Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የሌላ ደንበኛ ሂሳብን ‘የእኔ ነው’ በማለት 12 ሚሊየን ብር ሊያዘዋውር የሞከረው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ

*******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሌላ ደንበኛ ሂሳብ ‘ባለቤት ነኝ’ ብሎ 12 ሚሊየን ብር ሊያዘዋውር ሲሞክር በባንኩ ሰራተኞች የተያዘው ተከሳሽ በአምስት ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ወሰነ።

ተከሳሹ መምህር መንግስቱ ተመስገን በወንጀል ምርመራ ሂሳቡ የታገደበትን ተማም መሃር የተባለ ግለሰብ ስም ተመሳስሎ የተዘጋጀ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ በመያዝ መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ በገፈርሳ ጉጂ ክፍለ ከተማ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡራዩ ቅርጫፍ በመሄድ ለባንኩ ባለሙያዎች ተማም መሃር የተባለ ቡና ላኪ ባለሃብት እንደሆነ በመግለጽ እንደተዋወቃቸው በክሱ ላይ ተጠቅሷል።

ተከሳሹ በሌላ ቅርንጫፍ ከ12 ሚሊየን በላይ ገንዘብ ያለው ሂሳብ መክፈቱን በመግለጽ እንዲሁም "ያንን ሂሳብ ዘግቼ እናንተ ቅርጫፍ አዲስ ሂሳብ ልክፈትና 12 ሚሊየን ብሩን በዚህ ቅርጫፍ ወደ ምከፍተው ሂሳቤ አዘዋውሩልኝ " በማለት መጠየቁ ተመላክቷል፡፡

በባንኩ አሰራር መሰረት የጠየቀው የገንዘብ መጠን ከፍ ያለ በመሆኑ የባንኩ ማናጀር ማረጋገጫ መስጠት ስላለበት ባለሙያዎቹ ወደ ባንኩ ማናጀር ይልኩታል፡፡

የባንኩ ማናጀርም በቀረበው ጥያቄ መነሻ መንጃ ፍቃድ ወይም ፓስፖር፣ ቪዛ እንዲያሳየው ሲጠይቀው ተከሳሹ አለመያዙን መልስ የሰጠ ሲሆን የባንኩ ማናጀር ተማም መሃር በተባለ ግለሰብ ስም የተከፈተው ሂሳብ ባለቤት መሆኑንና አለመሆኑን ለማረጋገጥ ኮምፒዩተር ከፍቶ ሲመለከት ሂሳቡ በወንጀል ምርመራ እንዳይንቀሳቀስ የታገደ የሌላ ሰው ሂሳብ መሆኑን በማረጋገጥ ከሰራተኞቹ ጋር የባንኩን ጥበቃ ጠርቶ ተከሳሹን በማስያዝ ለፀጥታ አካላት አሳልፎ መስጠቱ በክስ ዝርዝሩ ላይ ተጠቅሷል።

ተከሳሹ በቁጥጥር ስር ከዋለና ምርመራ ከተደረገበት በኋላ የኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ዐቃቤ ሕግ ተከሳሹ ላይ የሙስና ወንጀልን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ጠቅሶ ክስ አቅርቦበታል።

ተከሳሹ የክሱ ዝርዝር ከደረሰው በኋላ የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃል በመስጠቱ፤ ዐቃቤ ሕግ የሰው ምስክርና የሰነድ ማስረጃ ማቅረቡን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሹ እንዲከላከል በሰጠው ብይን ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው ማስተባበል ባለመቻሉ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቶበታል።

በዚህም ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየትን መርምሮና ይዞ ተከሳሹን በአምስት ዓመት ጽኑ እስራትና በ5 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሙስናን መታገል ለነገ የማይባል ተግባር መሆኑን የጀኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ገለፀ

