Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.03K links
Download Telegram
"ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል ርዕስ ለፕላንና ልማት ዘርፍ አመራሮች ስልጠና እየተሠጠ ይገኛል

***

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 5/2017 ዓ.ም አዳማ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን “ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት” በሚል ርዕስ ለፕላንና ልማት ዘርፍ አመራሮች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ ክብርት ጥሩማር አባተ ሙስና የአንድን አገር መልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ እድገት እና የሰብአዊ መብት መከበር በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዳ፣ ሐቀኝነትን በማጓደል የሕገወጥነትን ባህሪ የሚያላብስ እና ሀገርን ሊበትን የሚችል አለምአቀፋዊ ወንጀል ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ሙስና በዓለም አቀፍ፣ በአህጉር አቀፍ እና በሀገር ደረጃ እያስከተለ ያለው ችግር በጣም ከባድና ውስብስብ እየሆነ መምጣቱን አመላክተዋል።

እንደ መንግስትም ሙስና የሚያስከትለውን የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ በመረዳት ችግሩ የከፋ ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት በርካታ አሰራርና ህጎችን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ሚንስትር ዴኤታዋ አክለውም ሁላችንም ብልሹ አሠራርን ለመታገል ከኔ በላይ ማንም የለም በሚል ስሜት ንቅናቄውን መቀላቀልና ከሌሎች በተሻለና ከፍ ባለ ሁኔታ ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት ለሀገር ዕድገትና ለህዝቦች ተጠቃሚነት ፀር የሆነውን ሙስና በጋራ መከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል።

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ፈቃዱ ሰቦቃ ስልጠናው ሲሰጥ የነበረው የሙስና ምንነት፣ አስፈላጊነትና መከላከያ ዘዴዎች መሆኑን አስታውሰው፥ አሁን ግን ዘርፍ ተኮር አሰራርን በመከተል በዘርፋ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ዳሰሳ ጥናት መነሻነት የሚሰጥ ስልጠና ነው ብለዋል።

ለዚህም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተወጣጡ ሙሁራን በተዘጋጁ የማሰልጠኛ ሞጅሎች የሚሰጥ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሆኑንም ጠቁመዋል።

ስልጠናው በመጀመሪያው ዙር ለዘርፋ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው፥ በቀጣይም በየደረጃው ለሚገኙ መካከለኛ አመራሮችና ሠራተኞች የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም አንድ ተቋም ውጤታማ የሚሆነው የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች በሥነምግባር አርዓያ ሲሆኑ መሆኑን ገልፀው፥ ለዚህም አመራሩ የተሰጣቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በዘርፋ የብልሹ አሰራር ችግሮች ሲኖሩም ችግር ፈጣሪዎችን ተጠያቂ በማድረግ ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።

ስልጠናው በዶ/ር ዮሐንስ ጴጥሮስ፣ በዶ/ር አራጋው እሸቴ እና በዶ/ር በለጠ ደበበ እየተሰጠ ሲሆን፣ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ለፀረ-ሙስና ትግል ሁሉም ሊያግዝ እንደሚገባ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ አሳሰቡ

***

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ብልሹ አሠራርን እና ሙስናን ለመከላከል ከሚመለከታቸው ተቋማት እና የሲቪክ ማኅበራት ጋር በጥምረት ለመሥራት ሥምምነት ተፈራርሟል።

በሥነሥርዓቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በምክትል ርዕሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴን (ዶ/ር) ጨምሮ የክልል ቢሮ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ተቋማት እና የሙያ ማኅበራት ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከተቋቋመባቸው ዓላማዎች መካከል አንዱ የሕዝብ ሀብት እና ንብረት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ሥነምግባርን በተከተለ መልኩ ሙስናን የመከላከል ሥራን መሥራት መኾኑን አንስተዋል።

ተጠያቂነትን አሠራር እንዲሰፍን ለተቋማት ግብዓት ማቅረብንም ጨምረዋል። ለምክር ቤቶች የጠራ መረጃ በማቅረብ እንዲታገሉበትና የሕዝብ ውክልናቸውንም እንዲወጡ እያደረገ መምጣቱንም አክለዋል።

