ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media
994 subscribers
8.92K photos
102 videos
110 files
1.38K links
ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ።

#የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል
#FTM
Download Telegram
በትላንትናው ዕለት በደብረዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት የታላቁ መልአክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ክብረበዓል በሰላም ተከብሮ አልፏል።

#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
#FTM
ስለትሕትና የሚነገሩ ቃላት ሁሉ ምን ያህል የተደነቁ ናቸው!
ትሕትና ሰይጣን እንዲገዛ ('ገ' ጠብቆ ይነበብ) ያደርገዋል። ይህ በታላቁ አባት አባ መቃርዮስ ሕይወት ግልፅ ሆኖ እናገኘዋለን። ሰይጣን ተገልጾ አባ መቃርዮስን እንዲህ አለው " ከአንተ መራቅ እፈልጋለሁ። መቃርዮስ እኛ ማድረግ የምንችለው ነገር ግን አንተ የማታደርገው ምንድን ነው? አንተ ትጾማለህ እኔም እንደ እንተ አልበላም፤ ነቅተህ ትጠብቃለህ እኔም አልተኛም፤ አነተ በበርሃ ብቻህን ትኖራለህ እኔም እንደ አንተ አደርጋለሁ ነገር ግን በእንድ ነገር አሸነፍከኝ" አለው። አባ መቃርዮስም በምን እንዳሸነፈው እንዲነግረው ሰይጣንን ጠየቀው። ሰይጣንም '' በትሕትና አሸነፍከኝ '' አለው። ይህ ግልፅ ነው ሰይጣን ትሑት መሆን አይችልም። ሁልጊዜም ለራሱ ክብር ይሰጣል። ለዚህም ነው ትሕትና ሰይጣንን የሚያሸንፈው። ሰይጣን ገንዘቡ ማድረግ የማይችለውን ትሕትና ቅዱሳን ገንዘባቸው አድርገዋል።

የሚየምኑትን ከማያምኑ ወገኖች፤ የእግዚአብሔር የሆኑ ወገኖችን የእግዚአብሔር ካልሆኑት የሚለያቸው ጥበብ ይሄ ነው። ሰይጣን ገንዘቡን ወዳጅ ነው፤ ማንም ወገን ገንዘቡን ከያዘበት ከእርሱ አይርቅም ስለዚህ የእግዚአብሔር ወገን መሆን ከፈለግህ የሰይጣንን ገንዘቡን መልስለትና የእግዚአብሔር ልጆች የያዙትን ገንዘብ ገንዘብህ አድርግ። የሰይጣን ገንዘቡ ትዕቢት፣ ራስን ማግነን፣ ከንቱ መታበይ ሲሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ገንዘብ ትህትና ነው።

#ብጽእ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
'የሕይወት መዓዛ ከተባለው መጽሐፍ የተወሰደ'
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞ ✞ እንኩዋን ለአራቱ ቅዱሳን አበው ሰማዕታት
ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ✞

=> #4ቱ_ቅዱሳን አበው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ሲሆኑ
ስማቸው #አባ_አክራ : #አባ_ዮሐንስ : #አባ_አብጥልማ
እና #አባ_ፊልዾስ ይባላሉ:: ከመከራ ዘመን በፊት
(ማለትም በቀደመ ሕይወታቸው) ካህናትና ሃብታሞች
ነበሩ:: ሀብቱ ግን በሥራ ብቻ የተገኘ ነው::

+ታዲያ ቅዱሳኑ በያሉበት ሆነው በሀብታቸው እንግዳ
እየተቀበሉ: ድሆችን እያበሉ: በክህነታቸው ደግሞ
እያስተማሩና እየናዘዙ ትጉሃን ስለ ነበሩ በሰውም ሆነ
በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ነበራቸው:: በእንዲህ ያለ
ግብር ሳሉ ዘመነ ሰማዕታት አሐዱ አለ:: "ክርስቶስን ካዱ:
ለጣዖት ስገዱ" እያሉ መኩዋንንቱና ነገሥታቱ ሕዝበ
ክርስቲያኑን ያሰቃዩ ገቡ::