*******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የጀኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሥነ-ምግባር ግንባታ፣ በሙስና ጽንሰ ሀሳብ እና መከላከል ዙሪያ ለኮሌጁ አሰልጣኞችና ለአስተዳደር ሰራተኞች ለ2 ቀናት ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የኮሌጁ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት አቦነህ በስልጠናው የተሳተፉ ከ300 በላይ የኮሌጁ አሰልጣኞችና የአስተዳደር ሰራተኞች በሥነምግባር የታነፀ ትውልድ በማፍራትና ሙስናን በመከላከል የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የስልጠናው ዓላማ የሙስና አስከፊነት ላይ ግንዛቤ በማዳበር ለፀረ-ሙስና ትግሉ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲችል ለማገዝ መሆኑን ዳይሬከረተሯ ገልፀዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጠው በአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ባለሙያ አቶ ደረጀ ግርማ ስልጠናው በመንግስት ተቋማት የሚታዩትን ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመቀነስ የሥራ ክፍሎችና ሰራተኞች የሚሰጡ አገልግሎቶች ከሙስና የፀዳ እንዲሆን ለማስቻልና የሙስና መከሰቻ መንገዶቹን በማወቅ ሙስናን ለመከላከል እንደሚረዳ አስረድተዋል፡፡

ሙስናን የሚጸየፍ ማህረሰብ ለመፍጠር ቤተሰብ፣ ት/ቤቶችና ማህበረሰቡ ትልቅ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ሙስናን መታገል ለነገ የማይባል ተግባር መሆኑን ባለሙያው መናገሩን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የስልጠና ተሳታፊዎችም የሙስና አስከፊነት ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ የሄደበት ሁኔታ ማህበረሰቡን እያማረረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ለዚህም በቅንጅት በመስራት ሙሰኞችን መታገልና በሙስና የተከሰሱ ወንጀለኞችም አስተማሪ ቅጣት አለማግኘታቸው ሙሰኞችን እያበረታታ መሄዱን ገልፀው፤ መንግስት፣ ህዝብና የሚመለከተው ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥቶ በጋራ ለመስራት ወሳኝ ወቅት ላይ ነን ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በክልሉ አዲስ ለተመደቡ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች የአሰልጣኝነት ስልጠና እየተሰጠ ነዉ

*******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲዳማ ክልል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በክልል፣ በወረዳና ከተማ አስተዳደር ሥር ለተመደቡ አዳዲስ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች የአንደኛ ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና በይርጋለም ከተማ መስጠት መጀመሩ ተገልጿል፡፡

በስልጠናዉ የተገኙት የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ዘላለም ለማ የስልጠናዉ ጠቀሜታና አላማ ሰልጣኞች ከስልጠናዉ የወሰዱትን እዉቀት ወደራሳቸዉ መስሪያቤት ነባራዊ ሁኔታ በመቀየር ሌሎችን ለማብቃት ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሙስና እና ብልሹ አሰራር በየደረጃው ባሉ ተቋማት ባህሪዉን በመቀያየር ለህዝብ የሚሰጥ የተቀላጠፈ አገልግሎትና ልማትን በመግታት እንዲሁም መልካም አስተዳደርን እንደሚያደናቅፍ ተናግረው፣ ለዚህም ችግር የሥነምግባር ዝቅጠት ትልቁን ድርሻ ይይወስዳል ብለዋል።

ይህንን ከመታገል አኳያ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች ሚናቸዉ የላቀ መሆኑን ገልፀው፣ ለዚህም ባለሙያዎች ትኩረት በመስጠት መስራት እንዳለባቸው አስረድተዋል።

ኮሚሽነሯ አክለውም የሙስና ትግል ስራ ከተደራጁ አካላት ጋር የሚደረግ መሆኑን በማንሳት፣ ትግሉ ጥበብና ብቃት የሚጠይቅ በመሆኑ ገልፀው፤ ሰልጣኞች በሚሰሩበት መስሪያቤት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በሙሉ ብቃት መወጣት የሚያስችል በመሆኑ ትኩረት ሰጥተዉ ስልጠናውን እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት በ10 የተለያዩ ይዘቶች ላይ የሚሰጥ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም በሥነምግባር ምንነትና የሞራል እሴት ላይ ትኩረት በማድረግ እየተሰጠ መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319