ለባህር ዳር አካዳሚ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የሥነምግባር ግንባታ ስልጠና ተሰጠ
*******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በክልሉ የትውልድ ሥነምግባርን ለመገንባት በት/ቤቶች ተከታታይ የሥነምግባር ግንባታ ስራ እየተሰራ ነው።
የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተማሪዎች በሥነምግባር ታንፀው ነገ እራሳቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውንና ሀገራቸውን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል እንዲችሉ በየትኛውም የትም/ት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች የሥነምግባር ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጿል።
የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ባለሙያ ወ/ሮ በላይነሽ አሰፋ በከተማው ለሚገኘው ለባህር ዳር አካዳሚ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከ9ኛ- 10ኛ ክፍል ለተወጣጡ ተማሪዎች የሥነምግባር ግንባታ ስልጠና ሰጥተዋል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

የጉምሩክ ኮሚሽን ሙስናን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የፀረ-ሙስና ትግል እያደረገ መሆኑ ተገለጸ
***********************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሙስናን ለመግታት ታማኝነትን ማጎልበት በሚል መሪ ቃል በዓለም ጉምሩኮች ድርጅት (WCO) አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሙስናን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያስችል የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አዝዘው ጫኔ፣ ሙስና የአንድ ተቋም ሀገር ብቻ ችግር ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው መሆኑን ጠቅሰው፣ ልማትን የሚጎትት፣ የሀገርን እና ተቋማትን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሊጠየፈው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ሙስናን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የፀረ-ሙስና ትግል እያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ተከታታይ ጥናቶችን በማድረግ፣ የሙስና አዝማሚያዎችን በመለየት እና የስጋት ስራ አመራር ስርዓትን በመዘርጋት ብሎም የአሰራር ግልጽነትን በማስፈን ሙስናን ለመከላከል እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የጉምሩክ ኮሚሽን ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እያደረገ ያለው ጥረት በተመለከተ በዓለም የጉምሩኮች ድርጅት የተጠና የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ውይይት መደረጉን ከጉምሩክ ኮሚሽን የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በመድረኩ የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አዝዘው ጫኔ፣ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ እሸቴ አስፋው፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

ሙስና እና ብልሹ አሰራር ለሀገር ዕድገት ፀር በመሆኑ መከላከል ላይ መሥራት እንደሚገባ ተገለፀ
***********************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ‘’ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት’’ በሚል መሪ ቃል ለጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ እና ለሞተር ቪሂክል ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ አመራርና ሠራተኞች ሙስና እና ብልሹ አሰራር መከላከል ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በሥልጠናው የተገኙት የጋፋት አርማመንት ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል ሀገሬ ተሰማ ሙስናን በመዋጋት የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን የሚፀየፍ ትውልድ ማፍራት ይገባል ብለዋል።
የሞተር ቨሂክል ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ሲሳይ ተሰማ በበኩላቸው ሙስና በሃገሪቱ ላይ እየፈጠረ ያለውን ቀውስ እያንዳንዱ ግለሰብ ተረድቶና በውስጡ ቁጭት ፈጥሮ ይህን የሀገር ስጋት በቃ ማለት እንዲችል ስልጠናው ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ከተፈጠረው ግንዛቤ በመነሳት ሁሉም ከሙስና እና ብልሹ አሰራር ራሱን መጠበቅ እንዳለበት መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከአሰራር ውጪ የ16 ሰራተኞች ቅጥር እንዲፈጸም ያደረገው በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ
*******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት በጥቅም በመመሳጠር ከአሰራር ውጪ የ16 ሰራተኞች ቅጥር እንዲፈጸም ያደረገው ተከሳሽ በ14 ዓመት እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ ወሰነ።
የዞኑ ዐቃቤ ሕግ ፈይሳ ዱደማ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 2 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ መተላለፉን ጠቅሶ ተደራራቢ ክስ አቅርቦበት ነበር።
በዚህም ተከሳሹ ፈይሳ ዱደማ በ2015 ዓ.ም በምዕራብ ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ የሰው ሃብት ልማት አስተዳደር ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ በተለያዩ ጤና ጣቢያዎች ለሚመደቡ ሰራተኞች በወጣ የቅጥር ማስታወቂያ መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰራተኞች እያሉ ተከሳሹ ከሌሎች ሶስት ግብረዓበሮቹ ጋር በጥቅም በመመሳጠርና ስልጣኑን ያለአግባብ በመጠቀም የማይመለከታቸውን ማለትም መስፈርቱን የማያሟሉ 16 ግለሰቦች የስራ ቅጥር እንዲፈጸምላቸው እና እንዲመደቡ በማድረግ ያልተገባ 732 ሺህ 823 ብር የደመወዝ ክፍያ እንዲፈጽምና በተመሳሳይ በመንግስት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጉ ተጠቅሶ ተደራራቢ ክሶች ቀርበውበት ነበር።
ተከሳሹ ችሎት ቀርቦ ክሱ ከደረሰው በኋላ የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸሙን ጠቅሶ ክዶ በመከራከሩ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦበታል።
ፍርድ ቤቱም የቀረበውን ማስረጃ መርምሮ በክሱ ላይ የተጠቀሰው የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን ጠቅሶ ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን ሰጥቷል።
በዚህም ተከሳሹ ተከላከል በተባለበት ድንጋጌ ስር የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን ማስተባበል ባለመቻሉ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል።
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት መርምሮ ተከሳሹን በ14 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።
በተጨማሪም ተከሳሹ ቀደም ሲል በተፈቀደለት የ25 ሺህ ብር የዋስትና መብት መነሻ የዋስትና ግዴታውን አክብሮ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ በመቅረቱ ምክንያት ተጨማሪ የ280 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኗል።
ፍርድ ቤቱ የኦሮሚያ ፖሊስ ተከሳሹን በቁጥጥር ስር አውሎ ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብና የተወሰነበትን የእስራት ውሳኔ እንዲያስፈጽም ትዕዛዝ መስጠቱን ኤፍኤምሲ ዘግቧል።
ይህ በእንዲህ እያለ የዞኑ ዐቃቤ ሕግ ከዞኑ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ኃብት ቢሮ ጋር በመሆን በህገ-ወጥ መንገድ የስራ ቅጥር የተፈጸመላቸው 16 ሰራተኞች ከስራ እንዲታገዱ በማድረግ የተከሳሹ ግብረ አበሮች ናቸው በተባሉ ሶስት ግለሰቦች ላይ በፍርድ ቤቱ ክስ ማቅረብ መቻሉን ለማወቅ ተችሏል።

