Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሃብት ማሳወቅና ምዝገባ ሂደት ላይ ለካፋ ዞን ማዕከል የመንግስት ሠራተኞች ስልጠና ሰጠ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከአስር ቀን በኋላ ተግባራዊ የሚደረገውን የሃብት ማሳወቅና ምዝገባ ሂደት አስመልክቶ ከካፋ ዞን ማዕከል ለተወጣጡ መንግስት ሠራተኞች በቦንጋ ከተማ የግንዛቤ ስልጠና ሰጥቷል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳግም ዳንኤል ሃብት ማሳወቅና ማስመዝገብ በመንግስት ተቋማት፣ በመንግስት የልማት ድርጅቶችና በህዝባዊ ድርጅቶች መካከል መልካም ሥነምግባርና እሴቶች እንዲጎለብቱ ከማድረግ ባሻገር ተቋማዊ አቅምን በመገንባት የመንግስትና የህዝብ ሥራዎች አሠራር ግልፀኝነት እንዲኖራቸው ያደርጋል ብለዋል።

የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዓለማና ተግባር የተሿሚዎችንና ሕጉ ግዴታ የጣለባቸዉን የመንግሥት ሠራተኞች እና የመንግስት ልማት ድርጅት ሠራተኞች ሀብትና የገቢ ምንጫቸዉን አሳወቀው እንዲያስመዘግቡ መሆኑን ተናግረዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መዘጋጀቱ ትክክለኛ መረጃ ለዜጎች በማድረስ ሃብታቸውን እንዲያሳውቁና እንዲያስመዘግቡ ለማስቻል እንደሆነም ገልጸዋል።

በየተቋማት የሚገኙ ሠራተኞች በሥነምግባርና በመልካም እሴት ተገንብተው ተገልጋዮቻቸውን በአገልግሎቶቻቸው ማርካት እንዲችሉ ያስችላል ብለዋል።

እንዲሁም የተቋማት አመራርና ሠራተኞች በሥራ ላይ ሥነ-ምግባር የታነጹ ሆነውና በቴክኖሎጂ ታግዘው በፍጥነትና በጥራት አገልግሎት እንዲሰጡ በሥራ ላይ ሥነ-ምግባር መቃኘት እንደሚገባቸውም ተጠቅሷል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩም የሥራ ሥነምግባር እና የሃብት ማሳወቅና ምዝገባ አፈፃፀም መመሪያ ሰነዶች የቀረቡ ሲሆን፥ በቀረቡ ሰነዶች ላይ በኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ታደሰ አይበራ ማጠቃለያና የሥራ መመሪያ መሰጠቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

በመጨረሻም የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ቅጽ ከዞኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን ጋር ርክክብ የተደረገ ሲሆን፥ በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ የሃብት ማሳወቅና ምዝገባ ተደርጎ ይጠናቀቃልም ተብሏል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል መሪ ቃል ለኢንዱስትሪ ዘርፍ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለኢንዱስትሪ ዘርፍ አመራሮች "ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ዘርፍ ተኮር የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠና መድረኩ የተገኙት በኢንዱስትሪ ዘርፍ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር ሐድጉ ኃይለኪሮስ (ዶ/ር) ስልጠናው በዘርፋ የሚስተዋለውን ሙስና እና ብልሹ አሰራር ለመከላከል የሚያግዝ ከመሆኑም ባሻገር የዘርፋን የሙስና ተጋላጭነት የምንለይበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

መንግስት ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በርካታ ተግባራት እየሰራ መሆኑን ገልፀው፥ የኢንዱስትሪ ዘርፍ አመራሮችም በተቋማችን የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን የመከላከል ኃላፊነታችን መወጣት ይኖርብናል ብለዋል።

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፈቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው የኢንዱስትሪ ዘርፍ እንደመንግስት በርካታ ኃላፊነት የተሰጠውና ግዙፍ በጀት የሚያቀሳቀስበት ተቋም በመሆኑ አመራሩ የመልካም ሥነምግባር አርዓያ በመሆን ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

ዘርፉ በርካታ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የሚንቀሳቀስበት መሆኑን ገልፀው፥ ይህን ተስፋ ሰጭ እንቅስቃሴ በሙስና እና ብልሹ አሰራር ተጋላጭ እንዳይሆን አመራሩ በኃላፊነት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም የተቋማት አመራሮች ደካማ መሆን የሙስና እና ብልሹ አሰራር መባባስ ምክንያት መሆኑን ገልፀው፥ አመራሩ ከብልሹ አሰራር ነፃ በመሆን ከህዝብ የሚጠበቅበትን አገልግሎት መስጠት አለበት ብለዋል።

ስልጠናው ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እንደሚያግዝ ገልፀው፥ ከማስተማሩ ባሻገር ችግር ፈጣሪዎችን አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል።

ስልጠናው ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እየተሰጠ ሲሆን፣ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319