Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.9K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ኮሚሽኑ ዘርፍ ተኮር ድጋፍና ክትትል እያደረገ ነው

**,****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ26 የዘርፍ ተቋማት በ2017 በጀት ዓመት የ2ኛውን ሩብ ዓመት የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራዎች ላይ የድጋፍና ክትትል (ሱፐርቪዥን) ሥራ እያካሄደ ይገኛል።

ሱፐርቪዥኑ በዘርፎች የሚካሄደውን ሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ተግባር ለማጠናከር ያስችላል ፡፡

ሱፐርቪዥዠኑ በመንግስት ተቋማት፣ በመንግስት የልማት ድርጅቶች እና ህዝባዊ ድርጅቶች ከታህሳስ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን፥ እስከ ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበት በእስር ላይ የነበረውን እስረኛ ጉቦ በመቀበል ያስመለጡ የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ቀረበባቸው

*****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበት በእስር ላይ የነበረውን እስረኛ ጉቦ በመቀበል ያስመለጡ የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ቀርቦባቸዋል።

የሀዲያ ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ዓቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ላይ በክስ አንድ እንደተጠቀሰው ተከሳሾች 1ኛ. ዋ/ሣጅን ሠላሙ ሙሉነህ፣ 2ኛ. ሳጅን አብዮት ደቦጭ፣ 3ኛ. ኮንስታብል መስፍን መስቀሎ፣ 4ኛ. ረዳት ሳጅን ሙላቱ ብርሃኑ እና 5ኛ ኮንስታብል ደገፈ ማቴዎስ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 10/1/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ መከሰሳቸው ተገልጿል።

ክሱም በሥራ ግዴታቸው የማይገባውን ለማድረግ እና ለራሳቸው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በቀን 08/03/2017 ዓ.ም በሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ ውስጥ የዕለቱ ተረኛ የእስረኞች ጥበቃ እና መውጫ በር ላይ በጥበቃ ተመድበው እየሰሩ ባሉበት በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበት ዋስትና ተነፍጎ በመምሪያው ውስጥ ታስሮ የነበረውን አቶ ጥላሁን ሞላ የተባለውን እስረኛን ለማስመለጥ በማቀድ 3,500 ብር የተቀበሉ በመሆኑ ተከሳሾች አስበው በፈጸሙት ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡

በተጨማሪም በክስ ሁለት ዓቃቤ ህግ ተከሳሾቹን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አዋጅ ቁጥር 414/1996 አንቀጽ 425/2/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ በፈፀሙት እስረኛን ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ መፍታት ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።

የዓቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ላይ የቀረበው የወንጀል ዝርዝር እንደሚያስረዳው ተከሳሾች ሕግን በሚቃረን መንገድ አስቀድሞ በዓቃቤ ህግ በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበት ዋስትና ተነፍጎ በሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የነበረውን አቶ ጥላሁን ሞላ የተባለውን ግለሰብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ያሉ ተከሳሾች የዕለቱ ተረኛ የእስረኞች ጥበቃ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

እንዲሁም 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች መውጫ በር ላይ በጥበቃ ተመድበው እየሰሩ ባሉበት ወቅት በቀን 08/03/2017ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ እስረኛውን ፈተው የለቀቁ በመሆኑ፥ ተከሳሾች እሥረኛን ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ መፍታት ወንጀል መከሰሳቸው ከሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ተከሳሾችም በዛሬው ዕለት የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመቅረብ ክሱ የደረሳቸው ሲሆን፥ ጉዳዩ የቀረበለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ለመስማትና የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመቀበል ለታህሳስ 24/2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት እንቅፋት የሆነውን ሙስናን ለመከላከል የአመራሮች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

*****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) "ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል በመከላከያ ዘርፍ ሥር ላሉ ተቋማት የሙሰናና ብልሹ አሰራሮች መከላከል ስልቶች ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ሙስናን መዋጋት የሚያሥችሉ ስትራቴጂዎች ተነድፈው በትግበራ ላይ ቢሆኑም የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ሁሉንም ያሳተፈ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን የሚፀየፍ ዜጋ ማፍራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ሙስና በሃገር ሁለንተናዊ እድገት ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ በማስከተል ሃገር እንደ ሃገር በማይቀጥልበት ደረጃ የማድረስ ወይም ተቋማትን የማፋረስ አደጋ ሊያስከትል የሚችል ተለዋዋጭ ባህሪ ያለው አደገኛ የሆነ የወንጀል አይነት መሆኑን የገለፁት ደግሞ ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር ኮማንደር ደመላሽ ካሳዬ (ዶ/ር) ናቸው።

በተጨማሪ ማብራሪያቸው የሙስና መንሰራራት የህግ የበላይነትን ያጠፋል፣ የኢኮኖሚ እድገትን ያቀጭጫል፣ የማህበራዊ አገልግሎቶችን ተደራሽነትን ያዳክማል፣ የኢንቨስትመንት ፉሰት ይገታል እንዲሁም ስርዓት አልበኝነት እንዲሰራፋ ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥር ሁሉም ዜጋ በፅናት ሊታገለው እንደሚገባ አመላክተዋል።

ስልጠናው የሚሰጠው በመጀመሪያው ዙር ላልወሰዱ በየደረጃው ለሚገኙ የዘርፉ መካከለኛ አመራሮች ሲሆን፣ ትላንትን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሕብረተሰቡ ህግና ሥርዓትን ተከትሎ ፍትህ ማግኘት እንደሚችል ማሳየት ይገባናል - አቶ መሀመድ መሀሙድ

**************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር በፍርድ ቤቶች ስለሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ድርጊቶች፣ በር ስለሚከፍቱ የአሰራር ሂደቶችና መፍትሔዎቻቸውን በሚመለከት ለከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ዳኞችና የአስተዳደር ሠራተኞች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎትን በማድረስ ሕብረተሰቡ ህግና ሥርዓትን ተከትሎ ፍትህ ማግኘት እንደሚችል ማሳየት እንደሚገባ የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ መሀመድ መሀሙድ ገልፀዋል፡፡

በስልጠናው የተነሱ ጉዳዮችን ወደ እራስ በመውሰድም እራስን መፈተሽና ማስተካከል እንደሚገባ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

ሥነምግባር የሁሉም ነገር መሰረት ነው ያሉት አቶ መሀመድ መሀሙድ፥ የተትረፈረፈ እውቀትና አቅም በሥነምግባር ካልተመራ ትርጉም እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

የሥነምግባር ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤቶች ሲመጣም ድርብ ኃላፊነት እንደሚሆንና የፍትህ ዘርፉ በጥብቅ ሥነምግባር መመራት እንዳለበተ አሳስበዋል፡፡ ለተግባራዊነቱም አበክሮ መስራት እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።

ሥልጠናውን የሰጡት በኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነምግባር ትምህርትና ሥልጠና ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ ገዛኸኝ የኔው ሲሆኑ፥ ሥነምግባር በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ የትክክለኝነትና የስህተት መለኪያ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የፍርድ ቤቶችን አገልግሎት አሰጣጥ በሚመለከት ተገልጋዮችን በማነጋገር የተሰራ አጭር ዳሰሳ ዋቢ በማድረግ ተገልጋዮች ባቀረቧቸው ክፍተቶች ላይ መሰድ ስለሚገባቸው መፍትሄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናው ከሥራቸው ጋር የሚሄድ፣ የሚያነቃቸውና የሚያጠናክራቸው መሆኑን የገለፁት ተሳታፊዎች፥ መሰል ሥልጠናዎች ተከታታይነት እንዲኖራቸው መጠየቃቸውን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319