ከሆነ፥ የደሜ፥የአጥንቴ እና የመቅንዬ አካል ከሆነ መላው አለም በአንድ ወገን ሊሆን ቢችል እንካን እኔ ትክክል ነኝ። የሚለው ኦሾ ምንም የሚያስጨንቀኝ ነገር የለም። እኔ ትክክል መሆኔ እንዲሰማኝ የእነሱ የድጋፍ ድምጽ አያስፈልገኝም። የሌሎች ድጋፍ የሚሹት የሌሎችን አመለካከት የያዙ ብቻ ናቸው"።
ህያውነት
#ኦሾ/OshO
እኛ ኢትዮጵያውያን ከታሪክ የተማርነው ነገር ቢኖር ከታሪክ አለመማራችንን ነው።"
ሰበዝ
#ዓለማየው እሸቴ ዋሴ
የማንዴላ ወርቃማ ምክሮች
:
#"እኔን በማስገኘው ስኬት አትገምግሙኝ፣ ይልቅስ ምን ያህል ጊዜ እንደወደቅሁ እና ለስኬት ምን ያህል ጥረት በማድረግ እንደተነሳሁ እንጅ" ውድቀት ኃጢአት አይደለም። ለመሞከር አለመቻል ነው ውድቀት ማለት። በህይወት ስንክሳር
"ታላቁ ዝና ፍጹም አለመውደቅ አይደለም፣ ነገር ግን
ትልቁ ነገር በወደቅን ቁጥር ለመነሳት የምናደርገው
ጥረት ነው።" ማንዴላ ወጣቶቹ ሲመክሩ ወጣቶች
በስኬት ማማ ላይ ፊጥ ለማለት ጥረት ማድረግ ብቻ
ሳይሆን ትከሻቸውን በማጠንከር ሊመጡ የሚችሉትን ችግሮቸ ሁሉ በመጋፈጥ በድል አድራጊነት ለመውጣት ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል ለዚህም "ትልቁን ተራራ ከወጣህ በኋላ ሌሎች ብዙ ሊወጡ የሚችሉ ተራሮች እንዳሉ መገንዘብ አስፈላጊ ነው።" በማለት አስተምረዋል።
የኦሾ ቁልፍ መልዕክት
#የተነገራችሁን ሁሉ ቀጥታ እንደወረደ አምናችሁ አትቀበሉ ከዚያ ይልቅ እውነትን በብልሃትና በንቃት ለማግኘት ሞክሩ።
/Osho/
#የኦሾ ትልቁ ጉዳይ "ራስን መሆን" ነው።ማለትም ለራስ ከፍተኛ ማስተማርአመለካከት መስጠት(ego) ነው ይላል።
ኦሾ በአንድ ወቅት ለምንድን ነው የሴት ተከታዮችህ ቁጥር በጣም ከወንዶች የበለጠው ተብሎ ሲጠየቅ ፤ ለምንድን ነው ሰይጣን መጀመሪያ ሔዋንን ያታለላት? የሚል መልስ ሰጥቶ ነበር። ወንድ ተሎ አይሰማም ተከራካሪ ነው ፤ ቢሰማም ውስጡን ነው የሚያዳምጠው ። ሰይጣን ምናልባት የኋላ ኋላ ሊያሳምነው ቢችልም እግዚአብሄር ሊደርስበት ይችል ነበር።ሴቷ ግን የምታዳምጠው ከልቧ ነው ልብ ደግሞ ፈጣን ነው። አዕምሮ ቀርፍፍ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ማሳመኛዎችን ይፈልጋል።እጅግ ሲበዛ ተጠራጣሪም ነው። በዛ ላይ የሚያቀርባቸው ጥያቄዎች (ወንዱ በአእምሮው ስለሚሰም በኦሾ ) ማብቂያ የላቸውም። ሰይጣን መጀመሪያ የተገናኘው ከተጠራጣሪው ተጠያቂ(ወንድ) ጋር ቢሆን ኖሮ ጠያቂው (ወንዱ)ሁሉንም ነገር ግልፅልፅ እስኪልለት ድረስ ማወቅ ስለሚፈልግ እስካሁን ድረስ እንኳን ጥያቄውን አይጨርስም ነበር።
ምንጭ ራስን መሆን
osho።
ፍቅር ነፍስን በሚወዱት ሰው ውስጥ መግደል ነው!
Osho/ ኦሾ
💘
ለማንኛውም የህይወት ዘርፍ የስኬት ቁልፍ ፍቅር ነው። #ዳቪንቺ ስዕልን ከምንም በላይ አፈቀራት ታወቀባትም። #ሞዛርት ሙዚቃን አፈቀራት ፥ ከፍ ከፍም አረገችው። #ሼክስፒር ስነፅሁፍ ፍቅረኛው ሆነች፥በስሟም አነገሰችው። #የፍቅር ንጉስ እየሱስ ክርስቶስ በፍቅሩ አለምን ማረከ ፥ አለም ተንበረከከችለትም።
#እውነተኛ ታላቅነት እንግዲ ሚመጣው ከማፍቀር ነው። እየሱስን መምሰል ሚቻለው በፍቅር ብቻ ነው። ቡድሃን ለመሆን ማፍቀር ግዴታ ነው። #ቡድሃ ማፍቀር ስትችል እግዚሃብሔርን መምሰል ትጀምራለህ ይላል።

