Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.91K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የተጀመሩ ልማቶቻችንን በማሳለጥ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን የመታገል ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የተጀመሩ ልማቶችን በማሳለጥ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን የመታገል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ፣ የከተሞች የልማት ፍላጎት ከህዝብ የሚመነጭ መሆኑን የገለፀ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማም እየለሙ ያሉ አካባቢዎች ልማትም ህዝቡ በባለቤትነት ልማቱን ተቀብሎ ከአስተዳደሩ ጎን በመሰለፉ በባለቤትነት በመያዙና በመሳተፍ የከተማዋን ታሪክ የለወጡ ሥራዎች መተግበር ችለዋል ብሏል።

"ይሁን እንጅ ከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን ፈተናዎች ባሏት ፀጋዎቿ በማሻገር ሁለንተናዊ ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ በሚጥርበት በዚህ ወቅት የኮሪደር ልማትን መነሻ በማድረግ የግል ፍላጎታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚሯሯጡ አልጠፉም" ሲል ገልጿል፡፡

ከልማት የፍርስራሽ ግምት ለግል ጥቅማቸው ሊያውሉ የሞከሩ አመራሮችንም አስተዳደሩ በዘረጋው የህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ በከተማው የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 በካዛንችስ የኮሪደር ልማት ላይ ባልተገባ አካሄድና መንግስትና ህዝብ የጣለባቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከኮሪደር ልማት ፍርስራሽ ላይ ለግል ጥቅማቸው ሊያውሉ የነበሩ የወረዳ አመራሮችን በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር በማዋል አስተዳደሩ ሌብነትና ብልሹ አሰራር የልማት ዕንቅፋት እንዳይሆን ተገቢውን እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

ከዚህ አንፃር በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ራሄል ኃ/ኢየሱስ ጨምሮ የወረዳው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደበበ ጉልማ፣ የወረዳው የፋይናስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ ግዛቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ የኮሪደር ልማትን መነሻ አድርገው የፍርስራሽ ግምት ለግል ጥቅም ለማዋል በመሞከር ላይ እያሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከከተማ እስከ ክ/ከተማ የፀጥታ መዋቅሩን በመጠቀምና ክትትል በማድረግ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

በዚህም መሠረት የወንጀል ማጣራት ሂደቱ በሚመለከተው አካል እየተካሄደ ይገኛል ተብሏል። ህብረተሰቡ አሁንም ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በማረም እና ጥቆማ በመስጠት የሚያደርገውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳስቧል።

በቀጣይም የተጀመሩ ልማቶችን በማሳለጥ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን አጥብቆ ለመታገል የሚያደረገውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከተማ አስተዳደሩ ማረጋገጡን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሙስና የብልጽግና ፓርቲ ቀይ መስመር በመሆኑ ከፓርቲው ጋር ቅንጅታዊ አሠራር በመዘርጋት ችግሩን መከላከል እንደሚገባ ተገለፀ

***********************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ከክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ሙስናን ለመከላከል የሚያስችል የምክክር መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሶፎንያስ ደስታ ኮሚሽኑ ሙስናን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

በሥነምግባር የታነፁ ዜጎችን ማፍራት በተለይ ህፃናት ላይ መስራት፣ አስቸኳይ የመከላከል ስራ በመስራት የህግ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ የኮሚሽኑ ቀዳሚ ተግባራት መሆናቸውን ገልፀዋል።

በ2016 በጀት ዓመት ኮሚሽኑ ሙስናን በመከላከል ረገድ በሰራዉ ስራ 181 ሚሊዮን 305 ሺህ 174 ብር ማዳን እንደቻለ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ መልኩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ2017 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ በ6 ዞኖች በተደረገ ክትትል ከ327 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን እንደተቻለ ተገልጿል።

በክልሉ የከተማና ገጠር መሬት፣ ግዢና ጨረታ፣ ገቢ፣ ኮንስትራክሽን፣ ልማትና እርዳታ እና የንግድ ስርዓት ከፍተኛ ምዝበራ የሚስተዋልባቸዉ ዘርፎች መሆናቸው ተጠቁሟል።

ሙስና የብልጽግና ፓርቲ ቀይ መስመር በመሆኑ በፓርቲው አስተባባሪነት በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው የአደረጃጀት ዘርፍ አስተባባሪዎች፣ የመሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢዎች የበኩላቸውን ትግል እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች፣ የዞን የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎች፣ የመሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢዎች እና የኮሚሽኑ አመራሮች እየተሳተፉ መሆኑን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በሙስና እና በተደራጁ ወንጀሎች ምክንያት ከዓለምዓቀፉ ማህበረሰብ ሰፊ ሀብት እየተመዘበረ መሆኑ ተጠቆመ

