ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media
993 subscribers
8.92K photos
102 videos
110 files
1.38K links
ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ።

#የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል
#FTM
Download Telegram
  ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ሚያዝያ ፳፰ ❖

❖ ሚያዝያ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ ሜልዮስ ሰማዕት +"+

=>ቅዱስ ሜልዮስ ልጅነቱን በመንፈሳዊ ትምሕርት
ያሳለፈ:
በጉብዝናው ወራት ፈጣሪውን ያሰበ ደግ ክርስቲያን ነው::
ይሕችን
ዓለም ከነ ክፋቷ ንቆ ኮራሳት ወደሚባል በርሃ ሔዶ
በተራራውና በደኑ ውስጥ በጾምና በጸሎት: በትሕርምትም
ለበርካታ ዓመታት
ተጋድሏል::

+በነዚህ የብሕትውና ዘመናቱ ልብሱን ፀሐይና ብርድ
ቆራርጦ ስለ ጨረሳቸው ፈጣሪው ጸጉርን አልብሳታል::
የአባ ሜልዮስ
ጸጉሩ እስከ እግሩ: ጽሕሙ እስከ ጉልበቱ ነበር::

+እድሜው ገፍቶ ሲያረጅ እንዲያገለግሉት እግዚአብሔር
ሁለት ወጣት ምስጉን ክርስቲያኖችን ላከለት:: እነርሱም
አባ ኢያሱና
አባ ዮሴፍ ይባላሉ:: 2ቱ ቅዱሳን አምላካቸውን
እግዚአብሔርንና አባታቸው ቅዱስ ሜልዮስን በፍጹም
ቅንነት አገልግለዋል::

+ከቆይታ በኋላ ግን በአካባቢው የነበሩ ጣዖት
አምላኪዎች አራዊት እናጠምዳለን ብለው በዘረጉት
መረብ ቅዱስ ሜልዮስን ያዙት::
ክርስቲያን መሆኑን ሲያውቁ "ለፀሐይ ስገድ" ብለው
ደበደቡት::

+ደቀ መዛሙርቱ ተሯሩጠው መጥተው አባታቸውን
በመከራ መሰሉት:: ክርስቶስን አንክድም ስላሉ ሁለቱንም
በሰይፍ አንገታቸውን
መቷቸው:: ቅዱስ ሜልዮስን ግን ለ15 ቀናት ካሰቃዩት
በኋላ በዚህች ቀን በቀስት በተደጋጋሚ ወግተው
ገድለውታል:: ጻድቅና
ሰማዕት ቅዱስ ሜልዮስ ብዙ ተአምራትን አድርጓል::

+ገዳዮች ግን ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ የሜዳ አህያ
ሊያድኑ የወረወሩትን ቀስት የእግዚአብሔር መልአክ
ወደነርሱ መልሶባቸው
ልብ ልባቸውን ተወግተው ሙተዋል::

❖ቸር አምላክ ከቅዱሱ ሜልዮስና ከደቀ መዛሙርቱ
በረከትን ያካፍለን::

❖ሚያዝያ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሜልዮስ ዘደብረ ኮራሳን (ጻድቅና ሰማዕት)
2.አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ (ደቀ መዛሙርቱ)
3.ቅዱስ ብስጣውሮስ ሰማዕት (ተንባላት የገደሉት)

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ አምላካችን አማኑኤል
2፡ ቅዱሳን አብርሃም ፡ ይስሐቅ ፡ ወያዕቆብ
3፡ ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
4፡ ቅዱሳን እንድራኒቆስ ወአትናስያ
5፡ ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
6፡ ቅዱሳን አባዲር ወኢራኢ
7፡ ቅድስት ሶስና

++"+ ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ:: እነሆ
እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ
ሊያገባችሁ
አለው:: አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ:: እስከሞት
ድረስ የታመንህ ሁን:: የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ::
+"+
(ራዕይ. 2:10)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://t.me/felegetibebmedia
የ2016 ዓ.ም የትንሳኤ ክብረበዓል የማስፈሰኪያ መርሀግብር በደብረዘይት ደብረመዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት የፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት አስተባባሪነት ተከናወነ።

መልካም በዓል
✝️✝️✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✝️✝️✝️

❖ ሚያዝያ ፳፱  ❖

✞✞ እንኩዋን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርሐዊ በዓለ ልደትና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ ✞✞

+"+ ተዝካረ በዓሎሙ ለቅዱሳን ቅዱስ አርስጦስ ሐዋርያ ወአባ አካክዮስ ጻድቅ +"+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዕለት ከምታስባቸው ቅዱሳን ሐዋርያው ቅዱስ አርስጦስና አባ አካክዮስ ቅድሚያውን ይይዛሉ::

+"+ አርስጦስ ሐዋርያ +"+

=>ቅዱስ አርስጦስ ከ72ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን ከጌታችን እግር ለ3 ዓመታት ቁጭ ብሎ የተማረ: ፈጣሪው ከዋለበት ውሎ: ካደረበት አድሮ: የእጁን ተአምራት ያየ: የቃሉንም ትምሕርት ያደመጠ ሐዋርያ ነው::

