Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.9K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
የክልሉ ሁለቱ ኮሚሽኖች በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት ተፈራረሙ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲዳማ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ በሥነምግባር ግንባታ፣ በሙስና መከላከል እና በአሰራር ሥርዓት ጥናት እንዲሁም በመረጃ ልውውጥ ዙሪያ ተቀናጅቶ መሥራት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

ስምምነቱን የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ዘላለም ለማ እና በፓርቲዉ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ሰብሳቢ ወ/ሮ አመቤት ኢሳያስ ተፈራርመዋል።

ሠነዱ የሁለቱም ተቋማት አመራሮች በተገኙበት በክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ፊሊጶስ ናሆም ቀርቦ ውይይት ተካሄዶበታል።

በቀረበዉ ሠነድ ላይም በቂ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶበት በቀጣይ ለሥራ የሚያስገባ የጋራ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ተግባር ላይ እንዲውል የጋራ መደረጉን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ለተቋሙ አመራሮች ሙስናን መከላከል የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል መሪ ሀሳብ ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት አመራሮች የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው የተገኙት የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ ስልጠናው የተለያዩ ሀገራት የዋና ኦዲተር ተቋማት ሙስናን ከማጋለጥና ተጠያቂነትን ከማስፈን አንጻር በሚያደርጉት የሥራ እንቅስቃሴ በየሀገራቱ ከሚገኙ የፀረ-ሙስና ተቋማት ጋር በትብብር መስራት እንደሚገባቸው በ24ኛው የአለምዓቀፍ የኦዲት ተቋማት ጉባኤ (INCOSAI) የተቀመጠውን አቅጣጫ መነሻ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ዋና ኦዲተሯ አክለውም ይህንኑ የአለምዓቀፍ የዋና ኦዲተሮች ተቋማት ጉባኤ አቅጣጫ መሰረት በማድረግም በሰኔ ወር 2015 ዓ.ም የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትና የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጋራ የሥራ የመግባቢያ ስምምነት (MOU) መፈራረማቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የሁለቱ ተቋማት መሠረታዊ አላማና ተግባር በመንግስት ተቋማት ተጠያቂነትና ህጋዊ አሠራር እንዲረጋገጥ ማድረግ ነው ብለዋል።

ስለሆነም ተቋማቱ ተመጋጋቢ መረጃዎችን በመለዋወጥና ሌሎች የጋራ ስራዎችን በመስራት ተቋማዊ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ከመዋጋት አንጻር በትብብር እንደሚሰሩ ከብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ተናግረዋል።

ይህ ስልጠናም በስምምነቱ ከተካተቱት የጋራ ስራዎች መካከል የስልጠና መደጋገፍ የሚለውን መሠረታዊ ነጥብ ለመተግበር የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከመ/ቤቱ ተልዕኮና ተግባር አንጻር የስልጠናውን ተገቢነትና ጠቃሚነት ጨምረው የገለጹት ክብርት ዋና ኦዲተሯ፥ የመ/ቤቱ አመራሮች ስልጠናውን በትኩረትና በንቃት እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡

ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የሚያስችል እውቀትና ክህሎት ለማስጨበጥና የአመለካከት ለውጥ እንዲኖር ለማድረግ የሚሉ አላማዎችን መሠረት ያደረገው የሁለት ቀናት ስልጠና የሙስና ወንጀል ምንነትና አይነቶች፣ የሙስና ወንጀል ባህርያትና ወንጀሎች ላይ ትኩረት አድርጓል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለሙስና እና ብልሹ አሠራር ያለው ተጋላጭነት እንዲሁም ሙስና እና ብልሹ አሠራሮች የሚያስከትሉት ጉዳትና መከላከያ ስልቶች ላይ ትኩረት ያደረገውን ሥልጠና የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታና ፀረ-ሙስና ስልጠና ዴስክ ኃላፊ አቶ ከፊያለው አለሙ እና የስልጠና ባለሙያ ፍቃዱ ባረና እየተሰጠ ይገኛል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የአገልግሎት አሰጣጡን ከሙስና እና ብልሹ አሠራር ለመከላከል ቅንጅታዊ አሠራር ላይ በትኩረት ይሰራል - አቶ አበበ ከበደ