በድሬዳዋ ከተማ በሕገ ወጥ ተከማችቶ የተገኘ ከ12 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከሰባት ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ
*******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በሕገ ወጥ መንገድ በቤት ውስጥ የተከማቸ ከ12 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከሰባት ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን የአስተዳደሩ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው ሕገ ወጥ የነዳጅ ግብይት በሚፈፅሙ ማደያዎች ላይ ጥብቅና አስተማሪ እርምጃ የመውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
የድሬደዋ ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያውን ተከትሎ በከተማው እየተካሄደ የሚገኘውን የነዳጅ አቅርቦትና ግብይት የተመለከተ መግለጫ ለመገናኛ ብዙሃን ሰጥቷል።
በቢሮው የንግድ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሚኖ ጠሃ እንደተናገሩት፤ በከተማዋ የሚገኙ ማደያዎች በተሻሻለው የነዳጅ ዋጋ መሠረት ነዳጅን በፍትሃዊነት ለተጠቃሚው እንዲያቀርቡ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል።
ነገር ግን አንዳንድ ማደያዎች መንግስት በከፍተኛ ድጎማ የሚያመጣውን ነዳጅ በሕገ ወጥ መንገድ እያሰራጩ መሆኑ ተደርሶበታል ብለዋል።
ችግሩን ለመከላከል እና ነዳጅን በፍትሃዊነት ለታለመለት አላማ ለማዋል የፀጥታና የፍትህ አካላት የተካተቱበት ግብረሃይል ተቋቁሞ የተቀናጀ ክትትል እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
በዚሁ መሰረተ በተደረገ ክትትል እና ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ በህገ ወጥ መንገድ በቤት ውስጥ ተከማችቶ የተገኘ ከ12 ሺህ 700 ሊትር ቤንዚን መያዙን ተናግረዋል።
ቤንዚኑን በመኖሪያ ቤታቸው የደበቁ እና በህገ ወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑንም ተናግረዋል።
ነዳጅን በበርሜል በህገ ወጥ መንገድ ሲሸጡ የተደረሰባቸው ሁለት የነዳጅ ማደያዎች ሀላፊዎች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን ገልጸዋል።
በእነዚህ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ የሚወሰድባቸው መሆኑን ጠቅሰው ሌሎቹም ማደያዎች ከመሰል ህገ ወጥ ተግባር ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስበዋል።
በህገ ወጥ ተግባራት ላይ በተሰማሩ ማደያዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።