Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ከፍትሕ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት የፀረ-ሙስና ትግሉን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሙስናን ለመከላከል እና ተጠያቂነትን ለማስፈን ከፍትሕ ቢሮ እና ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር ቅንጅታዊ አሠራርን ለማጠናከር ውይይት አድርጓል። የመግባቢያ ሠነድም ተፈራርሟል።

በውይይቱ የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ብርሃኑ ጎሽም፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስየ ደጀን፣ የክልሉ ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕ እና አሥተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ ደሴ ጥላሁን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በውይይቱ መልዕክት ያስተላለፉት በአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕ እና አሥተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ ደሴ ጥላሁን (ዶ/ር) የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከተሰጡት ተግባራት ውስጥ አንዱ ሙስናን መከላከል መኾኑን ጠቅሰዋል።

በዚህ ተልዕኮም ትውልድን በመልካም ሥነምግባር ማነጽ እና ዜጎች ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

የሥነምግባር እና የፀረሙስና ኮሚሽን፣ ፍትሕ እና ፖሊስ ተቋማት ተቀናጅተው በመሥራት ተልዕኳቸውን ዳር ለማድረስ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይቱ ትኩረት ማድረጉን ገልጸው፣ ችግሮችን ገምግሞ በማረም ለመሥራትም እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በምዝገባ እና መረጃ አያያዝ ውስጥ የሚያገኛቸውን መረጃዎች የሚቀበል እና የፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ አጣርቶ ለሕግ በማቅረብ በኩል እየገጠሙ ያሉ ችግሮችን በመወያየት መፍትሔ ማበጀት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ወደፊትም ከሌሎች የፍትሕ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት የፀረ-ሙስና ትግሉ መጠናከር አለበት ብለዋል። የሙስና ተግባራትን የሕግ ተጠያቂነት ከፍ ለማድረግ መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴም የፀረ-ሙስና ትግሉ ውጤታማ እንዲኾን እየተከታተለ እንደሚደግፍ ገልጸዋል።

የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሐብታሙ ሞገስ ኮሚሽኑ በሕግ በተሰጡት ሥልጣን እና ተግባራት መሠረት የሥነምግባር ግንባታ፣ የሙስና መከላከል እና የሃብት ምዝገባ እና ማጣራት ተግባራትን እንደሚያከናውን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታትም እነዚህን ተግባራት ሲፈጽም መቆየቱን ጠቅሰዋል።

ሙሰና በሀገር ምጣኔ ሃብት፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ሥርዓት ላይ ችግር እያስከተለ መኾኑንም አስገንዝበዋል። ባለፉት ዓመታት በርካታ የሙስና ወንጀሎች ተፈጽመዋል ብለዋል።

ወንጀሎቹን በመመርመር እና በማጣራት ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ የውይይቱ ተሳታፊዎች ትልቅ ሚና አላቸው ነው ያሉት።

በተያዘው በጀት ዓመትም የተቋማት ነጻነት እንደተጠበቀ ኾኖ ከፖሊስ እና ከፍትሕ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት በሚቻልበት ኹኔታ ላይ ለመወያየት መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በውይይቱ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሙስናን ለመታገል እና ሙሰኞችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የሠራቸውን ሥራዎች እና ያጋጠሙትን ችግሮች ለውይይት አቅርቧል።

ፖሊስ ኮሚሽንም ሙስናንን ለመከላከል በትኩረት እየሠራ መኾኑ ተመላክቷል። የተሠሩ የምርመራ መዝገቦች እና ከምዝበራ የዳነ ሃብት መኖሩም ተገልጿል።

በፍትሕ ቢሮ በኩል በቀረበ የመወያያ ሃሳብም በፀረ-ሙስና ትግሉ የተሠሩ ሥራዎች፣ በቀጣይ በቅንጅት ሊሠሩ እና ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ተመላክተዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ባለፉት 5 ወራት በሀሰተኛ የተጭበረበረ ደረሰኝ መንግስት ሊያጣ የነበረውን ከ345 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን ተችሏል - የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በ2017 በጀት ዓመት 5 ወራት በሀሰተኛ ደረሰኝ ግብይት ተጭበርብሮ ያለ አግባብ ሊቀር የነበረ ከ345 ሚሊዮን ብር በላይ በማዳን የመንግስትን ጥቅም ማስጠበቅ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ እንደገለፁት፣ ሀሰተኛ ደረሰኝ እንዲጣራ ከቀረቡት አጠቃላይ 16 ሺ 425 ደረሰኞች 2 ሺ 654 ሀሰተኛ ሆነው ተገኝተዋል።

ሀሰተኛ ደረሰኞቹ የያዙት 345 ሚሊየን 526 ሺህ 600 ብር በመሆኑ ይህንን ማዳን መቻሉን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ በዚህም ወጪና ያልተገባ ታክስ ያለ አግባብ እንዳይወራረድ መደረጉ ተገልጿል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የሙያ ሥነ-ምግባር የተላበሰ ሰራተኛን መፍጠር የተቋም ሀብት ከማዳን ባለፈ የመፈፀም አቅም እንደሚያሳድግ ተገለፀ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከአዲስ አበባ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር የሥነምግባር ምንነት፣ ሙያዊ ሥነምግባር፣ የሙስና ፅንሰ ሀሳብና መከላከያ ስልቶች ላይ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ዳይሬክተር አቶ ጀንበሩ ኢርኮ እንደገለፁት የሙያ ሥነምግባር መበላሸት ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚያባብስና ሰራተኞች ባልተገባ መንገድ ኃላፊነታቸውን እንዳይወጡ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ጀንበሩ የሙያ ሥነ-ምግባር የተላበሰ ሰራተኛን መፍጠር የተቋሙን ሀብት ከብክነት ለመጠበቅ እና የመፈፀም አቅምን ለማሳደግ አዎንታዊ አስተዋፆኦ የሚያበረክት መሆኑን በመድረኩ ላይ አብረርተዋል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አባተ ገብረአምላክ በበኩላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚያንቀሳቅሰው ሰፊ ሀብት አንፃር ለሙስና እና ብልሹ አሰራር የሚኖረውን ተጋላጭነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ስልጠናው መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም የሠራተኛውን ግንዛቤ የሚያሰፉ መሰል ስልጠናዎች መዘጋጀታቸው ፋይዳው የጉላ መሆኑን ጠቁመው፥ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሀብት ሳይባክን ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል ማድረግ የሁሉም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ኃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።
ይህን ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ስልጠናው በሦስት ዙር የተሰጠ ሲሆን 300 የሚሆኑ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319