በክልሉ አዲስ ለተመደቡ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች የአሰልጣኝነት ስልጠና እየተሰጠ ነዉ
*******************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲዳማ ክልል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በክልል፣ በወረዳና ከተማ አስተዳደር ሥር ለተመደቡ አዳዲስ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች የአንደኛ ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና በይርጋለም ከተማ መስጠት መጀመሩ ተገልጿል፡፡
በስልጠናዉ የተገኙት የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ዘላለም ለማ የስልጠናዉ ጠቀሜታና አላማ ሰልጣኞች ከስልጠናዉ የወሰዱትን እዉቀት ወደራሳቸዉ መስሪያቤት ነባራዊ ሁኔታ በመቀየር ሌሎችን ለማብቃት ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሙስና እና ብልሹ አሰራር በየደረጃው ባሉ ተቋማት ባህሪዉን በመቀያየር ለህዝብ የሚሰጥ የተቀላጠፈ አገልግሎትና ልማትን በመግታት እንዲሁም መልካም አስተዳደርን እንደሚያደናቅፍ ተናግረው፣ ለዚህም ችግር የሥነምግባር ዝቅጠት ትልቁን ድርሻ ይይወስዳል ብለዋል።
ይህንን ከመታገል አኳያ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች ሚናቸዉ የላቀ መሆኑን ገልፀው፣ ለዚህም ባለሙያዎች ትኩረት በመስጠት መስራት እንዳለባቸው አስረድተዋል።
ኮሚሽነሯ አክለውም የሙስና ትግል ስራ ከተደራጁ አካላት ጋር የሚደረግ መሆኑን በማንሳት፣ ትግሉ ጥበብና ብቃት የሚጠይቅ በመሆኑ ገልፀው፤ ሰልጣኞች በሚሰሩበት መስሪያቤት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በሙሉ ብቃት መወጣት የሚያስችል በመሆኑ ትኩረት ሰጥተዉ ስልጠናውን እንዲከታተሉ አሳስበዋል።
ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት በ10 የተለያዩ ይዘቶች ላይ የሚሰጥ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም በሥነምግባር ምንነትና የሞራል እሴት ላይ ትኩረት በማድረግ እየተሰጠ መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ከኮሚሽኑ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ የማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ አስታወቀ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በሚደረግ ዘርፈ ብዙ ትግል ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በቅርበት መስራት እንደሚፈልጉ የማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ አስታውቋል፡፡
የማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሐብቴ እንዳሉት ሙስና እና ብልሹ አሰራር ለመከላከል ልዩ ወረዳው በሚያደረገው ጥረት ኮሚሽኑ ቀጣይነት ያለው የሙስና መከላከል ሥራ በመስራት እንዲያግዛቸው ጠይቀዋል፡፡
የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ የሙስና መከላከል ስራዎች እየተሰሩ ያሉበትን ሁኔታ በሚመለከት የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በቀጣይም የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በለያቸው ክፍተቶች መነሻነት የሥራ ሥነ-ምግባርና የሙስና መከላከል ይዘቶች ላይ በወረዳው ለሚሰሩ አመራሮችና ሰራተኞች ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