ፍቅር ነፍስን በሚወዱት ሰው ውስጥ መግደል ነው ይለናል ኦሾ። ፍቅር ከስግብግብነት የፀዳ ማንነት ነው። እውነተኛ አፍቃሪ የሚያፈቅረውን ሰው ደስታ ለማየት
ለመሰዋት የተዘጋጀ ነው።
ሀዲስ አለማየው ስለ ፍቅር እንዲ ይላሉ፥ አይንን ክፉ ከማየት ምላስን ክፉ ከማውራት ጆሮንም ከመስማት ፥ምናብንም ከፉ ከማለም የማይከለክል ፍቅር ፥ ፍቅር አይደለም። ፍቅር ለ አሉታዊ ውጤት ምንም ግምት አይሰጥም። ለፍቅር አለም ሁሌም ብሩህ ናት።
ፍቅር ሙሉነትን የመፈለግ መንገድ ነው። ግን ይለናል ኦሾ ቀጥሎ ፦ እንደመሰለው እንደመሰላት እንደመሰለን እንፋቀራለን። በማይረባ መንገድ። እራስ ወዳድነትን በተላበሰ መንገድ እናፈቅራለን። ማፍቀር ግዴት ይመስል እናፈቅራለን። ጥላቻ አርግዘን እናፈቅራለን። እራስ ወዳድነትን አርግዘን እናፈቅራለን። ፈርተን እናፈቅራለን። ከዛም ሲሰለችን ስለ እውነተኛ ፍቅር መሞት ማላዘን እንጅምራለን። ባዶነት ይሰማናል። ትላንት ያፈቀርነው ዛሬ ጠላት ይሆንብናል። የማናውቀው ሰው ጠላት ሊሆነን አይችልም ። ጠላት እንኳን ጠላት ለመሆን የግድ በጓደኝነት ውስጥ ማለፍ አለበት። ልክ ያልሆነ ፍቅር ወዳጅ ሳይሆን ጠላት ያተርፋል። የማፍቀር ብቸኛው ምክንያት ፍቅር ካልሆነ ሌላው አላፊ ነውና ጭንቀትን ይወልዳል።

