ብሔራዊ የሙስና ወንጀል መረጃ ጥቆማ መስጫ መተግበሪያ አጠቃቀም እና በውስጡ የያዛቸው አገልግሎቶች
*******
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ ሥርዓትን እንዴት መጠቀም እንችላለን? ምን አይነት አገልግሎቶችንስ አካቷል? የሚለውን እንደሚከተለው ተመላክቷል።
✍️ ሥርዓቱ በኮምፒዩተር ብራውዘር አማካኝነት ወይም በስልኮቻችን በመጫን በኢንተርኔት አማካኝነት መጠቀም እንድንችል ተደርጎ የበለፀገ ነው፡፡
✍️ መተግበሪያውን በስልክ ለመጠቀም አፕስቶር እና ፕሌይስቶር ላይ “NCRS” ብለን በመፈለግ ማውረድ እንችላለን፡፡
✍️ መተግበሪያውን ለመጠቀም በስልክ ቁጥራችን መመዝገብና የይለፍ ቃል መጠቀም ይኖርብናል፡፡
✍️ ማንኛውንም አይነት የሙስና ወንጀል ጥቆማ ለመስጠትም ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ በተቀመጡልን አማራጮች መሠረት ለፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን መላክ ያስችለናል፡፡
✍️ የሙስና ወንጀል ጥቆማዎችን በምስል፣ በጽሁፍ፣ በድምጽ፣ በቪዲዮ ወይም በሰነድ አስደግፈን መላክ ከፈለግን መተግበሪያው አማራጮች አሉት፡፡
✍️ ጥቆማ ከላክን በኋላም፥ የላክነው ጥቆማ የደረሰበትን ሂደት ለመከታተል ያስችላል፡፡
✍️ ሥርዓቱ በአምስት የቋንቋ አማራጮች ጥቆማዎችን እንድንሰጥ ያስችለናል፡፡ ቋንቋዎቹም ከአገር ውስጥ አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ እና ሶማሌኛ ሲሆኑ፥ ከውጭ ደግሞ እንግሊዘኛ ቋንቋን አካቷል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

በህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅን ፍላጎት ለማስከበር ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞው አሜሪካዊው ሴናተር ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው ተጠየቀ
*******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅን ፍላጎት ለማስከበር ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞው አሜሪካዊው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው የአሜሪካ ፌደራል ዓቃቤ ሕጎች ጠይቀዋል።
የአሜሪካ ፌደራል ዓቃቤ ሕጎች፣ ከግብጽ መንግሥት ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብና የወርቅ ሥጦታ በመቀበል የግብጽን ጥቅም ለማስጠበቅ በሞከር ጥፋተኛ በተባሉት የቀድሞው የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ ቦብ ሜኔንዴዝ ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው ጠይቀዋል።
ሜኔንዴዝ ጥፋተኛ ከተባሉባቸው ክሶች መካከል፣ የኢትዮጵያና ግብጽ የሕዳሴ ግድብ ውዝግብን ለመፍታት በሚደረገው ድርድር የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሚና እንዲጫወት በመጠየቅ ያልተገባ ተጽዕኖ ለመፍጠር ሞክረዋል የሚል ይገኝበታል።
ክሱን ተከትሎ ሜኔንዴዝ የምክር ቤቱን መቀመጫቸውን መልቀቃቸውን አስታውሶ ሲኤንኤን ዘግቧል። የፌደራሉ ፍርድ ቤት በሜኔንዴዝ ላይ የእስር ብይኑን ጥር 21 ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
የቀድሞው የኒው ጀርሲው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የውጭ መንግሥት ፍላጎትን ለመፈጸም ሥልጣናቸውን መጠቀም፣ ጉቦ መቀበል፣ ማጭበርበር፣ ፍትሕን ማደናቀፍን ጨምሮ በ16 የወንጀል ድርጊቶች ተከሰው በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ መባላቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና ግብዓት በመሰወር የተከሰሰው ግለሰብ ተቀጣ
