ሙስና የብልፅግና ጉዞአችን አደናቃፊ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሊታገል ይገባል - ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል
****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ እና በዞኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል በጋራ ሙስናን ለመከላከል የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የወላይታ ዞን የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል ሙስናን የሚፀየፍ እና የሚታገል ህብረተሰብ በየደረጃው መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።
የህግ ተጠያቂነትን በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ የህዝቡና የመንግስት ሀብትን ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።
ሙስናን ለመታገል ከራስ በመጀመር አርዓያ መሆን ይጠይቃል ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት፣ በየደረጃው ያሉ የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶችን በተገቢው ማሳተፍ ያስፈልጋል ብለዋል።
በመሠረታዊ ድርጅትና ህዋሳት ላይ ለሙስና ትግል ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።
በግብይት ወቅት ደረሰኝ ባለመስጠት መንግስት ማግኘት ያለበትን በማሸሽ የሚፈጸም ሙስናን ለመከላከል አደረጃጀቶችን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።
ከሙስና የጸዱ ተቋማትንና መዋቅሮችን ለመፍጠር የፓርቲ አባላት ትግል ሊጠናክር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ሙስና ለሀገርና ህዝብ ጠንቅ ነው ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት፣ በየጊዜው ህዝቡን የሚያማርሩ ሌብነትና የአገልግሎት ችግር ከስሩ መንቀል እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።
የወላይታ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን መሪ ዶ/ር ፋኖስ ዛና በበኩላቸው በፀረ-ሙስና ትግሉ ላይ ህብረተሰቡ በንቃት እንዲሳተፍ መሰራት ይሻል ብለዋል።
ሙስና ለልማት፣ ለመልካም አስተዳደርና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፍ መሆኑን ገልጸዋል።
የፀረ-ሙስና ትግሉ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው በልዩ ትኩረት መስራት እንዳለበትም መናገራቸውን ከወላይታ ብልፅግና ፖርቲ ፅ/ቤት የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በመጨረሻም የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ እና የዞኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎች እንዲሁም የዞንና የክልል ተቋማት የመሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢዎች ሙስናን በጋራ ለመከላከል የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ኮሚሽኑ ዘርፍ ተኮር ድጋፍና ክትትል እያደረገ ነው
**,****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ26 የዘርፍ ተቋማት በ2017 በጀት ዓመት የ2ኛውን ሩብ ዓመት የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራዎች ላይ የድጋፍና ክትትል (ሱፐርቪዥን) ሥራ እያካሄደ ይገኛል።
ሱፐርቪዥኑ በዘርፎች የሚካሄደውን ሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ተግባር ለማጠናከር ያስችላል ፡፡
ሱፐርቪዥዠኑ በመንግስት ተቋማት፣ በመንግስት የልማት ድርጅቶች እና ህዝባዊ ድርጅቶች ከታህሳስ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን፥ እስከ ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል።

በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበት በእስር ላይ የነበረውን እስረኛ ጉቦ በመቀበል ያስመለጡ የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ቀረበባቸው
*****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበት በእስር ላይ የነበረውን እስረኛ ጉቦ በመቀበል ያስመለጡ የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ቀርቦባቸዋል።
የሀዲያ ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ዓቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ላይ በክስ አንድ እንደተጠቀሰው ተከሳሾች 1ኛ. ዋ/ሣጅን ሠላሙ ሙሉነህ፣ 2ኛ. ሳጅን አብዮት ደቦጭ፣ 3ኛ. ኮንስታብል መስፍን መስቀሎ፣ 4ኛ. ረዳት ሳጅን ሙላቱ ብርሃኑ እና 5ኛ ኮንስታብል ደገፈ ማቴዎስ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 10/1/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ መከሰሳቸው ተገልጿል።
ክሱም በሥራ ግዴታቸው የማይገባውን ለማድረግ እና ለራሳቸው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በቀን 08/03/2017 ዓ.ም በሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ ውስጥ የዕለቱ ተረኛ የእስረኞች ጥበቃ እና መውጫ በር ላይ በጥበቃ ተመድበው እየሰሩ ባሉበት በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበት ዋስትና ተነፍጎ በመምሪያው ውስጥ ታስሮ የነበረውን አቶ ጥላሁን ሞላ የተባለውን እስረኛን ለማስመለጥ በማቀድ 3,500 ብር የተቀበሉ በመሆኑ ተከሳሾች አስበው በፈጸሙት ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
በተጨማሪም በክስ ሁለት ዓቃቤ ህግ ተከሳሾቹን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አዋጅ ቁጥር 414/1996 አንቀጽ 425/2/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ በፈፀሙት እስረኛን ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ መፍታት ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።
የዓቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ላይ የቀረበው የወንጀል ዝርዝር እንደሚያስረዳው ተከሳሾች ሕግን በሚቃረን መንገድ አስቀድሞ በዓቃቤ ህግ በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበት ዋስትና ተነፍጎ በሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የነበረውን አቶ ጥላሁን ሞላ የተባለውን ግለሰብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ያሉ ተከሳሾች የዕለቱ ተረኛ የእስረኞች ጥበቃ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
እንዲሁም 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች መውጫ በር ላይ በጥበቃ ተመድበው እየሰሩ ባሉበት ወቅት በቀን 08/03/2017ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ እስረኛውን ፈተው የለቀቁ በመሆኑ፥ ተከሳሾች እሥረኛን ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ መፍታት ወንጀል መከሰሳቸው ከሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ተከሳሾችም በዛሬው ዕለት የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመቅረብ ክሱ የደረሳቸው ሲሆን፥ ጉዳዩ የቀረበለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ለመስማትና የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመቀበል ለታህሳስ 24/2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።