Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.9K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ሕብረተሰቡ ህግና ሥርዓትን ተከትሎ ፍትህ ማግኘት እንደሚችል ማሳየት ይገባናል - አቶ መሀመድ መሀሙድ

**************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር በፍርድ ቤቶች ስለሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ድርጊቶች፣ በር ስለሚከፍቱ የአሰራር ሂደቶችና መፍትሔዎቻቸውን በሚመለከት ለከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ዳኞችና የአስተዳደር ሠራተኞች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎትን በማድረስ ሕብረተሰቡ ህግና ሥርዓትን ተከትሎ ፍትህ ማግኘት እንደሚችል ማሳየት እንደሚገባ የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ መሀመድ መሀሙድ ገልፀዋል፡፡

በስልጠናው የተነሱ ጉዳዮችን ወደ እራስ በመውሰድም እራስን መፈተሽና ማስተካከል እንደሚገባ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

ሥነምግባር የሁሉም ነገር መሰረት ነው ያሉት አቶ መሀመድ መሀሙድ፥ የተትረፈረፈ እውቀትና አቅም በሥነምግባር ካልተመራ ትርጉም እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

የሥነምግባር ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤቶች ሲመጣም ድርብ ኃላፊነት እንደሚሆንና የፍትህ ዘርፉ በጥብቅ ሥነምግባር መመራት እንዳለበተ አሳስበዋል፡፡ ለተግባራዊነቱም አበክሮ መስራት እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።

ሥልጠናውን የሰጡት በኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነምግባር ትምህርትና ሥልጠና ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ ገዛኸኝ የኔው ሲሆኑ፥ ሥነምግባር በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ የትክክለኝነትና የስህተት መለኪያ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የፍርድ ቤቶችን አገልግሎት አሰጣጥ በሚመለከት ተገልጋዮችን በማነጋገር የተሰራ አጭር ዳሰሳ ዋቢ በማድረግ ተገልጋዮች ባቀረቧቸው ክፍተቶች ላይ መሰድ ስለሚገባቸው መፍትሄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናው ከሥራቸው ጋር የሚሄድ፣ የሚያነቃቸውና የሚያጠናክራቸው መሆኑን የገለፁት ተሳታፊዎች፥ መሰል ሥልጠናዎች ተከታታይነት እንዲኖራቸው መጠየቃቸውን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የመንግስት ሠራተኞች የሥራ ላይ ሥነምግባርን በመተግበር በቅንነትና በታማኝነት ህዝቡን ማገልገል ይገባቸዋል - ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ

**************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከቤንች ሸኮ ዞን የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በሥራ ላይ ሥነምግባር እና በሀብት ማስመዝገብ ላይ ለዞን ማዕከል የመንግስት ሠራተኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ የመንግስት ሠራተኞች የመንግስትን ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ሕጎችን በመፈፀምና በማስፈፀም ሰላምን፣ ልማትንና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ሚናቸው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።

የሥራ ሥነምግባር የህዝብን አገልጋይነት ኃላፊነታችንን ለመወጣትና በማህበረሰባችን ውስጥ መተማመንን በማጎልበት እንዲሁም ውጤታማ አስተዳደርን በማረጋገጥ ረገድ ዋነኛ መሳሪያችን ነው ብለዋል።

የመንግስት ሠራተኛው የህዝብ አገልጋይ እንደመሆኑ መጠን ማህበረሰቡን በትጋትና በቅንነት የማገልገል ኃላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም የህዝብ አመኔታ ለሀገራዊ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፤ ሙስናን ነቅቶ መጠበቅና ከግል ጥቅም ይልቅ የህዝብን ደህንነት ማስቀደም ይገባል ብለዋል።

