Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
አመራሩ በመልካም ሥነምግባር አርዓያ በመሆንና ከብልሹ አሰራር በመራቅ የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣት አለበት - አብርሃም በላይ (ዶ/ር)

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም ቢሾፍቱ) ለመስኖና ቆላማ አካባቢ ዘርፍ አመራሮች "ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ዘርፍ ተኮር የሥነ-ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው መድረክ የተገኙት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚንስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) አመራሩ በመልካም ሥነምግባር አርዓያ በመሆንና ከብልሹ አሰራር በመራቅ የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣት አለበት ብለዋል።

ሚንስትሩ አክለውም ስልጠናው ከሥነምግባር እና ከሞራል አንፃር ራሳችን የምናይበት በመሆኑ በትኩረት መከታተል እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው ኮሚሽኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ሥራን የማስተባበር ሚናን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀው፥ በየዘርፉ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ችግሮችን የመከላከል ኃላፊነት የተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች መሆኑን ጠቁመዋል።

መንግስት ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ አመራሩ በፀረ-ሙስና ትግል ላይ በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት ገልፀዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ዘርፍ በርካታ ፕሮጀክቶችን የሚያንቀሳቅስ ግዙፍ ተቋም መሆኑን ገልፀው፥ ተቋሙ በብልሹ አሰራር እንዳይዘፈቅ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች የተሰጣችሁን ኃላፊነት መወጣት ይኖርባችኋል ብለዋል።

ስልጠናው የሙስና ምንነት፣ ባህሪያትና አይነቶች ላይ ያተኮረ ብቻ ሳይሆን በዘርፋ በተደረገ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ተጋላጭነት ዳሰሳ ጥናት መነሻነት ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተወጣጡ ምሁራን በተዘጋጀ የማሰልጠኛ ሞጁል የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል።

ስልጠናው ለመስኖና ቆላማ አካባቢ ዘርፍ አመራሮች እየተሰጠ ሲሆን፥ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የሀሰተኛ ማንነት ማስረጃ የሚያዘጋጅ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ሀሰተኛ ማስረጃ እያዘጋጀ ለተለያዩ ግለሰቦች ሲሰጥ የነበረ ግለሰብ በተሰጠ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረጉን አሳወቀ፡፡

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ወደ ኤጀንሲው ዋና መስርያ ቤት ሃሰተኛ መታወቂያ እና ያላገባ ማስረጃ በመያዝ አገልግሎት ለማግኘት የመጣች ተገልጋይ በሰጠችው ጥቆማ መሆኑን የኤጀንሲው የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አስናቀች ሙህዬ አስታውቀዋል፡፡

ከግለሰቧ በተሰጠ ጥቆማ መሰረት ሀሰተኛ ሰነድ በሚያዘጋጀው ግለሰብ በተሰራ ኦፕሬሽን በብር 20,000 መታወቂያና ልደት እንዲያዘጋጅ በመደራደር መረጃው የሚያዘጋጅላት ግለሰብ ፎቶና ሌሎች መረጃዎችን እንዲሁም የቀብድ ክፍያ 10,000 ብር በሚቀበልበት ወቅት ከለሚ ኩራ ፖሊስ መመሪያ ጋር በመተባበር ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኤጀንሲው ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሯ ገልፀዋል፡፡

ግለሰቡ በፖሊስ ዝርዝር ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በዘርፉ ያለውን ብልሹ አሰራር ለመከላከል የተጀመሩ የዲጂታል አሰራሮችን አጠናክረን እንቀጥላለን - አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ አመራሮች "ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ዘርፍ ተኮር የሥነ-ምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ላይ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዘርፉ ያለውን ብልሹ አሰራር ለመከላከል የተጀመሩ የዲጂታል አሰራሮችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም ማህበራዊ እሴት የሆኑትን የሃይማኖት እና ባህል አስተምሮት ሙስናን ለመከላከል ጉልህ ሚና ስላላቸው እሴቶች ማጉላት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ሙስና እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ተቋም መኖሩን ገልፀው፥ በዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሌብነት የማይመች አደረጃጀት የመፍጠር ኃላፊነት አለብን ብለዋል።

ሀገርን እና ህዝብን የሚጎዳ ተግባር የሚፈፅም አካል ሲኖርም ጠበቅ ያለ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ሙስናን አስቀድሞ ለመከላከል በሰዎች የባህሪ ለውጥ እና ግንዛቤ መፍጠር ስለሚያስፈልግ እንዲህ ያለ ስልጠና መሰጠቱ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የቀድሞ መስሪያ ቤቱን ስም በመጠቀም የማታለል ወንጀል ሲፈፅም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ነው

********

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሥነምግባር ጉደለት ከሚሰራበት ተቋም የተሰናበተው ግለሰብ የመስሪያ ቤቱን ስም በመጠቀም የተቋሙ ሰራተኛ መስሎ የማታለል ወንጀል ሲፈፅም በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ፖሊስ ገለፀ።

ከዚህ ቀደም የፌዴራል ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኛ የነበረው እና በሥነምግባር ጉደለት ከተቋሙ የተሰናበተው ተጠርጣሪ ታረቀኝ ክፍሌ ይባላል።

ግለሰቡ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ እንደሆነ በማስመሰል የተለያዩ ግለሰቦች ባሉባቸው የመንግሥት የኪራይ ቤቶች እየተዘዋወረ የቤቶቹ ታፔላ ወደ ዲጂታል እየተቀየረ ነው በማለት ሰዎችን ሲያታልል እንደነበር ተገልጿል።

ተጠርጣሪው ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም እና በተቋሙ ስም የተዘጋጁ ቅፆችን የያዘ በማስመሰል ታፔላውን ወደ ዲጂታል ማስቀየር አለባችሁ በማለት ከሁለት የግል ተበዳዮች ከእያንዳንዳቸው 1 ሺህ 700 ብር መቀበሉም ታውቋል።

ግለሰቡ በግል ተበዳዮች ጥቆማ ሰጭነት በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

የማታለል ወንጀሉ የተፈፀመው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጎጃም በረንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ የመንግሥት ኪራይ ቤቶች ውስጥ በሚሰሩ ነጋዴዎች ላይ መሆኑም ተገልጿል።

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319