ሀገር አቀፍ የዳኝነትና የፍትህ አካላት የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄ ይገኛል
*******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የጆይንድ አፕ ጀስቲስ ሴክረተሪያት ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ለሁለት ቀናት የሚቆየው የፌደራል እና የክልል የዳኝነት እና የፍትህ አካላት እንዲሁም የመንግስት ተቋማትን ያሳተፈ ሀገር አቀፍ የዳኝነትና የፍትህ አካላት የጋራ የምክክር መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ጸሀይ ዋረሳ እና የጋሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳደር ክብርት ወ/ሮ ልሳነወርቅ ካሳዬ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የምክክር መድረኩ በዋናነት በፍትህ አካላት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርና የጋራ ችግሮች ላይ መክሮ የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ በፍትህ አካላት መካከል የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር አላማውን አድርጎ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
መድረኩ በፍትህ አካላት ውስጥ የተበታተነና የማይናበብ ስርዓት የሚፈጥረውን ተግዳሮት ከግምት በማስገባት በአፈጻጸም እና በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ መናበብ እንዲኖር የሚያደርግ በመሆኑ አገራዊ ፋይዳው ከፍተኛ ነውም ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ አክለውም የዳኝነትና የፍትህ ዘርፉ አፈጻጻጸም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ እና በሌሎችም ዘርፎች የሚንጸባረቅ እንዲሁም ሀገራዊ ህልውና እና የዜጎች ዋስትና ላይ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ለህዝብ ጥያቄዎች በወቅቱና በአግባቡ ምላሽ ከመስጠት ባሻገር ስኬቶችን በማላቅና ጉድለቶችን በመሙላት፣ በየተቋማቱ ያሉ የማሻሻያ ስራዎችን በማጋራት እንዲሁም የተለያዩ ተሞክሮዎች ላይ ለመወያየት እድል በመፍጠር የፍትህ ስርዓቱ ውጤታማ እንዲሆን ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሬ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስተር ክብርት ወ/ሮ ሃና ዓርአያስላሴ በበኩላቸው የፍትህና የዳኝነት ተቋማት ተልዕኳቸውን ሲወጡ ህግን ባከበረ መልኩ መንቀሳቀስና የህግ የበላይነትን በማስከበር ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ገልጸው፥ እንዲህ አይነት የቅንጅት መድረክ ትርጉም ያለውና ጠንካራ የትብብር ማዕቀፍ በመፍጠር ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላማዊ እና የበለጸገ ማህበረሰብ ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
በመድረኩ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ) ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት እየተሳተፋ ሲሆን፥ ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ፍትህ ሚኒስቴር የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው እንደሚሆን ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

መንግስት በ2017 በጀት ዓመት በመልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ በሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች ላይ ትኩረት አደርጎ እየሰራ ይገኛል - ክቡር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)
*******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ዘርፍ አመራሮች "ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ዘርፍ ተኮር የሥነ- ምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
በስልጠናው መድረክ የተገኙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) መንግስት በ2017 በጀት ዓመት በመልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ በሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች ላይ ትኩረት አደርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
መንግስት በፌደራል የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጥናት ማድረጉን ጠቁመው፥ ከተቋማቱ መካከል የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ዘርፍ አንዱ ነው ብለዋል። በጥናቱም በትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ዘርፍ የብልሹ አሰራር አዝማሚያዎች መመላከቱን ተናግረዋል።
ሚኒሰትሩ አክለውም ለዘርፋ ይህን መሰል ስልጠና በየጊዜው በመስጠት የአመራሩንና የሠራተኛውን ብሎም የተገልጋዩን ባህሪ መቀየር ያስፈልጋል ብለዋል። እንዲሁም ሰዎችን የሚያግዝ የዲጂታል የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል።
በዘርፋ ውስጥ የሚፈፀም ብልሹ አሰራር የሰዎችን ህይወትን እንደሚቀጥፍ ጠቅሰው፥ ለአብነት የመንጃ ፍቃድ አሰጣጥ ተጠቃሽ መሆኑን አመላክተዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም በሙስና እና ብልሹ አሰራር ላይ ተዘፍቀው የሚገኙ ጥፋተኛ ግለሰቦችን ጠንከር ያለ ተጠያቂ የሚያደርግ ህግ እንደሚያስፈልግ ገልፀው፥ አንዳንድ አገሮች ሙሰኞችን በህይወት እስከመቅጣት ይደርሳሉ ብለዋል።
የፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፈቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው በዘርፋ የሚፈፀሙ የብልሹ አሰራር ችግሮች ከሰው ህይወት ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልፀው፥ ስለሆነም በሥነምግባር አርዓያ የሆነ አመራርና ሠራተኛ ያስፈልጋል ብለዋል።
በተለይ ከመንጃ ፍቃድ አሰጣጥና ከመኪና የቴክኒክ ምርመራ ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ብልሹ አሰራሮች የሠውን ህይወት እንደሚቀጥፍ ገልፀው፥ ችግሩን ለመፍታት በየጊዜው ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ስልጠናው ለትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እየተሰጠ ሲሆን፥ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።