Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
246 videos
32 files
3.06K links
Download Telegram
ባለፉት 6 ወራት ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ከምዝበራ ማዳን መቻሉ ተገለፀ

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲዳማ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራርና ባለሙያዎች የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም በመገምገም በቀጣይ ወራት ትኩረት ተሰጥቶ በሚሰራባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ በቱላ ከተማ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ዘላለም ለማ በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም መታየቱን ገልፀዉ፥ በቀጣይ የሚሰሩ ተግባራት ጊዜዉንና በጀቱን በቆጠበ መልኩ መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በቀረበው ሪፖርት ኮሚሽኑ የትዉልድን ሥነምግባርና ሞራላዊ እሴቶችን በመገንባት ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል ስራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሰራቱ ተገልጿል።

በተለይም በንሳ ኤፍ ኤም እና ከሻሸመኔ ኤፍ ኤም 103.4 ሬዲዮ ጣቢያ ጋር በተደረሰዉ ስምምነት መሰረት የሥነምግባር ግንባታ ላይ ያተኮረ ትምህርት መሰጠቱም ተመላክቷል፡፡

ሀብት ምዝገባ በሚመለከት ባለፉት ስድስት ወራት ዉስጥ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በመንግስት ልማት ተቋማትና ህዝባዊ ተቋማት ዉስጥ የሚሰሩ አመራርና ሠራተኞች ለመጀመሪያ ጊዜ ሀብታቸውንና የገቢ ምንጫቸውን እንዲያስመዘግቡ መደረጉን ቀደም ሲል አስመዝግበዉ የነበሩ 3,368 ሀብት አስመዝጋቢዎች እንዲያድሱ ተደርጓል።

ሙስና እና ብልሹ አሰራርን የመከላከል አቅም ከማሳደግ አኳያ 72 ጥቆማዎች ወደ ኮሚሽኑ የቀረበ ሲሆን፥ በቀረበው ጥቆማ መነሻነት የአስቸኳይ ቅድመ መከላከል ስራ መሰራቱን አንስተዋል።

በዚህም በዓይነትና በገንዘብ ሊመዘበር የነበረ የመንግስትና ህዝብ ሀብት ማዳን ተችሏል። በአጠቃላይ 12,585,511.54 ብር ማዳን መቻሉን በሪፖርቱ ቀርቧል።

በውይይቱ በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉና እንደ ክፍተት የታዩት በቀሪ ወራት ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰሩ አቅጣጫ በማስቀመጥ መጠናቀቁን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኞች የመልካም ሥነምግባር አርዓያ መሆን አለባቸው - ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ)

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም አዳማ) ለፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአስተዳደር አገልግሎት ዘርፍ አመራርና ሠራተኞች የሥራ ቦታ ሥነምግባር ስልጠና እንዲሁም የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ ተገኝተው የሥራ አቅጣጫ የሰጡት ክቡር ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ) የኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኞች ለሌሎች ተቋማት በመልካም ሥነምግባር አርአያ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።

ክቡር ኮሚሽነሩ አክለውም የአስተዳደር አገልግሎት ዘርፍ የሥራ ኃላፊና ሠራተኞች ቅንጅት በመፍጠር ለሌሎች የሥራ ክፍሎች የተሳለጠ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በመድረኩ የሥራ ክፍሎች የ6 ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ የጋራ ውይይት ተካሂዶበታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319