Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የትምህርት ተቋማት ከመደበኛ የመማር ማስተማር ጎን ለጎን ሥነምግባር እና ሞራል ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ

******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የትምህርት ተቋማት ከመደበኛ የመማር ማስተማር ጎን ለጎን ሥነምግባር እና ሞራል ላይ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ይህን ያሉት በትላንትናው ዕለት 21ኛው ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የማጠቃለያ መድረክ ‘‘ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!'' በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት በተከበረበት ወቅት ነው፡፡

በመርኃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፥ የሙስና ወንጀል የቆዩ ማህበራዊ ጥሪቶችና ወረቶችን የሚያሽመደምድ እና ከድህነት የመውጣት ተስፋን የሚያቀጭጭ በመሆኑ የጋራ ትግል ይጠይቃል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ለሙስና ባህላዊና ሃሳባዊ ሽፋን ሲሰጠው መቆየቱን አስታውሰው፣ ወንጀሉ ከሚያስከትለው ውስብስብ ችግር አንጻር በመደበኛ ክስ እና ምርመራ ለመፍታት ቀላል አለመሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም የሙስና ወንጀልን በተቋማዊ አሰራር በጽናት መታገልና በዘላቂነት መከላከል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በሁሉም ረገድ ልማትን በማስቀጠል ብልፅግናዋን እውን ለማድረግ እየሰራች መሆኑን ገልፀው፣ ለዚህ ዋነኛ እንቅፋት የሆነውን ሙስና መከላከልና መታገል ተገቢ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ መሻት እውን እንዲሆን በዋነኝነት ወጣቶችን መሰረት ያደረገ አሰራር በመዘርጋት ዘላቂ ልማትና እድገትን ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑንም ተናግረዋል።

የትምህርት ተቋማት ከመደበኛ የመማር ማስተማር ጎን ለጎን ሥነምግባር እና ሞራል ላይ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም ፕሬዝዳንቱ አስገንዝበዋል።

የመገናኛ ብዙሃንም ሙስናን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የላቀ ሚናቸውን መወጣት ይገባቸዋል ብለዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የሙስና እና ሥነምግባር ችግሮችን መቀነስ የሚቻለው በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ጭምር ነው

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሙስና እና ሥነ-ምግባር ችግሮችን መቀነስ የሚቻለው በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ጭምር መሆኑን የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ገለጸ፡፡

የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ፍቃዱ ሰቦቃ ኮሚሽኑ ሙስናን ለመከላከል በተቋማት መካከል ትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ ማኅበራዊ ቀውስ እንዲስፋፋ ጉልህ ድርሻ የሚጫወቱትን የሙስና እና ሥነ-ምግባር ችግሮች መቀነስ የሚቻለው በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ጭምር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በዜጎች ስብዕና እና ሥነምግባር ግንባታ ላይ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የሥነምግባር ግንባታን በተመለከተ ለተቋማት የሚሰጡ ስልጠናዎች ሙስናን በመከላከል ረገድ ውጤት እያስገኙ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የሙስና መከላከል ስራውን መሰረት ለማስያዝ 25 ዘርፎች ተለይተው የሥነምግባር ግንባታ ስልጠናና አቅም መገንቢያ ማኑዋሎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ማኑዋሎቹ በመንግሥት ስልጣን ያለ አግባብ መጠቀም፣ ብልሹ አሰራር፣ ብክነትና የሥነምግባር ጉድለት፣ ሌብነት፣ ምዝበራና የሙስና ባህርያት፣ ምልክቶችና ተጋላጭነት ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋም ተልዕኮ ስኬት ወሳኝ ነው

*******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 03/2017 ዓ.ም አዳማ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለሚኒስቴር መስሪያቤቱና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ‘‘ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት’’ በሚል ርዕስ በአዳማ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት የግብርና ሚኒስቴር እንስሳት እና ሀብት ሚንስትር ድኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) በግብርናው ዘርፍ ስኬት ለማምጣት በሄድነው ልክ፣ መልካም አሰተዳደር እና ሙስናን መከላከል ላይ በቁርጠኝነት መታገል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

እንደዘርፍ ሙስናን ከመከላከል ባሻገር በአመት ሶስት ግዜ ማምረት የተቻለበት ወቅት በመሆኑ የተሻለ ምርታማነትን ለማምጣት አመራሩ እራሱን በሥነምግባር በማነጽ አምራች ዜጋን መፍጠር ይኖርብናል ብለዋል።

ሚንስትር ድኤታ አክለውም የግብርና ስራችንን ውጤታማ ለማድረግ እንደነዚህ አይነት አቅም የሚገነቡ ስልጠናዎችን መውሰድ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በስልጠናዉ የተገኙት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፈቃዱ ሰቦቃ ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋም ተልዕኮ ስኬት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፣ ሙስና ለመከላከል ትውልድን የሚገነባ የሥነምግባር ስልጠናዎችን መውሰድ ሲቻል እንደሆነ ጠቁመዋል።

ስልጠናው የሙስና ስጋት ዳሰሳዊ ጥናት ግኝት መነሻ ተደርጎ፣ የብልሹ አሰራር መገለጫዎችና ምልክቶቹን በማየት የሙስና እና ብልሹ አሰራር መከላከያ ስልቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አመራሩ እራሱን ከሙስና እና ብልሹ አሰራር በማራቅ ከመንግስትና ከህዝብ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልኮ መወጣት እንደሚገባ አሳስበው፣ እንደዘርፍ በተቋም ለሚፈጠሩ አስተዳደራዊ ችግሮች በራሱ አቅም እርምጃ የመውሰድ እና የማስወሰድ ግዴታ እንዳለውም ጠቁመዋል።

የሙስና መከላከል ስራው መሰረት እንዲኖረው ለማድረግ 26 ዘርፎች ተለይተው የሥነምግባር ግንባታ ስልጠናና አቅም መገንቢያ ማሰልጠኛ ሞጅሎች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም በትቂት ግለሰቦች ብልሹ አሰራር ተቋማት እና የንፁሃን ግለሰቦች ስም መጥፋት እንደሌለበት ገልፀው፣ አመራሩ እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎች በትኩረት በመውሰድ ተቋምንና ሠራተኛውን በሥነምግባር ማብቃት አለበት ብለዋል፡፡

ምክትል ኮሚሽነሩ አያይዘውም የተጀመሩ የሙስና መከላከል ስራዎች በማጠናከር ዘርፉን በግልፅነትና ተጠያቂነት ለመምራት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በሙስና መከላከል ሂደት ውስጥ አመራሩና ፈፃሚ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ ስልጠና መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።

ስልጠናው በዶ/ር ተስፋዬ ሂርጳሳ እየተሰጠ ሲሆን፣ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በ2016 በጀት ዓመት በፀረ-ሙስና ትግል የተሻለ ጥረት ያደረጉ የክልል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች

*******************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሙስና ወንጀልን በተቋማዊ አሰራር በጽናት መታገልና በዘላቂነት መከላከል ይገባል - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ
*******************
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በኮሚሽኑ የሚዘጋጀው የህዳር ወር የአስራ አምስት ቀን የፀረ-ሙስና ዲጂታል ጋዜጣ

*******************

የዲጂታል ፀረ-ሙስና የጋዜጣውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ሊኩን ያስፈጥሩ...https://drive.google.com/file/d/1rd-3GaBE5yinMBgJlpg0lymp4gOfNf3p/view?usp=sharing

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319