#ጥበብ ከጲላጦስ ቅፅ አንድ የተቀነጫጨበ
ምርጥ መንግስት ፤መንግስት ያልሆነ ነው !" #ኦሾ
"የፖለቲካ ጠቅላላ ደስታ ጠላት ውስጥ የተደበቀ ነው!"
መንግሥት በአለም ላይ የተጫነ የፖለቲከኞች አስቀያሚ ጫወታ ነው ። በዝቅተኛ የንቃት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎች ይወዱታል ። እነዚህ ሰዎች ፖለቲከኞች ይባላሉ ፤ የፖለቲከኛ ብቸኛው ደስታ ፦ መምራት ፣ስልጣን መያዝ ፣ ሰዎችን በባርነት መጠፈር ነው ።
አዶልፍ ሒትለር ራሱ በፃፈው ታሪኩ ውስጥ ብዙ እይታዎቹን አስፍሯል ።ሰውየው ትልቅ ግንዛቤ የነበረው የጠራ ፖለቲከኛ ነበር ። ማለቴ የወጣለት # ቆሻሻ ። "በስልጣን ለመቆየት ጦርነት የግድ አስፈላጊ ነው" ይላል ። ሂትለር "ጦርነት ከሌለ ሰዎች እንደማንኛውም ሰው ይመለከቱሃል ፣ጦርነት ሲኖር ብቻ ነው ጀግኖች የሚወለዱት " ይል እንደነበረ በታሪኩ ፅፎታል ።
ትክክል ነው ። ጦርነት ባይኖር ፖለቲከኞች ምን ይሆኑ ነበር? ታላቁ እስክንድር ምን ይሆን ነበር ?ናፖሊዮን ቦናፖርት ምን ይሆን ነበር?ዊኒስተን ቸርቸል ምን ይሆን ነበር ? ቤኔቶ ሞሶሎኒ ምን ይሆን ነበር ? ጆሴፍ ስታሊን ?አዶልፍ ሂትለር ራሱ ምን ይሆን ነበር? ??
#ኦሾ ፦ ህያውነት ሦስት#ንቃት
ብሩስሊ የተባለው ታዋቂው የሆሊውድ አክተር በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፦ "የምትጓዝበት መንገድ ወደ ጥሩ አሊያም ወደ መጥፎ የሚመራው አንተን እንጂ ተመልካችህን አይደለም፤የምትለብሠው ልብስ የሚያሞቀውም ሆነ የሚያበርደው አንተኑ እንጂ የሚያይህን አይደለም፤የምትበላው ምግብ የሚጣፍጠው ወይም የሚመረው አንተን እንጂ ሌላውን አይደለም። እናም አንድን ነገር ለታይታ ማድረግ ሞኞች የፈለሠፉት የመከበር ሙከራ መሆኑን ተረድተህ" በቀጥተኛው መንገድ ለመጓዝ ሞክር....!!
"ለሕይወት ክብር በመስጠት ላይ ያልተመሰረተ ማንኛውም ሃይማኖት ወይም ፍልስፍና፤ እውነተኛ ሃይማኖት ወይም ፍልስፍና አይደለም፡፡"
ከሰው ጋር አትወዳደር። አለም ላይ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ስላሉ በውድድሩ እግሮችህ ተጠላልፈው ትወድቃለህ። ውድድርህን ከራህ ጋር አድርግ።" ዛሬህን ከትናንትናህ ጋር እያወዳደርክ ለነገም እያቀድክ መኖር!

#ከእሳት የወጣች ነፍስ
የኦሾ እይታዎች።።።።።።።።።
#ሀይማኖትና #ፖለቲካ ተመሳሳይ እብዶች ናቸዉ:: ሁለቱም አንተ ባልፈፀምካቸዉ ስህተቶች ተጠያቂ ያደርጉሃል::ገና አንተ ይችን አለም ከመቀላቀልህ በፊት የአንተ የዘር ሀረግ የሚመዘዝበት ትዉልድ ስህተት ስለ ሰራ አንተም የእሱ ዘር ነህና ወንጀለኛ ነህ ይሉሃል:: #ኦሾ /ቻንድራ ሞሃንጄ/
ተራ ዕውቀት (knowledge) ተግባራዊ አይደለም፡፡ በልምድ የካበት ጥበብ (wisdom) ግን ተግባራዊ እና ተጨባጭ ነው፡፡

ዕውቀት ተጨባጭነት ይጎድለዋል፡፡ ጥበብ ወይም ብልህነት ግን ወደ መሬት የወረደ እና ተጨባጭ ነው፡፡

ዕውቀት ተራ የቃላት ጨዋታ ነው፤ ጥበብ እና ብልህነት ግን ከሕይወት ልምድ የተጨለፉ ናቸው፡፡
Osho/ኦሾ
የትኛውም መሻትና ፍላጎትህ ወይም ውድቀትህና ስኬትህ በአንተ ማንነት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚገለጥ እውነት ነው::
ስለዚህ አንተ ከምታውቀውና ከምታምነው በላይ ሌላ ማንነት አለህና እሱን ፈልገህ አግኝ::''
።።።።
#ተዓምራት እና ጣዖታት
ማንበብ ፊደልና ቁጥር መለየት አይደለም!
መማር ጥቁር ጋዋን እና መነሳነስ ማድረግ አይደለም!
ንቃተህሊና የምስክር ወረቀት መያዝ አይደለም!

