Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የትምህርት ተቋማት ከመደበኛ የመማር ማስተማር ጎን ለጎን ሥነምግባር እና ሞራል ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ

******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 2/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተገኙበት 21ኛው ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የማጠቃለያ መድረክ ‘‘ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!'' በሚል መሪ ሀሳብ በአድዋ ሙዚየም መታሰቢያ አዳራሽ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡

በመርኃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፥ የሙስና ወንጀል የቆዩ ማህበራዊ ጥሪቶችና ወረቶችን የሚያሽመደምድ እና ከድህነት የመውጣት ተስፋን የሚያቀጭጭ በመሆኑ የጋራ ትግል ይጠይቃል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ለሙስና ባህላዊና ሃሳባዊ ሽፋን ሲሰጠው መቆየቱን አስታውሰው፣ ወንጀሉ ከሚያስከትለው ውስብስብ ችግር አንጻር በመደበኛ ክስ እና ምርመራ ለመፍታት ቀላል አለመሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም የሙስና ወንጀልን በተቋማዊ አሰራር በጽናት መታገልና በዘላቂነት መከላከል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በሁሉም ረገድ ልማትን በማስቀጠል ብልፅግናዋን እውን ለማድረግ እየሰራች መሆኑን ገልፀው፣ ለዚህ ዋነኛ እንቅፋት የሆነውን ሙስና መከላከልና መታገል ተገቢ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ መሻት እውን እንዲሆን በዋነኝነት ወጣቶችን መሰረት ያደረገ አሰራር በመዘርጋት ዘላቂ ልማትና እድገትን ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑንም ተናግረዋል።

የትምህርት ተቋማት ከመደበኛ የመማር ማስተማር ጎን ለጎን ሥነምግባር እና ሞራል ላይ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም ፕሬዝዳንቱ አስገንዝበዋል።

የመገናኛ ብዙሃንም ሙስናን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የላቀ ሚናቸውን መወጣት ይገባቸዋል ነው ያሉት።

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ) በበኩላቸው ትውልድን በሥነ-ምግባር በመቅረጽ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና እንዲረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽነር ሳሙኤል በመድረኩ ላይ እንዳሉት ኮሚሽኑ በሥነ-ምግባር ግንባታና ሙስና በመከላከል ረገድ ጠንካራ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

ይሁን እንጂ ሕግን በማስከበር በኩል የተሰራው ሥራ ውስንነት የታየበት በመሆኑ በቀጣይ ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራበታል ብለዋል።

ሙስና ትውልድን የሚገድልና አገር እንዳትበለጽግ የሚያደርግ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ይህን ከወዲሁ መግታት እንደሚገባ አስምረውበታል።

በመሆኑ ትውልድን በሥነ-ምግባር በመቅረጽ ለኢትዮጵያ ብልጽግና መሳካት ኮሚሽኑ በዚህ ላይ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

እየተደረገ ያለው የፀረ-ሙስና ትግል አሁን ላይ ተስፋ ሰጭ መሆኑን ኮሚሽነሩ ጠቅሰው፣ ትግሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

ሙስናን የመከላከል ሥራ ለመንግሥት ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ሁሉም የጋራ አጀንዳ ሊያደርገው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል። ሥምምነቱ በሥነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ ለመገንባት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ከሥምምነቱ በኋላ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ባደረጉት ንግግር፤ ከቤተሰብ ጀምሮ በልጆችና ታዳጊዎች ላይ በመስራት ሙስናን አምርሮ የሚታገል ትውልድ መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።

በሥነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ ግንባታ ላይ በማተኮር ለሀገር ልማትና እድገት ጥሩ መሰረት ማኖር አስፈላጊ መሆኑን አንስተው፣ ለዚህም በጋራ መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የመገንባት ጥረቱ እውን የሚሆነው ሙስናን የሚጠየፍና በፅኑ የሚታገል ትውልድ መገንባት ሲቻል ነው ብለዋል።

በመሆኑም በጥሩ ስብእና የተገነባ ትውልድ የመፍጠር ጥረቱ በልዩ ትኩረት የሚሰራበት መሆኑን ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል።

ኮሚሽኑ በዕለቱ ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር የሥነምግባር ሥልጠና የበይነመረብ ሲስተም ፕሮጀክት ሥራ ላይ የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ሥነስርዓት አካሂዷል፡፡

በመድረኩ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የለማውን የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዲጂታል አሠራር ሥርዓትን በመመረቅ የሥራ ማስጀመሪያ ሥነስርዓት ተካሄዳል።

እንዲሁም በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ የፀረ-ሙስና ትግል እንቅስቃሴ ለነበራቸው ዘርፎች፣ ለክልል እና ከተማ አስተዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች እንዲሁም ለሚዲያ ተቋማት ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል።

በመድረኩ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ የምክር ቤት አባላት፣ የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች፣ ሚኒስትሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሙስናን የሚፀየፍና በሥነምግባር የታነጸ ትውልድ ለመፍጠር የተቀናጀ ርብርብ ያስፈልጋል

