ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media
991 subscribers
8.84K photos
102 videos
110 files
1.35K links
ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ።

#የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል
#FTM
Download Telegram
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምስራቅ ሸዋ ሀገረስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በ8 ወረዳዎች በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ያስተማራቸውን 6997 ተማሪዎችን የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የማጠቃለያ ፈተና መርሐግብር እሁድ 29/11/2016ዓ.ም አከናወነ።
በቢሾፍቱ እና አከባቢው ቤተክህነት በተካሄደው መርሐግብር በደ/መ ቅዱስ ሚካኤል እና ደ/ብ ቅ/ ገብርኤል ቤ/ክ ፈለገ ጥበብ ሰ/ት/ቤት በመገኘት የሀገረስብከቱ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሀላፊ መ/ሐ አባ ሀ/ገብርኤል ተስፋ ፈተናውን ያስጀመሩ ሲሆን በሌሎች አጥቢያዎች ጉብኝት አድርገዋል ።

በቀጣይ የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ /የእርከን መሸጋገሪያ / ፈተና ነሀሴ 19/2016 እንደሚሰጥ እና ፈናውን ላለፉ ተማሪዎች የምርቃት እና ካርድ የሽልማት መርሐግብር በሀገረስብከቱ እንደሚሰጥ አንድነቱ አሳውቋል ።


ፈለገ ጥበብ ሚዲያ
#FTM

የመርሀግብሩብ ሙሉ ፎቶ በፈለገ ጥበብ ፎቶግራፊ(የፎቶ ማህደር)( ፎቶ  ብቻ የሚለቀቅበት  ቻናል) ያገኙታል
https://t.me/felegetibebimage
https://t.me/felegetibebimage
#እንድታውቁት
የተጀመረውን የሰ/ት/ቤቶች ስርአተ ትምህርት የሚኒስትሪ ፈተናበሀገር አቀፍ ደረጃ ለ 4 እና 8 ክፍል ተማሪዎች በነሀሴ 19/2016 ዓ.ም ፈተናው የሚሰጥ ይሆናል ።
በመሆኑም ይሄንን በማወቅ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አባሎቻቸውን ለፈተናው እንድትዘጋጁ ስንል እናሳስባለን ።ስለፈተናው አዲስ መረጃዎች ካሉ የምናስተላልፍላችሁ ይሆናል

ሀምሌ 27/2016
ደብረዘይት/ቢሾፍቱ
ፈለገ ጥበብ ሚዲያ
#FTM
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለሐዋርያው "ቅዱስ እንድርያስ" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳቸሁ ✞✞✞

=>መሐሪ #እግዚአብሔር ኃጢአታችሁ በዛ : ሰውነታችሁ ከፋ ሳይል በአባታዊ ርሕራሔው ጠብቆ ይሔው ወርኀ ሐምሌን በሰላም አስፈጸመን:: አይመስለንም እንጂ በእነዚህ 30 ቀናት ሚሊየኖች አንቀላፍተዋል:: ሚሊየኖች በደዌ ዳኝነት ተይዘዋል:: በርካቶቹም ከሃይማኖታቸው ወጥተዋል::

+ታዲያ እኛ ይህ ሁሉ ያልደረሰብን በጐ ስለሆንን አይደለም:: ይልቁኑ ቸርነቱ በእኛ ላይ ስለበዛ ብቻ ነው እንጂ:: አሁንም በሰላም ከአዲሱ ዘመን እንዲያደርሰን ልንማጸነው ይገባል::

=>በዚህች ዕለት ደግሞ እነዚህን ቅዱሳን እናከብራለን:-

+*" ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ "*+

=>ቅዱሱ ሐዋርያ ተወልዶ ያደገው #በቤተ_ሳይዳ አካባቢ ሲሆን የሊቀ ሐዋርያት #ቅዱስ_ዼጥሮስ ትንሽ ወንድም ነው:: አባቱም #ዮና ይባላል:: ገና ከልጅነቱ ጀምሮ አሣ ማጥመድን ከትልቅ ወንድሙ ተምሯል:: እድሜው ከፍ ባለ ጊዜ ኦሪትን ተምሮ የመጥምቁ #ቅዱስ_ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆኗል::

+ከእርሱም እያገለገለ ለ6 ወራት ተምሯል:: በወቅቱ ከወንጌላዊው (ወልደ ዘብዴዎስ) #ዮሐንስ ጋር ቅርብ ባልንጀራም ነበር:: ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ ያን ድንቅ #ምሥጢረ_ሥላሴ ከተመለከቱትም አንዱ ነው::