ማወቅ አራቱን የሂሳብ ስሌቶችን ወይም የካልኩለስ ጥበብን መረዳት አይደለም። እውቀት ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ወይም ረዣዥም ድልድዮች መገንባት አይደለም። መለወጥ እጅግ ፈጣን የሆኑ ማይክሮቺፖችን መፈልሰፍ አይደለም። ወይም ከድምፅ ፍጥነት የፈጠኑ ኮንኮርድ አውሮፕላኖች መፈብረክ አይደለም። መሰልጠን ትላልቅ ከተማዎችን፣ ቅንጡ ተሽከርካሪዎችን መስራት አይደለም።

ማንበብ መንገድ ነው። መድረሻው የብርሃን ልብ፣ አስተዋይ አእምሮ ነው። መማርህ እንዲህ ካላደረገህ ተወው ይቅርብህ። ማወቅህ ለክፋትህ መሳሪያ ከሆነ አትጠጋው። የአእምሮ እውቀት በልብ ጥበብ ካልተገራ ሁሉም ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ ነው። አእምሮ መሳሪያ ልብ ደግሞ ባለቤት ነው። ልባችን በሚመራን በዚያ መንገድ አእምሮአችን ያድርሰን። እውቀት በጥበብ ልጓም ካልተበጀለት ግን በዚያ ከፍተኛ አደጋ አለ! ሁሌም ቢሆን አለም የምትታመሰው ልባቸውን፣ ሰብአዊነታቸውን ችላ ብለው አእምሮአቸውን ብቻ ባሰለጠኑ ክፉ ሰዎች ነው። ታሪኩ ትላንትም፣ ዛሬም፣ ነገም ይኼው ነው። እራሳችንን ሳንለውጥ አለምን ብንለውጥ ድካማችን ሁሉ ረብ ቢስ ነው። መለወጥ ከራስ ይጀምራል።
በእውነት ጎዳና ለመሄድ መወሰን በእሳት ላይ የመራመድ ያህል ነው ። እሳቱ ይፈጃችኋል።
ከእሳቱ የሚተርፈው ትንሽ አካላችሁ የእናንተ እውነተኛ ማንነት ነው።
እሳቱ የሚበላው በሙሉ ግን ዋጋ ቢስ እና በሌሎች የተጫነባችሁ ማንነታችሁ ነው ። ማንም እውነትን ሊያቃጥልም ሆነ ሊያጠፉ አይቻለውም ።
እውነትን ለማግኘት የግድ ሸክማችሁን ማራገፍ ይኖርባችኃል።

#Osho/ኦሾ

#እውነት፥እምነትና ሕይወት
ከማያውቀው ነገ ተበድሮ ዛሬ ሲጨነቅ የሚኖርና መኖሩን ሳያውቅ የሚሞት ፍጡር ሰው!!
* * *
በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡
* * *
#ሜሎሪና
#በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)
ወደ ኋላ ቀርታችሁ አልዘገያችሁም
ወደ ፊትም ሄዳችሁ አልፈጠናችሁም
የኒውዮርክ የሰዓት አቆጣጠር ከካሊፎርኒያ በ3 ሰዓት ይቀድማል፡፡ ይህ ማለት ግን ካሊፎርኒያ ቀርፋፋ ናት ማለት ግን አይደለም።
አንዳንዶቹ በ22 አመታቸው ትምህርታቸውን ጨርሰው ይመረቃሉ ግን ትክክለኛውን ስራ እስከሚያገኙ ድረስ 5 አመት ሊጠብቁ ይችላሉ..
አንዳንዱ በ25 አመቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ ግን በ50 አመቱ ሊሞት ይችላል። አንዳንዱ ደግሞ በ50 አመቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ ነገር ግን በ90 አመቱ ሊሞት ይችላል።
አንዱ ወንደላጤ ሲሆን እኩያው አግብቶ ሊሆን ይችላል።
ኦባማ በ55 አመቱ ከፕሬዜዳንትነት ጡረታ ቢወጣም ትራምፕ ግን ይህንን ስራ አሃዱ ብሎ የጀመረው በ70 አመቱ ነው።
ሁሉም እዚህ አለም ላይ እየኖረ ያለው በራሱ የጊዜ ኡደት ውስጥ ነው።
አጠገብህን የከበቡት ሰዎች ገሚሱ የቀደመህ ሊመስልህ ይችላል ገሚሱ ደግሞ ከኋላህ ሊመስልህ ይችላሉ ነገር ግን ሁሉም የራሱን ሩጫ በራሳቸው ጊዜ እየሮጡ ነው..ስለዚህ በዙሪያ ያሉትን ሰዎች አትመቀኝባችው እንዲሁም አትሳቅባቸው!
ሁሉም በራሱ የጊዜ ኡደት ውስጥ በመሆኑ ከራስህ ጊዜ ጋር አታነፃፅራቸው።
ህይወት ማለት ትክክለኛውን ነገር በትክክለኛው ጊዜ ማድረግ ማለት ነው!!
#ዶ/ር ምህረት ደበበ
እኛው ነን
(ጌትነት እንየው )