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 2/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሙስናን የሚፀየፍና በሥነምግባር የታነጸ ትውልድ ለመፍጠር የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የ21ኛው ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የማጠቃለያ መድረክ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተገኙበት 21ኛው ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የማጠቃለያ መድረክ በአድዋ መታሰቢያ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የትምህርት እና ስልጠና ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሙክታር ሁሴንም ሙስናን የሚጠየፍና በሥነምግባር የታነጸ ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት መገናኛ ብዙሃን ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።

በዘርፉ የተጀመሩ ስራዎች ውስንነት እንዳለባቸው ገልጸው፥ በቀጣይ የመገናኛ ብዙሃን ዋና የትኩረት አቅጣጫ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል በበኩላቸው መንግስት እና የሃይማኖት ተቋማት አብረው ሊሰሩባቸው ከሚችሉ ጉዳዮች መካከል ትልቁ ሥነምግባር መሆኑን ተናግረዋል።

ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በመተባበርና የማስተማሪያ ስልቶችን በመንደፍ ሥነምግባርን ከቃላት አጠቃቀም አንስቶ እንዲረዱ ለማስቻል በትብብር መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።


በኮሚሽኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥልጠና መሪ ስራ አስፈጻሚ ሐረጎት አብርሃ በበኩላቸው ወጣቶች የተጠያቂነት ስሜትንና የእኔነትን ባህል እንዲያዳብሩ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

መልካም ነገሮችን ማስቀጠል፣ መልካም ያልሆኑ ተግባራትን ደግሞ ማረም እንደሚገባ የገለጹት ደግሞ ቀሲስ መዝገቡ ካሳ(ዶ/ር) መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሥነምግባርን የሚያጎለብቱ ስራዎችን በስፋት መስራት፣ ሙስናን የሚያበረታቱ ነገሮችን ማረም እና ማስተካከል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የትምህርት ተቋማት ከመደበኛ የመማር ማስተማር ጎን ለጎን ሥነምግባር እና ሞራል ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ

******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የትምህርት ተቋማት ከመደበኛ የመማር ማስተማር ጎን ለጎን ሥነምግባር እና ሞራል ላይ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ይህን ያሉት በትላንትናው ዕለት 21ኛው ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የማጠቃለያ መድረክ ‘‘ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!'' በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት በተከበረበት ወቅት ነው፡፡

በመርኃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፥ የሙስና ወንጀል የቆዩ ማህበራዊ ጥሪቶችና ወረቶችን የሚያሽመደምድ እና ከድህነት የመውጣት ተስፋን የሚያቀጭጭ በመሆኑ የጋራ ትግል ይጠይቃል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ለሙስና ባህላዊና ሃሳባዊ ሽፋን ሲሰጠው መቆየቱን አስታውሰው፣ ወንጀሉ ከሚያስከትለው ውስብስብ ችግር አንጻር በመደበኛ ክስ እና ምርመራ ለመፍታት ቀላል አለመሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም የሙስና ወንጀልን በተቋማዊ አሰራር በጽናት መታገልና በዘላቂነት መከላከል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በሁሉም ረገድ ልማትን በማስቀጠል ብልፅግናዋን እውን ለማድረግ እየሰራች መሆኑን ገልፀው፣ ለዚህ ዋነኛ እንቅፋት የሆነውን ሙስና መከላከልና መታገል ተገቢ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ መሻት እውን እንዲሆን በዋነኝነት ወጣቶችን መሰረት ያደረገ አሰራር በመዘርጋት ዘላቂ ልማትና እድገትን ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑንም ተናግረዋል።

የትምህርት ተቋማት ከመደበኛ የመማር ማስተማር ጎን ለጎን ሥነምግባር እና ሞራል ላይ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም ፕሬዝዳንቱ አስገንዝበዋል።

የመገናኛ ብዙሃንም ሙስናን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የላቀ ሚናቸውን መወጣት ይገባቸዋል ብለዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የሙስና እና ሥነምግባር ችግሮችን መቀነስ የሚቻለው በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ጭምር ነው

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሙስና እና ሥነ-ምግባር ችግሮችን መቀነስ የሚቻለው በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ጭምር መሆኑን የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ገለጸ፡፡

የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ፍቃዱ ሰቦቃ ኮሚሽኑ ሙስናን ለመከላከል በተቋማት መካከል ትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ ማኅበራዊ ቀውስ እንዲስፋፋ ጉልህ ድርሻ የሚጫወቱትን የሙስና እና ሥነ-ምግባር ችግሮች መቀነስ የሚቻለው በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ጭምር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በዜጎች ስብዕና እና ሥነምግባር ግንባታ ላይ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የሥነምግባር ግንባታን በተመለከተ ለተቋማት የሚሰጡ ስልጠናዎች ሙስናን በመከላከል ረገድ ውጤት እያስገኙ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የሙስና መከላከል ስራውን መሰረት ለማስያዝ 25 ዘርፎች ተለይተው የሥነምግባር ግንባታ ስልጠናና አቅም መገንቢያ ማኑዋሎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ማኑዋሎቹ በመንግሥት ስልጣን ያለ አግባብ መጠቀም፣ ብልሹ አሰራር፣ ብክነትና የሥነምግባር ጉድለት፣ ሌብነት፣ ምዝበራና የሙስና ባህርያት፣ ምልክቶችና ተጋላጭነት ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319