*******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ መድሐኒት አቅራቢ ድርጅት ተረክቦ ለኦሮሚያ ክልል ማስረከብ የነበረበትን የህክምና ግብዓት ሳያስረክብ ሰውሮ ለግል ጥቅም በማዋል የተከሰሰው ግለሰብ በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወሰነ።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ መድሐኒት አቅራቢ ድርጅት ሾፌር በነበረው መስፍን መክብብ ላይ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 31 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2 ስር እንዲሁም በሙስና አዋጁ አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር 2/ሀ እና ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፍ በሚል ሁለት ክሶችን አቅርቦበት ነበር።
አንደኛው ክስ ላይ ተከሳሹ የድርጅቱ ሾፌር ሆኖ በሚሰራበት ወቅት ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ድርጅቱ ለጤና ተቋማት የሚያከፋፍላቸውን መድሐኒቶችና የህክምና ግብዓትን ለማድረስ በተሰጠው ሀላፊነት መነሻነት ሚያዝያ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በወጭ ማድረጊያ ደረሰኝ የተረከበውን 9 ሺህ 500 እሽግ የእጅ ጓንቶችን፣ 1 ቤዚን ኪድኒ እና 2 እስፕሪተር የተባለ የህክምና መሳሪያ፤ 2 ሚዘን ቢኤም ትሪፕል የህክምና መሳሪያ አጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው 5 ሚሊየን 515 ሺህ 227ብር ከ30 የሆኑ የህክምና መሳሪያዎችን ለኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ እንዲያደርስ ከተረከበ በኋላ ሳያስረክብ ለራሱ ወስዶ የሰወረ በመሆኑ ከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበት ነበር።
በ2ኛ ክስ ደግሞ ተከሳሹ ከድርጅቱ ወደ ኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ለማድረስ በሚያዝያ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በወጭ ማድረጊያ ደረሰኝ የተረከባቸውን የህክምና መሳሪያዎች ለጤና ቢሮው ባላስረከበበት ሁኔታ በኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ለደም ባንክና የህክምና ግብዓቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም በመረካከቢያ ደረሰኝ እንዳስረከበ በማስመሰል ሀሰተኛ የመረካከቢያ ሰነድ ለኢትዮጵያ መድሐኒት አቅራቢ ድርጅት ያቀረበ በመሆኑ በፈጸመው በሀሰተኛ መንግስታዊ ሰነድ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሷል።
ተከሳሹ የክስ ዝርዝር ከደረሰውና በንባብ ከተሰማ በኋላ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦበታል።
ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን ተመልክቶና መርምሮ በክሱ ላይ የተጠቀሰው የወንጀል ተግባር መፈጸሙን ማረጋገጡን ጠቅሶ ሁለቱ ክሶች ተጣምረው እንዲከላከል ብይን መስጠቱን አፍኤምሲ ዘግቧል።
ተከሳሹ የቀረበበትን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት መርምሮና የተከሳሹን 4 የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕርከን 22 መሰረት በ6 ዓመት ጽኑ እስራትና በ6 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኗል።

1,165 ሃሰተኛ ደረሰኞች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ተደርጓል - ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ
***********************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ባለፉት ስድስት ወራት የህግ ተገዢነትን ለማስፈን በተደረገው ጥረት 1,165 ሃሰተኛ ደረሰኝ ጥቅም ላይ እንዳይውል መደረጉን የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ገለጹ፡፡
ደረሰኞቹ በ153 ድርጅቶች ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበር ሲሆን፣ በዚሁም 1,210,091,184 ብር ሃሰተኛ ግብይት ለታክስ ዓላማ እንዳይውሉ መደረጉም ተመላክቷል፡፡
ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም አክለውም የህግ ተገዢነትን ለማስፈን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
እንዲህ ባለ አላስፈላጊ ህገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉ አካላትም ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሚኒስቴሩ ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው
*******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) አለአግባብ ትርፍ ለማግኘት በማሰብ ከ10 እስከ 15 ቀናት በጢሻ ውስጥ ተደብቀው በነበሩ 250 የነዳጅ ቦቴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከነዳጅ ምርቶች ስርጭትና ግብይት ጋር ተያይዞ በሚስተዋሉ ሕገወጥ ተግባራት ላይ መንግስት ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑንም አስታውቋል።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ከሰሞኑ አለአግባብ ትርፍ ለማግኘት በማሰብ ከ10 እስከ 15 ቀናት በጢሻ ውስጥ ተደብቀው በነበሩ 250 የነዳጅ ቦቴዎች ላይ ቅጣት መጣሉን ገልጸዋል።
በዚህም ቦቴዎቹ ለስድስት ወራት ምንም አይነት የነዳጅ ምርት እንዳያዘዋውሩ ታግደዋል። በዚህ ሕገወጥ ተግባር ተባባሪ የነበሩ 19 ማደያዎችም ለስድስት ወራት ከግብይቱ መታገዳቸው ተገልጿል።
ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባቸውም ጠቅሰዋል። 35 ማደያዎች ተመሳሳይ እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል።
385 ሺህ ሊትር ነዳጅ በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተወርሶ 27 ሚሊዮን ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉንም ጠቅሰዋል።
በቀጣይ ከዲጂታል የግብይት ሥርዓት ውጭ ግብይት የሚፈጽሙ ማደያዎችን ከንግድ ሥርዓቱ የማስወጣት እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል ብለዋል።
ሚኒስትሩ መንግስት እየወሰደ ያለው ጠንካራ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መጠቆማቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

በመዲናዋ ሊመዘበር የነበረን 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ማዳን ተቻለ
*******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 6/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአዲስ አበባ በህገ ወጥ መንገድ ሊመዘበር የነበረ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ሃብት ማዳን መቻሉን የከተማዋ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ም/ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷በመዲናዋ ብልሹ አሰራሮችን ከመቅረፍ አንጻር በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡
በተለይም በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ለማስተካከል በትብብር መሠራቱን አንስተዋል።
ባለፉት አምስት ወራትም በ3 ሺህ 933 ጉዳዮች ክሶች ቀርበው የፍርድ ቤት ክርክሮች እንደተደረጉ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ውስጥም 1ሺህ 314 መዝገቦችን በመከራከር በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያገኙ መደረጉን ነው ያስረዱት።
ቢሮው በ1 ሺህ 266 መዝገቦች ማሸነፋን ጠቁመው ÷ በዚህም መንግስት ሊያጣው የነበረ 1ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል፡፡
በመዲናዋ የሚስተዋሉ ሕገ ወጥ ተግባራትን ከስር መሠረታቸው ለማድረቅም ነዋሪዎች ጥቆማ በመስጠት የበኩላቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውን ኤፍኤምሲ ዘግቧል።

ምክር ቤቱ በብልሹ አሰራር ላይ ተገኝተዋል ያላቸውን ሁለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን አሰናበተ
*******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 6/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት 6ኛ ዙር ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡
የፌደራል ዳኞች አስተዳዳር ጉባዔ ሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ ያቀረበውን የስንበት ውሳኔ አስመልክቶ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መመርመሩን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
