በክልሉ የትውልድ ሥነምግባር ግንባታን ለማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ መካሄዱ ተገለፀ
*****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአብክመ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የትውልድ ሥነምግባር ግንባታን ለማጠናከር ከትምህርት ቢሮ አመራሮች፣ ከ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሀብታሙ ሞገስ ኮሚሽናችን በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል። ባለፋት ጊዜያትም ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።
በዚህ ዓመትም የትውልዱን ሥነምግባር ለመገንባት በትኩረት ተይዞ በተለያዩ ጊዜያት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር እንደተደረገ አመላክተዋል።
ኮሚሽነሩ አክለውም ይህ መድረክ ወጣቶችንና ህፃናትን በሥነምግባር ለመገንባት የት/ቤቶች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በቅንጅት ለመስራት የምንመካከርበት ነው ብለዋል።
በቀጣይም በት/ቤቶች ላይ ሀገር ሊረከብ የሚችል ዜጋ ለማፍራት በወጣቶችና ህፃናት ላይ የሥነምግባር ግንባታ ስራን በቅንጅት፣ በመተባበርና በመደጋገፍ የላቀ ርብርብ ልናደርግ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በተለይ በት/ቤቶች ውስጥ የሚታዩ የሥነምግባር ጥሰቶችን መቅረፍና ማስተካከል የሚቻለው የሥነምግባር ክበባትን ለውጥ ሊያመጡ በሚችል መልኩ በማደራጀትና ተከታታይ የሥነምግባር ግንባታ ስራ በመስራት ነው ብለዋል።
በመሆኑም በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የክልሉ ት/ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ በበኩላቸው የትምህርት አመራሮች በብዙ የስራ ልምድ የዳበሩና በእውቀትም የተካኑ በመሆኑ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆነውን ትውልድ ሥነምግባሩን ለመቅረፅ ለነገ የማይባልና ወደየትም ሳንገፋ በግንባር ቀደምትነት ልንሰራው ይገባል ብለዋል።
በሁሉም ት/ቤቶች ችግር ያለባቸውን መምህራንና ተማሪዎች በመለየት የተለየ የሥነምግባር ሥልጠና እና የሥነ ልቦና የምክር አገልግሎት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በት/ቤታችን ዉስጥ ክበባትን በማደራጀትና ጥሩ አመራር በመስጠት በሰውነቱ ሰው አክባሪ፣ በት/ቤት ህግና ደንብ ተገዥ የሆነ፣ ከስርቆትና ኩረጃ እራሱን ነፃ አድርጎ ሀገር ሊረከብና ሞዴል ሊሆን የሚችል ተማሪ ልንፈጥር ይገባል ብለዋል።
የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ማሩ ቸኮል በበኩላቸው የትውልዱን ሥነምግባር ት/ቤቶች ላይ ማነፅ እንደሚያስፈልግ ገልፀው፥ እርስ በእራሳችን ከመገፋፋት ወጥተን ክበባትን በማቋቋምና ውጤት እንዲያመጡ በማድረግ በኩል የትምህርት ተቋማት በግንባር ቀደምትነት በመስራት የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ መፍጠር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ባለሙያ ወ/ሮ በላይነሽ አሰፋ "ሥነምግባርን የማስተማርና የማስረፅ ስልቶች" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መነሻ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት መደረጉን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ኮሚሽኑ መድረኩን ማዘጋጀቱን አመስግነው፥ ሥነምግባር የሁሉም ነገር መጀመሪያ ተግባር በመሆኑ ሁሉም በቅንጅትና በአንድነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ
*****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ የሙስና ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ መቀጣታቸው ተገልጿል።
1ኛ ተከሳሽ አበበ ጌቴው በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ የአስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ሠራተኛ ሁኖ በፊት የመዘጋጃ ቤቱ ኃላፊዎች የነበሩ ግለሰቦችን ስምና ፊርማ በመጠቀም በከተማው 01 ቀበሌ ላይ ለሁለተኛ ተከሳሽ አበራ ክብረት የ150 ካ.ሜ ቦታ ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ በመስጠቱና ድርጊቱን ለመፈፀም ከሁለተኛ ተከሳሽ 38,000.00 ብር ጉቦ መቀበልና በፈፀመው ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀት ወንጀል ተከስሷል።
2ኛ ተከሳሽ አበራ ክብረት በጋዝጊብላ ወረዳ አስ ከተማ 01 ቀበሌ በአንደኛ ተከሳሽ ተዘጋጅቶ የተሰጠውን ሀሰተኛ ካርታና ፕላን ሲገለገል በመገኘቱ በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል የተከሰሰ እና ይህንን ተግባር እንዲፈፀም ለአንደኛ ተከሳሽ 38,000 ብር ጉቦ መስጠት ወንጀል ተከሷል።
የጋዝጊብላ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ድርጊቱን በማጣራት መዝገቡን ለዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፍትህ መምሪያ እንደላከ ተገልጿል።
የፍትህ መምሪያው የወንጀል የሥራ ሂደትም መዝገቡን ከመረመረ በኋላ በ1ኛ ተከሳሽ ላይ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 (1) እና አንቀጽ 10 (1) በመተላለፍ፣ 2ኛ ተከሳሽ የአዋጁን አንቀጽ 23 (1) እና አንቀጽ 25 (1) የተመለከተውን መተላለፋቸው ተመላክቷል።
