Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
በትራንስፖርት ዘርፉ የሚታየውን ብልሹ አሰራር ለማስቀረት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 2/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በትራንስፖርት ዘርፍ የሚታየውን ብልሹ አሰራርና የህዝብ እንግልትን ለማስቀረት ዘርፉን የማዘመንና ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለክልል የትራንስፖርት ዘርፍ ተቋማት ተሞክሮ ለማጋራት የሚያስችል መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን እንደገለጹት በትራንስፖርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራርና የህዝብ እንግልትን ለማስቀረት እየተሰራ ነው፡፡

በተለይ የዲጂታላይዜሽን ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ እንደሚገኝ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

እስካሁን በተከናወኑ የአገልግሎት ማዘመን ሥራዎችም ተገልጋዮች በዲጂታል ስርዓት አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በሥነምግባር የታነጸ ትውልድ ለማፍራት የትምህርቱ ማህበረሰብ ከፍተኛ ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 2/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሀረሪ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ትውልድን በሥነምግባር ማነጽ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለትምህርቱ ማህበረሰብ ሰጥቷል።

በሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የዜግነትና ግብረገብ ትምህርት ባለሙያ አቶ ታሪኩ ተካ እንዳሉት፥ ትውልዱን በሥነምግባር ለማነጽ ከተማሪ ወላጅ ጀምሮ የአጠቃላይ የትምህርቱ ማህበረሰብን ርብርብ እንደሚጠይቅ ገልፀዋል።

የትምህርት ሴክተሩ በሚጠበቀው ልክ ውጤታማ እንዲሆን በሥነምግባር የታነጸ፣ ራዕይ ያለው ትውልድ መገንባት ወሳኝ በመሆኑ መምህራን በተግባርም ጭምር ለተማሪው አርአያ በመሆን ሊያሳዩ እንደሚገባ አቶ ታሪኩ ጠቁመዋል።

የአዕምሮ አቅም ለመገንባት፣ ጥበብን ለመቅሰም፣ ለፈጠራ ግኝት፣ ተፈጥሮን ለመጠቀም፣ በአጠቃላይ ችግር ፈቺ ትውልድ ለመፍጠር በሥነምግባር የታነጸ፣ ባለራዕይ ትውልድ መፍጠር ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

በዚህም የግብረገብና የዜግነት ትምህርት አይነቶች የሚያስተምሩ መምህራን ትልቁን ድርሻ ወስደው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተማሪ ውጤትን ከማሻሻል ባሻገር በሥነምግባር ግንባታው ላይ ለውጥ ያመጣል ተብሎ እንደሚታመን ጠቁመው፥ በዚህም ተማሪው በተግባር ጭምር የሚማሩበት ስርዓትን የዘረጋ ነው ብለዋል።

ይህ ስልጠና በመልካም ሥነምግባር አርአያ ከመሆን አንጻር ራሳቸውንም የፈተሹበትና የበለጠ ተማሪዎቻቸውን ለማነጽ ተነሳሽነትን የፈጠረባቸው መሆኑን ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።

ትውልድን ለመገንባት የትምህርት ማህበረሰቡ ብቻ ሳይሆን የወላጅና የአካባቢው ማህበረሰብ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ወላጆች ልጆቻቸውን በቅርበት የመከታተል ኃላፊነቱን ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ነገ ለምንጠብቃት ኢትዮጵያ ችግር ፈቺ የሆነ ትውልድ ለማበርከት የተጣለብንን የሀገር አደራ ለመወጣት በቁርጠኝነት እንሰራለን ማለታቸውን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ሁሉም ትምህርት ቤቶች ያደራጁትን የሥነምግባር ክበባት በሚገባ በማንቀሳቀስ በተማሪው ሥነምግባር ላይ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እና ኮሚሽኑም የሚጠበቅበትን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በኮሚሽኑ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አልፊያ አህመድ ገልጸዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የተገኘው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 2/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በባህርዳር ከተማ በህብረተሰቡ ጥቆማ መነሻነት በተደረገ ክትትል የመንግስትና የግል ተቋማትን የሚገልፁ ልዩ ልዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የተገኘው ተጠርጣሪ በፖሊስ መያዙ ተገልጿል።

ፖሊስ ባደረገው ፍተሻ ሀሰተኛ የትምርት ማስረጃወች፣ የቀበሌ መታወቂያዎች፣ ልዩ ልዩ ማህተሞች አብረው የተገኙ ሲሆን፥ ምርመራው እየተጣራ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

