Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.03K links
Download Telegram
ባለፉት ዓመታት በክልሉ የመንግስት እና የህዝብ ሀብትን በመስረቅና በማጭበርበር የተሳተፉ አካላትን ወደ ህግ በማቅረብ ተጠያቂነትን ማስፈን ይገባል - አፈ ጉባኤ ወንድሙ ኩርታ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ባለፉት ዓመታት በክልሉ የመንግስት እና የህዝብ ሀብትን በመስረቅና በማጭበርበር የተሳተፉ አካላትን ወደ ህግ በማቅረብ ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወንድሙ ኩርታ ተናግረዋል፡፡

በኦዲት ግኝት አመላለስ፣ የፋይናንስ አስተዳደር እና ሂሳብ አያያዝ ዙሪያ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ እያደረገ ነው።

በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክርቤት ዋና አፈጉባዔ አቶ ወንድሙ ኩርታ የህዝብ ሀብት ከብክነት ለመታደግ ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል መደረግ አለበት ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በክልሉ የመንግስት እና የህዝብ ሀብትን በመስረቅና በማጭበርበር የተሳተፉ አካላትን ወደ ህግ በማቅረብ ተጠያቂነትን ማስፈን ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ በበኩላቸው የሂሳብ አያያዝና አወቃቀርን ያልተከተለ የበጀት ምዝገባ፣ ተቀባይነት ያላቸውን አሰራሮች አለመከተል፣ የሂሳብ አያያዝ መርህን አለመከተል ለሀብት ብክነት መነሻ የሆኑ የአሰራር ክፍተቶች መሆናቸውን አመላክተዋል።

የመንግስት እና የህዝብ ሀብት ብክነትን ለመከላከል የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች መከናዎን ይኖርበታል ሲሉም ወ/ሮ ወሰነች ተናግረዋል።

የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ እንዳመለከተው ለዚህም ውጤታማነት የህግና ፍትህ አካላት እንዲሁም ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት የኦዲት ግኝት ሪፖርትን መሠረት በማድረግ የባከኑ ሀብቶችን የማስመለስና አጥፊዎች በህግ የሚጠየቁበት ሁኔታ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

በክልሉ በኦዲት ግኝት አፈጻጸም የምክክር መድረክ የክልሉ ኦዲት ግኝት አስመላሽ ግብረሃይል የ6ቱ ዞን ዋና አፈ ጉባዔዎች፣ የፋይናንስ መምሪያ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
"ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል ርዕስ ለፋይናንስ ዘርፍ አመራሮች እየተሠጠ ይገኛል

***************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 4/2017 ዓ.ም አዳማ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን “ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት” በሚል ርዕስ ለፋይናንስ ዘርፍ አመራሮች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

ስልጠናው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ያልወሠዱ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመሮች ያካተተ ነው፡፡

በዕለቱ የተገኙት በገንዘብ ሚኒስቴር የፊሲካል ፓሊሲ እና ፐብሊክ ፋይናንስ ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክቡር እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ሚኒስተር መሥሪያ ቤቱ በፋይናንስ ዘርፍ የሚታዩ የአሠራር ሥርአቶችን በማዘመን ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ሥርዓት በመዘርጋት ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ እንደሆነ ገልፀዋል።

ሚንስትር ዴኤው አክለውም በፋይናንስ ዘርፍ ሥር ያሉ ተቋማት የሥነምግባር መከታተያ ክፍልን በማስተባበር፣ በመደገፍ እና በመከታተል ተቋማዊ ሀላፊነትን የመወጣት ስራ መሠራቱን ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው በሥነምግባር የታነፁ፣ ሙስናን የሚጠየፉ ህዝብና መንግስትን በታማኝነት የሚያገለግሉ ሠራተኞች የማፍራት ሀላፊነትን ለመወጣት የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመዋል።

በስልጠናዉ የተገኙት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፈቃዱ ሰቦቃ ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋም ተልዕኮ ስኬት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፣ ተቋሙን ከሙስና እና ብልሹ አሰራር እንዲቆጠብ የአመራር ሚና ከፍተኛ በመሆኑ እንደነዚህ አይነት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመውሰድ ቆራጥ፣ ሙስናን የሚፀየፍ ሰራተኛ መፍጠር ይገባል ብለዋል።

ስልጠናው በኮሚሽኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥልጠና መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሐረጎት አብርሃ እና የስልጠና ጥራት እና ተገቢነት ዴስክ ኃላፊ በአቶ የኋላሸት ደሳለኝ እየተሰጠ ሲሆን፣ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ኮሚሽኑ ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል ርዕስ ስልጠና ካካሄዱ ሰባት ዘርፎች ጋር ግምገማ አደረገ