በመሆኑም በእያንዳንዳቸው ክሶችን በማዘጋጀት ለብሄረሰብ አስተዳደር ዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ክርክር ሲደረግ ከቆዬ በኋላ ፍ/ቤቱ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ በሁለቱም ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ3 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3,000 ብር ተቀጥቷል።
2ኛ ተከሳሽ በሁለቱም ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ2 ዓመት ጽኑ እስራትና በ1,000 ብር እንዲቀጣ ውሳኔ መሰጠቱን ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ብራዚል የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዝዳንትን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል መክሰሷ ተገለፀ
*
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ብራዚል የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ማንጌ በተጭበረበረ ገንዘብ የ2.5 ሚሊዮን ዶላር አፓርታማ ግዥ እና እ.ኤ.አ በ2018 የቅንጦች እቃዎችን እና 16 ሚሊዮን ዶላር ጥሬ ገንዘብ ይዘው ወደ ሀገሯ ለመግባት ሞክረዋል በሚል መክሰሷ ተገልጿል።
በዚህም የብራዚል ፌደራል ፖሊስ መሪነት በተደረገው ምርመራ ገንዘቦቹ በህገወጥ የተገኙ መሆናቸውን የሀገሪቱ ሚዲያ ዘገባ አመልክቷል።
የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት የበኩር ልጅ የሆኑት ኦቢያንግ በፈረንሳይ እና በአሜሪካ የገንዘብ ማጭበርበር የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ ተደርጎባቸው እንደነበር አስታውሶ ቢቢሲ ኒውስ አፍሪካ ዘግቧል።

ብሔራዊ የሙስና ወንጀል መረጃ ጥቆማ መስጫ መተግበሪያ አጠቃቀም እና በውስጡ የያዛቸው አገልግሎቶች
*******
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ ሥርዓትን እንዴት መጠቀም እንችላለን? ምን አይነት አገልግሎቶችንስ አካቷል? የሚለውን እንደሚከተለው ተመላክቷል።
✍️ ሥርዓቱ በኮምፒዩተር ብራውዘር አማካኝነት ወይም በስልኮቻችን በመጫን በኢንተርኔት አማካኝነት መጠቀም እንድንችል ተደርጎ የበለፀገ ነው፡፡
✍️ መተግበሪያውን በስልክ ለመጠቀም አፕስቶር እና ፕሌይስቶር ላይ “NCRS” ብለን በመፈለግ ማውረድ እንችላለን፡፡
✍️ መተግበሪያውን ለመጠቀም በስልክ ቁጥራችን መመዝገብና የይለፍ ቃል መጠቀም ይኖርብናል፡፡
✍️ ማንኛውንም አይነት የሙስና ወንጀል ጥቆማ ለመስጠትም ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ በተቀመጡልን አማራጮች መሠረት ለፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን መላክ ያስችለናል፡፡
✍️ የሙስና ወንጀል ጥቆማዎችን በምስል፣ በጽሁፍ፣ በድምጽ፣ በቪዲዮ ወይም በሰነድ አስደግፈን መላክ ከፈለግን መተግበሪያው አማራጮች አሉት፡፡
✍️ ጥቆማ ከላክን በኋላም፥ የላክነው ጥቆማ የደረሰበትን ሂደት ለመከታተል ያስችላል፡፡
✍️ ሥርዓቱ በአምስት የቋንቋ አማራጮች ጥቆማዎችን እንድንሰጥ ያስችለናል፡፡ ቋንቋዎቹም ከአገር ውስጥ አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ እና ሶማሌኛ ሲሆኑ፥ ከውጭ ደግሞ እንግሊዘኛ ቋንቋን አካቷል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...

በህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅን ፍላጎት ለማስከበር ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞው አሜሪካዊው ሴናተር ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው ተጠየቀ
*******
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅን ፍላጎት ለማስከበር ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞው አሜሪካዊው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው የአሜሪካ ፌደራል ዓቃቤ ሕጎች ጠይቀዋል።
የአሜሪካ ፌደራል ዓቃቤ ሕጎች፣ ከግብጽ መንግሥት ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብና የወርቅ ሥጦታ በመቀበል የግብጽን ጥቅም ለማስጠበቅ በሞከር ጥፋተኛ በተባሉት የቀድሞው የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ ቦብ ሜኔንዴዝ ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው ጠይቀዋል።
ሜኔንዴዝ ጥፋተኛ ከተባሉባቸው ክሶች መካከል፣ የኢትዮጵያና ግብጽ የሕዳሴ ግድብ ውዝግብን ለመፍታት በሚደረገው ድርድር የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሚና እንዲጫወት በመጠየቅ ያልተገባ ተጽዕኖ ለመፍጠር ሞክረዋል የሚል ይገኝበታል።
ክሱን ተከትሎ ሜኔንዴዝ የምክር ቤቱን መቀመጫቸውን መልቀቃቸውን አስታውሶ ሲኤንኤን ዘግቧል። የፌደራሉ ፍርድ ቤት በሜኔንዴዝ ላይ የእስር ብይኑን ጥር 21 ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
የቀድሞው የኒው ጀርሲው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የውጭ መንግሥት ፍላጎትን ለመፈጸም ሥልጣናቸውን መጠቀም፣ ጉቦ መቀበል፣ ማጭበርበር፣ ፍትሕን ማደናቀፍን ጨምሮ በ16 የወንጀል ድርጊቶች ተከሰው በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ መባላቸውን መዘገባችን ይታወሳል።