Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
ኮሚሽኑ ከብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽን እና ሥነምግባር ኮሚሽን ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 9/2017 ዓ.ም ቢሸፍቱ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በመልካም ሥነምግባር የታነፀ አመራርና አባላት ለማፍራት የሚያስችለውን ስምምነት ከብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽን እና ሥነምግባር ኮሚሽን ጋር ተፈራርሟል።

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ) ኮሚሽኑ በትውልድ ሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ካለዉ ሰፊ የአደረጃጀት መዋቅርና አባላት ብዛት እንዲሁም መንግስትን የመምራት ሚና አንፃር ስምምነቱ ትልቅ ቦታ እንዳለዉ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በቀጣይ የብልፅግና ፓርቲ አመራርና አባላትን ሙስና እና ብልሹ አሠራር ያለውን የችግር ስፋት ተረድተው እራሳቸውን በመልካም ሥነምግባር እንዲያንፁ የሚያደርጉ የሥነምግባር ግንባታ ስልጠናዎችን ይሰጣል ብለዋል።

የሁለቱ ኮሚሽኖች ስምምነት በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥራ ላይ እስከታችኛው መዋቅራቸው ድረስ በቅንጅት ለመስራት እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

ስምምነቱ በቀጣይ በሙስና እና ብልሹ አሰራር የሚጠረጠሩ የፓርቲው አመራርና አባላት ሲያጋጥሙ አስተዳደራዊና ህጋዊ ውሳኔ ለመውሰድ ይረዳል ብለዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም ሌሎች የፓለቲካ ፓርቲዎችም ይህንኑ አርአያነት ያለዉ ተግባር ቢከተሉ ሀገርን ከሙስና እና ብልሹ አሰራር ለመታደግ በሚደረገው ትግል ዉስጥ አወንታዊ ሚና እንዲኖራቸው ያግዛል ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽን እና ሥነምግባር ኮሚሽን ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊ ዳዊት በበኩላቸው ስምምነቱ ፖርቲው በፀረ-ሙስና ትግል ላይ ያለዉን አርአያነትና አቋም የሚያሳይና በመጀመሪያው የጉባኤ ዉሳኔ መሰረትም ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ለመታገል እንደሆነ አስረድተዋል።

ወ/ሮ ሰላማዊት አክለውም ሁለቱ ተቋማት በጥናትና ስልጠና እንዲሁም በመረጃ ልዉዉጥ ላይ አብረው እንደሚሰሩ ገልፀው፥ የስምምነቱ ተፈፃሚነትም በፓርቲው አመራሮች፣ አባላትና በፓርቲው ሌሎች አካላት ላይ በመሆኑም በፍፁም ከመንግስታዊ ስራ ጋር እንደማይደባለቅ አስረድተዋል።

የብልፅግና ፖርቲ የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ የስምምነቱን ሰነድ ሲያቀርቡ እንዳሉት የብልፅግና ፓርቲ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የፓርቲው አባላት ወደ ፓርቲው ሲቀላቀሉ በመልካም ሥነምግባር የታነፁና ከብልሹ አሰራር ነፃ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ ሀብታሙ አክለውም ከብልፅግና ፓርቲ 13 የዲሲፕሊን ጥሰቶች መካከል ሙስና አንዱ መሆኑን ገልፀው፥ ስለሆነም በቀጣይ በፀረ-ሙስና ትግሉ ላይ በቅንጅት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዋና እና ምክትል ኮሚሽነሮች እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽን እና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሙስናን መታገል እና ብልሹ አሠራርን ማሥወገድ የሁሉም ድርሻ መሆን እንዳለበት ተገለፀ

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ‘’ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት’’ በሚል መሪ ቃል ለመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ አመራርና ሠራተኞች ሙስና እና ብልሹ አሰራር መከላከል ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በሥልጠናው የተገኙት የመከላከያ ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ የፋይናንስ ሥራ አመራር ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀኔራል ሙስጠፌ መሐመድ እየተፋጠነ የሚገኘው የሀገራችንን ዕድገት የሚያጓትተውን የሙስና ችግር ለመቅረፍ በሀገር ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ሙስናን መታገል እና ብልሹ አሠራርን ማሥወገድ የሁሉም ድርሻ መሆን እንዳለበት አመላክተዋል።

ትምህርቱ ሙስናን ለመታገል እና ብልሹ አሰራርን ለማስወገድ መልካም አጋጣሚ በመሆኑ የዋና መምሪያው የሠራዊት አባላትም ሆኑ ሲቪል ሠራተኞች ትኩረት መሥጠት እንዳለባቸው አሥገንዝበዋል፡፡

የመከላከያ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክተር ተወካይ ሌተናል ኮሎኔል ሲሳይ ተስፋሁን ሥልጠናው በሀገር ላይ የሚሥተዋለውን ችግር ለመቅረፍና ብልሹ አሠራርን ለማሥወገድ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የሃብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ሂደቱ መንግስት ይዞታውን እንዲቆጣጠርና ሙሰኞችን ለማደን የሚረዳ በመሆኑ ለሀገር ዕድገት ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ማስረዳታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የሥነ-ምግባር ክትትል ቡድን መሪ ተወካይ ሻለቃ ዘላለም ዓለሙ በበኩላቸው እንደ ሀገር የታለመውን ፈጣን ዕድገት ማሳካት የምንችለው ሙስናን አስወግደን በፍትሃዊነት ልማታችን ላይ ብቻ ማተኮር ስንችል ነው ብለዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሙስናን መዋጋት የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑ ተገለፀ

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለብራና ማተሚያ ድርጅት ሠራተኞች በሙስና እና የሙስና መከላከያ ስልቶች ላይ ያተኮረ ስልጠና ለሁለት ቀናት ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማተሚያ ድርጅቱ ም/ሥራ አስፈፃሚ እና የሠው ሃብት መምሪያ ኃላፊ አቶ በለጠ ፀጋዬ ሙስና የሃገር ስጋት በመሆኑ ሁሉን አቀፍ ትግል ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ከስልጠናው የሚገኘውን ግንዛቤ በጥልቀት በመረዳት ብልሹ አሰራርን የሚፀየፍ አምራች ማህበረሰብ እንዲፈጠር በቁርጠኝነት መታገል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በስልጠናው ማጠቃለያ የተገኙት የተቋሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ያለው መኮንን አሁን ላለንበት የሥነ-ምግባር ውድቀትና የሙስና ስጋት በማህበረሰቡ እያደገ የመጣው የሥነምግባር እጦትና ብልሽት ስለሆነ ሙስናን መዋጋት የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ሰልጣኞች በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ በሰጡት አስተያየት በተለይ በሙስና ወንጀሎች ላይ የተሻለ ግንዛቤን ያስጨበጠ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል።

ሰልጣኞች አክለውም ቀጣይነት ያለው መሰል ስልጠና በየጊዜው ቢሰጥ ለሙስና ትግል የሚኖረው ድርሻ የጎላ ይሆናል ማለታቸውን ከመከላከያ ዘርፍ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319