በዚህም መሰረት አዱኛ ነጋሳ እና አክሊሉ ዘሪሁን የተባሉ ሁለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በሙስና እና በብልሹ አሰራር ላይ በመገኘታቸውና ሁለቱ ዳኞች በሥራ ላይ በነበሩ ጊዜ ኃላፊነታቸውን ያላግባባ በመጠቀማቸው ምክር ቤቱ የቀረበውን የስንብት ደብዳቤ አጽድቋል፡፡

የዩኬ የግምጃ ቤት ሚኒስትር በባንግላዴሽ በቀረበባቸው የሙስና ክስ ከሥልጣናቸው ለቀቁ
***********************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 7/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የዩናይትድ ኪንግደም የግምጃ ቤት ሚኒስትር ቱሊፕ ሲዲቅ በባንግላዴሽ እየተካሄደባቸው ካለው የሙስና ምርመራ ጋር በተያያዘ በደረሰባቸው ጫና ከሥልጣናቸው ለቀቁ።
ሚኒስትሯ ባለፈው ዓመት ከሥልጣናቸው ከተወገዱት አክስታቸው ጋር ባላቸው ግንኙነት ላይ ጥያቄ ከተነሳባቸው በኋላ ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሲር ላውሪ ማንጉሰ ጋር ወስደውት ነበር።
ሰር ላውሪም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ትክክለኛ ማስረጃ እንዳላገኙ፤ ነገርግን ሚኒስትሯ ከአክስታቸው ጋር ባላቸው ግንኙነት ሳቢያ የስም ማጥፋት አደጋ ሊገጥማቸው እንደሚችል በማሰብ ጥንቃቄ አለማድረጋቸው የሚያፀፅት ነው ብለዋል።
ሲዲቅ በበኩላቸው በኃላፊነታቸው ላይ መቆየት ለመንግሥታቸው ጥሩ ሊሆን እንደማይችል ገልጸው፤ ነገር ግን ምንም የሰሩት ወንጀል እንደሌለ ተናግረዋል።
የሲዲቅ ከሥራ መልቀቅ ከመገለጹ አስቀድሞ በባንግላዴሽ የሙስና ምርመራ ከሚካሄድባቸው ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ስማቸው ተካቷል።
የወግ አጥባቂው መሪ ኬሚ ባደኖች በኤክስ ገጻቸው ባጋሩት ጽሑፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚኒስትሯን ለመከላከል እና ለመጠበቅ ዘግይተዋል ሲሉ ወቅሰዋል።
መሪው ጨምረውም አሁንም ባንግላዲሽ በቱሊፕ ላይ የወንጀል ክስ ሲመሰርት ሚኒስትሯ ከሥራ በመልቀቃቸው ሃዘናቸውን ከመግለጽ ባሻገር ያደረጉት ነገር የለም ሲሉ ኮንነዋል።
"ከደካማ ጠቅላይ ሚኒስትር ደካማ አስተዳዳር" ሲሉም ተችተዋል።
ሰር ኬር የሲዲቅን የሥራ መልቀቂያ መቀበላቸውን በገለጹበት ደብዳቤ ለሳዲቅ በራቸው ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ገልጸዋል።
በዩኬ የፋይናንስ ገበያ ያለውን ሙስና መከላከልን ጨምሮ ለግምጃ ቤቱ የኢኮኖሚ ኃላፊነት ሚና የነበራቸው ሲዲቅ፣ ባለፈው ወር ቤተሰባቸው በባንግላዴሽ በተሰራ የመሰረተ ልማት ግንባታ ጋር በተያያዘ 3.9 ቢሊየን ፓውንድ ገንዘብ ዘርፈዋል በሚል ስማቸው ተጠቅሶ ነበር።
የቀድሞው የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አክስታቸው ሼይክህ ሃሲና የአዋሚ ሊግ ኃላፊ የነበሩ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ በስደት ነው ያሉት።
ቢቢሲ የተመለከተው የፍርድ ቤት ሰነድ ሃጃጂ፣ እአአ በ2013 በባንግላዴሽ አዲስ የኒውክሌር ኃይል ጋር በተያያዘ አክስቷ ከሩሲያ ጋር ለማስማማት ሲዲቅ ረድተዋል ሲሉ ከሰዋል።
የኃይል ማበልጸጊያውን የስምምነት ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙ ሲሆን፣ ከሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ፎቶ ተነስተዋል።
ሆኖም ሰር ላውሬ እና ሲዲቅ በወቅቱ የነበረውን አውድ ማህበራዊ ግንኙነትና ጉብኝት እንደነበር አስረድተዋል።
ሰር ላውሪ እንዳሉት ሲዲቅ በባንግላዴሽ እና በሩሲያ መንግሥታት መካከል በተካሄደው ውይይት ምንም ዓይነት ግንኙነት የላትም።
የባንግላዴሽ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሲዲቅ እናቷን ሬሂና ሲዲቅ ሃሲናን ሥልጣኗን በመጠቀም በጣም ወሳኝ በሆነ እና ዲፕሎማቲክ ቦታ መሬት ለማግኘት ተፅዕኖ ለማሳደር እናቷን ስትደግፍ ነበር ሲል ከሷል።
ከዚህም በተጨማሪ የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን አክስታቸውን ለመርዳት ሥልጣናቸውን ተጠቅመዋል ብሏል።
የሲዲቅ ቃል አቀባይ በበኩላቸው በሚኒስትሯ ላይ ለቀረቡት ክሶች ምንም አይነት ማስረጃ አልቀረበም ብለዋል።
የሲዲቅን ከሥልጣን መልቀቅ ተከትሎም የሌበር የፓርላማ አባል ኢማ ሪይኖልድስ ለግምጃ ቤቱ አዲስ የኢኮኖሚ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