+ጌታ ከጾም (ከገዳመ ቆረንቶስ) በተመለሰ ጊዜ እንድርያስ #መንፈስ_ቅዱስ አነሳስቶት ተከትሎታል:: መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ "ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘያዐትት ኃጢአተ ዓለም - የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ" ማለቱን ሰምቶ ቅዱስ እንድርያስ ጌታን ተከተለ::

+በዚህም የመጀመሪያው የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመባል በቃ:: (ዮሐ. 1:47) ሊቁ #ማር_ገላውዴዎስም እመቤታችንን ሲያመሰግናት
"ለሐዋርያ #እንድርያስ ቀዳማዊ ማርያም ሃይማኖቱ::
ለመጀመሪያው ሐዋርያ ለእንድርያስ ሃይማኖቱ ማርያም አንቺ ነሽ::" ብሏል:: (#መልክዐ_ስዕል)

+ቅዱሱ ሐዋርያ ስሉጥ (ፈጣን) አገልጋይ እንደ ነበርም ወንጌል ይነግረናል:: (ዮሐ. 6:5) ለ3 ዓመታት ከ3 ወት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ : በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሎ : ምን ሃገረ ስብከቱ #ልዳ ብትሆን ብዙ አሕጉረ ዓለምን ሰብኩዋል::

+ይህች ቀን ሐዋርያው ከጌታ ጋር በመርከብ ውስጥ የተነጋገረባትና ቅዱስ ማትያስን ሰውን ከሚበሉ ሰዎች እጅ ያዳነባት ናት:: ቅዱስ እንድርያስ 30 ቀናት የሚፈጅ የባሕር ላይ ጉዞ ለማድረግ ከአርድእቱ ጋር ወደ ወደብ ቢሔድም መርከበኞች ሁሉ አናሳፍርም በማለታቸው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወጣት መርከበኛ መስሎ ሐዋርያውንና አርድእቱን የሠላሳውን ቀን መንገድ በሰዓታት ልዩነት እንዲጨርሱ አድርጉዋል::

+ቅዱስ እንድርያስም ፍጡር (እንዲሁ ሰው) መስሎት ለጌታችን ስለ ጌታችን ሰብኮለታል:: መርቆታልም:: መርከበኛው ጌታችን መሆኑን ሲያውቅም ደንግጦ አልቅሷል::

"ሶበ አእመረ ኪያሁ ወጠየቀ አምሳሎ::
ዘተናገርኩ በድፍረት ምስሌከ ኩሎ::
ሥረይ ሊተ ጌጋይየ ወኅድግ ይቤሎ::" እንዲል::

+"ማረኝ?" ብሎታል:: ጌታችንም "አይዞህ እኔ ካንተ ጋር ነኝ" ብሎታል:: ቅዱሱ ሐዋርያ ለወንጌል አገልግሎት ተግቶ ያረፈው ታሕሳስ 4 ቀን ነው::

+*" ቅዱስ ዻውሎስ መናኒ "*+

=>ይህ ቅዱስ መላ ሕይወቱ ድንቅ ነው:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ ሲሆን የተባረከች ሚስት እና 2 ቡሩካን ልጆች የነበሩት አባት ነው:: #ቅዱስ_ዻውሎስ የነዳያን አባት : እጅግ ባለ ጸጋ : ቤተሰቡን የቀደሰና ባለ ሞገስ ሰውም ነው::

+ታዲያ ምጽዋት ወዳጅ ነውና ሲመጸውት : ሲመጸውት ሃብቱ አለቀ:: አሁንም መመጽወቱን አላቆመምና ቤቱ : ንብረቱ አልቆ ከነ ቤተሰቡ ነዳያን ሆኑ:: እርሱ ግን ያለ ምጽዋት ማደር አይችልምና አንድ ሃሳብ መጣለት:: ሚስቱንና ልጆቹን መሸጥ እንዳለበት ወሰነ::

+እነርሱ እንደ መሪያቸው ፍጹማን ናቸውና በደስታ ሃሳቡን ተቀበሉት:: መጀመሪያ ትልቁ ልጅ ተሸጠ:: ገንዘቡ ግን አሁንም በምጽዋት አለቀ:: ቀጥሎ ትንሹ ልጅ ተሸጠ:: አሁንም በምጽዋት አለቀ:: 3ኛ ደግ ሚስት ተሸጠችና እርሱም ተመጸወተ::

