Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የሞባይል ቀፎዎችንና ካርዶችን ለግል ጥቅሙ አውሏል የተባለው ሠራተኛ በእስራት ተቀጣ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የሞባይል ቀፎዎችንና ካርዶችን ለግል ጥቅም አውሏል የተባለው የቀድሞ የህዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር ሰራተኛ በእስራት መቀጣቱ ተነግሯል፡፡

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የድሬዳዋ ምድብ ጅግጅጋ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ቀጠሮ መስፍን ኣሰፋ በተባለ ተከሳሽ ላይ የግራ ቀኝ ማስረጃዎች መርምሮ ጥፋተኛ በማለት የጽኑ እስራትና የገንዘብ መቀጮ ውሳኔ አስተላልፎበታል።

በፍትህ ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅርጫፍ ጽህፍት ቤት ዐቃቤ ህግ በተከሳሹ ላይ በ1996 ዓ/ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 676 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፉን ጠቅሶ ሚያዚያ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ዝርዝር ክስ አቅርቦበት ነበር።

በዚህ በቀረበበት ክስ ዝርዝር ላይ እንደተመላከተው ተከሳሽ ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የህዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የምስራቅ ዲስትሪክት በጎዴ አካባቢያዊ ጽህፈት ቤት ሱፐርቫይዘር ሆኖ በሚያገለግልበት ወቅት ከጳጉሜን 3 ቀን 2003 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ድረስ ከአክሲዮን ማህበሩ የተረከባቸውን የተለያዩ ዋጋ ያላቸው የሞባይል ካርዶችን፣ ሲም ካርዶች እና የሞባይል ቀፎዎች ጠቅላላ ዋጋው 2 ሚሊየን 703 ሺህ 635 ብር የሆነ ንብረት ለአክሲዮን ማህበሩ ገቢ ማድረግ ሲገባው የተጣለበትን እምነት ወደ ጎን በመተው ለግል ጥቅሙ ያዋለ መሆኑ ተጠቅሶ ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ነበር።

ተከሳሹ በጅግጅጋ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ክሱ የደረሰውና በንባብ እንዲሰማ ከተደረገ በኋላ በክሱ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል፡፡

ከሳሽ ዐቃቤ ህግ ወንጀሉን ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮች ዝርዝር ጠቅሶና አቅርቦ የምስክር ጭብጥ በማስመዝገብ የምስክርነት ቃላቸውን በችሎት አሰምቷል፡፡

ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግ ማስረጃን መርምሮ የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን ማረጋገጡን ጠቅሶ ተከሳሹ በተከሰሰበት ድንጋጌ ስር እንዲከላከል በሰጠው ብይን መሰረት ተከሳሹ የመከላከያ ማስረጃ አቅርቧል።

ተዘዋዋሪ ችሎቱ ተከሳሹ ያቀረበውን የመከላከያ ማስረጃን ከዐቃቤ ህግ ማስረጃ ጋር አመዛዝኖና መርምሮ ተከሳሹ የዐቃቤ ህግ ማስረጃን መከላከል አለመቻሉን ጠቅሶ የጥፋተኝነት ፍርድ ማስተላለፉን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት በመመርመርና የተከሳሹን የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶችን በመያዝ ተከሳሹን በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራትና በ1 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ በዛሬው የችሎት ቀጠሮ ውሳኔ ሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ከደረሰኝ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ የ10 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበሉ 3 የቁጥጥር ባለሙያዎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገለፀ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የንፋስ ስልክ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት 3 የደረሰኝ ቁጥጥር ባለሙያዎች ከደረሰኝ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ የ10 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበሉ በፖሊስ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተጠቁሟል፡፡

የፅኅፈት ቤቱ የህግ ማስከበር ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ይታይሽ ቢረሳው ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት የቁጥጥር ባለሙያዎቹ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ የቻሉት የአዲስ አበባ ቁጥር 2 የገቢዎች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ግብር ከፋይ የሆነ ግለሰብ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ ነው።

ተጠርጣሪዎቹ ድርጊቱን የፈፀሙት አርብ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፔፕሲ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ጉልደን የታሸጉ ውሃዎች አምራችና አከፋፋይ ድርጅት ላይ ነው፡፡

ጥቆማው የደረሰው የክፍለ ከተማው ፖሊስ የኢንቨስትጌሽን ስራ በማከናወን ከውሃ አምራችና አከፋፋይ ድርጅቱ ባለቤት ከሆኑ ግለሰብ ጥቆማው እንደደረሰው ወዲያውኑ ባካሄደው የኦፕሬሽን ስራ ተጠርጣሪዎቹ የ10 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻሉንም ተናግረዋል።