በዚህም የመንግስት ሠራተኛው አገልግሎቱን ከሙስና እና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ሊፈጽም እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በኮሚሽኑ የትምህርት ሥርዓት ዳይሬክቶሬት አቶ በፍቃዱ ዘለቀ የስልጠና ሠነድ ያቀረቡ ሲሆን፤ በመድረኩ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር፣ ምክትል ኮሚሽነሮች እና የዞን ማዕከል አጠቃላይ ሠራተኞች መገኘታቸውን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ኮሚሽኑ በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ሥራ የአንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የግዢ ጨረታ ሂደትን አቋረጠ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ሥራ የአንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የግዥ ጨረታ ሂደትን አቋረጠ።

ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 1236/2013 አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀፅ 4 መሠረት ሙስና ለመፈፀም የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሲጠረጥር ወይም ጥቆማ ሲደርሰው ድርጊቱ ከመፈፀሙ በፊት አስቸኳይ የሙስና መከላከል ጥናት በማካሄድ ሂደቱ እንዲቋረጥ የሚያደርግ በመሆኑ በህዳሴ ቴሌኮም አ.ማ ሊከናወን የነበረውን የ1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሶላር ላተርን እና ሆም ሲስተም የግዥ ጨረታ ሂደት እንዲቋረጥ አድርጓል፡፡

ለግዥ ሂደቱ መቋረጥ ምክንያት ከሆኑ የጥናት ግኝቶች መካከል የጨረታ ሠነድ ለተጫራቾች በግልፅ እና በፍትሃዊነት አለመቅረቡ፣ የቴክኒክ ኮሚቴ ግልፅ በሆነ መልኩ ግምገማ አለማድረጉ፣ ለእቃው ጥራት የተሰጠው የቴክኒክ ምዘና ነጥብ ዝቅተኛ መሆን እንዲሁም ለሌሎች ተያያዥነት ላላቸው የምዘና ነጥቦች ከፍተኛ ነጥብ መሰጠቱ፣ የግዢ መመሪያን በከፍተኛ ደረጃ መጣሱ እና በግዥ ጨረታ ሂደቱ ያልተገባ ትስስርን በመፍጠር ለጥቅም ግጭት ክስተት መጋለጡ የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የኮሚሽኑ አመራሮች እና የህዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እና የድርጅቱ ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የግዥ ጨረታ ሂደቱ የጥናት ግኝት ሪፖርት ተገምግሟል፡፡

በቀጣይ በድርጅቱ የሚከናወኑ የግዥ ሂደቶች ከሙስና እና ብልሹ አሠራር የጸዱ ሆነው እንዲፈጸሙ የሚያስችል ምክረ-ሐሳብ ተሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ምዝበራንና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት የኦዲት ስራን በይበልጥ ማጠናከር ያስፈልጋል - ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ጸሀይ ወራሳ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የ2017 በጀት አመት የኦዲት ግኝት ክትትልና ቁጥጥር ግብረ ሀይል የ6 ወር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ ማከናወኑ ተገልጿል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤና የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ ወ/ሮ ጸሀይ ወራሳ በመድረኩ እንዳሉት በየጊዜው የአሰራር ስርአትና ደንቦች ባለመጠበቃቸው የመንግስትና የህዝብ ሀብት ለምዝበራ የተጋለጠ በመሆኑ ጠንካራ የኦዲት ቁጥጥር አግባብ ሊኖር ይገባል ብለዋል።

የተጠያቂነት መርህ አለመጠናከር በየጊዜው አዳዲስ የኦዲት ግኝቶች እንዲፈጠሩ በር ከፍቷል ያሉት ወ/ሮ ጸሀይ፥ ያለንን ውስን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም የአሰራር ጥሰትን በማስቀረት የሚስተዋለውን ክፍተት ማረም እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዋና ኦዲተር አቶ አበባየሁ ኤርምያስ በኦዲት ረገድ ጠንካራ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም መሻሻሎች ቢኖሩም አሁንም የኦዲት ግኝት ተመሳሳይ መሆን፣ አዳዲስ የኦዲት ግኝት በአንዳንድ ተቋማት ላይ መታየት፣ ባልተሟላ ሰነድ ክፍያ መፈጸም፣ የተሰብሳቢና የተከፋይ ሂሳብ ማበጥና ሌሎች የኦዲት ግኝቶች መኖራቸው በይበልጥ ሰፊ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ አመላካች ነው ብለዋል።