+በመጨረሻ ቅዱስ ዻውሎስ ራሱንም ሽጦ መጸወተና ይህ ድንቅ ሥራ ተጠናቀቀ:: ( ነገሩ ግራ እንዳያጋባን "ተሸጡ" ስንል ለአሕዛብ ወይም ለሌላ ሰው አይደለም:: 4ቱም የተሸጡት ለገዳማት ሲሆን ገዥዎቹ አበ ምኔቶቹ ናቸው:: ) ቅዱስ ዻውሎስ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መትቶ ምጽዋትንም : ገዳማዊ ሕይወትንም አትርፏል::

+በሁዋላ ወደ ተሸጠበት ገዳም ገብቶ እንዲህ ብሎ ጮኸ:- "ጌታ ሆይ! የሰጠኸኝን ሁሉ ላንተ መልሼ ይሔው መጥቻለሁ::" ጌታም ከሰማይ መለሰለት:- "ወዳጄ ሆይ! ባንተ ደስ ብሎኛል:: ተቀብዬሃለሁ" አለው:: 4ቱም #ቅዱሳን በንጹሕ ተጋድሎ ኑረው በዚህች ቀን ዐርፈው የማታልፈውን ርስት ወርሰዋል::

+*" ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት "*+

=>ከታላላቅ ሊቃናት አንዱ የሆነው #ቅዱስ_ሱርያል ክብሩ ብዙ ቢሆንም ብዙ ምዕመናን አያውቁትም:: የመላእክት መዓርግ ሲነገር #ሚካኤል : #ገብርኤል : #ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ሱርያል ነው::

+በ3ቱ ሰማያት ካሉት 9ኙ ዓለመ መላእክት የአንዱ (#የሥልጣናት) መሪ (አለቃ) ነው:: መልአኩ እጅግ ርሕሩሕ እና ተራዳኢ ነውና አንዘንጋው:: #ለኖኅ መርከብርን ያሳራው : ከጥፋት ውሃም ያዳነው ይህ ቅዱስ መልአክ ነው::

+በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝም ነው:: #ቅዱስ_ሱርያል በሌላ ስሙ "#እሥራልዩ" ይባላል:: "የእሥራኤል ረዳት" እንደ ማለት:: ዛሬ ደግሞ የሊቀ መልአኩ ቅዳሴ ቤቱ ነው::

+*" ቅዱሳን መርቆሬዎስና ኤፍሬም "*+

=>እነዚህ ወጣቶች በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ሲሆን ከተወለዱባት #ገሊላ ወደ ግብጽ (#ገዳመ_አስቄጥስ) በምናኔ መጥተዋል:: ለ20 ዓመታትም በክህነት አገልግሎትና በተጋድሎ ኑረዋል::

+አንድ ቀን መናፍቃን (አርዮሳውያን) በወታደር ተከበው መጥተው በገዳሙ እንቀድሳለን አሉ:: የራሳቸውን መስዋዕት መንበሩ ላይም አኖሩ:: ከዛ ያሉ አበው አዘኑ:: ወጣቶቹ መርቆሬዎስና ኤፍሬም ግን ለአምላካቸው ቀኑ::

+ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው መናፍቃኑን "በክርስቶስ አምላክነት የማያምን በዚህ መቅደስ ውስጥ አይሰዋም" ብለው በድፍረት የመናፍቃንን መስዋዕት ወደ ውጪ በተኑት:: በዚያች ሰዓት መናፍቃኑ 2ቱን ቅዱሳን ወደ መሬት ጥለው ደበደቧቸው:: ረገጧቸው:: የቅዱሳኑ አጥንቶችም ተሰባበሩ:: በመጨረሻ በስቃዩ ብዛት 2ቱም በአንድነት ዐረፉ::

=>የእነዚህ ሁሉ ቅዱሳን አምላክ ተረፈ ዘመኑን የንስሃ : የፍቅርና የአንድነት ያድርግልን:: ከወዳጆቹም በረከትን ያድለን::

=>ሐምሌ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ዻውሎስ መናኒ (ከቤተሰቡ ጋር)
3.ቅዱስ ሱርያል (እሥራልዩ) ሊቀ መላእክት
4.ቅዱሳን መርቆሬዎስና ኤፍሬም (ሰማዕታት)
5.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት (ፍልሠቱ)
6.እናታችን ማርያም ክብራ ኢትዮዽያዊት (የዐፄ ናዖድ ሚስት)=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
5.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት

=>+"+ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ጌታ ኢየሱስን ተከተሉት:: ጌታ ኢየሱስም ዘወር
ብሎ : ሲከተሉትም አይቶ:- "ምን ትፈልጋላችሁ?" አላቸው:: እነርሱም:- "ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" አሉት:: ትርጉዋሜው "መምሕር ሆይ!"ማለት ነው:: "መጥታችሁ እዩ" አላቸው:: መጥተው የሚኖርበትን አዩ:: በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ:: አሥር ሰዓት ያህል ነበረ:: ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን #ዼጥሮስ ወንድም #እንድርያስ ነበረ:: +"+ (ዮሐ. 1:47)

=>+"+ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ:: በኀዘን ወይም በግድ አይደለም::
"በተነ:: ለምስኪኖች ሰጠ:: ጽድቁ ለዘለዓለም ይኖራል"
ተብሎ እንደ ተጻፈ:: +"+ (2ቆሮ. 9:7)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/felegetibebmedia
#እንድታውቁት
በቀጣይ የ8ኛ እና 4ኛ ክፍል ሚኒስትሪ /የእርከን መሸጋገሪያ / ፈተና ነሀሴ 19/2016 እንደሚሰጥ እና ፈናውን ላለፉ ተማሪዎች የምርቃት እና ካርድ የሽልማት መርሐግብር በሀገረስብከቱ እንደሚሰጥ አንድነቱ አሳውቋል ።


ፈለገ ጥበብ ሚዲያ
#FTM
ውድ የፈለገ ጥበብ ሚዲያ ተከተታታዬቻችን የደብረታቦር (ቡሄ) ክብረበዓልን አስመልክቶ የፈለገ ጥበብ ሚዲያ ልዩ የጥያቄ አለኝ መርሀግብር በማዘጋጀት ላይ ይገኛል በመሆኑም እርሶ ደብረታቦር(ቡሄ) ክብረበዓልን አስመልክቶ እንዲብራራሎት የሚፈልጎትን ማንኛውም ጥያቄዎች ከስር ባለው ሊንክ ላይ በመግባት ጥያቄያችሁን እንድትልኩልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።

ጥያቄዎትን የምንቀበለው ይህ ማስታወቂያ ከተለቀቀበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 3ቀናት የሚሆን ይሆናል


የጥያቄ አለኝ መርሀግብር ጥያቄ ማሰባሰቢያ ቦት 👉👉 https://t.me/QuestionFTM12bot 👈👈

ሀምሌ 30/2016 ዓ.ም
#የፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
#FTM
የናንተው ሚዲያ!!!
🥀ጾመ ፍልሰታ
(ጾመ ማርያም)🥀

ክብርን የለበሽ ጸጋን የተጎናጸፍሽ ማርያም ሆይ በዕንቁ ባሕር ለተመሰለ ፤ በሰው ልብ ላልታሰበ የሥጋሽ ፍልሰት ሰላምታ ይገባል። በብሩህ ደመና ሥጋሽ ወደ ሰማይ ሲያርግ በአየና በተመለከተ ጊዜ ሞት የአፈረ አይደለምን!

    «መልክአ ፍልሰታ» ሀምሌ 30/2016 ዓ.ም
#የፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ
#FTM
የናንተው ሚዲያ!!!
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጾመ ፍልሰታን በማስመልከት ያስተላለፉት መልእክት፣ ቃለ በረከትና ቡራኬ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል።
      
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በሀገር ውስጥና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ!

በማሕፀነ ማርያም በፈጸመው እውነተኛ ተዋሕዶ የሰው ልጅን ከኃሣር ወደ ክብር የመለሰ እግዚአብሔር አምላካችን፣ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመተ ምሕረት ጾመ ቅድስት ማርያም በደኅና አደረሰን አደረሳችሁ!፤