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ከክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለኤጀንሲው አመራርና ሠራተኞች በሙስና ፅንሰ ሀሳብና በመልካም አስተዳደር መርሆዎች ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።

በስልጠናው የተገኙት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አበበ ከበደ ከቀበሌ ጀምሮ በየደረጃው የሚሰጡ አገልግሎቶች ከሙስና እና ብልሹ አሰራር ለማፅዳት ከሚመለከታቸው የህግ አካላት ጋር የተጀመረው ቅንጅታዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

ኤጀንሲው ባለፉት ወራት ከስር መዋቅሮች ባደረገው የጋራ እንቅስቃሴ በርካታ አካላት በህግ እንዲጠየቁ መደረጉን ገልፀው፥ ሙስናን መከላከል ከራስ ስለሚጀምር ሠራተኛው ራሱን ለለውጥ በማዘጋጀት የሪፎርም ስራዎች አተገባበር ላይ በንቃት ሊሳተፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኤጀንሲው ም/ዳይሬክተር አቶ በድሩ ሀሰን በበኩላቸው ሙስናን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ሁሉም የትግሉ አካል ሊሆን እንደሚገባው ጠቁመው፥ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች በየዳይሬክቶሬቶች በጥንቃቄ ሊተገበሩ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ ከኤጀንሲው ተግባር ጋር በቀጥታ ተያያዥነት ያለው በመሆኑ በቂ እውቀት ማግኘታቸውን ሰልጣኞች ገልፀው፥ ተጨማሪ ማብራሪያ በሚያስፈልጋቸው ነጥቦች ዙሪያ ጥያቄና አስተያየቶችን አቅርበዋል።

ለቀረቡት ጥያቄዎች በክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሙስና እና ብልሹ አሰራር መከላከል አማካሪ አቶ ደመቀ ታደሰ እና በክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ፍትህአወቅ ፋንታሁን ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በሀሰተኛ ሰነድ ለመገልግል የሞከረች ግለሰብ በቁጥጥር ማዋሉን ኤጀንሲው አስታወቀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሀሰተኛ መሸኛ የተዘጋጀ መታወቂያና ልደት ሰርትፍኬት በመያዝ አገልግሎት ለማግኘት የሞከረች ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

በኤጀንሲው የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ዳ/ዳይሬክተር ወ/ሮ አስናቀች ሙህየ መጋቢት 3/2017 ዓ.ም በሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በየካ ቅርንጫፍ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ስም በሀሰተኛ መሸኛ የተዘጋጀ መታወቂያና ልደት ሰርትፍኬት በመያዝ አገልግሎት ለማግኘት የሞከረች ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ተናግረዋል፡፡

ግለሰቧን የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በቁጥጥር ስር በማዋል ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው የሙስና ወንጀል መከላከል ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ከኤጀንሲው የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ፍርድ ቤቱ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወሰነ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞ የከተማዋ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አሳለፈ።

የከተማዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሌሎች ተከሳሾች ላይም የቅጣት ውሳኔውን አሳልፏል።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ወንጀሉን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 17 ንዑስ 2 እና አንቀጽ 9 ንዑስ 2 በተደነገገው መሰረት ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ነው።

በዚህም አንደኛ ተከሳሽ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጸጋዬ ቱኬ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ጥፋተኛ በመባላቸው የ13 ዓመት ጽኑ እስራትና የ21 ሺህ ብር ቅጣት ተወስኖባቸዋል።

ሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ተሰማ ዳንጉሼ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል የሦስት ዓመት ጽኑ እስራትና 1 ሺህ ብር የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

በተጨማሪም ሦስተኛ ተከሳሽ አቶ ታሪኩ ታመነ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል 10 ዓመት ጽኑ እስራትና 41ሺህ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

እንዲሁም 4ኛ ተከሳሽ አቶ ታፈሰ ቱናሻ እና 5ኛ ተከሳሽ አቶ ሰይፉ ዴሊሳ እያንዳንዳቸው በስምንት ዓመት ጽኑ እስራትና በቅደም ተከተላቸው 51 እና 76 ሺህ ብር እንዲቀጡ የቅጣት ውሳኔ ተሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319