ሌብነት የልማት፣ የእኩልነትና የፈትሃዊነት ጠላት ነው - አቶ መልካሙ ጌትነት
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ 21ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ መልዕክት ከተለያዩ ተቋማት ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር አክብረዋል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መልካሙ ጌትነት መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ ሌብነት ከባህላችንም ሆነ ከእሴታችን ያፈነገጠ፣ በህግም ሆነ በፈጣሪ ያልተቀደ፣ በየትኛውም አሰራር ብንመዝነው ቀይ መስመር የሆነ ተግባር ነው ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት ሙስና በብሔር፣ በዘር፣ በሀይማኖትና በፖለቲካ ሰበብ በመደራጀት የዘረፋ ወንጀል እየተፈፀመ ነው ያሉት አቶ መልካሙ፥ ሌብነት የልማት፣ የእኩልነትና የፍትሃዊነት ጠላት በመሆኑ ሁሉም አካል ያለርህራሄ አምርሮ ሊታገለው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የአብክመ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ባለሙያ አቶ ዘላለም ንጉሴ የውይይት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፥ በሥነምግባር ግንባታና ግብረገብ ምንነት፣ በሥነምግባር ጥሰትና ብልሹ አሰራሮች ዙሪያ፣ የሙስና ወንጀል ውስብስብነት፣ የሥነምግባርና ሙስና መፍተሔዎችና ለውጦች፣ የመንግስት ሰራተኞችና የአመራሩ ሚና በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ አድርገው አቅርበዋል።
ተሳታፊዎችም በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተው፥ በአመራሮች ምላሽና ማብራሪያ መሰጠቱን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት እየተከበረ ነው
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 2/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሀገር አቀፍ ደረጃ 21ኛውን አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ''ወጣቶችን ያመከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!'' በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እያከበረ ይገኛል።
በበዓሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽነሮች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎችና የኮሚሽኑ ሠራተኞች እየተሳተፋ ነው።
በፕሮግራሙ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መልዕክት የሚያስተላልፋ ሲሆን፥ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዲጂታል አሠራር ሥርዓትን በመመረቅ የሥራ ማስጀመሪያ ሥነስርዓት ይካሄዳል።
ኮሚሽኑ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በወጣቶች ስብዕና ግንባታ እና ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር የሥነምግባር ሥልጠና የበይነመረብ ስይስተም ፕሮጀክት ሥራ ላይ የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ሥነስርዓት እንደሚያካሄድ ከመርሃ ግብሩ ተመላክቷል።
እንዲሁም በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ የፀረ-ሙስና ትግል እንቅስቃሴ ለነበራቸው ዘርፎች፣ ለክልል እና ከተማ አስተዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች እንዲሁም ለሚዲያ ተቋማት ዕውቅና እና ሽልማት ይሰጣል።
በመድረኩ ወጣቶች በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ እና በፀረ-ሙስና ትግሉ ያላቸውን ሚና እና ኃላፊነት እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።