Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
በዘርፉ ያለውን ብልሹ አሰራር ለመከላከል የተጀመሩ የዲጂታል አሰራሮችን አጠናክረን እንቀጥላለን - አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ አመራሮች "ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ዘርፍ ተኮር የሥነ-ምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ላይ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዘርፉ ያለውን ብልሹ አሰራር ለመከላከል የተጀመሩ የዲጂታል አሰራሮችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም ማህበራዊ እሴት የሆኑትን የሃይማኖት እና ባህል አስተምሮት ሙስናን ለመከላከል ጉልህ ሚና ስላላቸው እሴቶች ማጉላት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ሙስና እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ተቋም መኖሩን ገልፀው፥ በዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሌብነት የማይመች አደረጃጀት የመፍጠር ኃላፊነት አለብን ብለዋል።

ሀገርን እና ህዝብን የሚጎዳ ተግባር የሚፈፅም አካል ሲኖርም ጠበቅ ያለ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ሙስናን አስቀድሞ ለመከላከል በሰዎች የባህሪ ለውጥ እና ግንዛቤ መፍጠር ስለሚያስፈልግ እንዲህ ያለ ስልጠና መሰጠቱ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የቀድሞ መስሪያ ቤቱን ስም በመጠቀም የማታለል ወንጀል ሲፈፅም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ነው

********

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሥነምግባር ጉደለት ከሚሰራበት ተቋም የተሰናበተው ግለሰብ የመስሪያ ቤቱን ስም በመጠቀም የተቋሙ ሰራተኛ መስሎ የማታለል ወንጀል ሲፈፅም በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ፖሊስ ገለፀ።

ከዚህ ቀደም የፌዴራል ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኛ የነበረው እና በሥነምግባር ጉደለት ከተቋሙ የተሰናበተው ተጠርጣሪ ታረቀኝ ክፍሌ ይባላል።

ግለሰቡ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ እንደሆነ በማስመሰል የተለያዩ ግለሰቦች ባሉባቸው የመንግሥት የኪራይ ቤቶች እየተዘዋወረ የቤቶቹ ታፔላ ወደ ዲጂታል እየተቀየረ ነው በማለት ሰዎችን ሲያታልል እንደነበር ተገልጿል።

ተጠርጣሪው ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም እና በተቋሙ ስም የተዘጋጁ ቅፆችን የያዘ በማስመሰል ታፔላውን ወደ ዲጂታል ማስቀየር አለባችሁ በማለት ከሁለት የግል ተበዳዮች ከእያንዳንዳቸው 1 ሺህ 700 ብር መቀበሉም ታውቋል።

ግለሰቡ በግል ተበዳዮች ጥቆማ ሰጭነት በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

የማታለል ወንጀሉ የተፈፀመው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጎጃም በረንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ የመንግሥት ኪራይ ቤቶች ውስጥ በሚሰሩ ነጋዴዎች ላይ መሆኑም ተገልጿል።

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ስልጠናው በሚኒስቴር መስሪያቤታችን ሥነምግባራዊነትን የተላበሰ አመራር እንዲኖር የሚያግዝ ነው - ሰልጣኞች

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም ቢሾፍቱ) ለመስኖና ቆላማ አካባቢ ዘርፍ አመራሮች "ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ዘርፍ ተኮር ሥልጠና ተጠናቋል።

በስልጠናው ማጠቃላያ ላይ ንግግር ያደረጉት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አብዱረህማን አብደላ ስልጠናው በዘርፉ የሙስና ተጋላጭነት ዳሰሳ ጥናት መነሻነት ትኩረት በማድረግ በምሁራን በተዘጋጁ የማሰልጠኛ ሞጅሎች መሰጠቱ የሚያበረታታና መቀጠል ያለበት ነው ብለዋል፡፡

የሚኒስቴር መስሪያቤታችን አመራርና ሠራተኛ በሥነምግባሩ አርዓያ በመሆን በፀረ-ሙስና ትግል ላይ በቁርጠኝነት መሳተፍ አለበት ብለዋል፡፡

የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር እንድርያስ ጌታ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሀገራችንን ፈጣን የለውጥ ጉዞ ከሚገቱ ችግሮች መካከል አንዱ ሙስና እና ብልሹ አሰራር መሆኑን ገልፀው፤ ስለሆነም ሁላችንም በስልጠናው ያገኘነውን እውቀት፣ ግንዛቤና አመለካከት ወደ ተግባር በማውረድ በቀጣይ የተግባር ሰው መሆን እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ሙስና እና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ጉዳይ በተቋማችን ያሉ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ብቻ ሳይሆን የሁላችንም መሆን አለበት ብለዋል፡፡

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፈቃዱ ሰቦቃ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ችግር የሥነምግባርና የሞራል ዝቅጠት መሆኑን ገልፀው፤ ሁላችንም አስተሳሰባችንና አመለካከታችን መቀየር አለብን ብለዋል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት ተከታታይነት ያላቸው የሥነምግባር ግንባታ ስልጠናዎችን መውሰድ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ስልጠናው በሚኒስቴር መስሪያቤታችን ሥነምግባራዊነትን የተላበሰ አመራር እንዲኖር የሚያግዝና ወቅታዊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ራሳችንን ወደ ውስጥ በማየትና በሥነምግባር አርዓያ በመሆን ሙስና እና ብልሹ አሰራረን ለመካላከል የሚያነሳሳ ስልጠና መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ስልጣኞች አክለውም ኮሚሽኑ በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንዳለበት ገልፀው፤ ከስልጠናው በዘለለም ሙሰኞችን አስተማሪ ቅጣት መቅጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319