Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
ኮሚሽኑ በግማሽ ዓመቱ ስኬታማ ተግባራት ማከናወን መቻሉን አስታወቀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 1/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በጠቅላላ ካውንስል ገምግሟል።

በግምገማው ወቅት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጀማል ረዲ እንደተናገሩት ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ በዕቅድ ከተያዙ ተግባራት መካከል በትውልድ ሥነምግባር ግንባታና ሙስናን በመከላከል የተሰራው ሥራ ስኬታማ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በተለይ 21ኛውን አለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በከተማ ደረጃ በድምቀት መከበሩ በየደረጃው ለሚገኘው የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ ከመፍጠሩ ባሻገር የትግሉ ባለቤት እንዲሆኑ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ኮሚሽነሩ አስረድተዋል፡፡

የኮሚሽኑን የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የዕቅድና በጀት ቡድን መሪ ተወካይ አቶ ግዛቸው ማሩ ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎችን በማጠናከር፣ በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ፣ በሙስና መከላከል ሥራዎች ላይ ውጤታማ ተግባራት ያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይ የከተማዋ ነዋሪዎች የሙስና ትግሉ ባለቤት እንዲሆኑ በስልጠና፣ በተለያዩ ሚዲያዎችና በሶሻል ሚዲያ ተከታታይ የግንዛቤ የመፍጠር ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን መጠቆማቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሃብት ምዝገባ፣ በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ሥራዎች ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንፃር የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡን አብራርተዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ለሪስፒንስ ዓለምአቀፍ ት/ቤት ተማሪዎች የሥነምግባር ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 1/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአብክመ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተማሪዎች በሥነምግባር ታንፀው ነገ እራሳቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውንና ሀገራቸውን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል እንዲችሉ በክልሉ ውስጥ በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች የሥነምግባር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

በዛሬው እለትም በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ለሪስፒንስ ዓለምአቀፍ ት/ቤት ከ7ኛ-12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሥነምግባር ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።

የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ባለሙያ ወ/ሪት መስከረም አዲስ በት/ቤቱ በመገኘት በአመለካከት፣ በስብዕና ምንነት፣ በሥነምግባር ዙሪያ፣ ህግና ደንብን ከማክበር፣ መብትና ግዴታን ከማወቅ፣ ሰውን ከማክበር፣ ጊዜን በአግባቡና ቴክኖሎጂን ከመጠቀም፣ ትህትናን ከመላበስ እና አለባበስን ከማስተካከል ጀምሮ ምን እንደሚጠበቅባቸውጨእንዲሁም ት/ቤቶች የእውነት፣ የእውቀት እና የጥበብ መቅሰሚያ መሆናቸውን በማብራራት ግንዛቤ መፍጠር ችለዋል።

በስልጠና መድረኩም የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር፣ መምህራን፣ የሥነ ዜጋና ሥነምግባር መምህርና የሥነምግባር ክበብ አስተባባሪ መገኘታቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በትራንስፖርት ዘርፉ የሚታየውን ብልሹ አሰራር ለማስቀረት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 2/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በትራንስፖርት ዘርፍ የሚታየውን ብልሹ አሰራርና የህዝብ እንግልትን ለማስቀረት ዘርፉን የማዘመንና ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለክልል የትራንስፖርት ዘርፍ ተቋማት ተሞክሮ ለማጋራት የሚያስችል መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን እንደገለጹት በትራንስፖርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራርና የህዝብ እንግልትን ለማስቀረት እየተሰራ ነው፡፡

በተለይ የዲጂታላይዜሽን ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ እንደሚገኝ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

እስካሁን በተከናወኑ የአገልግሎት ማዘመን ሥራዎችም ተገልጋዮች በዲጂታል ስርዓት አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በሥነምግባር የታነጸ ትውልድ ለማፍራት የትምህርቱ ማህበረሰብ ከፍተኛ ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 2/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሀረሪ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ትውልድን በሥነምግባር ማነጽ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለትምህርቱ ማህበረሰብ ሰጥቷል።

በሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የዜግነትና ግብረገብ ትምህርት ባለሙያ አቶ ታሪኩ ተካ እንዳሉት፥ ትውልዱን በሥነምግባር ለማነጽ ከተማሪ ወላጅ ጀምሮ የአጠቃላይ የትምህርቱ ማህበረሰብን ርብርብ እንደሚጠይቅ ገልፀዋል።

