Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
የፍትህና የፀጥታ አካላት በፀረ-ሙስና ትግል ላይ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ መወጣት አለባቸው - ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሀረሪ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለክልሉ ፖሊስ አባላት ሙስናን በመከላከል ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።

በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን እንደገለፁት የፀረ-ሙስና ትግሉን የመዋጋት ሥራ ላይ የፀጥታ አካላት ሚናቸው ከፊተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም የስልጠና እድሉን የወሰዱ አባላት ሙስና የመከላከል ሥራ ዉስጥ የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ መናገራቸውን የሀረሪ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ዘግቧል።

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ወሂብ በድሪ በበኩላቸው ስልጠናው በዋናነት ለፖሊስ አባላት የተሰጠበት ምክንያት የህዝቡን የአገልግሎት ፍላጎት ባልተገባ ጥቅም የሚያስተጓጉል ሁኔታ ሲፈጠር የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንዲወጡና ብልሹ አሰራርን እንዲታገሉ ለማድረግ አላማ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

በክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክቶሬት አቶ ታጁዲን ኢብራሂም እንደተናገሩት የፀጥታ አባላቱ ማህበረሰቡን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል አንዳለባቸዉ መልዕክት አስተላለፈዋል።

ስልጠናውን የወሰዱት የፖሊስ አባላት ተቋሙ የሰጣቸው ስልጠና ለሥራ እንቅስቃሴያቸው የሚጠቅም መሆኑን በማንሳት፥ ሙስናን የሚፀየፍ አሥራር ተግባራዊ ለማድረግና ተቋም ለመገንባት ያላቸውን ቁርጠኝነት አንስተዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በቻይና መንግስት ባለቤትነት የተያዘው የCITIC ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ጉቦ በመቀበል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 29/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በቻይና ውስጥ ከፍተኛ የመንግስት ኢንቨስትመንት ኩባንያ የሆነው የCITIC ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት ሹ ዙኦ ጉቦ በመቀበል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

የቻይና ዕለታዊ ጋዜጣ ፒዲ ቻይና እንደዘገበው፥ የCITIC ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት ሹ ዙኦ ጉቦ በመቀበል እና በስልጣን ላይ ከነበሩበት ኩባንያ ጋር ተመሳሳይ ሥራ በመስራት በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።

ሹ ዙኦ የፖርቲ ዲሲፕሊን እና ህጎችን በመጣሳቸው ከቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ አባልነታቸው መባረራቸውንም የቻይና ዕለታዊ ጋዜጣ ፒዲ ቻይና አስታውሷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት 68 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው በሙስና የተመዘበረ ሃብትን ማስመለስ ተችሏል - ቢሮው

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 68 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው በሙስና የተመዘበረ ሃብት በፍርድ ቤት ክርክር ማስመለስ መቻሉን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ ገለጸ፡፡

የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ቢሮው በወንጀልና በፍትሐ-ብሔር ህጎች ረገድ የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጉዮ ዋሪዮ በሰጡት መግለጫም፥ ባለፉት ስድስት ወራት ከ23 ሺህ 394 መዛግብት ላይ ክስ መመስረት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም 22 ሺህ 095 የሚሆኑ መዛግብት የወንጀል ክስ መመስረቱን ተናግረው ቢሮ ክስ ከመሰረተባቸው መዝገቦች መካከል 90 በመቶ የሚሆኑት ላይ ውሳኔ ማሰጠት መቻሉን ጠቁመዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት 703 የሚሆኑ መዛግብቶች በሙስና ወንጀል ክስ እንዲመሰረት ማድረግ መቻሉን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሙስና ወንጀል ክስ ከተመሰረተባቸው መካከልም 91 በመቶ የሚሆኑት ውሳኔ እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

በሙስና ወንጀል ከ927 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን ሃብቶች በማሳገድ ምርመራ ሲያካሄድ መቆየቱን ጠቁመው፥ እስካሁን 68 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ሃብት በፍርድ ቤት ክርክር ማስመለስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ከፍርድ ቤት ክርክር በተጨማሪ በአስተዳደራዊ እርምጃም በርካታ መጠን ያላቸውን ሃብቶች ማስመለስ መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ ፍትሕን ለማስፈን እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ኮሚሽኑ የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ድጋፍ አደረገ

******************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ድጋፍ አደረጓል፡፡

በኮሚሽኑ የሴቶችና ማህበራዊ አካቶ ትግበራ ሥራ ክፍል አስተባባሪነት ለምግብነት የሚውል ዱቄት፣ የንፅህና መጠበቂያ ሳሙና እና ሶፍት እንዲሁም አተር ክክ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሄደው 14ኛ መደበኛ ጉባኤው ለፀረ-ሙስና ትግል ከፍተኛ ፋይዳ ያለውን የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል

**

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሄደው 14ኛ መደበኛ ጉባኤው ለፀረ-ሙስና ትግል ከፍተኛ ፋይዳ ያለውን የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ጉባዔ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሄደው መደበኛ ጉባዔው፤ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በህግና ፍትህና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ነገ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ለፀረሙስና ትግል ከፍተኛ ፋይዳ አለው!

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ለፀረ-ሙስና ትግል ከፍተኛ ፋይዳ ያለው የንብረት ማስመለስ አዋጅ ጸደቀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 1/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፀረ-ሙስና ትግል ከፍተኛ ፋይዳ ያለው የንብረት ማስመለስ አዋጅ አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው14ኛ መደበኛ ስብሰባው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

አዋጁ በሕገ-ወጥ መንገድ የተፈራን ንብረት ማስመለስ የሚያስችሉና የሕግ-ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዕጸገነት መንግስቱ በረቂቅ አዋጁ የተደረጉ ማስተካከያዎችና የተጨመሩ አንቀጾችን አስመልክተው ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በአዋጁ ላይ በአስረጅ፣ በህዝብና የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ግብዓት እንደሰበሰበ ገልጸዋል።

የንብረት ማስመለስ አዋጅ የመንግስትና የህዝብ ንብረትን ለማስመለስ የነበረውን የሕግ ክፍተት የሚሞላ እንደሆነ አስረድተዋል።

አዋጁ ዜጎች በላባቸውና በወዛቸው ንብረት እንዲያፈሩ የሚያበረታታ፣ በወንጀል ንብረት የሚያፈሩትን ተጠያቂ የሚያደርግ፣ የአገርን ዕድገት የሚያሳልጥ እንደሆነ አስተያየት የሰጡ የምክር ቤት አባላት አንስተዋል።

ግለሰቦች በወንጀልና በሙስና ያፈሩትን ንብረት የሚያስመልስ በመሆኑ በተፈጻሚነቱ ላይ ጥንቃቄ ማድረግና አስፈጻሚ አካላትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ እና የዜጎችን ንብረት የማፍራት መብት እንዳይጋፋ መታየት አለባቸው ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል።

የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዕጸገነት መንግስቱ በአዋጁ ሃብት የማፍራትና የማውረስ ሕገ-መንግስታዊ መብትን የሚቃረን ድንጋጌ አለመካተቱንም ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የጸረ-ሙስና ትግል እንዲጠናከር የሚያደርግ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘና የተመዘበረ የአገር ሃብትን ለማስመለስ የሚያስችልና ሕገ-ወጥነትን የሚያስቆም አዋጅ እንደሆነም ጨምረዋል።

ምክር ቤቱ በአዋጁ አስፈላጊነትና ወቅታዊነት ላይ ዝርዝር ውይይት በማድረግ በ ሶሰት ተቃውሞ እና በአራት ድምጸ ታቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319