************************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ኢትዮጵያ "በወንጀል የተገኘ ሃብት ማስመለስን ቀጣይነት ላለው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያ ልማት መሳካት" በሚል ርዕስ ከሀምሳ ሀገራት የተውጣጡ እና ከተለያዩ ዓለምዓቀፍ ተቋማት የመጡ ተሳታፊዎችን ያካተተ ዓለምአቀፍ የባለሙያዎች የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሄዷል።

በመድረኩ የተገኙት የፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ በሙስና፣ በኢኮኖሚ እና በተደራጁ ወንጀሎች ምክንያት ከዓለምዓቀፉ ማህበረሰብ ሰፊ ሀብት እየተመዘበረ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከዚህ በፊት ይህን መሰል አደገኛ ወንጀል የሚሰሩ ወንጀለኞች የመዘበሩትን ሀብት ለማስመለስ ተገቢው ትብብር ሳይደረግ በመቅረቱ ወንጀለኞቹ እየተጠናከሩ መምጣታቸውና ወንጀል በመፈጸም ያገኙትን ሀብት ለሽብር ወንጀል መፈጸሚያ ሲያውሉት በመስተዋሉ ዓለምዓቀፉ ማህበረሰብ ተገቢ የሆነ ዓለምዓቀፋዊ ምላሽ ለመስጠት እንዲያስብ ያስቻሉ አጋጣሚዎች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው እንደገለጹት የኢትዮጵያ መንግስትም በወንጀል የተገኘ ሃብትን ለማስመለስ ቁርጠኛ መሆኑን የሚያረጋግጥ ህግ አዘጋጅቶ በሥራ ላይ ለማዋል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በውይይት ላይ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም የፍትህ ሚኒስቴር ተገቢውን ህግ ከማርቀቅ ባለፈ እራሱን የቻለ የሃብት ምርመራና ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጀነራል አቋቁሞ ወደስራ ከገባ በኋላ ጥሩ ሊባል የሚችል ውጤት ማሳየቱን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም የኢትዮጵያ መንግስት በወንጀል የተገኘ ሀብትን ለማስመለስ ከሌሎች ሀገራትና ዓለምዓቀፍ ተቋማት ጋር ተገቢውን የህግ ትብብር ስራ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመድረኩም ሀገራት በዓለም-ዓቀፍ የሀብት ማስመለስ ሂደት የሚያስመልሱትን ሀብት ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት መሳካት የሚያውሉበት ሁኔታዎች ላይ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።

ኢትዮጵያን በተመለከተ በወንጀል የተገኘ ሀብትን ከሀገር ውስጥም ሆነ ውጭ ሀገራት ለማስመለስ የሚያስችል ህግ በፍትህ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደቀረበ እና ህጉም መሰረታዊ የሚባል ለውጥን ሊያመጣ የሚችል ይዘት እንዳለው ተጠቅሶ ቀርቧል፡፡

ሕጉ ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን በተመለከተ ማንኛውም ሰው ተጠያቂ የሚሆንበትን አሰራር ይዞ መምጣቱ እንደጥሩ አቋም መወሰዱ ተጠቅሶ ከተሳታፊዎችም አስተያየት ተስጥቷል፡፡

በሌላ በኩል የፍትህ ሚኒስቴር የወንጀል ክስ በተለያየ ምክንያት ሲቋረጥ ሀብት በድርድር የሚመለስበትን ሁኔታ የሚገዛ አሰራር ቀርጾ ወደስራ ከገባ በኋላ በዚህ አሰራር ምክንያት የወንጀል ክስና ምርመራቸው በተለያየ ምክንያት ከተቋረጠ የህገወጥ የሀዋላ ዝውውር መዛግብት ብር 200,000,000.00 (ሁለት መቶ ሚሊዮን) ለማስመለስ ስምምነት ተደርጎ እስካሁን ብር 73,000,000.00 (ሰባ ሶስት ሚሊዮን) ያስመለሰ ስለመሆኑ እንዲሁም ለብሔራዊ ባንክ ገቢ መረግ ከነበረበት የውጭ ምንዛሪ ውስጥ እስካሁን USD 8,000,000.00 (ስምንት ሚሊዮን) የአሜሪካን ዶላር ለማስመለስ ስምምነት ተደርጎ USD 3,677,107.99 (ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሰባት) የአሜሪካን ዶላር የተመለሰ መሆኑ እንደተሞክሮ ቀርቧል፡፡

