ለውጭ ጉዳይ ዘርፍ አመራሮች "ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ዘርፍ ተኮር ስልጠና እየተሰጠ ነው
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለውጭ ጉዳይ ዘርፍ አመራሮች "ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ሃሳብ ዘርፍ ተኮር የሥነ-ምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ስልጠናው ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እየተሰጠ ሲሆን፥ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

በሙስና ወንጀል የተመዘበረ ከአራት መቶ ሰባት ሺህ በላይ ብር ከተጠርጣሪዎች ማስመለሱን የዳውሮ ዞን ፖሊስ አስታወቀ
*****
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ስድስት ተጠርጣሪዎች በዳዉሮ ዞን ገና ወረዳ ወልደሃነ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት የትምህርት ቤቱ ዋና ርዕሰ መምህር እና ሰራተኞች ሆነው በሚሰሩበት ጊዜ ከ2012 ዓ.ም እስከ 2016 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜያት 550,655.2 (አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ አምስት ብር ከሁለት ሳንቲም ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን የዳውሮ ዞን ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል፡፡
የዳውሮ ዞን ፖሊስ የሙስና ወንጀል ምርመራ ዲቪዥን በደረሰዉ ጥቆማ መሰረት አንደኛ ተጠርጣሪ እና ሌሎች ከ2ኛ እስከ 6ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች በትምህርት ቤቱ ቋሚና ጊዚያዊ ዉክልና የትምህርት ቤቱን የፋይናንስ እንቅስቃሴ እንዲመሩ ተመድበው እየሰሩ ከፋይናንስ ተቋሙ አሰራር ዉጭ ገንዘቡን አዘው ተጠቅመዋል፡፡
በዚሁ መሰረት በ1ኛ ተጠርጣሪ ትዕዛዝ ሰጭነትና አፅዳቂነት ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች ሰነድ በማዘጋጀት፣ ክፍያ በመፈፀምና ገንዘብ በመቀበል በማይነጣጠሉበት ሁኔታ ለሲሚንቶ ግዥ፣ ለአሸዋ ግዥ፣ ለህንፃ መሣሪያ ግዥ፣ ለጥገና እና ለትምህርት ቤቱን ግብ አጥር ለማስጠገን ጥገና በሚል ምንም አይነት መረጃ በሌለበት ብክነት መፈፀማቸዉ ተረጋግጧል።
የሰዉንና ሰነድ ማስረጃዎችን አደራጅተዉ ለዞኑ ሙስና ወንጀሎች ምርመራ ዲቭዥን ክስ እንዲመሰረትባቸው ሲል ተጠርጣሪዎቹ 407,305.2/ አራት መቶ ሰባት ሺህ ሦስት አምስት ብር ከሁለት ሳንቲም ወደ መንግስት ካዝና ገቢ አድርገዋል፡፡
የመንግስት ቀሪ ገንዘብ 143,350.2 (አንድ መቶ አርባ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ሃምሳ ብር ከሁለት ሳንቲም ለማስመለስ የዳዉሮ ዞን የሙስና ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገበት መሆኑ መታወቁን ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለባህል እና ስፓርት ዘርፍ አመራሮች "ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ስልጠና እየተሰጠ ነው
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለባህል እና ስፖርት አመራሮች "ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ሃሳብ የሥነ- ምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
በስልጠናው ተገኝተው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባህል እና ስፖርት ሚኒሰቴር የኪነ-ጥበብና ሥነ-ጥበብ ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ነፊሳ አለመሀዲ የዘርፉ አመራሮች ተግባራትን ከሙስና እና ብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ማከናወን እንዳለባቸው ገልፀዋል።
የኮሚሽኑ ሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥልጠና መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሐረጎት አብርሃ በበኩላቸው ሥልጠናው ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፥ ሥነምግባራዊ አመራር በስሩ ላሉት ሠራተኞች ምሳሌ ከመሆን ባለፈ ለሀገር እና ተቋም እድገት ግንባታ ሚናው የላቀ ነው ብለዋል።
ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

ወቅታዊና ጥራት ያለው ግዥ በመፈፀም ያለንን ውስን ሀብት ከብክነት መከላከል እንደሚገባ ተገለፀ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ በሥራ ሥነምግባርና በግዢ አስተዳደር ሥርዓት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ ለባለድርሻ አካላት በወልቂጤ ከተማ እየሰጠ ነው።
በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የቢሮው ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ኑሪዬ ሙስና እንደሀገር ማደግና መበልፀግ እንዳንችል እንቅፋት እየፈጠረ ያለ ችግር መሆኑን ተናግረዋል።
ሙስና በሀገር ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ላይ ቀውስ የሚፈጥር በመሆኑ ለተግባራዊነቱ አመራሩ ቁርጠኝነት መሳተፍ እንደሚገባውም ተናግረዋል።
በቢሮው በርካታ ለህዝብ ተደራሽ የሆኑ የመንገድ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ያነሱት ዶክተር መሀመድ፥ በግዢ ሥርዓት የሚፈፀሙ ብልሹ አሰራሮችን መከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
መመሪያን የተከተለ፣ ወቅታዊና ጥራት ያለው ግዥ በመፈፀም ያለንን ውስን ሀብት ከብክነት በመከላከል ለዜጎች ልማት ማዋል እንደሚገባ ኃላፊው መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
በውይይት መድረኩ የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፋሲካ ጌታቸው ጨምሮ የቢሮው አመራርና ሠራተኞች እና የዞንና ልዩ ወረዳ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።