Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት እየተከበረ ነው

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 2/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሀገር አቀፍ ደረጃ 21ኛውን አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ''ወጣቶችን ያመከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!'' በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እያከበረ ይገኛል።

በበዓሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽነሮች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎችና የኮሚሽኑ ሠራተኞች እየተሳተፋ ነው።

በፕሮግራሙ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መልዕክት የሚያስተላልፋ ሲሆን፥ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዲጂታል አሠራር ሥርዓትን በመመረቅ የሥራ ማስጀመሪያ ሥነስርዓት ይካሄዳል።

ኮሚሽኑ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በወጣቶች ስብዕና ግንባታ እና ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር የሥነምግባር ሥልጠና የበይነመረብ ስይስተም ፕሮጀክት ሥራ ላይ የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ሥነስርዓት እንደሚያካሄድ ከመርሃ ግብሩ ተመላክቷል።

እንዲሁም በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ የፀረ-ሙስና ትግል እንቅስቃሴ ለነበራቸው ዘርፎች፣ ለክልል እና ከተማ አስተዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች እንዲሁም ለሚዲያ ተቋማት ዕውቅና እና ሽልማት ይሰጣል።

በመድረኩ ወጣቶች በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ እና በፀረ-ሙስና ትግሉ ያላቸውን ሚና እና ኃላፊነት እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319