እኛው ነን የገፋን እኛው ነን የከፋን
እኛው ነን ያጠፋን እኛው ነን የጠፋን
ከዘመን ጋር አብሮ መዘመን ተስኖን
ሰፊ ሀገር ይዘን በሀሳብ የጠበብን
በፍቅር ተሳስቦ አብሮ መራመድ አቀበት የሆነብን
ቂም እየቆጠርን ቂም እየመነዘርን
በዛሬ መንጋጋ የትላንት ድርቆሽ የምናመነዥክ
በዛሬ ምድጃ የትላንቱን አመድ ታቅፈን የምንሞቅ
በአንድ ላይ ከመጓዝ በየፊና ሩጫ አረፋ የምንደፍቅ

እኛው ነን እኛው ነን
ከእምነት የተፋታን ከፈጣሪ የራቅን
እኛው ተጋፊዎች እኛው ተገፊዎች
እኛው አሳዳጆች እኛው ተሳዳጆች
ካሳለፍነው ህይወት ካሳለፍነው መከራ መማር የተሳነን ደመና ወራሾች
እኛው ነን እኛው ነን እኛው የዛሬዎች
የነገ የታሪክ የሀገር ባለዳዎች

እኛው ነን

በንፍገት ፣ በስስት ፣ በስግብግብ መዳፍ
ከድሆች ጉሮሮ ካ'ፋቸው መንጭቀን
ሌሎችን እረግጠን ሌሎችን ጨፍልቀን
በሌሎቹ ጀርባ በሌሎች ጫንቃ ላይ
ወደላይ መሳቡ ቅንጣት የማይጨንቀን
በማስመሰል ጥበብ በአድርባይ አንደበት በሸፍጥ የሰለጠንን
ከብዞዎች ድርሻ ተሻምተን ተናጥቀን
ለአንድ ለእራሳችን በወርቅ ላይ አልማዝ በህንፃ ላይ ህንፃ
ስንቆልል ስንከምር የማይሰቀጥጠን
የመንፈስ ድዊዎች የንዋይ ምርኮኞች
የወንበር ሱሰኞች የሆድ አምላኪዎች
ከሰውነት ወርደን በነፍስ የኮሰመንን የስጋ ቡኩኖች
የራሳችን ኃጢያት የራሳችንን ሲኦል እኛው ነን መርገምቶች

እኛው ነን!
እስቲ አፍቅሩ !
(አሌክስ አብርሃም )

