በክልሉ አዲስ ለተመደቡ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች የአሰልጣኝነት ስልጠና እየተሰጠ ነዉ
*******************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲዳማ ክልል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በክልል፣ በወረዳና ከተማ አስተዳደር ሥር ለተመደቡ አዳዲስ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች የአንደኛ ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና በይርጋለም ከተማ መስጠት መጀመሩ ተገልጿል፡፡
በስልጠናዉ የተገኙት የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ዘላለም ለማ የስልጠናዉ ጠቀሜታና አላማ ሰልጣኞች ከስልጠናዉ የወሰዱትን እዉቀት ወደራሳቸዉ መስሪያቤት ነባራዊ ሁኔታ በመቀየር ሌሎችን ለማብቃት ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሙስና እና ብልሹ አሰራር በየደረጃው ባሉ ተቋማት ባህሪዉን በመቀያየር ለህዝብ የሚሰጥ የተቀላጠፈ አገልግሎትና ልማትን በመግታት እንዲሁም መልካም አስተዳደርን እንደሚያደናቅፍ ተናግረው፣ ለዚህም ችግር የሥነምግባር ዝቅጠት ትልቁን ድርሻ ይይወስዳል ብለዋል።
ይህንን ከመታገል አኳያ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች ሚናቸዉ የላቀ መሆኑን ገልፀው፣ ለዚህም ባለሙያዎች ትኩረት በመስጠት መስራት እንዳለባቸው አስረድተዋል።
ኮሚሽነሯ አክለውም የሙስና ትግል ስራ ከተደራጁ አካላት ጋር የሚደረግ መሆኑን በማንሳት፣ ትግሉ ጥበብና ብቃት የሚጠይቅ በመሆኑ ገልፀው፤ ሰልጣኞች በሚሰሩበት መስሪያቤት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በሙሉ ብቃት መወጣት የሚያስችል በመሆኑ ትኩረት ሰጥተዉ ስልጠናውን እንዲከታተሉ አሳስበዋል።
ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት በ10 የተለያዩ ይዘቶች ላይ የሚሰጥ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም በሥነምግባር ምንነትና የሞራል እሴት ላይ ትኩረት በማድረግ እየተሰጠ መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ከኮሚሽኑ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ የማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ አስታወቀ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በሚደረግ ዘርፈ ብዙ ትግል ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በቅርበት መስራት እንደሚፈልጉ የማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ አስታውቋል፡፡
የማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሐብቴ እንዳሉት ሙስና እና ብልሹ አሰራር ለመከላከል ልዩ ወረዳው በሚያደረገው ጥረት ኮሚሽኑ ቀጣይነት ያለው የሙስና መከላከል ሥራ በመስራት እንዲያግዛቸው ጠይቀዋል፡፡
የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ የሙስና መከላከል ስራዎች እየተሰሩ ያሉበትን ሁኔታ በሚመለከት የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በቀጣይም የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በለያቸው ክፍተቶች መነሻነት የሥራ ሥነ-ምግባርና የሙስና መከላከል ይዘቶች ላይ በወረዳው ለሚሰሩ አመራሮችና ሰራተኞች ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

በሀሰተኛ ሰነድ የአፈር ማዳበሪያ በማዘዋወር የተከሰሰው ግለሰብ በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ
****
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በሀሰተኛ ሰነድ ሲያዘዋውር የተያዘው ተከሳሽ በጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ ተወሰነ፡፡
በተከሳሹ ላይ ዛሬ ከሰዓት የጽኑ እስራትና የገንዘብ መቀጮ ቅጣት የወሰነው የኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ነው፡፡
የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ የሸገር ከተማ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ዐቃቤ ህግ አብርሃም ዘሪሁን በተባለ ተከሳሽ ላይ የሙስና ወንጀልን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ጠቅሶ ባሳለፍነው 2016 ዓ.ም ዝርዝር ክስ አቅርቦበት ነበር።