የትምህርት ሴክተሩ በሚጠበቀው ልክ ውጤታማ እንዲሆን በሥነምግባር የታነጸ፣ ራዕይ ያለው ትውልድ መገንባት ወሳኝ በመሆኑ መምህራን በተግባርም ጭምር ለተማሪው አርአያ በመሆን ሊያሳዩ እንደሚገባ አቶ ታሪኩ ጠቁመዋል።

የአዕምሮ አቅም ለመገንባት፣ ጥበብን ለመቅሰም፣ ለፈጠራ ግኝት፣ ተፈጥሮን ለመጠቀም፣ በአጠቃላይ ችግር ፈቺ ትውልድ ለመፍጠር በሥነምግባር የታነጸ፣ ባለራዕይ ትውልድ መፍጠር ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

በዚህም የግብረገብና የዜግነት ትምህርት አይነቶች የሚያስተምሩ መምህራን ትልቁን ድርሻ ወስደው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተማሪ ውጤትን ከማሻሻል ባሻገር በሥነምግባር ግንባታው ላይ ለውጥ ያመጣል ተብሎ እንደሚታመን ጠቁመው፥ በዚህም ተማሪው በተግባር ጭምር የሚማሩበት ስርዓትን የዘረጋ ነው ብለዋል።

ይህ ስልጠና በመልካም ሥነምግባር አርአያ ከመሆን አንጻር ራሳቸውንም የፈተሹበትና የበለጠ ተማሪዎቻቸውን ለማነጽ ተነሳሽነትን የፈጠረባቸው መሆኑን ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።

ትውልድን ለመገንባት የትምህርት ማህበረሰቡ ብቻ ሳይሆን የወላጅና የአካባቢው ማህበረሰብ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ወላጆች ልጆቻቸውን በቅርበት የመከታተል ኃላፊነቱን ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ነገ ለምንጠብቃት ኢትዮጵያ ችግር ፈቺ የሆነ ትውልድ ለማበርከት የተጣለብንን የሀገር አደራ ለመወጣት በቁርጠኝነት እንሰራለን ማለታቸውን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ሁሉም ትምህርት ቤቶች ያደራጁትን የሥነምግባር ክበባት በሚገባ በማንቀሳቀስ በተማሪው ሥነምግባር ላይ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እና ኮሚሽኑም የሚጠበቅበትን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በኮሚሽኑ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አልፊያ አህመድ ገልጸዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የተገኘው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 2/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በባህርዳር ከተማ በህብረተሰቡ ጥቆማ መነሻነት በተደረገ ክትትል የመንግስትና የግል ተቋማትን የሚገልፁ ልዩ ልዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የተገኘው ተጠርጣሪ በፖሊስ መያዙ ተገልጿል።

ፖሊስ ባደረገው ፍተሻ ሀሰተኛ የትምርት ማስረጃወች፣ የቀበሌ መታወቂያዎች፣ ልዩ ልዩ ማህተሞች አብረው የተገኙ ሲሆን፥ ምርመራው እየተጣራ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

በሀሰተኛ ሰነድ ወንጀለኞች ህጋዊ መስለው እየተንቀሳቀሱ በህብረተሰቡና በመንግስት ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት በተለይም ባልተማረበት የትምህርት መስክ ማስረጃ አለኝ ብሎ በግልም ሆነ በመንግስት ተቋም የሚያደርሰውን ችግር በጋራ መከላከል እንደሚገባ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን በማህበራዊ ትስስር ገጹ መልዕክት አስተላልፏል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ባለስልጣኑ ለቴሌ የመለሱትን ስልክ ቁጥር ተጠቅሞ ከግለሰቦች መሬት ለማሰጠት በሚል ገንዘብ የተቀበለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 2/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑ ግለሰብ ለቴሌ የመለሱትን የቀድሞ ስልክ ቁጥር በመጠቀም ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ በማዘጋጀት ባለስልጣን ነኝ በማለት ለሰባት ግለሰቦች በቴሌግራምና በኢሞ መልዕክት በመላክ የኢንቨስትመንት መሬት እና ቦታ ይመቻችላችኋል በማለት ለጉዳይ ማስፈጸሚያ ገንዘብ በባንክ እንዲላክለት ያደረገውና በሙስና ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በ15 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ወስኗል።