***************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል ርዕስ ስልጠና ካካሄዱ ሰባት ዘርፎች ጋር ግምገማ አድርጓል።

ግምገማው በዋናነት በስልጠናው የታዩ ደካማ እና ጠንካራ ጎኖችን በመለየት በቀጣይ ለሚሰጡ ስልጠናዎች ግብዓት ለመውሰድና ስልጠናዎች ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲያዘጋጁ ታሳቢ ያደረገ ነው።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ከ5 ሚሊየን ብር በላይ እንዲመዘበር በማድረግ የሙስና ወንጀል የተከሰሱ በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ

***

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የባንክ መመሪያና የአሰራር ስርዓትን በመጣስ ከደንበኛ ሂሳብ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ወጪ በማዘዝ እና በመመዝበር በከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሱ 5 ግለሰቦች ከ4 እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ወሰነ።

ተከሳሾቹ 1ኛ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተፈራ ደግፌ ቅርንጫፍ ተጠባባቂ ተቀዳሚ ቅርንጫፍ ባንኪንግ መኮንን በረከት ሙሉ፣ 2ኛ በቅርንጫፉ ተጠባባቂ የውስጥ ተቆጣጣሪ ማርታ ሃይሉ፣ 3ኛ በንግድ ስራ ይተዳደራል የተባለው ተስፋ ገ/ስላሴ፣ 4ኛ ጌትነት አለማየሁ እና 5ኛ ሪያን ሰይድ ናቸው።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በ2016 ዓ.ም በተከሳሾቹ ላይ ማለትም በአንደኛው ክስ በ1ኛ እና በ2ኛ ተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32 (1) (ሀ) እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 9 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና ንዑስ ቁጥር (2) ስር የተመላከተውን ድንጋጌ መተላለፍ የሚል ክስ አቅርቧል።

በሁለተኛው ክስ ደግሞ ከ3ኛ እስከ 5ኛ ተራ ቁጥር በተጠቀሱ ተከሳሾች ላይ ብቻ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብን እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 780/200 5 አንቀጽ 29 ንዑስ ቁጥር 1 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል።

በዚህ መልኩ በቀረበው በአንደኛው ክስ ላይ እንደተመላከተው 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥቅምት 2013 ዓ.ም ያጸደቀው የቅርንጫፍ ባንኮች የአሰራር ስርዓት መመሪያ ደንብን በመተላለፍ የባንኩ ደንበኛ የሆኑት የግል ተበዳይ አቶ ይትባረክ ይኩኑ አምላክ ከሂሳብ ቁጥራቸው ላይ ገንዘብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ሌላ ሂሳብ እንዲተላለፍ ጥያቄ ባላቀረቡበት ሁኔታ ላይ ከደንበኛው ሂሳብ ያለአግባብ የገንዘብ ዝውውር ለመፈፀም እንዲያስችላቸው በባንኩ ተጥሎ የነበረውን የክልከላ ገደብ መተላለፋቸውን በክሱ ተጠቅሷል።

በዚህ መልኩ 1ኛ ተከሳሽ በባንኩ የተሰጠውን የሚስጥር ቁጥር ለ2ኛ ተከሳሽ አሳልፎ በመስጠት 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ በመስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ ምንም አይነት ግብይት በሌለበት ሁኔታ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች የሆኑ ሰራተኞችን ኮምፒውተር በመጠቀም የደንበኛው የቀሪ ሂሳብ እና ፊርማ ምልከታ በማድረግ ፎቶ በማንሳት መረጃውን አሳልፋ ለሌላ የሰጠች መሆኑ ተመላክቷል።

በመስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም ለጊዜው ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ ከቅርንጫፉ ውጪ የተዘጋጁ እና በግል ተበዳይ ያልተፈረሙ ሁለት በሐዋላ ገንዘብ መላኪያ ቅጽ ይዞ በመቅረብ ለ1ኛ ተከሳሽ የሰጠው ሲሆን ተከሳሹም 4ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ደንበኞች እያስተናገደች የነበረችበትን ኮምፒውተር በመጠቀም ለ3ኛ ተከሳሽ ሂሳብ ቁጥር ብር 3 ሚሊየን 240 ሺህ ብር እና ለ4ኛ ተከሳሽ ደግሞ 2 ሚሊየን 160 ሺህ ብር በአጠቃላይ 5 ሚሊየን 400 ሺህ ብር ዝውውር ከፈፀመ በኃላ በራሱ የኮምፒውተር መጠቀሚያ ዩዘር ግብይቶችን ያፀደቀ መሆኑ በክሱ ተዘርዝሯል።