+ከጌታችን ዕርገት በሁዋላም በጽርሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ወጥቷል:: መጀመሪያ ከዋኖቹ ሐዋርያት ጋር በረዳትነት አገልግሏል:: ከቆይታ በሁዋላ ግን ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ብዙ ነፍሳትን ማርኩዋል:: አሕዛብንም ካለማመን ወደ ማመን አምጥቷል::

+በነዚህ ጊዜያት ጭንቅ ጭንቅ መከራዎች ደርሰውበታል:: ቅዱስ አርስጦስ ሐዋርያ በተሰጠው መክሊት አትርፎ ፈጣሪውንም ደስ አሰኝቶ በዚሕች ቀን አርፏል::

+"+ አባ አካክዮስ +"+

=>ዳግመኛ በዚህ ቀን አባ አካክዮስ አርፏል:: ቅዱሱ ከሕጻንነቱ ጀምሮ ንጽሕናን ያዘወተረ: በገዳማዊ የቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ነው:: ምሑርነቱንና ቅድስናውን የተመለከቱ ሰዎች በኢየሩሳሌም ላይ ዽዽስናን ሹመውታል::

+በመንበረ ዽዽስናውም ላይ እያለ ዕረፍት አልነበረውም:: ኢ-አማንያን ይገርፉት: ያስሩት: ያረሰቃዩትም ነበር:: ቤተ ክርስቲያን ስለ ተጋድሎው ጻድቅ: የዋሕና ንጹሕ ብላ ትጠራዋለች::

=>እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ረድኤት: ጸጋና በረከት ይክፈለን::

=>ሚያዝያ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አርስጦስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.አባ አካክዮስ ዘኢየሩሳሌም (ጻድቅና ንጹሕ)
3.አባ ገምሶ ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
2.ቅድስት አርሴማ ድንግል
3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
5.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
6.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)

=>+"+ ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው ጌታ ሆይ! አጋንንት
ስንኩዋ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት:: እንዲህም
አላቸው:- 'ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ
አየሁ:: እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም
ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችሁአለሁ::
የሚጐዳችሁም ምንም የለም:: ነገር ግን መናፍስት ስለ
ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ:: ስማችሁ ግን
በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ:: +"+
(ሉቃ.10:17-20)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/felegetibebmedia
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

❖ ሚያዝያ ፳፱  ❖

✞✞ እንኩዋን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርሐዊ በዓለ ልደትና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ ✞✞

+"+ ተዝካረ በዓሎሙ ለቅዱሳን ቅዱስ አርስጦስ ሐዋርያ ወአባ አካክዮስ ጻድቅ +"+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዕለት ከምታስባቸው ቅዱሳን ሐዋርያው ቅዱስ አርስጦስና አባ አካክዮስ ቅድሚያውን ይይዛሉ::

+"+ አርስጦስ ሐዋርያ +"+

=>ቅዱስ አርስጦስ ከ72ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን ከጌታችን እግር ለ3 ዓመታት ቁጭ ብሎ የተማረ: ፈጣሪው ከዋለበት ውሎ: ካደረበት አድሮ: የእጁን ተአምራት ያየ: የቃሉንም ትምሕርት ያደመጠ ሐዋርያ ነው::

+ከጌታችን ዕርገት በሁዋላም በጽርሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ወጥቷል:: መጀመሪያ ከዋኖቹ ሐዋርያት ጋር በረዳትነት አገልግሏል:: ከቆይታ በሁዋላ ግን ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ብዙ ነፍሳትን ማርኩዋል:: አሕዛብንም ካለማመን ወደ ማመን አምጥቷል::

+በነዚህ ጊዜያት ጭንቅ ጭንቅ መከራዎች ደርሰውበታል:: ቅዱስ አርስጦስ ሐዋርያ በተሰጠው መክሊት አትርፎ ፈጣሪውንም ደስ አሰኝቶ በዚሕች ቀን አርፏል::

+"+ አባ አካክዮስ +"+

=>ዳግመኛ በዚህ ቀን አባ አካክዮስ አርፏል:: ቅዱሱ ከሕጻንነቱ ጀምሮ ንጽሕናን ያዘወተረ: በገዳማዊ የቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ነው:: ምሑርነቱንና ቅድስናውን የተመለከቱ ሰዎች በኢየሩሳሌም ላይ ዽዽስናን ሹመውታል::

+በመንበረ ዽዽስናውም ላይ እያለ ዕረፍት አልነበረውም:: ኢ-አማንያን ይገርፉት: ያስሩት: ያረሰቃዩትም ነበር:: ቤተ ክርስቲያን ስለ ተጋድሎው ጻድቅ: የዋሕና ንጹሕ ብላ ትጠራዋለች::

=>እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ረድኤት: ጸጋና በረከት ይክፈለን::

=>ሚያዝያ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አርስጦስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.አባ አካክዮስ ዘኢየሩሳሌም (ጻድቅና ንጹሕ)
3.አባ ገምሶ ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
2.ቅድስት አርሴማ ድንግል
3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
5.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
6.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)

