Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.88K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ

*****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ የሙስና ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ መቀጣታቸው ተገልጿል።

1ኛ ተከሳሽ አበበ ጌቴው በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ የአስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ሠራተኛ ሁኖ በፊት የመዘጋጃ ቤቱ ኃላፊዎች የነበሩ ግለሰቦችን ስምና ፊርማ በመጠቀም በከተማው 01 ቀበሌ ላይ ለሁለተኛ ተከሳሽ አበራ ክብረት የ150 ካ.ሜ ቦታ ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ በመስጠቱና ድርጊቱን ለመፈፀም ከሁለተኛ ተከሳሽ 38,000.00 ብር ጉቦ መቀበልና በፈፀመው ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀት ወንጀል ተከስሷል።

2ኛ ተከሳሽ አበራ ክብረት በጋዝጊብላ ወረዳ አስ ከተማ 01 ቀበሌ በአንደኛ ተከሳሽ ተዘጋጅቶ የተሰጠውን ሀሰተኛ ካርታና ፕላን ሲገለገል በመገኘቱ በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል የተከሰሰ እና ይህንን ተግባር እንዲፈፀም ለአንደኛ ተከሳሽ 38,000 ብር ጉቦ መስጠት ወንጀል ተከሷል።

የጋዝጊብላ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ድርጊቱን በማጣራት መዝገቡን ለዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፍትህ መምሪያ እንደላከ ተገልጿል።

የፍትህ መምሪያው የወንጀል የሥራ ሂደትም መዝገቡን ከመረመረ በኋላ በ1ኛ ተከሳሽ ላይ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 (1) እና አንቀጽ 10 (1) በመተላለፍ፣ 2ኛ ተከሳሽ የአዋጁን አንቀጽ 23 (1) እና አንቀጽ 25 (1) የተመለከተውን መተላለፋቸው ተመላክቷል።

በመሆኑም በእያንዳንዳቸው ክሶችን በማዘጋጀት ለብሄረሰብ አስተዳደር ዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ክርክር ሲደረግ ከቆዬ በኋላ ፍ/ቤቱ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ በሁለቱም ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ3 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3,000 ብር ተቀጥቷል።

2ኛ ተከሳሽ በሁለቱም ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ2 ዓመት ጽኑ እስራትና በ1,000 ብር እንዲቀጣ ውሳኔ መሰጠቱን ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ብራዚል የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዝዳንትን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል መክሰሷ ተገለፀ

*

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ብራዚል የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ማንጌ በተጭበረበረ ገንዘብ የ2.5 ሚሊዮን ዶላር አፓርታማ ግዥ እና እ.ኤ.አ በ2018 የቅንጦች እቃዎችን እና 16 ሚሊዮን ዶላር ጥሬ ገንዘብ ይዘው ወደ ሀገሯ ለመግባት ሞክረዋል በሚል መክሰሷ ተገልጿል።

በዚህም የብራዚል ፌደራል ፖሊስ መሪነት በተደረገው ምርመራ ገንዘቦቹ በህገወጥ የተገኙ መሆናቸውን የሀገሪቱ ሚዲያ ዘገባ አመልክቷል።

የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት የበኩር ልጅ የሆኑት ኦቢያንግ በፈረንሳይ እና በአሜሪካ የገንዘብ ማጭበርበር የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ ተደርጎባቸው እንደነበር አስታውሶ ቢቢሲ ኒውስ አፍሪካ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ብሔራዊ የሙስና ወንጀል መረጃ ጥቆማ መስጫ መተግበሪያ አጠቃቀም እና በውስጡ የያዛቸው አገልግሎቶች

*******

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ ሥርዓትን እንዴት መጠቀም እንችላለን? ምን አይነት አገልግሎቶችንስ አካቷል? የሚለውን እንደሚከተለው ተመላክቷል።

✍️ ሥርዓቱ በኮምፒዩተር ብራውዘር አማካኝነት ወይም በስልኮቻችን በመጫን በኢንተርኔት አማካኝነት መጠቀም እንድንችል ተደርጎ የበለፀገ ነው፡፡

✍️ መተግበሪያውን በስልክ ለመጠቀም አፕስቶር እና ፕሌይስቶር ላይ “NCRS” ብለን በመፈለግ ማውረድ እንችላለን፡፡

✍️ መተግበሪያውን ለመጠቀም በስልክ ቁጥራችን መመዝገብና የይለፍ ቃል መጠቀም ይኖርብናል፡፡

✍️ ማንኛውንም አይነት የሙስና ወንጀል ጥቆማ ለመስጠትም ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ በተቀመጡልን አማራጮች መሠረት ለፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን መላክ ያስችለናል፡፡