‹‹ተፈሥሒ ኦ ምልእተ ጸጋ፣ ተፈሥሒ እስመ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር፡- ምልእተ ጸጋ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ በእግዚአብሔ ዘንድ ሞገስን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ›› (ሉቃ. 1÷28-30")
የክብር አምላክ እግዚአብሔር የሰው ልጅን ከወደቀበት ዐዘቅተ ኵነኔ የሚያድንበት ዕድል እንዳዘጋጀ በብሉይ ኪዳን በስፋት ገልፆል፤ የማዳን ስራውም ከሰው ወገን ከሆነች ቅድስት ድንግል በሚወለደው መሲሕ እንደሚፈጸም አስረድቶአል፤ የማዳን ቀኑ በደረሰ ጊዜም መልእክቱን በፊቱ በሚቆመው በቅዱስ ገብርኤል በኩል ልኮአል፤ ቅዱስ ገብርኤልም የተነገረውን መልእክት ለድንግል ማርያም አድርሶአል፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ለድንግል ማርያም እንዲነግር ከታዘዘባቸው መካከል ‹‹ጸጋን የተመላሽ ደስተኛይቱ ሆይ÷በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ›› የሚል አስደናቂ መልእክት ይገኝበታል፡፡

የተወደዳችሁ ሕዝበ ክርስቲያን!

ከእግዚአብሔር መንጭቶ በቅዱስ ገብርኤል በኩል ለድንግል ማርያም የተነገረ ይህ መልእክት፣ የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብር ከመግለጽ ባሻገር ለሰው ልጆች ሁሉ ያለው ፋይዳ በእጅጉ የላቀ ነው፤

‹‹ጸጋ›› የሚለው ቃል እንደ ቅዱስ መጽሐፍ አስተምህሮ ያልተወሰነ፣ ገደብና ቅድመ ሁኔታ የሌለው ስጦታን ሲያመለክት ‹‹ሞገስ›› የሚለው ቃል ደግሞ ተወዳጅነትን ተደማጭነትን ተሰሚነትን የሚያመለክት የክብርና የባለሟልነት መግለጫ ቃል ነው፡፡

እነዚህ ቃላት ከእግዚአብሔር ዘንድ በቅዱስ ገብርኤል በኩል ለቅድስት ድንግል ማርያም ተነግረዋል፤ የእግዚአብሔር ቃል የማይለወጥ ነውና ቃላቶቹ ለድንግል ማርያም ቃል ኪዳን ሆነው የተሰጡ ናቸው፤ የተሰጡበትም ምክንያት ሰውን ለማዳን ስራ እንዲውሉ እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡

ምክንያቱም የእግዚአብሔር የማይናወጥ ፈቃድ ሰውን ማዳን ነውና፤ በመሆኑም ቅድስት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር በተሰጣት በዚህ ገደብ የሌለው ቃል ኪዳኗ ሰውን ልትታደግ በቅታለች፤ይህም በቃና ዘገሊላ ባደረገችው ምልጃ በጭንቀት የተዋጡትን ሠርገኞች እንዴት እንደታደገች በቅዱስ ወንጌል ተጽፎ እናገኘዋለን፤ቅድስት ድንግል ማርያም ቀድሞውኑም ከፍ ያለ ሞገስ ተሰጥቶአታልና የሠርጉ አሳላፊዎችን ‹‹የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ›› በማለት ስታዝዝ እናያለን፤ ይህ ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ አስደናቂ የትድግና ስጦታ ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!

የድንግል ማርያም የጸጋ ስጦታ በብሥራተ ገብርኤል ተገልጾ፣ በቃና ዘገሊላ ተተግብሮ በዕለተ ስቅለት ‹‹እነሆ ልጅሽ፣ እነኋት እናትህ›› በሚል መለኮታዊ ማኅተም የታተመ ነው፤ ይህ ቃል እሷ እናታችን መሆኗን፤ እኛም ልጆችዋ መሆናችንን ያረጋገጠ ማኅተመ ቃል ኪዳን ነው፤ የቃል ኪዳኑ ይዘት እሷ በአማላጅነቷ እንደ ልጅ ልትንከባከበን እኛም እንደ እናት  ልናከብራትና ልንማፀናት የሚገባን መሆኑን ያሳያል፤ የእናትነትና የልጅነት ማረጋገጫ የሆነ ይህንን የቃል ኪዳን ማኅተም ሊሰርዝም ሆነ ሊፍቅ ሊደመስስም የሚችል ኃይል የለም፡፡