ከአፍሪካ ህብረት ሂሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ለመመዝበር ሙከራ በማድረግ የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ ጥፋተኛ ተባሉ
*******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 7/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከአፍሪካ ህብረት ሂሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ለለመዝበር ሙከራ በማድረግ የሙስና ወንጀል የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ ጥፋተኛ ተባሉ።
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ የቀረቡ የግራ ቀኝ ማስረጃዎችን መርምሮ በዛሬው የችሎት ቀጠሮ በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ቀሲስ በላይ መኮንን፣ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ፣ በኮሚሽን ስራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ እና አለምገና ሳሙኤል እንዲሁም የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ በተባሉ ተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ ቁጥር 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና የሙስና ወንጀሎች ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 2 እና ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ እና በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ ቁጥር 382 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ከአፍሪካ ህብረት ምንም አይነት የክፍያ ትዕዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ ተከሳሾች በተለያየ መጠን ክፍያ እንዲፈጸምላቸው የሚል አጠቃላይ የ6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሀሰተኛ የክፍያ ሰነድ በአንደኛ ተከሳሽ አማካኝነት ለባንኩ መቅረቡ ተጠቅሶ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።
በዚህ መልኩ የቀረበው ክስ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተከሳሾች ብቻ ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በአድራሻቸው ባለመገኘታቸውና በተደጋጋሚ ቀጠሮ ባለመቅረባቸው ለጊዜው ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል።
ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ክሱ እንዲሻሻልላቸው ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ ክስ መቃወሚያ ነጥቦችን ፍርድ ቤቱ መርምሮ ወደፊት በማስረጃ የሚጣራ መሆኑን ገልጾ መቃወሚያቸውን አልተቀበለውም።
ከዚህም በኋላ ተከሳኞቹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው የዕምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ የአፍሪካ ህብረት ቅርጫፍ የባንክ ባለሙያዎችን አጠቃላይ ሶስት ምስክሮችን አቅርቦ ምስክርነታቸውን አሰምቶ ነበር።
ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል መርምሮ በክሱ ዝርዝር የተጠቀሰው የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን በዐቃቤ ሕግ በማስረጃ ማረጋገጡን ጠቅሶ በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር እንዲከላከሉ በሰጠው ብይን ተከሳሾቹ ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ በተገቢው ማስተባበል አለመቻላቸውን ጠቅሷል።
በዚህም በዛሬው ቀጠሮ 1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን በሙሉ ድምጽ የጥፋተኝነት ፍርድ የተሰጠባቸው ሲሆን፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በአንድ ዳኛ የሀሳብ ልዩነት በአብላጫ ድምጽ ጥፋተኛ ተብለዋል።
