Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.9K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
በገቢው ዘርፍ የሚደረገው የፀረ-ሙስና ትግል የተቀናጀ ጥረትን የሚጠይቅ ነው - የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ

************************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል መሪ ሀሳብ ለገቢዎች ዘርፍ አመራሮች የሥነምግባርና ሙስና መከላከል ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በስልጠናዉ መክፈቻ ላይ የተገኙት የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ፤ ሙስና ለዘላቂ ልማት፣ ለዴሞክራሲና ለመልካም አስተዳደር ማነቆ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በገቢው ዘርፍ የሚደረገው የፀረ-ሙስና ትግል የተቀናጀ ጥረትን የሚጠይቅ እንደሆነ ገልፀው፤ ከፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በገቢው ዘርፍ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ሥር ከመስደዱ በፊት ተጋላጭነትን የመለየት፣ ክፍተቶችን የመዝጋት እና አሰራሮችን የማሻሻል ስራዎች እየተሰሩም ነው ብለዋል፡፡

የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው ስልጠናው በዘርፉ የተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶችን መሠረት በማድረግ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተመረጡ ምሁራን እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

ዘርፉ ለሙስና እና ብልሹ አሠራር ተጋላጭ በመሆኑ በየደረጃው ለሚገኙ አመራርና ሠራተኞች ይህን መሰል ስልጠና መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡

የአንድን ተቋም ተልዕኮ ለማሳካት አመራር እና ሠራተኞችን በሥነምግባር ማነፅ ቁልፍ ተግባር መሆኑንም ገልፀዋል።

በተቋማት ላይ የሚስተዋሉ ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን በጥናት በመለየት ቀዳዳዎችን መድፈን እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው በዶ/ር ዮሐንስ ጴጥሮስ እና በዶ/ር የሱፍ ኢብራሒም እየተሰጠ ሲሆን፤ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በከተማው የሚስተዋሉ ብልሹ አሠራሮችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊንቀሳቀሱ ይገባል - ከንቲባ አቶ ዳዊት ጡምደዶ

********

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች በአሠራር ስርዓት ጥናት ላይ ያተኮረ የስልጠና መድረክ አካሄዷል።

በመድረኩ የተገኙት የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ጡምደዶ የግንዛቤ መፍጠሪያ ሥራዎችን በማጠናከር ሙስናን አስቀድሞ መከላከል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

ሙስና እና ብልሹ አሠራሮች በመንግስትና በህዝብ ሀብት የሚፈፀሙ ወንጀሎች በመሆናቸው ሁሉም ዜጋ በቁርጠኝነት ሊታገል እንደሚገባም አሳስበዋል።

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፋሲካ ጌታቸው በበኩላቸው ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት የሚበረታቱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ችግሩን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ ከቤተሰብ ጀምሮ በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ ሲቪክ ማህበራት ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባም ገልፀዋል።

ሠራተኛው የሥራ ሰዓት አለማክበር እና ትኩረት በመስጠት ካለመስራት ጋር የተያያዙ የሥነምግባር ችግሮችን ለመፍታት ከፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤትና ከሰው ሀብት ልማት ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት ሊሠራ እንደሚገባ ሰልጣኞች ማሳሰባቸውን የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

በስልጠና መድረኩ ላይ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ጡምደዶ፣ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፋሲካ ጌታቸው፣ የሀዲያ ዞን የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን መሪ አቶ ገብረየስ ጡሞሮ፣ የሆሳዕና ከተማ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን መሪ አቶ ንጉሴ ተመስገን እና የሴክተር የሥነምግባር ቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የክልሉ ሁለቱ ኮሚሽኖች በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት ተፈራረሙ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲዳማ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ በሥነምግባር ግንባታ፣ በሙስና መከላከል እና በአሰራር ሥርዓት ጥናት እንዲሁም በመረጃ ልውውጥ ዙሪያ ተቀናጅቶ መሥራት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

ስምምነቱን የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ዘላለም ለማ እና በፓርቲዉ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ሰብሳቢ ወ/ሮ አመቤት ኢሳያስ ተፈራርመዋል።

ሠነዱ የሁለቱም ተቋማት አመራሮች በተገኙበት በክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ፊሊጶስ ናሆም ቀርቦ ውይይት ተካሄዶበታል።

በቀረበዉ ሠነድ ላይም በቂ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶበት በቀጣይ ለሥራ የሚያስገባ የጋራ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ተግባር ላይ እንዲውል የጋራ መደረጉን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319