እንደ ምክትል ስራ አስኪያጇ ገለፃም ተጠርጣሪዎቹ የቁጥጥር ባለሙያዎቹ ከአንድ ሳምንት በፊት ከዚሁ ድርጅት የሽያጭ ባለሙያ ከደረሰኝ ቁጥጥር ጋር የ20 ሺህ ብር ጉቦ መቀበላቸው በመረጃ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪዎቹ በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የህግ ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጇ ተናግረዋል፡፡

አክለውም ወንጀሉን ለፖሊስ በማጋለጥ በሌብነት ድርጊት ውስጥ የገቡ የቁጥጥር ባለሙያዎች ጉዳያቸው በህግ እንዲታይና በገቢ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በኩል አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ላደረጉ የጎልደን የታሸጉ ውሃ አምራችና አከፋፋይ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ባለቤት ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የቁጥጥር ባለሙያዎችና ሌሎች በገቡት ቃል መሰረት ተግባሮቻቸውን ከሌብነትና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ሊፈፅሙ እንደሚገባ በመጠቆም በአሁኑ ወቅት በሌብነት ድርጊት ተጠርጥረው በህግ ጥላ ስር የሚገኙ የቅንጫፍ ፅ/ቤቱ የቁጥጥር ባለሙያዎችም ሌሎች አስተማሪ የሆነ እርምጃ ይወሳደል የሚል እምነት እንዳላቸው መናገራቸውን ከገቢዎች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ለጥቂት ግለሰቦች የብዙሃን ሀብት እንዲመዘበር በር የከፈተላቸው ዋነኛ ምክኒያት የመንግስት ሃላፊዎችን ስልጣን በመሳሪያነት በመጠቀማቸው ነው - አቶ ሞቱማ መቃሳ

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለውሃ እና ኢነርጂ ዘርፍ አመራሮች "ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ዘርፍ ተኮር የሥነ-ምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠና መድረኩ ላይ የተገኙት በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ የውሃ እና ኢነርጂ ዘርፍ በርካታ ለሙስና ተጋላጭ መሆኑን ገልፀው፥ ከችግሩ በመጠበቅ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ማሳደግና የኢነርጂ አቅርቦትን ማስፋፋት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በሀገራችን ለጥቂት ግለሰቦች የብዙሃን ሀብት እንዲመዘበር በር የከፈተላቸው ዋነኛ ምክኒያት ህጋዊ ስልጣን የተሰጣቸውን የመንግስት ሃላፊዎችን በመሣሪያነት በመጠቀም ነው ብለዋል።

የመንግስት ባለስልጣናት ሙስና ከሚፈፅሙ ግለሰቦች ጋር ተጣምረው የጥቅም ተቋዳሽ በመሆናቸው የሙስና ወንጀልንና ብልሹ አሰራርን መታገልና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ባለመቻሉ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ሞቱማ አክለውም ይህን የሙስና እና ብልሹ አሰራር ችግር ስር ሰዶ ወደ ተተኪ ትውልድ እንዳይዛመት በተቋማት የኋላፊነት ቦታ ላይ ያለን አመራሮች ከዚህ ፀያፍ ተግባር በመቆጠብ መንግስት እና ህዝብ የጣለብንን አደራ በታማኝነትና በሃቀኝነት በመወጣት ከህሊና ዕዳ ነፃ መሆን ይኖርብናል ብለዋል።

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፈቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው ዘርፉ እንደ ህዳሴ ግድብ ትልልቅ ፕሮጀክቶች የሚመመራበት መሆኑን ገልፀው፥ የሙስና እና ብልሹ አሰራር መንስኤ ከአስተሳሰብ ብልሹነት የመነጨ በመሆኑ ተቋማት በሥነምግባር አርዓያ የሆነ አመራርና ሠራተኛ ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል።

የህዳሴ ግድብ የህዝብ ፕሮጀክት እንደመሆኑ ሀገሪቱ ብዙ የምትጠቀምበት ነው፤ ሆኖም ግን ከለውጡ በፊት ሲታይ የነበረው የሙስና እና ብልሹ አሰራር ብዙ ዋጋ፣ ጊዜ እና አቅም ያስከፈለ መሆኑ እንደማይዘነጋ ጠቅሰው፤ እንደነዚህ አይነት ችግሮች እንዳይከሰቱ ተቋማት ከፍተኛ ሚኖ አለባቸው ብለዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም ለብልሹ አሰራር መነሻም፣ ተጎጂም እራሳቸው ተቋማት መሆናቸውን ገልፀው፣ የአመራሩ ጥንካሬ እና ድክመት ተቋምን የሚያሣይ በመሆኑ ቁርጠኛ አመራር ሊኖር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ስልጠናው ለውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እየተሰጠ ሲሆን፣ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ለሁለት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ከፍትሕ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት የፀረ-ሙስና ትግሉን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሙስናን ለመከላከል እና ተጠያቂነትን ለማስፈን ከፍትሕ ቢሮ እና ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር ቅንጅታዊ አሠራርን ለማጠናከር ውይይት አድርጓል። የመግባቢያ ሠነድም ተፈራርሟል።