ይህ ጸጋና ሞገስ በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይም የሚቀጥል እንጂ የሚገደብ አይደለም፤ ሞት፣ ቦታና ዘመንም አይወስኑትም፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን በሞት በቦታና በዘመን አይገደብምና ነው፤ ‹‹ኪዳኑንም ለዘለዓለም ያስባል›› ተብሎ የተገለጸውም ለዚህ ነው፤ (መዝ. )111÷5)
መንፈስ ቅዱስም በእሷ አንደበት ‹‹እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ነሽ ይሉኛል›› በማለት የተናገረው ይህንን ለማስረዳት እንደሆነ ማስተዋል ያሻል፡፡

በእግዚአብሔር  ተሰጥቶ፣ በቃል ኪዳን ታትሞ፣ በቅዱስ ገብርኤል ተብራርቶ፣ በጌታችን ተረጋግጦና በሐዋርያት በኩል የተላለፈልን፣ ሰውን ማዳን ግቡ የሆነ የድንግል ማርያም ምልጃ ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት፣ በሁሉ ያለች፣ አንዲትና ቅድስት ኦርቶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ሺሕ ዓመታት ያህል አምና እና ተቀብላ ስትጠቀምበት ኖራለች፤ አሁንም በዚሁ ትቀጥላለች፡፡

በኦርቶዶክሱ ዓለም ዛሬ የሚጀመረው የጾመ ማርያም ሱባዔም የዚሁ ጭብጥ ማሳያ ነው፤ ዋናው መልእክቱም ድንግል ማርያም በተሰጣት ጸጋና ሞገስ በጸሎቷ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትንና ይቅርታን የምታሰጠን ስለሆነች እሷን በመማፀን ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ የሚል ሆኖ ይመሰጠራል፡፡

የተወደዳችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ልጆቻችን!

ጾም ፈቃደ ሥጋን በማድከምና ፈቃደ ነፍስን በማጎልበት ምሕረተ እግዚአብሔር መሻታችንን የምናሳይበት መንፈሳዊ ማመልከቻ ነው፤ ጾም ከጥንት ጀምሮ የነበረ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ነው፤ ቀደምት አበው በጾም ምክንያት ከጥፋት ድነዋል፤ የለመኑትንም አግኝተዋል፤ ምስጢርም ተገልጾላቸዋል፤ ዲያብሎስም ድል አድርገውበታል፡፡

እኛም ዛሬ ጾምን ስንጾም በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን ብሎም በዓለም ዙሪያ ሁሉ ስጋትን እየጫረ ያለው የጥፋት እንቅስቃሴ እግዚአብሔር እንዲያስቆምልን ከልብ በመጸለይ ሊሆን ይገባል፤ ይህንንም ስናደርግ በጸሎት ብቻ ሳይሆን ንስሐ በመግባትና ቅዱስ ቁርባንን በመቀበል እንደዚሁም የሰላም የፍቅርና የዕርቅ ሰው ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት በመቆም ሊሆን ይገባል፡፡

ችግሮችንና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በምክክር ለመፍታት የሚደረገው ጥረትም በእጅጉ ሊደገፍ ይገባል፤ ግጭትና ጦርነት ከሚያጠፋን በቀር ሊያተርፍልን የሚችል አንዳች ጥቅም የለም፡፡

በመሆኑም በየትኛውም የሀገራችን አካባቢ ያላችሁ ልጆቻችን እባካችሁ ለሰላም ለውይይትና ለሰው ልጆች መብት መከበር ቅድሚያ ስጡ፤ ግድያ፣ ዕገታ፣ አብያተ ሃይማኖትን መዳፈር፣ ዘረፋና ቅሚያ፣ የሴት ልጅን መድፈርና ሰውን ማንገላታት አቁሙ፤
እነዚህ ድርጊቶች ሰብአዊነትን ዝቅ የሚያደርጉ፣ እግዚብሔርን የሚያስቆጡ፣ በታሪክም የሚያሳፍሩ ናቸው፤ እነዚህን ሳናርም   የምንጾመው ጾም ትርጉም ስለሌለው ንስሐ ገብተን ከእንደዚህ ያለው ድርጊ ርቀን ጾሙን መጾም ይገባል፤ ይህን ስናደርግ ጾማችን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ ይኖረዋል፡፡

በመጨረሻም
የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ በተለይም በጾመ ማርያም ሱባዔ በንስሐና በጸሎት የሚያሳልፉ ሕዝበ ክርስቲያን ስለ ሃይማኖት መጠበቅ፣ ስለሀገር ሰላምና አንድነት፣ እንደዚሁም ስለሕዝቦች ደኅንነትና ጤንነት አጥብቀው እንዲጸልዩ በእግዚአብሔር ስም መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
መልካም የሱባዔ ወቅት ያድርግልን
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

         አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
      
ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም.
ዋሽንግተን ዲሲ - ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ
🌻††† እንኳን ለቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም †††

††† ቸር #እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ #ጾም ነው:: የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም:: መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ ደግሞ ጾም: ጸሎትና ስግደት ናቸው:: ያለ እነዚህ ምግባራት መቼም ወደ #ጽድቅ መድረስ አይቻልም::

ይቅርና እኛ ክፉዎቹ የሰማይና የምድር ፈጣሪ: የክብር ሁሉ ባለቤት ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደ ጊዜ የመጀመሪያ ሥራው ያደረገው ጾምን ነው:: ስለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 7 አጽዋማትን በጉባዔ ሠርታ: በአዋጅ እንዲጾሙ ታደርጋለች:: ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሠታ ነው::

"ፈለሠ" - ሔደ: ተጉዋዘ እንደ ማለት ሲሆን " #ፍልሠታ" ማለት የእመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያምን የዕርገት ጉዞ የሚያዘክር ቃል ነው:: #እመ_ብርሃን በዚህ ዓለም ለ64 ዓመታት ኑራ ካረፈች በሁዋላ ሥጋዋ እንደ እኛ አልፈረሰም::

ለጊዜው በዕጸ ሕይወት ሥር ቆይታ እንደ ልጇ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: እርሷ በሁሉ ነገሯ ቀዳሚና መሪ ናትና:: ጾመ ፍልሠታን የጀመሩት አበው #ሐዋርያት ሲሆኑ እንድትጾምም ሥርዓት የሠሩ ራሳቸው ናቸው:: ከ7ቱ አጽዋማትም እጅግ ተወዳጅና እየተናፈቀች የምትፈጸም ናት::

ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል::
*የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ: ውሃ እየተጐነጩ ክብርን ያገኛሉ::
*ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን: በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜውን: በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ::
*የኔ ብጤ ደካማ ደግሞ ጠዋት ማታ ወደ ደጇ እየተመላለሰ "አደራሽን ድንግል" ይላታል::

††† በእርሷ አምነን አፍረን አናውቅምና ነጋ መሸ ሳንል እንማጸናታለን::

††† #ጽንዕት_በድንግልና: #ሥርጉት_በቅድስና #እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ልበለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን:: <3
*ጾሙን የፍሬ: የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን::*

††† ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ †††

††† እጅግ የተወደዱ: ሞገስ የሞላላቸውና ፈጣሪያቸውን በክብር ገንዘው የቀበሩ አባቶች ናቸው::

††† ቅዱስ ዮሴፍ ዘአርማትያስ †††

††† ቅዱሱ በእሥራኤል ምድር ተወልዶ ያደገ: ኦሪትን የተማረ ባለጠጋ ሰው ነው:: የተማረ ደግ ሰው ነውና የክርስቶስን መምጣት በተስፋ ይጠብቅ ነበር:: ባገኘውም ጊዜ በአዳኝነቱ (በመሲህነቱ) አምኖ በስውር ተከታዩ ነበር::

††† ቅዱስ ኒቆዲሞስ †††

††† ወንጌል እንደሚነግረን ይህ ሰው የአይሁድ አለቃ: መምሕር: ዳኛ እና ሃብታም ሰው ነበር:: እነዚህ ሁሉ ማነቆዎች ግን እርሱን ከፈጣሪው ሊያስቀሩት አልቻሉም:: ሌሊት እየመጣ ከጌታችን እግር ይማር ዘንድም አድሎታል:: በመካከልም ከአይሁድ ጋር ብዙ ተጋጭቷል::

ሁለቱ አባቶች መድኃኒታችን ስለ እኛ ሲል ሞቶ ባለበት ሰዓት ላይ በእርሱ የደረሰ ይደርስብናል ሳይሉ በድፍረት ሥጋውን ከዺላጦስ ተካሠው ለመኑ:: እንባቸው በፊታቸው እየወረደ ከመስቀል አውርደው በዮሴፍ በፍታና በኒቆዲሞስ ሽቱ ገነዙት::