የጥምረቱ መመሥረት ምክንያትም ተቋማት ከተናጠል ከሚሠሩት በተጨማሪ ኀላፊነታቸውን በጋራ በመሥራት የሙስናን ትግል ለማጠናከር እንደኾነም ነው አፈ ጉባኤዋ የገለጹት። ኮሚሽኑ ጥምረቱን ለማቋቋም የሕግ መሠረት እንዳለውም ጠቅሰዋል።

በሥነምግባር ግንባታ ሙስናን የሚጸየፍ ትውልድ በመፍጠር በኩል የሃይማኖት አባቶች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የሚዲያ ተቋማት፣ የሙያ ማኅበራት እና ሌሎቹም ትልቅ ኀላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ሥነምግባርን ከመገንባት አኳያ የሃይማኖት ተቋማት ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ጠቅሰዋል።

ኅብረተሰቡ ከተራ አገልግሎት ጀምሮ ለማንኛውም አገልግሎት ክፍያ እየተጠየቀ መኾኑን ያነሱት ዋና አፈ ጉባኤዋ ችገሩን ለመቀነስ ከጥምረቱ መቋቋም በኋላ በሚቀመጡ አሠራሮች አማካይነት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በመገንዘብ ሁሉም የአቅሙን ማበርከት እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል።

በየተቋማቱ ከእቅድ ጀምሮ ትኩረት በመስጠት የመሥራት ጅምር ቢኖርም ውጤቱ የሚጠበቀውን ያህል አይደለም። ይህንን ችግር ለመፍታት የጥምረቱ መመሥረት ታምኖበታል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

የሥነምግባር ግንባታውን በየተቋማቱ በመሥራት በትውልድ ላይ የሚሠራውን ሥራ ለማጠናከር ነው። ተቋማት ይህንን ሥራ ለመሥራት የሚያጋጥመውን ችግር በጋራ እየገመገምን የመንግሥት እና የሕዝብ ሀብት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ጥረት ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።

የጥምረቱ መቋቋም ግብ የፀረ-ሙስና ትግሉ በተገቢው ተመርቶ ሕዝብ ተገቢ አገልግሎት እንዲያገኝ ምቹ ኹኔታ ለመፍጠር ነው። ለዚህም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አደራ ብለዋል ዋና አፈ ጉባኤዋ።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የከተማና መሠረተልማት ዘርፍ ግዙፍ በጀት የሚንቀሳቀስበት በመሆኑ አመራሩ በላቀ ሥነምግባር መምራት እንደሚጠበቅበት ተገለፀ

***

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም፣ አለም ገና) ለከተማና መሠረተ ልማት ዘርፍ አመራሮች "ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማት ተልዕኮ ስኬት!" በሚል መሪ ቃል ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በመድረኩ ዘርፉን ወክለው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ነገዎ (ኢ/ር) የከተማና መሠረተልማት ዘርፍ በሀገር ደረጃ ግዙፍ የመንግስት እና የህዝብ ሀብት የሚንቀሳቀስበት በመሆኑ አመራሩ የላቀ ሥነምግባር ተላብሶ መምራት እንዳለበት አሳስበዋል።

የተበላሸ የአዕምሮ ውቅር ለብልሹ አሰራሮች መነሻ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ፥ ችግሩን ለመቅረፍ የሥነምግባር ግንዛቤ ማሳደግና ሥልጠና ማስፋት አንዱ መሣሪያ መሆኑን አንስተዋል።

የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ክቡር ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው የፀረ-ሙስና ትግሉን ዘርፍ ተኮር በማድረግ ዘርፎች የፀረ-ሙስና ትግሉ ባለቤት እንዲሆኑ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም ዘርፍ ተኮር አሠራር ከጥናት ጀምሮ መካሂዱን በመጠቆም፥ ጥናቱን መሠረት ያደረጉ የሥልጠና ሞጁሎች በዩኒቨርሲቲ ምሁራን በማዘጋጀት ሥልጠና መሠጠት መጀመሩን ጠቅሠዋል።

