Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ስልጠናው በሚኒስቴር መስሪያቤታችን ሥነምግባራዊነትን የተላበሰ አመራር እንዲኖር የሚያግዝ ነው - ሰልጣኞች

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም ቢሾፍቱ) ለመስኖና ቆላማ አካባቢ ዘርፍ አመራሮች "ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ዘርፍ ተኮር ሥልጠና ተጠናቋል።

በስልጠናው ማጠቃላያ ላይ ንግግር ያደረጉት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አብዱረህማን አብደላ ስልጠናው በዘርፉ የሙስና ተጋላጭነት ዳሰሳ ጥናት መነሻነት ትኩረት በማድረግ በምሁራን በተዘጋጁ የማሰልጠኛ ሞጅሎች መሰጠቱ የሚያበረታታና መቀጠል ያለበት ነው ብለዋል፡፡

የሚኒስቴር መስሪያቤታችን አመራርና ሠራተኛ በሥነምግባሩ አርዓያ በመሆን በፀረ-ሙስና ትግል ላይ በቁርጠኝነት መሳተፍ አለበት ብለዋል፡፡

የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር እንድርያስ ጌታ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሀገራችንን ፈጣን የለውጥ ጉዞ ከሚገቱ ችግሮች መካከል አንዱ ሙስና እና ብልሹ አሰራር መሆኑን ገልፀው፤ ስለሆነም ሁላችንም በስልጠናው ያገኘነውን እውቀት፣ ግንዛቤና አመለካከት ወደ ተግባር በማውረድ በቀጣይ የተግባር ሰው መሆን እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ሙስና እና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ጉዳይ በተቋማችን ያሉ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ብቻ ሳይሆን የሁላችንም መሆን አለበት ብለዋል፡፡

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፈቃዱ ሰቦቃ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ችግር የሥነምግባርና የሞራል ዝቅጠት መሆኑን ገልፀው፤ ሁላችንም አስተሳሰባችንና አመለካከታችን መቀየር አለብን ብለዋል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት ተከታታይነት ያላቸው የሥነምግባር ግንባታ ስልጠናዎችን መውሰድ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ስልጠናው በሚኒስቴር መስሪያቤታችን ሥነምግባራዊነትን የተላበሰ አመራር እንዲኖር የሚያግዝና ወቅታዊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ራሳችንን ወደ ውስጥ በማየትና በሥነምግባር አርዓያ በመሆን ሙስና እና ብልሹ አሰራረን ለመካላከል የሚያነሳሳ ስልጠና መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ስልጣኞች አክለውም ኮሚሽኑ በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንዳለበት ገልፀው፤ ከስልጠናው በዘለለም ሙሰኞችን አስተማሪ ቅጣት መቅጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የተጀመሩ ልማቶቻችንን በማሳለጥ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን የመታገል ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የተጀመሩ ልማቶችን በማሳለጥ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን የመታገል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ፣ የከተሞች የልማት ፍላጎት ከህዝብ የሚመነጭ መሆኑን የገለፀ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማም እየለሙ ያሉ አካባቢዎች ልማትም ህዝቡ በባለቤትነት ልማቱን ተቀብሎ ከአስተዳደሩ ጎን በመሰለፉ በባለቤትነት በመያዙና በመሳተፍ የከተማዋን ታሪክ የለወጡ ሥራዎች መተግበር ችለዋል ብሏል።

"ይሁን እንጅ ከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን ፈተናዎች ባሏት ፀጋዎቿ በማሻገር ሁለንተናዊ ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ በሚጥርበት በዚህ ወቅት የኮሪደር ልማትን መነሻ በማድረግ የግል ፍላጎታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚሯሯጡ አልጠፉም" ሲል ገልጿል፡፡

ከልማት የፍርስራሽ ግምት ለግል ጥቅማቸው ሊያውሉ የሞከሩ አመራሮችንም አስተዳደሩ በዘረጋው የህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ በከተማው የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 በካዛንችስ የኮሪደር ልማት ላይ ባልተገባ አካሄድና መንግስትና ህዝብ የጣለባቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከኮሪደር ልማት ፍርስራሽ ላይ ለግል ጥቅማቸው ሊያውሉ የነበሩ የወረዳ አመራሮችን በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር በማዋል አስተዳደሩ ሌብነትና ብልሹ አሰራር የልማት ዕንቅፋት እንዳይሆን ተገቢውን እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

ከዚህ አንፃር በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ራሄል ኃ/ኢየሱስ ጨምሮ የወረዳው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደበበ ጉልማ፣ የወረዳው የፋይናስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ ግዛቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ የኮሪደር ልማትን መነሻ አድርገው የፍርስራሽ ግምት ለግል ጥቅም ለማዋል በመሞከር ላይ እያሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከከተማ እስከ ክ/ከተማ የፀጥታ መዋቅሩን በመጠቀምና ክትትል በማድረግ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

በዚህም መሠረት የወንጀል ማጣራት ሂደቱ በሚመለከተው አካል እየተካሄደ ይገኛል ተብሏል። ህብረተሰቡ አሁንም ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በማረም እና ጥቆማ በመስጠት የሚያደርገውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳስቧል።

በቀጣይም የተጀመሩ ልማቶችን በማሳለጥ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን አጥብቆ ለመታገል የሚያደረገውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከተማ አስተዳደሩ ማረጋገጡን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሙስና የብልጽግና ፓርቲ ቀይ መስመር በመሆኑ ከፓርቲው ጋር ቅንጅታዊ አሠራር በመዘርጋት ችግሩን መከላከል እንደሚገባ ተገለፀ

***********************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ከክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ሙስናን ለመከላከል የሚያስችል የምክክር መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሶፎንያስ ደስታ ኮሚሽኑ ሙስናን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

በሥነምግባር የታነፁ ዜጎችን ማፍራት በተለይ ህፃናት ላይ መስራት፣ አስቸኳይ የመከላከል ስራ በመስራት የህግ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ የኮሚሽኑ ቀዳሚ ተግባራት መሆናቸውን ገልፀዋል።

በ2016 በጀት ዓመት ኮሚሽኑ ሙስናን በመከላከል ረገድ በሰራዉ ስራ 181 ሚሊዮን 305 ሺህ 174 ብር ማዳን እንደቻለ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ መልኩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ2017 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ በ6 ዞኖች በተደረገ ክትትል ከ327 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን እንደተቻለ ተገልጿል።

በክልሉ የከተማና ገጠር መሬት፣ ግዢና ጨረታ፣ ገቢ፣ ኮንስትራክሽን፣ ልማትና እርዳታ እና የንግድ ስርዓት ከፍተኛ ምዝበራ የሚስተዋልባቸዉ ዘርፎች መሆናቸው ተጠቁሟል።

ሙስና የብልጽግና ፓርቲ ቀይ መስመር በመሆኑ በፓርቲው አስተባባሪነት በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው የአደረጃጀት ዘርፍ አስተባባሪዎች፣ የመሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢዎች የበኩላቸውን ትግል እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች፣ የዞን የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎች፣ የመሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢዎች እና የኮሚሽኑ አመራሮች እየተሳተፉ መሆኑን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319