ከ132 ሚሊየን ብር በላይ በታክስ ማጭበርበር የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከ132 ሚሊየን ብር በላይ በታክስ ማጭበርበርና መሰወር የተጠረጠሩ 3 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አብዱሰላም መሃመድ÷ሕግን ለማስከበር በተሰራው ሥራ በታክስ ማጭበርበርና መሰወር ወንጀል የተጠረጠሩ 3 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡
የታክስ ማጭበርበርና መሰወር ወንጀል መፈፀማቸው በኦዲት የተደረሰባቸው ግለሰቦች በወንጀል ምርመራ በኩል የወንጀል ምርመራ ተደርጐባቸው እንዲከሰሱ የተላለፈ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በታክስ አስተዳደር አዋጅ ሕግ መሰረት የተጭበረበረና ሀሰተኛ ግብይት የተፈጸመባቸው ሂሳባቸው ውድቅ ተደርጎ እንደገና እየተሰራ መሆኑንና በቀጣይ በሕግ የሚጠየቁበት ሂደት መኖሩ ተጠቁሟል፡፡
ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል 132 ሚሊየን 443 ሺህ 47 ብር በተቋሙና በመንግስት ገቢ ላይ ጉዳት ማድረሱንም የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ሀሰተኛ ሰነዶችን ለግለሰቦች ሲያከፋፍል የነበረ የጥበቃ ሠራተኛ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ግለሰቡ ህገ-ወጥ ተግባሩን የሚፈፅመው በሚያርፍበት የጥበቃ ቤት ውስጥ መሆኑ ታውቋል።
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ለቡ አካባቢ ነው። ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ለግለሰቦች እንደሚያሠራጭ መረጃ የደረሰው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጥቆማውን መነሻ በማድረግ ተጠርጣሪውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል።
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ የፍርድቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ወረዳ1 ለቡ አካባቢ ከሚገኝ እና ጥበቃ እንዲሠራ በተረከበው ጅምር ቤት ውስጥ ብርበራ በሚደርገበት ወቅት 93 ሀሰተኛ የቤት ካርታ፣ 13 ክብ ማህተም፣ 91ሀሰተኛ የቀበሌ መታወቂያዎች፣ 2 የኃላፊ ቲተር የተያዘ መሆኑን የንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
የህገ-ወጦች የወንጀል አፈፃፀም ስልት ምንም እንኳን ድብቅና የተወሳሰበ ቢሆንም ከህዝብ ዓይን የሚሰወር እንደሌለ ያስታወቀው ፖሊስ ሁለተኛ ተጠርጣሪን ለመያዝ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ገልጿል።
የህገ-ወጥ ሰነዶች መበራከት የሚያስከትለውን ሀገራዊ ጉዳት በመገንዘብ ሀሰተኛ ሰነዶችን የሚያዘጋጁ እና የሚጠቀሙ ግለሰቦችን በመለየት መረጃ በመስጠትና በህግ እንዲጠየቁ በማድረግ ረገድ ህብረተሰቡ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።

ሌብነት የልማት፣ የእኩልነትና የፈትሃዊነት ጠላት ነው - አቶ መልካሙ ጌትነት
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ 21ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ መልዕክት ከተለያዩ ተቋማት ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር አክብረዋል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መልካሙ ጌትነት መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ ሌብነት ከባህላችንም ሆነ ከእሴታችን ያፈነገጠ፣ በህግም ሆነ በፈጣሪ ያልተቀደ፣ በየትኛውም አሰራር ብንመዝነው ቀይ መስመር የሆነ ተግባር ነው ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት ሙስና በብሔር፣ በዘር፣ በሀይማኖትና በፖለቲካ ሰበብ በመደራጀት የዘረፋ ወንጀል እየተፈፀመ ነው ያሉት አቶ መልካሙ፥ ሌብነት የልማት፣ የእኩልነትና የፍትሃዊነት ጠላት በመሆኑ ሁሉም አካል ያለርህራሄ አምርሮ ሊታገለው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የአብክመ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ባለሙያ አቶ ዘላለም ንጉሴ የውይይት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፥ በሥነምግባር ግንባታና ግብረገብ ምንነት፣ በሥነምግባር ጥሰትና ብልሹ አሰራሮች ዙሪያ፣ የሙስና ወንጀል ውስብስብነት፣ የሥነምግባርና ሙስና መፍተሔዎችና ለውጦች፣ የመንግስት ሰራተኞችና የአመራሩ ሚና በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ አድርገው አቅርበዋል።
ተሳታፊዎችም በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተው፥ በአመራሮች ምላሽና ማብራሪያ መሰጠቱን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት እየተከበረ ነው
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 2/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሀገር አቀፍ ደረጃ 21ኛውን አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ''ወጣቶችን ያመከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!'' በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እያከበረ ይገኛል።
በበዓሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽነሮች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎችና የኮሚሽኑ ሠራተኞች እየተሳተፋ ነው።
በፕሮግራሙ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መልዕክት የሚያስተላልፋ ሲሆን፥ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዲጂታል አሠራር ሥርዓትን በመመረቅ የሥራ ማስጀመሪያ ሥነስርዓት ይካሄዳል።
ኮሚሽኑ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በወጣቶች ስብዕና ግንባታ እና ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር የሥነምግባር ሥልጠና የበይነመረብ ስይስተም ፕሮጀክት ሥራ ላይ የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ሥነስርዓት እንደሚያካሄድ ከመርሃ ግብሩ ተመላክቷል።
እንዲሁም በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ የፀረ-ሙስና ትግል እንቅስቃሴ ለነበራቸው ዘርፎች፣ ለክልል እና ከተማ አስተዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች እንዲሁም ለሚዲያ ተቋማት ዕውቅና እና ሽልማት ይሰጣል።
በመድረኩ ወጣቶች በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ እና በፀረ-ሙስና ትግሉ ያላቸውን ሚና እና ኃላፊነት እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።