በውይይቱ የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ብርሃኑ ጎሽም፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስየ ደጀን፣ የክልሉ ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕ እና አሥተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ ደሴ ጥላሁን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በውይይቱ መልዕክት ያስተላለፉት በአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕ እና አሥተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ ደሴ ጥላሁን (ዶ/ር) የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከተሰጡት ተግባራት ውስጥ አንዱ ሙስናን መከላከል መኾኑን ጠቅሰዋል።

በዚህ ተልዕኮም ትውልድን በመልካም ሥነምግባር ማነጽ እና ዜጎች ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

የሥነምግባር እና የፀረሙስና ኮሚሽን፣ ፍትሕ እና ፖሊስ ተቋማት ተቀናጅተው በመሥራት ተልዕኳቸውን ዳር ለማድረስ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይቱ ትኩረት ማድረጉን ገልጸው፣ ችግሮችን ገምግሞ በማረም ለመሥራትም እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በምዝገባ እና መረጃ አያያዝ ውስጥ የሚያገኛቸውን መረጃዎች የሚቀበል እና የፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ አጣርቶ ለሕግ በማቅረብ በኩል እየገጠሙ ያሉ ችግሮችን በመወያየት መፍትሔ ማበጀት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ወደፊትም ከሌሎች የፍትሕ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት የፀረ-ሙስና ትግሉ መጠናከር አለበት ብለዋል። የሙስና ተግባራትን የሕግ ተጠያቂነት ከፍ ለማድረግ መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴም የፀረ-ሙስና ትግሉ ውጤታማ እንዲኾን እየተከታተለ እንደሚደግፍ ገልጸዋል።

የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሐብታሙ ሞገስ ኮሚሽኑ በሕግ በተሰጡት ሥልጣን እና ተግባራት መሠረት የሥነምግባር ግንባታ፣ የሙስና መከላከል እና የሃብት ምዝገባ እና ማጣራት ተግባራትን እንደሚያከናውን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታትም እነዚህን ተግባራት ሲፈጽም መቆየቱን ጠቅሰዋል።

ሙሰና በሀገር ምጣኔ ሃብት፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ሥርዓት ላይ ችግር እያስከተለ መኾኑንም አስገንዝበዋል። ባለፉት ዓመታት በርካታ የሙስና ወንጀሎች ተፈጽመዋል ብለዋል።

ወንጀሎቹን በመመርመር እና በማጣራት ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ የውይይቱ ተሳታፊዎች ትልቅ ሚና አላቸው ነው ያሉት።

በተያዘው በጀት ዓመትም የተቋማት ነጻነት እንደተጠበቀ ኾኖ ከፖሊስ እና ከፍትሕ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት በሚቻልበት ኹኔታ ላይ ለመወያየት መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በውይይቱ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሙስናን ለመታገል እና ሙሰኞችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የሠራቸውን ሥራዎች እና ያጋጠሙትን ችግሮች ለውይይት አቅርቧል።

ፖሊስ ኮሚሽንም ሙስናንን ለመከላከል በትኩረት እየሠራ መኾኑ ተመላክቷል። የተሠሩ የምርመራ መዝገቦች እና ከምዝበራ የዳነ ሃብት መኖሩም ተገልጿል።

በፍትሕ ቢሮ በኩል በቀረበ የመወያያ ሃሳብም በፀረ-ሙስና ትግሉ የተሠሩ ሥራዎች፣ በቀጣይ በቅንጅት ሊሠሩ እና ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ተመላክተዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ባለፉት 5 ወራት በሀሰተኛ የተጭበረበረ ደረሰኝ መንግስት ሊያጣ የነበረውን ከ345 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን ተችሏል - የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በ2017 በጀት ዓመት 5 ወራት በሀሰተኛ ደረሰኝ ግብይት ተጭበርብሮ ያለ አግባብ ሊቀር የነበረ ከ345 ሚሊዮን ብር በላይ በማዳን የመንግስትን ጥቅም ማስጠበቅ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ እንደገለፁት፣ ሀሰተኛ ደረሰኝ እንዲጣራ ከቀረቡት አጠቃላይ 16 ሺ 425 ደረሰኞች 2 ሺ 654 ሀሰተኛ ሆነው ተገኝተዋል።

ሀሰተኛ ደረሰኞቹ የያዙት 345 ሚሊየን 526 ሺህ 600 ብር በመሆኑ ይህንን ማዳን መቻሉን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ በዚህም ወጪና ያልተገባ ታክስ ያለ አግባብ እንዳይወራረድ መደረጉ ተገልጿል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319