የኦዲት ሪፖርት በወቅቱ ተደራሽ ከማድረግና ለክዋኔና ለአከባቢ ኦዲት ግብረ መልስ ከመስጠት አንጻር ሰፊ ውስንነት የሚታይ መሆኑንና በተገኙ የኦዲት ግኝቶች መነሻነት ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ የሁሉንም ቁርጠኝነት የሚጠይቅ መሆኑን አንስተዋል።

ዋና ኦዲተሩ አክለውም በ2015 በጀት ዓመት የከፋ የኦዲት አስተያየት ያገኙ 17 ፋይናንስ ተቋማትና የአምስት አመት የዞኖች ኦዲት ግኝት ለመድረኩ ያቀረቡ ሲሆን፥ እንደ ክልል የታየውን የ11 ቢሊየን የተሰብሳቢ ሂሳብ ማሰረጃ ካለ ቀርቦ እንዲወራረድ፣ ማሰረጃ መቅረብ የማይቻል ከሆነ ጥሬ ገንዘብን ወደ መንግስት ካዝና በመመለስ በኦዲት ግኝት ላይ የእርምት ርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል።

በመድረኩ በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኢንስፔክሽንና የውስጥ ኦዲት ዘርፍ የጥሬ ገንዘብና የአፈር ማዳበርያ ዕዳ የኦዲት ግኝት ሪፓርት የቀረበ ሲሆን፣ በዚህም የገንዘብ ዝውውርና የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ላይ የሚታይ ውስንነት መኖር ክፍያዎችን ያለ ዋስትና መስጠት የተፈቀደ በጀት ሳይኖር ክፍያ መፈጸም የተስተዋሉ ችግሮች መሆናቸው በሪፖርቱ ተነስቷል።

እንደዚሁም የ1,481,591,167 ብር የአፈር ማዳበርያ እዳ በኦዲት ግኝት የተጣራ መሆኑንና 99,347,423 ብር የተመለሰ ሲሆን፣ ያልተመለሰ ቀሪ እዳ 1,382,243,000 ብር በኦዲት ግኝት መኖሩ መታወቁን የደ.ሬ.ቴ.ድርጅት ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሌብነትና ብልሹ አሰራርን የሚፀየፍና በሥነምግባር የታነፀ ባለሙያ ማፍራት እንደሚገባ ተገለፀ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የልደታ ክ/ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ለአገልግሎት ጽ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች ስልጠና ተሰጥቷል።

በስልጠናው የተገኙት የአገልግሎት ፅ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ መቅደስ ያደታ ተቋማችን በርካታ የሪፎርም ስራዎችን እያደረገ ቢሆንም ሌብነትና ብልሹ አሰራር እየፈተነን ይገኛል ብለዋል።

ይህንን ችግር ለመቀነስ በርካታ ተግባራትን በመስራት ጥሩ ለዉጦች ቢታዩም ችግሩን በተግባር የሚፀየፍና በሥነምግባር የታነፀ ባለሙያ ማፍራት እንደሚያስፈልግ ገልፀው፥ ለዚህም ስልጠናው የአመለካከት ለዉጥ የምናመጣበት ይሆናል ብለዋል።

ስልጠናው በሥራ ሥነምግባር እና ብልሹ አሰራር ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን፥ በከተማ አስተዳደሩ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ስልጠና ባለሙያ አቶ አቤል ሳኩሜ እና በአገልግሎት ጽ/ቤቱ ባለሙያ አቶ ሌንጮ ወዳጆ መሰጠቱን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319