✍️ የሙስና ወንጀል ጥቆማዎችን በምስል፣ በጽሁፍ፣ በድምጽ፣ በቪዲዮ ወይም በሰነድ አስደግፈን መላክ ከፈለግን መተግበሪያው አማራጮች አሉት፡፡

✍️ ጥቆማ ከላክን በኋላም፥ የላክነው ጥቆማ የደረሰበትን ሂደት ለመከታተል ያስችላል፡፡

✍️ ሥርዓቱ በአምስት የቋንቋ አማራጮች ጥቆማዎችን እንድንሰጥ ያስችለናል፡፡ ቋንቋዎቹም ከአገር ውስጥ አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ እና ሶማሌኛ ሲሆኑ፥ ከውጭ ደግሞ እንግሊዘኛ ቋንቋን አካቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅን ፍላጎት ለማስከበር ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞው አሜሪካዊው ሴናተር ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው ተጠየቀ

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅን ፍላጎት ለማስከበር ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞው አሜሪካዊው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው የአሜሪካ ፌደራል ዓቃቤ ሕጎች ጠይቀዋል።

የአሜሪካ ፌደራል ዓቃቤ ሕጎች፣ ከግብጽ መንግሥት ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብና የወርቅ ሥጦታ በመቀበል የግብጽን ጥቅም ለማስጠበቅ በሞከር ጥፋተኛ በተባሉት የቀድሞው የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ ቦብ ሜኔንዴዝ ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው ጠይቀዋል።

ሜኔንዴዝ ጥፋተኛ ከተባሉባቸው ክሶች መካከል፣ የኢትዮጵያና ግብጽ የሕዳሴ ግድብ ውዝግብን ለመፍታት በሚደረገው ድርድር የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሚና እንዲጫወት በመጠየቅ ያልተገባ ተጽዕኖ ለመፍጠር ሞክረዋል የሚል ይገኝበታል።

ክሱን ተከትሎ ሜኔንዴዝ የምክር ቤቱን መቀመጫቸውን መልቀቃቸውን አስታውሶ ሲኤንኤን ዘግቧል። የፌደራሉ ፍርድ ቤት በሜኔንዴዝ ላይ የእስር ብይኑን ጥር 21 ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የቀድሞው የኒው ጀርሲው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የውጭ መንግሥት ፍላጎትን ለመፈጸም ሥልጣናቸውን መጠቀም፣ ጉቦ መቀበል፣ ማጭበርበር፣ ፍትሕን ማደናቀፍን ጨምሮ በ16 የወንጀል ድርጊቶች ተከሰው በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ መባላቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና ግብዓት በመሰወር የተከሰሰው ግለሰብ ተቀጣ

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ መድሐኒት አቅራቢ ድርጅት ተረክቦ ለኦሮሚያ ክልል ማስረከብ የነበረበትን የህክምና ግብዓት ሳያስረክብ ሰውሮ ለግል ጥቅም በማዋል የተከሰሰው ግለሰብ በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወሰነ።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ መድሐኒት አቅራቢ ድርጅት ሾፌር በነበረው መስፍን መክብብ ላይ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 31 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2 ስር እንዲሁም በሙስና አዋጁ አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር 2/ሀ እና ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፍ በሚል ሁለት ክሶችን አቅርቦበት ነበር።

አንደኛው ክስ ላይ ተከሳሹ የድርጅቱ ሾፌር ሆኖ በሚሰራበት ወቅት ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ድርጅቱ ለጤና ተቋማት የሚያከፋፍላቸውን መድሐኒቶችና የህክምና ግብዓትን ለማድረስ በተሰጠው ሀላፊነት መነሻነት ሚያዝያ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በወጭ ማድረጊያ ደረሰኝ የተረከበውን 9 ሺህ 500 እሽግ የእጅ ጓንቶችን፣ 1 ቤዚን ኪድኒ እና 2 እስፕሪተር የተባለ የህክምና መሳሪያ፤ 2 ሚዘን ቢኤም ትሪፕል የህክምና መሳሪያ አጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው 5 ሚሊየን 515 ሺህ 227ብር ከ30 የሆኑ የህክምና መሳሪያዎችን ለኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ እንዲያደርስ ከተረከበ በኋላ ሳያስረክብ ለራሱ ወስዶ የሰወረ በመሆኑ ከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበት ነበር።