+በዚህ ጊዜ 4ቱ ቅዱሳን አንድ ነገር መከሩ:: በየእሥር
ቤቱ የተጣሉ ክርስቲያኖችን ለማገልገል ቆረጡ:: እግረ
መንገዳቸውን እያስተማሩ እሥረኞችን ያጽናኑ ገቡ::
የራበውን ያበላሉ: የተሰበረውን ይጠግናሉ: በቁስሉም ላይ
መድኃኒትን ያደርጉ ነበር:: የመከራው ዘመን ግን እየረዘመ:
ግፉም ከልክ እያለፈ መጣ::

+በዚህ ጊዜ 4ቱ ቅዱሳን ትልቁንና የመጨረሻውን ውሳኔ
አስተላለፉ:: ከሰማዕታት ወገን ይቆጠሩ ዘንድ
መርጠዋልና: ክርስቶስን በሞቱ ይመስሉት ዘንድ ሽተዋልና:
የሩጫቸው መጨረሻ ሰማዕትነት እንዲሆን መረጡ::

+አራቱም ያላቸውን ንብረት ሁሉ ሰብስበው ለነዳያን
አካፈሉ:: በትከሻቸው ካለች አጽፍ በቀር ስባሪ ገንዘብ
ከሃብታቸው አላስቀሩም:: ከዚያ ጉዞ ወደ ምስክርነት
አደባባይ (ዐውደ ስምዕ) አደረጉ::

+በዙፋኑ የተቀመጠው የመኮንኑ ግርማ: መሬት ላይ
የፈሰሰው የወገኖቻቸው ደም: የሠራዊቱ ድንፋታ ቅዱሳኑን
አላስፈራቸውም:: በይፋ "ክርስቲያን ነን" ሲሉ ተናገሩ::
በዘመኑ እንዲሕ ብሎ መናገር አንገት የሚያስቆርጥ ትልቅ
ድፍረት ነበር::

+መኮንኑም ከበጐ ሃይማኖታቸው ይለያቸው ዘንድ በእሳት
አቃጠላቸው:: እግዚአብሔር አዳናቸው:: በቀስትም:
በስለትም: በብረትም ለቀናት አሰቃያቸው:: ቅዱሳኑ ግን
አምላካቸውን አምነው ሁሉን በአኮቴት ተቀበሉ::
በመጨረሻ ግን በዚሕች ዕለት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው
ተገድለዋል:: ስለ ምጽዋታቸው: በጎ አገልግሎታቸውና
ሰማዕትነታቸው ጻድቅ: ፈራጅ ከሆነ ፈጣሪ አክሊልን
ተቀብለዋል::

=>የበረከት አምላክ ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን::

=>ሰኔ 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን አበው ሰማዕታት (አባ አክራ: አባ ዮሐንስ: አባ
አብጥልማ: አባ ፊልዾስ)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ስምዖን ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት

=>+"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ
አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ:
ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ
አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል
የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ
ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ
መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በጀርመን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ከሆኑት ከአምባሳደር ፈቃደ በየነ ጋር ተወያዩ።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ ሰኔ ፲፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ. ም በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተገኝተው ከአምባሳደር ፈቃዱ በየነ በጀርመን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ተወያይተዋል።

በጉብኝታቸውም ወቅት ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የጀርመንና አካባቢውና የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ የኢምባሲው የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።
ወቅታዊ መልዕክት

በአንዳንድ ማኅበራዊ ገጾች እየተዘዋወረ የሚገኘው እና በብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ስም ተፈርሞ እንደወጣ በማስመሰል የተለቀቀው ከዚህ በታች የሚታየው ደብዳቤ ፍጹም የሐሰትና ሆን ተብሎ ተቀነባብሮ በፎርጅድ ተሰርቶ የተለጠፈ መሆኑን እንገልጻለን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት።
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ሰኔ ፲፬ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም

ሀሰተኛ መረጃዎችን እንቃወም

መልካም ጊዜ
#ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
#FTM