በሀሰተኛ ሰነድ ወንጀለኞች ህጋዊ መስለው እየተንቀሳቀሱ በህብረተሰቡና በመንግስት ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት በተለይም ባልተማረበት የትምህርት መስክ ማስረጃ አለኝ ብሎ በግልም ሆነ በመንግስት ተቋም የሚያደርሰውን ችግር በጋራ መከላከል እንደሚገባ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን በማህበራዊ ትስስር ገጹ መልዕክት አስተላልፏል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ባለስልጣኑ ለቴሌ የመለሱትን ስልክ ቁጥር ተጠቅሞ ከግለሰቦች መሬት ለማሰጠት በሚል ገንዘብ የተቀበለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 2/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑ ግለሰብ ለቴሌ የመለሱትን የቀድሞ ስልክ ቁጥር በመጠቀም ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ በማዘጋጀት ባለስልጣን ነኝ በማለት ለሰባት ግለሰቦች በቴሌግራምና በኢሞ መልዕክት በመላክ የኢንቨስትመንት መሬት እና ቦታ ይመቻችላችኋል በማለት ለጉዳይ ማስፈጸሚያ ገንዘብ በባንክ እንዲላክለት ያደረገውና በሙስና ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በ15 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ወስኗል።

የክልሉ ፍትህ ቢሮ የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ መልካ አያና ላይ በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም ተደራራቢ ሰባት ዝርዝር ክሶችን አቅርቦበት ነበር።

በዚህም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር (3) ስር የተመላከተውን ድንጋጌ መተላለፍ የሚል እና በሙስና አዋጁ አንቀጽ 28 ንዑስ ቁጥር 3 ስር እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 33 እና አንቀጽ 29 ንዑስ ቁጥር 1 ለ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ማለትም በህገወጥ መንገድ የተገኘ ንብረትን ወይም ገንዘብን ምንጩን ለመደበቅ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሚል ክስ አቅርቦበታል።

በክሱ ላይ እንደተመላከተው ተከሳሹ በመስከረም 6 ቀን 2015 ዓ.ም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ያለ አግባብ መበልጸግ ወይም በሌላ ሰው ጥቅም ወይም መብት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ በሸገር ከተማ አስተዳደር ቡራዩ ክ/ከተማ ከመልካ ጋፋርሳ ወረዳ ሀሰተኛ መታወቂያ በማውጣትና በመጠቀም በመስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቱሉ ጃሞ ቅርንጫፍ እና ከአዋሽ ባንክ አብዲ ኖኖ ቅርንጫፍ በሀሰተኛ ስም ባወጣው የነዋሪነት መታወቂያ የባንክ ሂሳብ መክፈቱ በክሱ ላይ ተመላክቷል።

በ2015 ዓ.ም የመንግስት ሰራተኛ ሳይሆን የመንግስት ሰራተኛ እንደሆነ በማስመሰል ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ያልተገባ ሀብት ለማግኘት በማሰብ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑ ግለሰብ ከዚህ ቀደም ይጠቀሙበት የነበረና ለቴሌ መልሰውት በአጋጣሚ እጁ የገባውን ስልክ ተጠቅሞ በኢሞና በቴሌግራም ወደ ተለያዩ ሰባት ባለሀብቶች ተከሳሹ እራሱን ባለስልጣን በማስመሰል ለመኖሪያና ለኢንቨስትመንት ቦታ መሬት እየተመቻቸላቸው እንደሆነ ገልጾ መልዕክት ይልካል።

ግለሰቦቹ ስልክ ሲደውሉለት ስልኩን አንስቶ "የባለስልጣኑ የጽ/ቤት ሰራተኛ ነኝ" በማለት መሬቱና ቦታው እየተመቻቸላችው እንደሆነ በመግለጽ መልስ ይሰጣል።

በዚህ መልኩ አሳሳች ቃላቶችን በመጠቀምና በማግባባት በሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ በከፈታቸው የባንክ ሂሳቦች የመሬት ካርታ እና የቤት ግምት ገንዘብ ላኩ በማለት በተለያዩ ጊዜ በተለያዩ መጠኖች በአጠቃላይ 448 ሺህ 200 ብር እንዲላክለት አስደርጓል።

ተከሳሹ በተጨማሪም በሙስና ወንጀል የተቀበለውን ገንዘብ ወይም ንብረት ምንጭ ለመደበቅ በማሰብ የራሱን ፎቶ ግራፍ ተጠቅሞ በእለቱ የሀሰት የነዋሪነት መታወቂያ በማውጣት በሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም እና በመስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም ገላና ባዳዳ በሚል ስሙ ተሽከርካሪ ገዝቶ በኦዳ የተሽከርካሪ ማሰልጠኛ በሚል ተሽከርካሪውን ሲሰራበት የተያዘ መሆኑ በክስ ዝርዝሩ ተጠቅሷል።

ተከሳሹ በዚህ መልኩ የቀረበበት ክስ ዝርዝር ከደረሰው በኋላ የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃል በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦበታል።

ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሹ በተከሰሰባቸው ድንጋጌዎች ስር እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መከላከል አለመቻሉን ጠቅሶ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት በመመርመርና በመያዝ ተከሳሹን በ15 ዓመት ጽኑ እስራትና 5 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በሙስና ወንጀል የገዛው ተሽከርካሪ ተሽጦ ለግል ተበዳዮች ብሩ እንዲመለስ እንዲሁም የሚተርፈው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ትዕዛዝ መስጠቱን ኤፍኤምሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በኮሚሽኑ በወር ሁለት ጊዜ በየአስራ አምስት ቀን የሚዘጋጀው ዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣ

*

የዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ሊኩን ያስፈጥሩ...https://drive.google.com/file/d/1oWN09c3v9wSdwkeC3jk-AfG53xn-TGZi/view?usp=drivesdk

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
አሜሪካ በቀድሞ የናይጄሪያ ሚኒስትር ተመዝብሯል ያለችውን 50 ሚሊዮን ዶላር ለአገሪቱ መለሰች

*****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) አሜሪካ በቀድሞ የናይጄሪያ የነዳጅ ሚኒስትር ዲኤዛኒ አሊሰን ማዱኬ እና በሌሎች አጋሮቻቸው ተመዝብሮ ወደ አገሬ ገብቷል ያለችውን 50 ሚሊዮን ዶላር መመለሷ ተገለጸ።

ሚኒስትሮቹ በሕገወጥ መንገድ ከናይጄሪያ አስወጥተውታል የተባለው ወደ 53 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለሕዝባዊ አገልግሎቶች እንደሚውል የናይጄሪያ የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስትሯ የናይጄሪያን የነዳጅ ኩባንያ በሚመሩበት ወቅት የተለያዩ ውሎችን ለመስጠት ጉቦ እንደተቀበሉና ይህንንም ራሳቸውን እና ሌሎችን ለማበልጸግ እንደተጠቀሙበት ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል።

አሜሪካ ገንዘቡ ጋላክቲካ ስታር የተሰኘ 65 ሜትር ርዝማኔ ያለው መርከብ እንዲሁም በካሊፎርኒያ እና በኒው ዮርክ ቅንጡ ቤቶችን ለመግዛት ውሏል ብላለች።

የ64 ዓመቷ የቀድሞ ሚኒስትር አሊሰን ማዱኬ እነዚህን የምንዝበራ ውንጀላዎችን ውድቅ አድርገዋል።

ሚኒስትሯ በሕገወጥ መንገድ አካብተውታል የተባለው ሃብት መኖሪያቸውን ባደረጉባት ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ እየተጣራ ይገኛል።

ከሁለት ዓመት በፊት በዩናይትድ ኪንግደም ሉዊ ቩተን ከተሰኘው ምርት የቅንጦት እቃዎች ስጦታ፣ የግል ትምህርት ቤት ክፍያዎች እንዲሁም 127 ሺህ ዶላር ጥሬ ገንዘብ ጋር በተያያዘ በጉቦ ወንጀል ተከሰዋል።

በቀድሞው ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን አስተዳደር ውስጥ ቁልፍ ሰው የነበሩት ፖለቲከኛዋ የነዳጅ ላኪዎች ቡድን፣ ኦፔክ የመጀመሪያ ሴት ፕሬዚዳንትም ሆነው አገልግለዋል።

በናይጄሪያ የነዳጅ ሚኒስትርነትም ከአውሮፓውያኑ 2010 እስከ 2015 አገልግለዋል። ቀደም ሲል የትራንስፖርት ሚኒስትር፣ የማዕድን እና ብረታ ብረት ልማት ሚኒስትር ነበሩ።

የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት በቀድሞ ሚኒስትሯ እና በአጋሮቻቸው በሕገወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ ገብቶ በንብረት ላይ ውሏል ያለውን ገንዘብ በተመለከተ ሁለት የፍትሐብሔር ክሶች የመጨረሻ ውሳኔ ከሁለት ዓመታት በፊት አስታውቆ ነበር።

አርብ ጥር 2/2017 ዓ.ም አሜሪካ እና ናይጄሪያ 52.88 ሚሊዮን ዶላር ወደ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር እንደሚመለስ አረጋግጠዋል።

ይህ ከቀድሞዋ ሚኒስትር ጋር በተገናኘ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ናይጄሪያ የሚመለስ ገንዘብ ይሆናል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

በናይጄሪያ መዲና በተካሄደው የፊርማ ሥነሥርዓት ላይ የሀገሪቱ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና የፍትህ ሚኒስትር ላጢፍ ፋግቤሚ የገንዘቡ መመለስ ሙስናን ለመዋጋት በሚደረገው ትግል ውስጥ ትልቅ እርምጃ ነው ብለዋል።

ከገንዘቡ 50 ሚሊዮን ዶላር በዓለም ባንክ በኩር የገጠር የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶችን ለማስፋፋት የሚውል እንደሆነ ፋግቤሚ ተናግረዋል።

ቀሪው 2.88 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ የፍትህ ሥርዓቱን ለማጠናከር እንዲሁም የፀረ-ሙስና ጥረቶችን ለማበረታታት ለዓለም አቀፉ የፍትህ ተቋም እንደሚላክ ተገልጿል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319