Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.9K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት እንቅፋት የሆነውን ሙስናን ለመከላከል የአመራሮች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

*****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) "ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል በመከላከያ ዘርፍ ሥር ላሉ ተቋማት የሙሰናና ብልሹ አሰራሮች መከላከል ስልቶች ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ሙስናን መዋጋት የሚያሥችሉ ስትራቴጂዎች ተነድፈው በትግበራ ላይ ቢሆኑም የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ሁሉንም ያሳተፈ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን የሚፀየፍ ዜጋ ማፍራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ሙስና በሃገር ሁለንተናዊ እድገት ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ በማስከተል ሃገር እንደ ሃገር በማይቀጥልበት ደረጃ የማድረስ ወይም ተቋማትን የማፋረስ አደጋ ሊያስከትል የሚችል ተለዋዋጭ ባህሪ ያለው አደገኛ የሆነ የወንጀል አይነት መሆኑን የገለፁት ደግሞ ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር ኮማንደር ደመላሽ ካሳዬ (ዶ/ር) ናቸው።

በተጨማሪ ማብራሪያቸው የሙስና መንሰራራት የህግ የበላይነትን ያጠፋል፣ የኢኮኖሚ እድገትን ያቀጭጫል፣ የማህበራዊ አገልግሎቶችን ተደራሽነትን ያዳክማል፣ የኢንቨስትመንት ፉሰት ይገታል እንዲሁም ስርዓት አልበኝነት እንዲሰራፋ ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥር ሁሉም ዜጋ በፅናት ሊታገለው እንደሚገባ አመላክተዋል።

ስልጠናው የሚሰጠው በመጀመሪያው ዙር ላልወሰዱ በየደረጃው ለሚገኙ የዘርፉ መካከለኛ አመራሮች ሲሆን፣ ትላንትን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሕብረተሰቡ ህግና ሥርዓትን ተከትሎ ፍትህ ማግኘት እንደሚችል ማሳየት ይገባናል - አቶ መሀመድ መሀሙድ

**************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር በፍርድ ቤቶች ስለሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ድርጊቶች፣ በር ስለሚከፍቱ የአሰራር ሂደቶችና መፍትሔዎቻቸውን በሚመለከት ለከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ዳኞችና የአስተዳደር ሠራተኞች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎትን በማድረስ ሕብረተሰቡ ህግና ሥርዓትን ተከትሎ ፍትህ ማግኘት እንደሚችል ማሳየት እንደሚገባ የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ መሀመድ መሀሙድ ገልፀዋል፡፡

በስልጠናው የተነሱ ጉዳዮችን ወደ እራስ በመውሰድም እራስን መፈተሽና ማስተካከል እንደሚገባ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

ሥነምግባር የሁሉም ነገር መሰረት ነው ያሉት አቶ መሀመድ መሀሙድ፥ የተትረፈረፈ እውቀትና አቅም በሥነምግባር ካልተመራ ትርጉም እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

የሥነምግባር ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤቶች ሲመጣም ድርብ ኃላፊነት እንደሚሆንና የፍትህ ዘርፉ በጥብቅ ሥነምግባር መመራት እንዳለበተ አሳስበዋል፡፡ ለተግባራዊነቱም አበክሮ መስራት እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።

ሥልጠናውን የሰጡት በኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነምግባር ትምህርትና ሥልጠና ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ ገዛኸኝ የኔው ሲሆኑ፥ ሥነምግባር በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ የትክክለኝነትና የስህተት መለኪያ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የፍርድ ቤቶችን አገልግሎት አሰጣጥ በሚመለከት ተገልጋዮችን በማነጋገር የተሰራ አጭር ዳሰሳ ዋቢ በማድረግ ተገልጋዮች ባቀረቧቸው ክፍተቶች ላይ መሰድ ስለሚገባቸው መፍትሄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናው ከሥራቸው ጋር የሚሄድ፣ የሚያነቃቸውና የሚያጠናክራቸው መሆኑን የገለፁት ተሳታፊዎች፥ መሰል ሥልጠናዎች ተከታታይነት እንዲኖራቸው መጠየቃቸውን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የመንግስት ሠራተኞች የሥራ ላይ ሥነምግባርን በመተግበር በቅንነትና በታማኝነት ህዝቡን ማገልገል ይገባቸዋል - ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ

**************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከቤንች ሸኮ ዞን የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በሥራ ላይ ሥነምግባር እና በሀብት ማስመዝገብ ላይ ለዞን ማዕከል የመንግስት ሠራተኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ የመንግስት ሠራተኞች የመንግስትን ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ሕጎችን በመፈፀምና በማስፈፀም ሰላምን፣ ልማትንና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ሚናቸው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።

የሥራ ሥነምግባር የህዝብን አገልጋይነት ኃላፊነታችንን ለመወጣትና በማህበረሰባችን ውስጥ መተማመንን በማጎልበት እንዲሁም ውጤታማ አስተዳደርን በማረጋገጥ ረገድ ዋነኛ መሳሪያችን ነው ብለዋል።

የመንግስት ሠራተኛው የህዝብ አገልጋይ እንደመሆኑ መጠን ማህበረሰቡን በትጋትና በቅንነት የማገልገል ኃላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም የህዝብ አመኔታ ለሀገራዊ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፤ ሙስናን ነቅቶ መጠበቅና ከግል ጥቅም ይልቅ የህዝብን ደህንነት ማስቀደም ይገባል ብለዋል።

በዚህም የመንግስት ሠራተኛው አገልግሎቱን ከሙስና እና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ሊፈጽም እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በኮሚሽኑ የትምህርት ሥርዓት ዳይሬክቶሬት አቶ በፍቃዱ ዘለቀ የስልጠና ሠነድ ያቀረቡ ሲሆን፤ በመድረኩ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር፣ ምክትል ኮሚሽነሮች እና የዞን ማዕከል አጠቃላይ ሠራተኞች መገኘታቸውን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ኮሚሽኑ በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ሥራ የአንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የግዢ ጨረታ ሂደትን አቋረጠ

******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ሥራ የአንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የግዥ ጨረታ ሂደትን አቋረጠ።

ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 1236/2013 አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀፅ 4 መሠረት ሙስና ለመፈፀም የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሲጠረጥር ወይም ጥቆማ ሲደርሰው ድርጊቱ ከመፈፀሙ በፊት አስቸኳይ የሙስና መከላከል ጥናት በማካሄድ ሂደቱ እንዲቋረጥ የሚያደርግ በመሆኑ በህዳሴ ቴሌኮም አ.ማ ሊከናወን የነበረውን የ1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሶላር ላተርን እና ሆም ሲስተም የግዥ ጨረታ ሂደት እንዲቋረጥ አድርጓል፡፡

ለግዥ ሂደቱ መቋረጥ ምክንያት ከሆኑ የጥናት ግኝቶች መካከል የጨረታ ሠነድ ለተጫራቾች በግልፅ እና በፍትሃዊነት አለመቅረቡ፣ የቴክኒክ ኮሚቴ ግልፅ በሆነ መልኩ ግምገማ አለማድረጉ፣ ለእቃው ጥራት የተሰጠው የቴክኒክ ምዘና ነጥብ ዝቅተኛ መሆን እንዲሁም ለሌሎች ተያያዥነት ላላቸው የምዘና ነጥቦች ከፍተኛ ነጥብ መሰጠቱ፣ የግዢ መመሪያን በከፍተኛ ደረጃ መጣሱ እና በግዥ ጨረታ ሂደቱ ያልተገባ ትስስርን በመፍጠር ለጥቅም ግጭት ክስተት መጋለጡ የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የኮሚሽኑ አመራሮች እና የህዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እና የድርጅቱ ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የግዥ ጨረታ ሂደቱ የጥናት ግኝት ሪፖርት ተገምግሟል፡፡

በቀጣይ በድርጅቱ የሚከናወኑ የግዥ ሂደቶች ከሙስና እና ብልሹ አሠራር የጸዱ ሆነው እንዲፈጸሙ የሚያስችል ምክረ-ሐሳብ ተሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319