የክልሉ ፍትህ ቢሮ የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ መልካ አያና ላይ በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም ተደራራቢ ሰባት ዝርዝር ክሶችን አቅርቦበት ነበር።

በዚህም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር (3) ስር የተመላከተውን ድንጋጌ መተላለፍ የሚል እና በሙስና አዋጁ አንቀጽ 28 ንዑስ ቁጥር 3 ስር እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 33 እና አንቀጽ 29 ንዑስ ቁጥር 1 ለ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ማለትም በህገወጥ መንገድ የተገኘ ንብረትን ወይም ገንዘብን ምንጩን ለመደበቅ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሚል ክስ አቅርቦበታል።

በክሱ ላይ እንደተመላከተው ተከሳሹ በመስከረም 6 ቀን 2015 ዓ.ም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ያለ አግባብ መበልጸግ ወይም በሌላ ሰው ጥቅም ወይም መብት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ በሸገር ከተማ አስተዳደር ቡራዩ ክ/ከተማ ከመልካ ጋፋርሳ ወረዳ ሀሰተኛ መታወቂያ በማውጣትና በመጠቀም በመስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቱሉ ጃሞ ቅርንጫፍ እና ከአዋሽ ባንክ አብዲ ኖኖ ቅርንጫፍ በሀሰተኛ ስም ባወጣው የነዋሪነት መታወቂያ የባንክ ሂሳብ መክፈቱ በክሱ ላይ ተመላክቷል።

በ2015 ዓ.ም የመንግስት ሰራተኛ ሳይሆን የመንግስት ሰራተኛ እንደሆነ በማስመሰል ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ያልተገባ ሀብት ለማግኘት በማሰብ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑ ግለሰብ ከዚህ ቀደም ይጠቀሙበት የነበረና ለቴሌ መልሰውት በአጋጣሚ እጁ የገባውን ስልክ ተጠቅሞ በኢሞና በቴሌግራም ወደ ተለያዩ ሰባት ባለሀብቶች ተከሳሹ እራሱን ባለስልጣን በማስመሰል ለመኖሪያና ለኢንቨስትመንት ቦታ መሬት እየተመቻቸላቸው እንደሆነ ገልጾ መልዕክት ይልካል።

ግለሰቦቹ ስልክ ሲደውሉለት ስልኩን አንስቶ "የባለስልጣኑ የጽ/ቤት ሰራተኛ ነኝ" በማለት መሬቱና ቦታው እየተመቻቸላችው እንደሆነ በመግለጽ መልስ ይሰጣል።

በዚህ መልኩ አሳሳች ቃላቶችን በመጠቀምና በማግባባት በሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ በከፈታቸው የባንክ ሂሳቦች የመሬት ካርታ እና የቤት ግምት ገንዘብ ላኩ በማለት በተለያዩ ጊዜ በተለያዩ መጠኖች በአጠቃላይ 448 ሺህ 200 ብር እንዲላክለት አስደርጓል።

ተከሳሹ በተጨማሪም በሙስና ወንጀል የተቀበለውን ገንዘብ ወይም ንብረት ምንጭ ለመደበቅ በማሰብ የራሱን ፎቶ ግራፍ ተጠቅሞ በእለቱ የሀሰት የነዋሪነት መታወቂያ በማውጣት በሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም እና በመስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም ገላና ባዳዳ በሚል ስሙ ተሽከርካሪ ገዝቶ በኦዳ የተሽከርካሪ ማሰልጠኛ በሚል ተሽከርካሪውን ሲሰራበት የተያዘ መሆኑ በክስ ዝርዝሩ ተጠቅሷል።

ተከሳሹ በዚህ መልኩ የቀረበበት ክስ ዝርዝር ከደረሰው በኋላ የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃል በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦበታል።

ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሹ በተከሰሰባቸው ድንጋጌዎች ስር እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መከላከል አለመቻሉን ጠቅሶ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት በመመርመርና በመያዝ ተከሳሹን በ15 ዓመት ጽኑ እስራትና 5 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በሙስና ወንጀል የገዛው ተሽከርካሪ ተሽጦ ለግል ተበዳዮች ብሩ እንዲመለስ እንዲሁም የሚተርፈው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ትዕዛዝ መስጠቱን ኤፍኤምሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319