በ2ኛ ክስ ደግሞ ተከሳሹ ከድርጅቱ ወደ ኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ለማድረስ በሚያዝያ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በወጭ ማድረጊያ ደረሰኝ የተረከባቸውን የህክምና መሳሪያዎች ለጤና ቢሮው ባላስረከበበት ሁኔታ በኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ለደም ባንክና የህክምና ግብዓቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም በመረካከቢያ ደረሰኝ እንዳስረከበ በማስመሰል ሀሰተኛ የመረካከቢያ ሰነድ ለኢትዮጵያ መድሐኒት አቅራቢ ድርጅት ያቀረበ በመሆኑ በፈጸመው በሀሰተኛ መንግስታዊ ሰነድ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሷል።

ተከሳሹ የክስ ዝርዝር ከደረሰውና በንባብ ከተሰማ በኋላ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦበታል።

ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን ተመልክቶና መርምሮ በክሱ ላይ የተጠቀሰው የወንጀል ተግባር መፈጸሙን ማረጋገጡን ጠቅሶ ሁለቱ ክሶች ተጣምረው እንዲከላከል ብይን መስጠቱን አፍኤምሲ ዘግቧል።

ተከሳሹ የቀረበበትን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት መርምሮና የተከሳሹን 4 የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕርከን 22 መሰረት በ6 ዓመት ጽኑ እስራትና በ6 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኗል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
1,165 ሃሰተኛ ደረሰኞች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ተደርጓል - ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ

***********************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ባለፉት ስድስት ወራት የህግ ተገዢነትን ለማስፈን በተደረገው ጥረት 1,165 ሃሰተኛ ደረሰኝ ጥቅም ላይ እንዳይውል መደረጉን የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ገለጹ፡፡

ደረሰኞቹ በ153 ድርጅቶች ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበር ሲሆን፣ በዚሁም 1,210,091,184 ብር ሃሰተኛ ግብይት ለታክስ ዓላማ እንዳይውሉ መደረጉም ተመላክቷል፡፡

ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም አክለውም የህግ ተገዢነትን ለማስፈን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

እንዲህ ባለ አላስፈላጊ ህገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉ አካላትም ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሚኒስቴሩ ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) አለአግባብ ትርፍ ለማግኘት በማሰብ ከ10 እስከ 15 ቀናት በጢሻ ውስጥ ተደብቀው በነበሩ 250 የነዳጅ ቦቴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከነዳጅ ምርቶች ስርጭትና ግብይት ጋር ተያይዞ በሚስተዋሉ ሕገወጥ ተግባራት ላይ መንግስት ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑንም አስታውቋል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ከሰሞኑ አለአግባብ ትርፍ ለማግኘት በማሰብ ከ10 እስከ 15 ቀናት በጢሻ ውስጥ ተደብቀው በነበሩ 250 የነዳጅ ቦቴዎች ላይ ቅጣት መጣሉን ገልጸዋል።

በዚህም ቦቴዎቹ ለስድስት ወራት ምንም አይነት የነዳጅ ምርት እንዳያዘዋውሩ ታግደዋል። በዚህ ሕገወጥ ተግባር ተባባሪ የነበሩ 19 ማደያዎችም ለስድስት ወራት ከግብይቱ መታገዳቸው ተገልጿል።

ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባቸውም ጠቅሰዋል። 35 ማደያዎች ተመሳሳይ እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል።

385 ሺህ ሊትር ነዳጅ በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተወርሶ 27 ሚሊዮን ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉንም ጠቅሰዋል።

በቀጣይ ከዲጂታል የግብይት ሥርዓት ውጭ ግብይት የሚፈጽሙ ማደያዎችን ከንግድ ሥርዓቱ የማስወጣት እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል ብለዋል።

ሚኒስትሩ መንግስት እየወሰደ ያለው ጠንካራ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መጠቆማቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በመዲናዋ ሊመዘበር የነበረን 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ማዳን ተቻለ

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 6/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአዲስ አበባ በህገ ወጥ መንገድ ሊመዘበር የነበረ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ሃብት ማዳን መቻሉን የከተማዋ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ም/ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷በመዲናዋ ብልሹ አሰራሮችን ከመቅረፍ አንጻር በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

በተለይም በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ለማስተካከል በትብብር መሠራቱን አንስተዋል።

ባለፉት አምስት ወራትም በ3 ሺህ 933 ጉዳዮች ክሶች ቀርበው የፍርድ ቤት ክርክሮች እንደተደረጉ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም 1ሺህ 314 መዝገቦችን በመከራከር በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያገኙ መደረጉን ነው ያስረዱት።

ቢሮው በ1 ሺህ 266 መዝገቦች ማሸነፋን ጠቁመው ÷ በዚህም መንግስት ሊያጣው የነበረ 1ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በመዲናዋ የሚስተዋሉ ሕገ ወጥ ተግባራትን ከስር መሠረታቸው ለማድረቅም ነዋሪዎች ጥቆማ በመስጠት የበኩላቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውን ኤፍኤምሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319