ለልማት በሚል ገንዘብ ሰብስበው ለግል ጥቅም ያዋሉ በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ
************************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሸገር ከተማ አስተዳደር ለልማት በሚል ከማህበረሰቡ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ ለግል ጥቅም በማዋል የተከሰሱ በጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ወሰነ።
የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ የሸገር ከተማ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ዐቃቤ ሕግ 1ኛ በሸገር ከተማ በሱሉልታ ክፍለ ከተማ የወሰርቢ ወረዳ አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሲፈሌቴ ከበደ፣ 2ኛ የወረዳው የፋይናን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አሸብር ኦልጅራ፣ 3ኛ የማዘጋጃ ቤት ኃላፊ ጉታ ኤጀሬ እና የወረዳው የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ገመቹ ማሞ የተባሉ አመራሮች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ጠቅሶ ክስ አቅርቦባቸው ነበር።
በዚህ ባቀረበው ክስ ዝርዝር ላይ እንደተመላከተው ተከሳሾቹ ከሸገር ከተማ አስተዳደርም ሆነ ከክፍለ ከተማው ፍቃድ ሳይሰጣቸው በ2016 ዓ.ም በሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወሰርቢ ወረዳ ከተለያዩ ባለሃብቶች እና ከሌሎች የማህበረሰቡ ክፍል ለልማት በሚል በህገ ወጥ መንገድ በራሳቸው ስም በከፈቱት የባንክ ሂሳብ 3 ሚሊየን 80 ሺህ ብር ሰብስበው ገንዘቡን ከባንክ አውጥተው ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን ጠቅሶ ዝርዝር ክስ አቅርባባቸው ነበር፡፡
በዚህ መልኩ የቀረበባቸው ክስ ዝርዝርን 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸውና ክሱን በንባብ እንዲሰሙ ተደርጎ የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው የዕምነት ክህደት ቃል በመስጠታቸው ዐቃቤ ሕግ የሰው ምስክር ቃልና የሰነድ ማስረጃን አቅርቧል፡፡
ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር እንዲከላከሉ በሰጠው ብይን የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል ባለመቻላቸው ባሳለፍነው ሳምንት የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል።
ቀደም ሲል ሸሽታ ሳትያዝ የቀረችው የወረዳው አስተዳዳሪ ነበረች የተባለችው ሲፈሌቴ ከበደ በቁጥጥር ስር ውላ ችሎት ቀርባ የነበረ ሲሆን÷ ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ ለጊዜው በቁጥጥር ስር እስክትውል በፍርድ ቤቱ የተቋረጠው የተከሳሿ ጉዳይ ተነጥሎ እንዲቀጥል በችሎት ጠይቆተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።
ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ፍርድ ያስተላለፈባቸውን 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ያቀረቡትን የቅጣት አስተያየት በመያዝ እያንዳንዳቸውን በ5 ዓመት ከ6 ወራት ጽኑ እስራትና በ5 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ውጤታማ የሙስና መከላከል ተግባራትን ለመስራት ቴክኖሎጂን በግብዓትነት መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
************************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ ለዘርፉ ቅርብ ለሆኑ ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ወዲሻ እንደገለፁት ኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ መረጃዎች ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ፣ ወጭንና ጊዜን ሊቆጥብ በሚችል መልኩ መያዝ የሚያስችለውን የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ከክልሉ ሳይስና ቴክኖሎጅ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ሲያስለማ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
ይህም ውጤታማ የሙስና መከላከል ተግባራትን በመስራት ረገድ የሀብት ምዝገባ መረጃዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ቀልጣፋ አሰራር ለመዘርጋት እንደሚያስችል ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ ለዘርፉ ቅርብ ለሆኑ ባለሙያዎች በክልሉ የሳይንስና ቴክኖሎጅ ኤጀንሲ የሶፍትዌር ባለሙያ በአቶ ቢኒያም ተፈራ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የፍርድ ውሳኔን በመሻር ታራሚ እንዲፈታ ትዕዛዝ የሰጡ ዳኞች በእስራት ተቀጡ