=>+"+ ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው ጌታ ሆይ! አጋንንት
ስንኩዋ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት:: እንዲህም
አላቸው:- 'ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ
አየሁ:: እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም
ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችሁአለሁ::
የሚጐዳችሁም ምንም የለም:: ነገር ግን መናፍስት ስለ
ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ:: ስማችሁ ግን
በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ:: +"+
(ሉቃ.10:17-20)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://t.me/felegetibebmedia
ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ

ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ባሉት ዕለታት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚፈጸመው መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ልክ እንደ መጀመሪያው የትንሣኤ ሥርዓት ኾኖ ይከናወናል፡፡ ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ሳምንቱ እሑድ ድረስ የሚገኙት ዕለታትም ‹ሰሙነ ፋሲካ› ወይም ‹ትንሣኤ› እየተባሉ ይጠራሉ፤ የየራሳቸው ምሥጢራዊ ስያሜም አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም በአጭሩ እንደሚከተለው እንመለከታለን፤

ሰኞ

የትንሣኤው ማግሥት ዕለተ ሰኞ ‹ፀአተ ሲኦል› ወይም ‹ማዕዶት› ትባላለች፡፡ ይህቺውም ጌታችን በትንሣኤው ነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮ ለማስገባቱ መታሰቢያ ናት (ዮሐ. ፲፱፥፲፰፤ ሮሜ. ፭፥፲-፲፯)፡፡

ማክሰኞ

ይህቺ ዕለት፣ ለሐዋርያው ቶማስ መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቶማስ› ተብላ ትጠራለች፡፡ የትንሣኤው ዕለት እሑድ ማታ ጌታችን በዝግ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ሲገለጽ ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፡፡ በመጣ ጊዜ ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን ቢነግሩት ‹‹ሳላይ አላምንም›› ብሎ ነበር፡፡ በሳምንቱ እርሱ በተገኘበት ጌታችን በድጋሜ ለሐዋርያት ተገለጸ፡፡ ስለዚህም ይህቺ ዕለት በሐዋርያው ቶማስ ስም ተሰይማለች (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡

ረቡዕ

ጌታችን ከሞተና ከተቀበረ ከአራት ቀናት በኋላ ከመቃብር ጠርቶ ላስነሣው ለአልዓዛር መታሰቢያ ናት፡፡ በክርስቶስ ሥልጣን የአልዓዛርን ከሞት መነሣት አይተው ብዙ ሕዝብ በጌታችን ስለ አመኑ ዕለቲቱ (ረቡዕ) ‹አልዓዛር› ተብላ ትታሰባለች (ዮሐ. ፲፩፥፴፰-፵፮)፡፡

ኀሙስ

ይህቺ ዕለት ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ (አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዓመት ሲፈጸም) ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ፤›› ተብሎ ቃል የተገባለት የአዳም ተስፋው ተፈጽሞ ከነልጅ ልጆቹ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመግባቱ መታሰቢያ ኾና ‹የአዳም ኀሙስ› ወይም ‹አዳም› ተብላ ትከበራለች (ሉቃ. ፳፬፥፳፭-፵፱)፡፡

ዐርብ

የትንሣኤ እሑድ ስድስተኛዋ ዐርብ ደግሞ በክርስቶስ ደም ለተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቤተ ክርስቲያን› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱፤ ሐዋ. ፳፥፳፰)፡፡

ቀዳሚት ሰንበት

በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ቀዳሚት ሕዝቡ ከአንዳንዱ በቀር ገበያ እንኳን ስለማይገበያይባት ‹የቁራ ገበያ፣ የገበያ ጥፊያ› ተብላ ትጠራለች፡፡ በቤተ ክርስቲያን ደግሞ ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው በገንዘባቸውና ጕልበታቸው ላገለገሉት፤ በስቅለቱ ጊዜ እስከ ቀራንዮ ድረስ ለተከተሉት፤ በትንሣኤው ዕለት በሌሊት ወደ መቃብሩ ሽቱና አበባ ይዘው ለገሰገሱት፤ በትንሣኤውም ጌታችንን ከዅሉ ቀድሞ ለማየት ለበቁት ሴቶች መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቅዱሳት አንስት› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፭፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፫፥፳፯-፴፫፤ ፳፬፥፩-፲)፡፡

እሑድ ሰንበት

በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብላ ትዘከራለች፡፡ ከላይ እንደ ተጠቀሰው ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት ‹‹በኋላ እናንተ ‹አየን› ብላችሁ ልትመሰክሩ፤ ልታስተምሩ፤ እኔ ግን ‹ሰምቼአለሁ› ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም›› አለ፡፡

ስለዚህም የሰውን ዅሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት በመካከላቸው ቆመ፡፡ ቶማስንም ‹‹ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ፤›› ብሎ አሳየው፡፡

እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ ‹‹ጌታዬ፣ አምላኬ ብሎ መስክሮ›› የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ፡፡ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብሎ ይጠራል፤ ይከበራል (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡

ብርሃነ ትንሣኤውን የገለጸልን አምላካችን ለብርሃነ ዕርገቱም በሰላም ያድርሰን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