በምድር ላይ ያልባከነ ምርጥ ጊዜ ማለት በፍቅር ያሳለፋችኋቸው ደይቃዎች ናቸው … እስቲ አፍቅሩ …መልካችሁ ምንም ይሁን አፍቅሩ …እድሚያችሁ ምንም ይሁን አፍቅሩ … ኑሮ ቢከብዳችሁ ራሱ ኑሮ ከከበደው ጋር ተፋቀሩ …ፍቅር ተያይዞ ማደግ ብቻ አይደለም ተያይዞ መውደቅም ነው ! በጥላቻና በድርቅና ከመቆም ለፍቅር መውደቅ ተለማመዱ !
💗
``አገር፣ህዝብ ፣ፖለቲካ በሚል ግዙፍ ነገር ውስጥ እየዳከራችሁ የጤፍ ቅንጣት አክላችሁ አትሙቱ … ፍቅር የሚባል እጅግ ረቂቅ አየር ወደውስጥ ሳቡና አገር አክሉ ! የማታፈቅሩበት አገር ምን ያደርግላችኋል? ገብስ ልታመርቱበት ነው? …የማታፈቀሩበት ህዝብ ምን ያደርግላችኋል ቀብራችሁን እንዲያደምቅ ነው …?የማታፈቅሩበት ፖለቲካ ምን ያደርግላችኋል? ፓርላማ ልተሰየሙበት ነው? …የማታፈቅሩበት ህገ መንግስት ምን ያደርግላችኋል ሲጀመር ይልተጣመራችሁትን መገንጠል እንዲፈቅድላችሁ ነው? …
:
ተያዩ ተነጋገሩ ትዝብት ጥርጣሬ ፍርሃትን ወደዛ ጣሉና በፈገግታ በተሞላ ፊታችሁ የወደዳችኋትን ወደእናተ ሳቡ የወደድሽውን ወደራስሽ ጋብዥ ! ተቃቀፉ …አብራችሁ ቡና ጠጡ … ተደዋወሉ ‹ቴክስት› ተላላኩ ! በሚወዷችሁ ሰዎች እቅፍ ውስጥ ስጋችሁ ይድላው !ነፍሳችሁም ደስ ይበለው !ተሳሳሙ …ለመጨረሻ ጊዜ በፍቅር ከተሳማችሁ ስንት ቀን ስንት ወር ስንት ዓመት ሆናችሁ … ኪሳራ !
:
ህግ ስርዓትና አሉባልታ አትፍሩ …ደግሞ አትንቀዠቀዡ! ብቻ ማፍቀርም መፈቀርም ፈልጉ ..ራሳችሁን ብቻ ቀለል አድርጉት አየሩ ራሱ ወደየት እንደሚወስዳችሁ ያውቃል !…ለምርጫችሁ ብዙ መስፈርት አታስቀምጡለት ….ፈልጉ ተፈላለጉ ያለምንም ወሰን በነፍስም በስጋም ወደፍቅር ድንበር ቅረቡ ….ፀብ አትፍሩ መለያየት አያስጨንቃችሁ …ዘላለማዊ ጥላቻም ሆነ ጊዚያዊ ፍቅር ብሎ ነገር የለም ! አልፎ ሂያጅ ፍቅር የሚባል ነገር የለም ፍቅር ወደየትም አያልፍም …ፍቅር ራሱ መንገዱ ነው ! ተራመዱበት ፍጠኑበት …ብቻ አትቁሙ ! መንገድ ላይ በቆማችሁ ቁጥር ለሌላው እንቅፋት ትሆናላችሁ !
:
ማህበረሰቡ የሰከነ... ረጋ ያለ... ቁም ነገር …ሁነኛ ሰው… የማይሆን ሰው…የሚሆን ሰው… እያለ ከጫነባችሁ የጉልት ሂሳብ ውጡና እብደታችሁ በሰፈረላችሁ ልክ ከዚህ ነዝናዛ አዕምሮ ተላቃችሁ በልባችሁ ደስታ ኑሩ ! ካለፈ ታሪካችሁ ውጡ …ካለፈ ህመማችሁ አገግሙ … በዘፈን ስም ሙሾ ከሚያስወርዱ ሙዚቃዎች ራቁ ….እንዴ…! …እንዳሰባችሁና እንደተመኛችሁ እስከመቸ ትኖራላችሁ ?! ባለፈ ጥላቻችሁ ከሬዲዮና ከምናምን በተለቃቀመ የመካካድና ተጎዳሁ ተሰበርኩ ታሪክ (ያውም እንደዛም ብለው ማፍቀር ላያቆሙ) በፍርሃት ተሸማቃችሀ ትኖራላችሁ እንዴ ?!
:
አንዳንዴማ ልብሳችሁን ጣሉ …እራቁታችሁን መኖር ተለማመዱ …እራቁታችሁን ከሆናችሁ ልብስ አይኖራችሁም… ልብስ ከሌላችሁ ኪስ አይኖራችሁም ….ኪስ ከሌላችሁ በኪስ ከሚያዙ ነገሮች ሁሉ ነፃ ናችሁ … ምንም ነገር ልትይዙ የምትችሉት ብቸኛ ነገር ልባችሁ ብቻ ይሆናል … እንደልባችሁ ኑሩ ! የነፍሶቻችሁ ባሉን ላይ የተቋጠሩ ክሮችን ከራሳችሁ የፍርሃት እጅም ይሁን ከሌሎች ሰዎች የቁጥጥር እጅ ላይ አላቁና ወደሰፊው ህዋ ልቀቋቸው በአየሩ ላይ ይንሳፈፉ !
👉አሌክስ አብርሃም 👌