2ኛ ተከሳሽም ደግሞ ግብይቶችን ኦዲት በማድረግ ያረጋገጠች በመሆኑም በአጠቃላይ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች የአሰራር ስርዓት መመሪያ በግልጽ ተግባር በመተላለፍ ደንበኛው ባልቀረቡበትና የክፍያ ጥያቄ ባላቀረቡበት ሁኔታ ከሂሳባቸው ገንዘብ ወጪ በማድረግ በባንኩ ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ እና ለሌሎች ሰዎች ያልተገባ ጥቅም እንዲውል ያደረጉ መሆናቸው ተጠቅሶ ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት ስልጣንን አለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡

በሁለተኛው ክስ ደግሞ ከ3ኛ እስከ 5ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተከሳሾች ላይ በቀረበው ክስ እንደተገለጸው፤ ተከሳሾች የንብረቱን ህገ-ወጥ ምንጭ ለመደበቅ እና ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ በማሰብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድነት ቅርንጫፍ ደንበኛ ከሆኑት የግል ተበዳይ ከሂሳብ ቁጥራቸው ላይ ያለአግባብ ወጪ ከሆነው ብር ውስጥ በተለያዩ መጠኖች በተከፈተ ሒሳብ በማስተላለፍ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ተከሰዋል፡፡

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ችሎት ቀርበው ክሱ እንዲደርሳቸው ከተደረገ በኋላ በክሱ ዝርዝር የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ማስረጃዎችን መርምሮ የተጠቀሰው የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን መረጋገጡን ጠቅሶ ተከሳሾቹ በየደረጃው በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር እንዲከላከሉ ብይን መስጠቱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ሆኖም ተከሳሾቹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል( ማስተባበል) አለመቻላቸው ተጠቅሶ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት መርምሮና ተከሳሾች ያቀረቡትን የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶችን በመያዝ 1ኛ ተከሳሽን በ4 ዓመት ከ5 ወራት ጽኑ እስራት እና በ4 ሺህ ብር፣ 2ኛ ተከሳሽን በ4 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኗል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
"ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል ርዕስ ለፕላንና ልማት ዘርፍ አመራሮች ስልጠና እየተሠጠ ይገኛል

***

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 5/2017 ዓ.ም አዳማ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን “ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት” በሚል ርዕስ ለፕላንና ልማት ዘርፍ አመራሮች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ ክብርት ጥሩማር አባተ ሙስና የአንድን አገር መልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ እድገት እና የሰብአዊ መብት መከበር በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዳ፣ ሐቀኝነትን በማጓደል የሕገወጥነትን ባህሪ የሚያላብስ እና ሀገርን ሊበትን የሚችል አለምአቀፋዊ ወንጀል ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ሙስና በዓለም አቀፍ፣ በአህጉር አቀፍ እና በሀገር ደረጃ እያስከተለ ያለው ችግር በጣም ከባድና ውስብስብ እየሆነ መምጣቱን አመላክተዋል።

እንደ መንግስትም ሙስና የሚያስከትለውን የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ በመረዳት ችግሩ የከፋ ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት በርካታ አሰራርና ህጎችን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ሚንስትር ዴኤታዋ አክለውም ሁላችንም ብልሹ አሠራርን ለመታገል ከኔ በላይ ማንም የለም በሚል ስሜት ንቅናቄውን መቀላቀልና ከሌሎች በተሻለና ከፍ ባለ ሁኔታ ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት ለሀገር ዕድገትና ለህዝቦች ተጠቃሚነት ፀር የሆነውን ሙስና በጋራ መከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል።

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ፈቃዱ ሰቦቃ ስልጠናው ሲሰጥ የነበረው የሙስና ምንነት፣ አስፈላጊነትና መከላከያ ዘዴዎች መሆኑን አስታውሰው፥ አሁን ግን ዘርፍ ተኮር አሰራርን በመከተል በዘርፋ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ዳሰሳ ጥናት መነሻነት የሚሰጥ ስልጠና ነው ብለዋል።

ለዚህም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተወጣጡ ሙሁራን በተዘጋጁ የማሰልጠኛ ሞጅሎች የሚሰጥ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሆኑንም ጠቁመዋል።

ስልጠናው በመጀመሪያው ዙር ለዘርፋ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው፥ በቀጣይም በየደረጃው ለሚገኙ መካከለኛ አመራሮችና ሠራተኞች የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም አንድ ተቋም ውጤታማ የሚሆነው የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች በሥነምግባር አርዓያ ሲሆኑ መሆኑን ገልፀው፥ ለዚህም አመራሩ የተሰጣቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በዘርፋ የብልሹ አሰራር ችግሮች ሲኖሩም ችግር ፈጣሪዎችን ተጠያቂ በማድረግ ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።

ስልጠናው በዶ/ር ዮሐንስ ጴጥሮስ፣ በዶ/ር አራጋው እሸቴ እና በዶ/ር በለጠ ደበበ እየተሰጠ ሲሆን፣ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319