Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.88K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
የፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ መልካም ሥነምግባርን በመላበስ የተቋሙን ራዕይ ማሳካት እንደሚገባ ተገለጸ

********

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መልካም ሥነምግባራዊ ባህርይ የተላበሰ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጎልበት ስነልቦና፣ ሥነምግባርና አገልግሎት አሰጣጥ በሚል ርዕስ ከተቋሙ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ለተዉጣጡ ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሊዲያ ደምሴ ማህበረሰቡ ከፍርድ ቤቱ የሚፈልገዉን የዳኝነት አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ ለመስጠት መልካም ሥነምግባርን በመላበስ ከብልሹ አሰራሮች በፀዳ መንገድ አገልግሎት በመስጠት የተቋሙን ራዕይ የማሳከት ዓላማ ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተገበራቸዉ ያሉትን የለዉጥ ስራዎች ዉጤታማ ለማድረግ ሁሉም ሠራተኛ የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል፡፡

ወ/ሮ ሊዲያ ደምሴ አክለውም በፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ሁሉም ሠራተኛ የሥነምግባር መርሆችን መሰረት በማድረግና በመልካም ሥነምግባር በታነፀ መልኩ ተገልጋዩን ማህበረሰብ ማስተናገድ እንዳለበት አሳስበዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአዉሮፓ ህብርት የወንጀል ፍትህ ማሻሻያ ፕሮግራም ፕሮጀክት ማናጀር አቶ አሌክሳንደር አዳም የፍርድ ቤት አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች በሚኖራቸዉ ስነልቦና፣ስብዕና እና ባህሪ እንዲሁም ሥነምግባር በፍርድ ቤቱ የሚመጡ ተገልጋዮችን ስብዕና በማይነካና በትልቅ አክብሮት አገልግሎት መስጠት በፍትህ ስርዓቱ ለተቋማዊ ለዉጥ ያለዉን ከፍ ያለ ድርሻ የተለያዩ የዘርፉ ምሁራን የሰጡትን ንድፈ ሃሳብና ማሳያ የጥናት ውጤት በማንሳት እንዲሁም የሥነምግባር መርሆችን በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በምን መልኩ መተግበር እንዳለበት ገለፃ በማድረግ ስልጠናዉን ሰጥተዋል፡፡

በስልጠናው ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሃሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ መሰጠቱን ከተቋሙ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319