****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔን በመሻር ከስልጣናቸው ውጪ ታራሚ እንዲፈታ ትዕዛዝ የሰጡ ዳኞች በ1 ዓመት እስራት እንዲቀጡ የጋምቤላ ከተማ አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት ወንጀል ችሎት ወሰነ።
ተከሳሾቹ 1ኛ የአኘዋሃ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዳንትና ዳኛ አቡላ ሚዶ፣ 2ኛ ተከሳሽ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ዳኛ አገቱ ኤጋላ፣ 3ኛ ተከሳሽ የዞኑ ማረሚያ ቤት የደህንነትና መሠረታዊ ፍላጎት ምክትል አዛዥ ኢንስፔክተር ኡስማን አቶዋሉ ናቸው።
የጋምቤላ ክልል ፍትህ ቢሮ ዐቃቤ ሕግ በአንደኛው ክስ ዝርዝር ላይ በ1ኛ እና በ2ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር (1) ሀ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፋቸውን ጠቅሶ በስልጣን ያለአግባብ መገልገል የሚል ሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።
በዚህ በቀረበ ክስ ላይ እንደተመላከተው 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች የአኝዋሃ ብሔረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት አበኪዬው ኡጃሃ የተባለ ግለሰብ በተከሰሰበት አደንዛዥ ዕፅ ማዘዋወር ወንጀል በጋምቤላ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ፈጣን ችሎት የተጣለበትን የ7 ዓመት ፅኑ እስራት ተከሳሹ አግባብ አለመሆኑን ጠቅሶ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ለሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ የጠየቀ መሆኑ በክስ ዝርዝር ላይ ተጠቅሷል።
ይግባኙን የተመለከተው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ሆነ የሰበር ሰሚ ችሎት እስራቱ ተሻሽሎ ከ7 ዓመት ወደ 5 ዓመት በማውረድ በእስራት እንዲቀጣ በመወሰን እና እስራቱን ከጋምቤላ ከተማ ማረሚያ ቤት ወደ አኝዋሃ ዞን ማረሚያ ቤት ተዛውሮ እንዲፈፅም ይፈቀድለታል።
ከዚህ በኋላ ታራሚው "በጋምቤላ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ሆነ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የተወሰነብኝ ቅጣት የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኔን ግምት ውስጥ ያላስገባ ስለሆነ እንደገና እንዲታይልኝ " በሚል በነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ለአኝዋሃ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጽፎ ያቀረበውን የማመልከቻ አቤቱታ በመቀበል ከስልጣናቸው ውጪ በመዝገብ ቁጥር 04065 አቤቱታው በቀረበበት በዛው ዕለት በዋለው ችሎት ተከሳሾቹ የጠቅላይ ፍርድ ቤትንም ሆነ የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔን በመሻር ታራሚው የተወሰነበትን ገንዘብ ለመንግስት የከፈለ ስለሆነ ከእስር እንዲፈታ የሚል ውሳኔ በመወሰን ትዕዛዝ በመስጠት ታራሚው ከማረሚያ እንዲፈታ ማድረጋቸው ተጠቅሶ የጠቅላይ ፍ/ቤትን የመጨረሻ ውሳኔ የመሻርም ሆነ ጉዳዩን እንደገና የማየት ስልጣን ሳይኖራቸው የፈፀሙት ተግባር በመሆኑ በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
ሁለተኛው ክስ ደግሞ በ3ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ የቀረበ ሲሆን ይኸውም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 10 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ 3ኛ ተከሳሽ የአኝዋሃ ዞን ማረሚያ ቤት ም/አዛዥ ሆኖ በሚሰራበት ወቅት በ1ኛ ክስ ላን የተጠቀሰውን ክስ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ከታራሚው ባለቤት የተላከ ገንዘብ ብር 60 ሺህ ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አበቦ ቅርንጫፍ በስሙ በተከፈተ ሂሳብ ወጪ በማድረግ ለ2ኛ ተከሳሽ መስጠቱ ተጠቅሶ ጉቦ ማቀበል ሙስና ወንጀል ተከሷል፡፡
ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ ከክስ ዝርዝሩ ጋር የሰውና የሰነድ የማስረጃ ዝርዝር አያይዞ በማቅረቡ ተከሳሾቹ የቀረበባቸው ክስ ከደረሳቸው በኋላ የወንጀል ድርጊቱን መፈጸማቸው አምነው ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።
ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት መርምሮና ተከሳሾቹ አምነው ቃላቸውን መስጠታቸውን ከግምት በማስገባትና ያቀረቡትን የቅጣት አስተያየት በመያዝ እያንዳንዳቸውን በአንድ ዓመት እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

የፓርቲያችንና የመንግስት ቅቡልነትን ለማረጋገጥ ሙስና እና ብልሹ አሠራርን አምርሮ መታገል ያስፈልጋል - አቶ ዳዊት ገበየሁ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ከክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ ከዞን የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎች እንዲሁም ከ6 ቱም ማዕከላት የመሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢዎች ጋር ሙስናን በጋራ ለመከላከል የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ገበየሁ ክልሉ የሰላም፣ የልማትና የብልጽግና ተምሳሌት እንዲሆን ሙስናን መከላከል ይገባል ብለዋል።
የፓርቲያችንና የመንግስት ቅቡልነትን ለማረጋገጥ ሙስና እና ብልሹ አሠራርን አምርሮ መታገል ያስፈልጋል ያሉት ኃላፊው፥ በፓርቲ ደረጃ በሥነምግባር የታነፀ፣ ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የፀዳ አባል የአባልነት መመልመያ መስፈርት ሆኖ መምጣቱን ጠቅሰዋል።
ከፓርቲ አንፃር 2017 በጀት ዓመት በርካታ ተግባራት የሚከናወኑበት ዓመት በመሆኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ከህዋስ ጀምሮ ባሉ አደረጃጀቶች የመታገያ አጀንዳ በማድረግ ሰፊዉን የፓርቲ አባል ማነቃነቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በአርባምንጭ ከተማ በተካሄደው መድረክ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች፣ የዞን የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎች፣ የመሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢዎች፣ የኮሚሽኑ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የሞባይል ቀፎዎችንና ካርዶችን ለግል ጥቅሙ አውሏል የተባለው ሠራተኛ በእስራት ተቀጣ
****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የሞባይል ቀፎዎችንና ካርዶችን ለግል ጥቅም አውሏል የተባለው የቀድሞ የህዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር ሰራተኛ በእስራት መቀጣቱ ተነግሯል፡፡
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የድሬዳዋ ምድብ ጅግጅጋ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ቀጠሮ መስፍን ኣሰፋ በተባለ ተከሳሽ ላይ የግራ ቀኝ ማስረጃዎች መርምሮ ጥፋተኛ በማለት የጽኑ እስራትና የገንዘብ መቀጮ ውሳኔ አስተላልፎበታል።
በፍትህ ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅርጫፍ ጽህፍት ቤት ዐቃቤ ህግ በተከሳሹ ላይ በ1996 ዓ/ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 676 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፉን ጠቅሶ ሚያዚያ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ዝርዝር ክስ አቅርቦበት ነበር።
በዚህ በቀረበበት ክስ ዝርዝር ላይ እንደተመላከተው ተከሳሽ ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የህዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የምስራቅ ዲስትሪክት በጎዴ አካባቢያዊ ጽህፈት ቤት ሱፐርቫይዘር ሆኖ በሚያገለግልበት ወቅት ከጳጉሜን 3 ቀን 2003 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ድረስ ከአክሲዮን ማህበሩ የተረከባቸውን የተለያዩ ዋጋ ያላቸው የሞባይል ካርዶችን፣ ሲም ካርዶች እና የሞባይል ቀፎዎች ጠቅላላ ዋጋው 2 ሚሊየን 703 ሺህ 635 ብር የሆነ ንብረት ለአክሲዮን ማህበሩ ገቢ ማድረግ ሲገባው የተጣለበትን እምነት ወደ ጎን በመተው ለግል ጥቅሙ ያዋለ መሆኑ ተጠቅሶ ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ነበር።
ተከሳሹ በጅግጅጋ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ክሱ የደረሰውና በንባብ እንዲሰማ ከተደረገ በኋላ በክሱ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል፡፡