የሀሳብ ልዩነት ያቀረቡት አንደኛው ዳኛ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት የባንክ ሂሳባቸው በመገለጹ ብቻ የወንጀል ተግባሩ በስምምነት ተፈጽሟል ለማለት አያስችልም የሚል የሀሳብ ልዩነት እንዳላቸው ጠቅሰው ልዩነታቸውን አሳይተዋል።
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት ተመልክቶ የቅጣት ውሳኔ ለመወሰን ለጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም መቅጠሩን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል ።

የንብረት ማስመለስ አዋጁ ያለአግባብ ሀብት የማካበት እሳቤን ለማስቀረት ያግዛል - የህግ ምሁር
*******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 7/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የንብረት ማስመለስ አዋጁ ያለአግባብ ሀብት የማካበት እሳቤን ለማስቀረት እንደሚያግዝ የህግ ምሁሩ ገልጸዋል።
ኤኤምኤን የንብረት ማስመለስ አዋጁ አስፈላጊነት፣ አተገበባር እና በሚጠበቁ ውጤቶች ዙሪያ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቱ የህግ ምሁር እና ጠበቃ ከሆኑት አቶ ዘመድኩን መካሻ ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡
የንብረት ማስመለስ አዋጁ ህጋዊነትን የሚያሰፍን እና በአቋራጭ የመክበር እሳቤን በማስቀረት ሰርቶ ማደግ እና ሀብት ማካበት እንደሚቻል የሚረዳ፣ ትውልድን ለመቅረጽ እንደሚያስችል የህግ ምሁሩ አቶ ዘመድኩን ተናግረዋል፡፡
ለሚያካብትው ሀብትም ህጋዊ አሰራርን የሚከተል ትውልድን በመቅረጽ በኩል ትልቅ ትርጉም ያለው ስለመሆኑ ምሁሩ አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም አዋጁ ከዚህ ቀደም የነበሩ ህጎች ይስተዋልባችው የነበሩ ክፍተቶችን የሚሞላ እንዲሁም አለም አቀፍ ህጎች ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ለማስቻል ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
አዋጁ ተግባራዊ ሲሆን የመንግስትን የመፈፀምና ወንጀልን የመከላከል ምጣኔ ያሳድጋልም ብለዋል፡፡
እንዲሁም በህዝብ እና በሀገር ላይ ትልቅ ለውጥን የሚያመጣና በሀገር ኢኮኖሚ ላይም ሚናዉ የጎላ በመሆኑ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማዳበር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሰሞኑ ባካሄደው14ኛ መደበኛ ስብሰባው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምጽ ማጽደቁ ይታወሳል፡፡

በህገወጥ ድለላና የማጭበርበር ተግባር የተሰማሩ 126 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል - የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት
***
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 7/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በህገወጥ ድለላና የማጭበርበር ተግባር የተሰማሩ 126 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት አስታውቀዋል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት አገልግሎቱ የአሰራርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሻሻያ ማድረጉን ተከትሎ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን የኢ-ፓስፖርት ቡክሌቶች ተመርተው ወደ አገር ውስጥ እየገቡ መሆኑን ጠቁመዋል።
የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉ የመሰረተልማትና ቴክኖሎጂ ስራዎች መጠናቀቃቸውንም ገልፀዋል።
በህገወጥ ድለላና የማጭበርበር ተግባር የተሰማሩ 126 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በሀሰተኛና የተጭበረበረ የጉዞ ሰነድ ለመገልገል የሞከሩ ከ 13 ሺህ በላይ ዜጎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።
ተገልጋዮች የቀጠሮ ቀናቸውን አክብረው አገልግሎት ማግኘት እንዳለባቸውና ተመሳስለው በተሰሩ ሶሻል ሚዲያና ዌብሳይቶች እንዳይታለሉ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።