እንዲህ እያሉ:-
"ሙታንን የምታስነሳ ጌታ አንተ ሞትክን?! ደካሞችን የምታጸና ቸር አንተ ደከምክን?!"
*በዚያች ሰዓት ጐልጐታ አካባቢ ዝማሬ መላእክትን እየሰሙ የክብር ባለቤትን ቀብረውታል:: ጌታችንም ከተነሳ በሁዋላ በንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::

"እየሳማችሁ አክብራችሁ እንደ ገነዛችሁኝ እኔም በሰማይ በእንቁ ዙፋን ላይ አስቀምጣቹሃለሁ" ብሏቸዋል:: "አነ አብረክሙ ዲበ መንበረ ሶፎር" እንዲል:: ጻድቃን አበው ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በተረፈ ዘመናቸው ወንጌልን ሰብከው: ከአይሁድ መከራን ታግሰው: በበጐ ሽምግልና ዐርፈዋል::

††† ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት †††

††† ቅዱስ አቦሊ የሰማዕታቱ #ቅዱስ_ዮስጦስና #ቅድስት_ታውክልያ ልጅ ሲሆን በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ያበራ የቤተ ክርስቲያን ዕንቁ ሰማዕት ነው:: የሚገርመኝ ሦስቱ የግማሹ ዓለም አስተዳዳሪዎች ነበሩ:: ዮስጦስ ንጉሥ: ታውክልያ ንግሥት: አቦሊ ደግሞ ልዑል ነው::

ነገር ግን ይህንን ክብራቸውን #በክርስቶስ ፍቅር ጐን: ሚዛን ላይ ቢያኖሩት በጣም ቀሎ ታያቸው:: 3ቱም ከዙፋናቸው ወርደው: ወገባቸውንም ታጥቀው: ባሮቻቸው በነበሩ ሰዎች ስለ ክርስቶስ ብዙ ተንገላቱ:: መራራ ሞትንም ታገሱ::

በተለይ ቅዱስ አቦሊ ከአንጾኪያ ወደ ግብጽ (ብስጣ) ይዘው አምጥተው ክርስትናውን እንዲተው ያላደረጉት የለም:: በቁሙ ቆዳውን ገፈው: በቆዳው አቅማዳ ሰፍተው: ያንንም አሸክመው: የተገፈፈ አካሉን ጨውና ኮምጣጤ እየቀቡ አዙረውታል::

እርሱ ግን ጌታ በላከለት ድንቅ መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል ረዳትነት ሁሉን ችሎታል:: በዘመኑ ብዙ ተአምራትን የሠራ ሲሆን አንድ ጊዜ ቤት ተንዶ 16 ሰዎች ቢያልቁ የተገፈፈ ቆዳውን እየጣለባቸው ተነስተዋል:: በተአምራቱና በተጋድሎውም ብዙ ሺህ አሕዛብን ለክርስትና: ብሎም ለሰማዕትነት አብቅቷል::

እርሱም ከብዙ የመከራ ጊዜያት በሁዋላ በዚህች ቀን አንገቱን ተከልሏል:: ጌታችን "ዜናሕን የጻፈውን: ያነበበውንና የሰማውን ይቅር እለዋለሁ" ብሎ ቃል ኪዳንን ሰጥቶታል::

††† ፈጣሪ ከጻድቃንና ሰማዕታት በረከትን አይለይብን:: ወርሐ ነሐሴንም ለበረከት ይቀድስልን::

††† ነሐሴ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በአተ ጾመ ፍልሠታ
2.አበው ሐዋርያት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
3.ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት
4.ታላቁ ቅዱስ ዸላሞን ገዳማዊ
5.ቅድስት ሐና (የእመ ብርሃን እናት)
6.ቅድስት ሐና ነቢይት (ወለተ ፋኑኤል)
7.ደናግል ቅዱሳት (የንግስት ሶፍያ ልጆች)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

††† "የጌታ ኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ #ዮሴፍ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ዺላጦስን ለመነ:: ዺላጦስም ፈቀደለት:: ስለዚህም መጥቶ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ወሰደ:: ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ #ጌታ_ኢየሱስ መጥቶ የነበረ #ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ:: የጌታ ኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት::" †††
(ዮሐ. 19:38)

††† "በጽዮን መለከትን ንፉ:: ጾምንም ቀድሱ:: ጉባዔውንም አውጁ:: ሕዝቡንም አከማቹ:: ማሕበሩንም ቀድሱ:: ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ:: ሕጻናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ:: ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ::" †††
(ኢዩ. 2:15)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††

https://t.me/felegetibebmedia