ከሳሽ ዐቃቤ ህግ ወንጀሉን ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮች ዝርዝር ጠቅሶና አቅርቦ የምስክር ጭብጥ በማስመዝገብ የምስክርነት ቃላቸውን በችሎት አሰምቷል፡፡
ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግ ማስረጃን መርምሮ የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን ማረጋገጡን ጠቅሶ ተከሳሹ በተከሰሰበት ድንጋጌ ስር እንዲከላከል በሰጠው ብይን መሰረት ተከሳሹ የመከላከያ ማስረጃ አቅርቧል።
ተዘዋዋሪ ችሎቱ ተከሳሹ ያቀረበውን የመከላከያ ማስረጃን ከዐቃቤ ህግ ማስረጃ ጋር አመዛዝኖና መርምሮ ተከሳሹ የዐቃቤ ህግ ማስረጃን መከላከል አለመቻሉን ጠቅሶ የጥፋተኝነት ፍርድ ማስተላለፉን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት በመመርመርና የተከሳሹን የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶችን በመያዝ ተከሳሹን በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራትና በ1 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ በዛሬው የችሎት ቀጠሮ ውሳኔ ሰጥቷል።

ከደረሰኝ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ የ10 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበሉ 3 የቁጥጥር ባለሙያዎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገለፀ
****************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የንፋስ ስልክ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት 3 የደረሰኝ ቁጥጥር ባለሙያዎች ከደረሰኝ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ የ10 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበሉ በፖሊስ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተጠቁሟል፡፡
የፅኅፈት ቤቱ የህግ ማስከበር ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ይታይሽ ቢረሳው ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት የቁጥጥር ባለሙያዎቹ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ የቻሉት የአዲስ አበባ ቁጥር 2 የገቢዎች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ግብር ከፋይ የሆነ ግለሰብ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ ድርጊቱን የፈፀሙት አርብ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፔፕሲ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ጉልደን የታሸጉ ውሃዎች አምራችና አከፋፋይ ድርጅት ላይ ነው፡፡
ጥቆማው የደረሰው የክፍለ ከተማው ፖሊስ የኢንቨስትጌሽን ስራ በማከናወን ከውሃ አምራችና አከፋፋይ ድርጅቱ ባለቤት ከሆኑ ግለሰብ ጥቆማው እንደደረሰው ወዲያውኑ ባካሄደው የኦፕሬሽን ስራ ተጠርጣሪዎቹ የ10 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻሉንም ተናግረዋል።
እንደ ምክትል ስራ አስኪያጇ ገለፃም ተጠርጣሪዎቹ የቁጥጥር ባለሙያዎቹ ከአንድ ሳምንት በፊት ከዚሁ ድርጅት የሽያጭ ባለሙያ ከደረሰኝ ቁጥጥር ጋር የ20 ሺህ ብር ጉቦ መቀበላቸው በመረጃ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪዎቹ በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የህግ ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጇ ተናግረዋል፡፡
አክለውም ወንጀሉን ለፖሊስ በማጋለጥ በሌብነት ድርጊት ውስጥ የገቡ የቁጥጥር ባለሙያዎች ጉዳያቸው በህግ እንዲታይና በገቢ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በኩል አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ላደረጉ የጎልደን የታሸጉ ውሃ አምራችና አከፋፋይ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ባለቤት ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የቁጥጥር ባለሙያዎችና ሌሎች በገቡት ቃል መሰረት ተግባሮቻቸውን ከሌብነትና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ሊፈፅሙ እንደሚገባ በመጠቆም በአሁኑ ወቅት በሌብነት ድርጊት ተጠርጥረው በህግ ጥላ ስር የሚገኙ የቅንጫፍ ፅ/ቤቱ የቁጥጥር ባለሙያዎችም ሌሎች አስተማሪ የሆነ እርምጃ ይወሳደል የሚል እምነት እንዳላቸው መናገራቸውን ከገቢዎች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