በዚህ በቀረበው ክስ ዝርዝር ላይ እንደተመላከተው ተከሳሹ ከግብርና ሚኒስቴር ለሀረሪ ክልል አርሶ አደሮች የሚውል በዘኢላ ህብረት ስራ ማህበር በሚል የተሰጠን የወጪ ደረሰኝ ሰነድን ግርማ ወልደ ጎርጊስ በሚል ስም ሀሰተኛ የወጪ ሰነድ አዘጋጅቶ የጉዞ አቅጣጫውን ቀይሮ በተሳቢ ተሽከርካሪ 400 ኩንታል ማዳበሪያ ጭኖ በህገወጥ መንገድ ወደ ደብረ ብርሃን ሲጓዝ በግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ላይ በሸገር ከተማ በለገዳዲ ለገጣፍ ክፍለከተማ ልዩ ስሙ አባ ኪሮስ እየተባለ በሚጠራው ኬላ አካባቢ ሲደርስ በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር የዋለ መሆኑን ዐቃቤ ህግ በክስ ዝርዝሩ ላይ ጠቅሷል።
ተከሳሹ በዚህ መልኩ የቀረበበት ክስ ዝርዝር በችሎት ከደረሰው በኋላ የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸሙን ጠቅሶ የሰጠውን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ህግ የሰው ምስክርና ሀሰተኛ ሰነድ በማስረጃነት ለችሎቱ ማቅረቡን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ህግ ማስረጃን መርምሮ በክሱ ላይ የተጠቀሰው የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን አረጋግጫለሁ በማለት ተከሳሹ በተከሰሰበት ድንጋጌ ስር እንዲከላከል ብይን የሰጠ ሲሆን፥ ተከሳሹ ባቀረበው የመከላከያ ማስረጃ የዐቃቤ ህግ ማስረጃን በተገቢው ማስተባበል አለመቻሉ ተገልጾ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶበታል፡፡
ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየትን መርምሮ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በዋለው ቀጠሮ በተከሳሹ የቀረቡ የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶችን በመያዝ ተከሹን በ3 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።
በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የተያዘው 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ቀዳማዊ እመቤት በሙስና እና በአክሲዮን ዋጋ ማጭበርበር ወንጀል መዘፈቃቸው ባለቤታቸው ለደረሰባቸው ፖለቲካዊ ውድቀት ተጠያቂ እንደሆኑ ተገለፀ
****
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ባሳለፍነው ሀምሌ ወር በአክሲዮን ማጭበርበር እና ከፍተኛ ዶላር የሚያወጣ የቅንጦት ቦርሳ ጉዳይ በሙስና ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው የሚገኙት የደቡብ ኮሪያ ቀዳማዊ እመቤት ኪም ኪዮን ሂ በባለቤታቸው የፖለቲካ ውድቀት ተጠያቂ ተደርገዋል፡፡
የአልጀዚራ ዘገባ እንደሚያመለክተው የሙስና ቅሌቱ ባለቤታቸው የሆኑት ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ዮኦል ፓርቲያቸው በሚያዝያ ወር በተካሄደው ምርጫ እንዲሸነፋ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳርፏል። ይህ ቀዳማዊ እመቤቷ የተቀበሉት ስጦታ፣ ማንኛውም የደቡብ ኮሪያ መንግስት ባለስልጣናት እና ሚስቶቻቸው ከ750 ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ስጦታቸው እንዳይቀበሉ የሚከለክለውን ህግ የሚጥስ ነው።
የሀገሪቱ ፕሬዝደንት የደነገጉት ወታደራዊ ህግ ከከሸፈ በኋላ ጉዳዩን ከባለቤታቸው ጋር በማያያዝ በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ በተለይም ዮን ለባለቤቱ ወታደራዊ ህግ ያወጀ ታላቅ አፍቃሪ የሚሉ የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች ጎልተው ወጥተዋል፡፡ አንዳንዶቹም ቀዳማዊ እመቤት ኪም ኪዮን ሂ የደቡብ ኮሪያዋ "እመቤት ማክቤዝ" በማለት ገልፀዋቸዋል፡፡
በደቡብ ኮሪያ በሚያዝያ ወር በተካሄደው የፓርላማ ምርጫ የኮሪያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (DPK) ጨምሮ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የዮንን ህዝባዊ ሀይል ፓርቲ (PPP) አሸንፈው ብሔራዊ ምክር ቤትን መቆጣጠራቸው ይታወሳል።

ለውጭ ጉዳይ ዘርፍ አመራሮች "ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ዘርፍ ተኮር ስልጠና እየተሰጠ ነው
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለውጭ ጉዳይ ዘርፍ አመራሮች "ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ሃሳብ ዘርፍ ተኮር የሥነ-ምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ስልጠናው ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እየተሰጠ ሲሆን፥ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።