Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
ሙስናን መዋጋት የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑ ተገለፀ

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለብራና ማተሚያ ድርጅት ሠራተኞች በሙስና እና የሙስና መከላከያ ስልቶች ላይ ያተኮረ ስልጠና ለሁለት ቀናት ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማተሚያ ድርጅቱ ም/ሥራ አስፈፃሚ እና የሠው ሃብት መምሪያ ኃላፊ አቶ በለጠ ፀጋዬ ሙስና የሃገር ስጋት በመሆኑ ሁሉን አቀፍ ትግል ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ከስልጠናው የሚገኘውን ግንዛቤ በጥልቀት በመረዳት ብልሹ አሰራርን የሚፀየፍ አምራች ማህበረሰብ እንዲፈጠር በቁርጠኝነት መታገል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በስልጠናው ማጠቃለያ የተገኙት የተቋሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ያለው መኮንን አሁን ላለንበት የሥነ-ምግባር ውድቀትና የሙስና ስጋት በማህበረሰቡ እያደገ የመጣው የሥነምግባር እጦትና ብልሽት ስለሆነ ሙስናን መዋጋት የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ሰልጣኞች በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ በሰጡት አስተያየት በተለይ በሙስና ወንጀሎች ላይ የተሻለ ግንዛቤን ያስጨበጠ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል።

ሰልጣኞች አክለውም ቀጣይነት ያለው መሰል ስልጠና በየጊዜው ቢሰጥ ለሙስና ትግል የሚኖረው ድርሻ የጎላ ይሆናል ማለታቸውን ከመከላከያ ዘርፍ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ለህዝባዊ ድርጅቶች አመራሮች ‘‘ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት’’ በሚል መሪ ቃል የሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

***********************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ‘‘ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት’’ በሚል መሪ ቃል ለዳሸን ባንክ አመራሮች ለሁለት ቀናት የሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በሥልጠናው የተገኙት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው አለሙ እንዳሉት የባንክ ሥራ ለደንበኞች በመታመን ደንበኞች በአደራ የሰጡንን ሃብትና ንብረት መጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ይህንን ልናደርገው የምንችለው የባንኩ አመራርና ሠራተኞች ሥነምግባርን ተላብሰን ሥራችንን ስንሰራ፣ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ለደንበኞች ቀልጣፋና የሚያረካ አገልግሎትን ሥንሰጥ እና ሙስና መከላከል ስንችል ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በህዝባዊ ድርጅቶች የሚከሰቱ ሙስና እና የሙስና መከላከያ ስልቶች ላይ ትኩረት ያደረግውን ስልጠና ዶ/ር ሰለሞን ግርማ እና ዶ/ር ደስታ ሙሉጌታ መስጠታቸውን ከባንኩ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በስልጠናው የባንኩን ዋና ስራ አስፈጻሚ ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዋናው መ/ቤትና የዲስትሪክቶች የመምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

በተመሳሰይ ለንብ ባንክ አመራሮች ‘‘ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት’’ በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀናት በዶ/ር ደስታ ሙሉጌታ የሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የለንደን ከንቲባ ሳዲቅ ካሀን ከቴይለር ስዊፍት የሙዚቃ ኮንሰርት ጋር በተያያዘ የሙስና ምርመራ ተጀመረባቸው

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የከተማዋ ፖሊስ የቴይለር ስዊፍትን ኮንሰርት ለመጠበቅ ያወጣው የ500 ሺህ ፓውንድ ወጪ የተጋነነ ነው የሚል ትችቶች ቀርቦበታል።

አሜሪካዊቷ ሙዚቀኛ ቴይለር ስዊፍት በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት በአውሮፓ ሀገራት ከተሞች በርካታ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን አድርጋለች።

ኮንሰርቱ ከተካሄደባቸው ከተሞች መካከል ለንደን አንዷ ስትሆን፥ የከተማዋ ከንቲባ ሳዲቅ ካሀን ደግሞ ሶስት ሺህ ፓውንድ ዋጋ ያላቸው የኮንሰርት መግቢያ ቲኬቶችን በስጦታ ተቀብለዋል ተብሏል።

ከንቲባው ባልተገባ መልኩ ከቴይለር ስዊፍት ስጦታ መቀበላቸው ሙስና ነው በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

የለንደን ከንቲባ ቃል አቀባይ በበኩላቸው ከኮንሰርቱ ቲኬት ጋር በተያያዘ የአስተዳድር ስህተት እንደነበርና ስህተቱ ወዲያው እንደታረመ ለዴይሊ ሜይል ተናግረዋል።

