Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
ባለፉት 6 ወራት ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ከምዝበራ ማዳን መቻሉ ተገለፀ

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲዳማ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራርና ባለሙያዎች የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም በመገምገም በቀጣይ ወራት ትኩረት ተሰጥቶ በሚሰራባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ በቱላ ከተማ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ዘላለም ለማ በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም መታየቱን ገልፀዉ፥ በቀጣይ የሚሰሩ ተግባራት ጊዜዉንና በጀቱን በቆጠበ መልኩ መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በቀረበው ሪፖርት ኮሚሽኑ የትዉልድን ሥነምግባርና ሞራላዊ እሴቶችን በመገንባት ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል ስራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሰራቱ ተገልጿል።

በተለይም በንሳ ኤፍ ኤም እና ከሻሸመኔ ኤፍ ኤም 103.4 ሬዲዮ ጣቢያ ጋር በተደረሰዉ ስምምነት መሰረት የሥነምግባር ግንባታ ላይ ያተኮረ ትምህርት መሰጠቱም ተመላክቷል፡፡

ሀብት ምዝገባ በሚመለከት ባለፉት ስድስት ወራት ዉስጥ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በመንግስት ልማት ተቋማትና ህዝባዊ ተቋማት ዉስጥ የሚሰሩ አመራርና ሠራተኞች ለመጀመሪያ ጊዜ ሀብታቸውንና የገቢ ምንጫቸውን እንዲያስመዘግቡ መደረጉን ቀደም ሲል አስመዝግበዉ የነበሩ 3,368 ሀብት አስመዝጋቢዎች እንዲያድሱ ተደርጓል።

ሙስና እና ብልሹ አሰራርን የመከላከል አቅም ከማሳደግ አኳያ 72 ጥቆማዎች ወደ ኮሚሽኑ የቀረበ ሲሆን፥ በቀረበው ጥቆማ መነሻነት የአስቸኳይ ቅድመ መከላከል ስራ መሰራቱን አንስተዋል።

በዚህም በዓይነትና በገንዘብ ሊመዘበር የነበረ የመንግስትና ህዝብ ሀብት ማዳን ተችሏል። በአጠቃላይ 12,585,511.54 ብር ማዳን መቻሉን በሪፖርቱ ቀርቧል።

በውይይቱ በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉና እንደ ክፍተት የታዩት በቀሪ ወራት ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰሩ አቅጣጫ በማስቀመጥ መጠናቀቁን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኞች የመልካም ሥነምግባር አርዓያ መሆን አለባቸው - ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ)

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም አዳማ) ለፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአስተዳደር አገልግሎት ዘርፍ አመራርና ሠራተኞች የሥራ ቦታ ሥነምግባር ስልጠና እንዲሁም የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ ተገኝተው የሥራ አቅጣጫ የሰጡት ክቡር ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ) የኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኞች ለሌሎች ተቋማት በመልካም ሥነምግባር አርአያ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።

ክቡር ኮሚሽነሩ አክለውም የአስተዳደር አገልግሎት ዘርፍ የሥራ ኃላፊና ሠራተኞች ቅንጅት በመፍጠር ለሌሎች የሥራ ክፍሎች የተሳለጠ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በመድረኩ የሥራ ክፍሎች የ6 ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ የጋራ ውይይት ተካሂዶበታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የፍትህና የፀጥታ አካላት በፀረ-ሙስና ትግል ላይ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ መወጣት አለባቸው - ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሀረሪ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለክልሉ ፖሊስ አባላት ሙስናን በመከላከል ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።

በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን እንደገለፁት የፀረ-ሙስና ትግሉን የመዋጋት ሥራ ላይ የፀጥታ አካላት ሚናቸው ከፊተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም የስልጠና እድሉን የወሰዱ አባላት ሙስና የመከላከል ሥራ ዉስጥ የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ መናገራቸውን የሀረሪ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ዘግቧል።

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ወሂብ በድሪ በበኩላቸው ስልጠናው በዋናነት ለፖሊስ አባላት የተሰጠበት ምክንያት የህዝቡን የአገልግሎት ፍላጎት ባልተገባ ጥቅም የሚያስተጓጉል ሁኔታ ሲፈጠር የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንዲወጡና ብልሹ አሰራርን እንዲታገሉ ለማድረግ አላማ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

በክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክቶሬት አቶ ታጁዲን ኢብራሂም እንደተናገሩት የፀጥታ አባላቱ ማህበረሰቡን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል አንዳለባቸዉ መልዕክት አስተላለፈዋል።

ስልጠናውን የወሰዱት የፖሊስ አባላት ተቋሙ የሰጣቸው ስልጠና ለሥራ እንቅስቃሴያቸው የሚጠቅም መሆኑን በማንሳት፥ ሙስናን የሚፀየፍ አሥራር ተግባራዊ ለማድረግና ተቋም ለመገንባት ያላቸውን ቁርጠኝነት አንስተዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319