ውይይቱ ለሶስት ቀናት የተካሄደ ሲሆን፥ በወንጀል የተገኘ የሀብት ማስመለስ እና የሚመለሰውን ሐብት ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ውጤታማ በሆነ መልኩ ስለሚውልበት ሁኔታ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች በተለያዩ ሀገራት ባለሞያዎች ቀርቦ ውይይት መደረጉን ከፍትህ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ለልማት በሚል ገንዘብ ሰብስበው ለግል ጥቅም ያዋሉ በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ

************************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሸገር ከተማ አስተዳደር ለልማት በሚል ከማህበረሰቡ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ ለግል ጥቅም በማዋል የተከሰሱ በጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ወሰነ።

የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ የሸገር ከተማ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ዐቃቤ ሕግ 1ኛ በሸገር ከተማ በሱሉልታ ክፍለ ከተማ የወሰርቢ ወረዳ አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሲፈሌቴ ከበደ፣ 2ኛ የወረዳው የፋይናን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አሸብር ኦልጅራ፣ 3ኛ የማዘጋጃ ቤት ኃላፊ ጉታ ኤጀሬ እና የወረዳው የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ገመቹ ማሞ የተባሉ አመራሮች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ጠቅሶ ክስ አቅርቦባቸው ነበር።

በዚህ ባቀረበው ክስ ዝርዝር ላይ እንደተመላከተው ተከሳሾቹ ከሸገር ከተማ አስተዳደርም ሆነ ከክፍለ ከተማው ፍቃድ ሳይሰጣቸው በ2016 ዓ.ም በሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወሰርቢ ወረዳ ከተለያዩ ባለሃብቶች እና ከሌሎች የማህበረሰቡ ክፍል ለልማት በሚል በህገ ወጥ መንገድ በራሳቸው ስም በከፈቱት የባንክ ሂሳብ 3 ሚሊየን 80 ሺህ ብር ሰብስበው ገንዘቡን ከባንክ አውጥተው ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን ጠቅሶ ዝርዝር ክስ አቅርባባቸው ነበር፡፡

በዚህ መልኩ የቀረበባቸው ክስ ዝርዝርን 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸውና ክሱን በንባብ እንዲሰሙ ተደርጎ የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው የዕምነት ክህደት ቃል በመስጠታቸው ዐቃቤ ሕግ የሰው ምስክር ቃልና የሰነድ ማስረጃን አቅርቧል፡፡

ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር እንዲከላከሉ በሰጠው ብይን የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል ባለመቻላቸው ባሳለፍነው ሳምንት የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል።

ቀደም ሲል ሸሽታ ሳትያዝ የቀረችው የወረዳው አስተዳዳሪ ነበረች የተባለችው ሲፈሌቴ ከበደ በቁጥጥር ስር ውላ ችሎት ቀርባ የነበረ ሲሆን÷ ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ ለጊዜው በቁጥጥር ስር እስክትውል በፍርድ ቤቱ የተቋረጠው የተከሳሿ ጉዳይ ተነጥሎ እንዲቀጥል በችሎት ጠይቆተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ፍርድ ያስተላለፈባቸውን 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ያቀረቡትን የቅጣት አስተያየት በመያዝ እያንዳንዳቸውን በ5 ዓመት ከ6 ወራት ጽኑ እስራትና በ5 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ውጤታማ የሙስና መከላከል ተግባራትን ለመስራት ቴክኖሎጂን በግብዓትነት መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

************************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ ለዘርፉ ቅርብ ለሆኑ ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ወዲሻ እንደገለፁት ኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ መረጃዎች ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ፣ ወጭንና ጊዜን ሊቆጥብ በሚችል መልኩ መያዝ የሚያስችለውን የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ከክልሉ ሳይስና ቴክኖሎጅ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ሲያስለማ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

ይህም ውጤታማ የሙስና መከላከል ተግባራትን በመስራት ረገድ የሀብት ምዝገባ መረጃዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ቀልጣፋ አሰራር ለመዘርጋት እንደሚያስችል ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ ለዘርፉ ቅርብ ለሆኑ ባለሙያዎች በክልሉ የሳይንስና ቴክኖሎጅ ኤጀንሲ የሶፍትዌር ባለሙያ በአቶ ቢኒያም ተፈራ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319