ቴይለር ስዊፍት በዊምብሌይ ስታዲየም ባደረገችው ተከታታይ የሙዚቃ ኮንሰርት የሀገሪቱ መንግሥት ለአንድ ምሽት 99 ሺህ ፓውንድ በድምሩ 500 ሺህ ፓውንድ ገደማ ወጪ ማድረጉን አል አይን አማረኛ ዘግቧል።

ለኮንሰርቱ የደህንነት ጥበቃ ወጪ ተደርጓል የተባለው ገንዘብ በሌሎች የአውሮፓ ከተሞች ከተካሄዱት ተመሳሳይ ኮንሰርቶች ጋር ሲነጻጸር በትንሹ የ30 ሺህ ፓውንድ ብልጫ አሳይቷል ተብሏል።

ይህ መሆኑ ቴይለር ስዊፍት ለሳዲቅ ካሀን ሰጥተዋለች ከተባለው የኮንሰርት መግቢያ ቲኬት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል እየተገለጸ ይገኛል።

ይሁንና የከተማዋ ፖሊስ ወጪው የጨመረው ቴይለር ስዊፍት በኦስትሪያ ቬና ልታካሂደው የነበረው ኮንሰርት በሽብር ጥቃት ስጋት ምክንያት በመራዘሙና ተጨማሪ ጥበቃ ማድረግ በማስፈለጉ እንደሆነ ተገልጿል።

ያልተገባ ስጦታ ወይም ግብዧ መቀበል ወይም መስጠት አንዱ የጥቅም ግጭት መንስኤ ሲሆን፥ የመንግስትን አሰራር ሂደት ሊያደናቅፍ የሚችል ነው።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለከተራ እና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

***

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በህገ-ወጥ ድርጊት የሚሳተፉ አካላት ላይ የሚወሰደው ርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል - የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 12/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በህገ-ወጥ ድርጊት የሚሳተፉ አካላት ላይ የሚወሰደው ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።

አገልግሎቱ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ፣ የፋይናንስ ወንጀሎች በአገር ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ዘርፈ ብዙ እና ከፍተኛ በመሆኑ ኢትዮጵያ ወንጀሎቹን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተለያዩ ህጎችን አውጥታ በመተግባር ላይ እንደምትገኝ ገልጿል።

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 እየተተገበረ መሆኑን መግለጫው አስታውሷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቀድሞ በተለያዩ ህጎች ውስጥ ተበታትነው የሚገኙ የህግ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ ራሱን የቻለ የንብረት ማስመለስ አዋጅ በቅርቡ መጽደቁንም አስታውሷል።

የንብረት ማስመለስ አዋጁም ሆነ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጠጠር የወጣው አዋጅ ዓላማ የፋይናንስ ወንጀሎች አትራፊ አለመሆናቸውን በማረጋገጥ በአገር ላይ የሚያደርሰው ሁሉን አቀፍ አደጋ መግታት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ በሌላ ለጤናማ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ምቹ መደላድል መፍጠር መሆኑ ተመላክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ግለሰቦች የወጡ ህጎችን ለማደናገሪያነት በመጠቀም እንዲሁም የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት እና የሌሎች የፀጥታ አካላትን ስም በመጥቀስ በማጭበርበር እና በማስፈራራት በህገ-ወጥ ድርጊት ገንዘብ ለማግኘት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ክትትል ማድረጉን አገልግሎቱ አስታውቋል።

በዚህም በተደራጀ አግባብ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት ውስጥ 3 ግለሰቦች ዓርብ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም እጅ ከፈንጅ ተይዘው ጉዳዩ በምርመራ ላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ሌሎችንም በቁጥጥር ስራ ለማዋል ከህግ አስከባሪ አካላት እየተሰራ ይገኛል ተብሏል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ከራሱ ምንጮችና ከጥቆማ በሚደርሱት መረጃዎች መሰረት የማጭበርበር የወንጀል ድርጊቶችን ጨምሮ የተለያዩ የፋይናንስ ወንጀሎች ድርጊት ውስጥ የተሳተፉ አካላትን በህግ ተጠያቂ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል። በርካታ ጉዳዮችም በህግ ተይዘው ይገኛሉ ተብሏል።

የወንጀል ድርጊት ፈጻሚዎች የህግ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ አገልግሎቱ የሚወስዷቸውን ርምጃዎች የበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

ህብረተሰቡም ማጭበርበርን ጨምሮ ሌሎች የፋይናንስ ወንጀል በመፈጸም የሚገኝን ገንዘብ ህጋዊ ለማስመሰል የሚፈጸሙ ድርጊቶችን ሲመለከት በ9796 ነፃ ስልክ ለተቋሙ ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በመደወል ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፏል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319