በተጀመረው ሥልጠና የአመራር ሥነምግባር በመገንባት በዘርፍ ተቋማት ለፀረ-ሙስና ትግል አመቺ ሁኔታ እንደሚፈጠር ገልፀዋል።

ስልጠናው በዩኒቨርስቲ ምሁራን እየተሰጠ ሲሆን፥ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የሌላ ደንበኛ ሂሳብን ‘የእኔ ነው’ በማለት 12 ሚሊየን ብር ሊያዘዋውር የሞከረው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ

*******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሌላ ደንበኛ ሂሳብ ‘ባለቤት ነኝ’ ብሎ 12 ሚሊየን ብር ሊያዘዋውር ሲሞክር በባንኩ ሰራተኞች የተያዘው ተከሳሽ በአምስት ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ወሰነ።

ተከሳሹ መምህር መንግስቱ ተመስገን በወንጀል ምርመራ ሂሳቡ የታገደበትን ተማም መሃር የተባለ ግለሰብ ስም ተመሳስሎ የተዘጋጀ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ በመያዝ መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ በገፈርሳ ጉጂ ክፍለ ከተማ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡራዩ ቅርጫፍ በመሄድ ለባንኩ ባለሙያዎች ተማም መሃር የተባለ ቡና ላኪ ባለሃብት እንደሆነ በመግለጽ እንደተዋወቃቸው በክሱ ላይ ተጠቅሷል።

ተከሳሹ በሌላ ቅርንጫፍ ከ12 ሚሊየን በላይ ገንዘብ ያለው ሂሳብ መክፈቱን በመግለጽ እንዲሁም "ያንን ሂሳብ ዘግቼ እናንተ ቅርጫፍ አዲስ ሂሳብ ልክፈትና 12 ሚሊየን ብሩን በዚህ ቅርጫፍ ወደ ምከፍተው ሂሳቤ አዘዋውሩልኝ " በማለት መጠየቁ ተመላክቷል፡፡

በባንኩ አሰራር መሰረት የጠየቀው የገንዘብ መጠን ከፍ ያለ በመሆኑ የባንኩ ማናጀር ማረጋገጫ መስጠት ስላለበት ባለሙያዎቹ ወደ ባንኩ ማናጀር ይልኩታል፡፡

የባንኩ ማናጀርም በቀረበው ጥያቄ መነሻ መንጃ ፍቃድ ወይም ፓስፖር፣ ቪዛ እንዲያሳየው ሲጠይቀው ተከሳሹ አለመያዙን መልስ የሰጠ ሲሆን የባንኩ ማናጀር ተማም መሃር በተባለ ግለሰብ ስም የተከፈተው ሂሳብ ባለቤት መሆኑንና አለመሆኑን ለማረጋገጥ ኮምፒዩተር ከፍቶ ሲመለከት ሂሳቡ በወንጀል ምርመራ እንዳይንቀሳቀስ የታገደ የሌላ ሰው ሂሳብ መሆኑን በማረጋገጥ ከሰራተኞቹ ጋር የባንኩን ጥበቃ ጠርቶ ተከሳሹን በማስያዝ ለፀጥታ አካላት አሳልፎ መስጠቱ በክስ ዝርዝሩ ላይ ተጠቅሷል።

ተከሳሹ በቁጥጥር ስር ከዋለና ምርመራ ከተደረገበት በኋላ የኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ዐቃቤ ሕግ ተከሳሹ ላይ የሙስና ወንጀልን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ጠቅሶ ክስ አቅርቦበታል።

ተከሳሹ የክሱ ዝርዝር ከደረሰው በኋላ የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃል በመስጠቱ፤ ዐቃቤ ሕግ የሰው ምስክርና የሰነድ ማስረጃ ማቅረቡን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሹ እንዲከላከል በሰጠው ብይን ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው ማስተባበል ባለመቻሉ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቶበታል።

በዚህም ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየትን መርምሮና ይዞ ተከሳሹን በአምስት ዓመት ጽኑ እስራትና በ5 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319