በለውጡ ሂደት በፀረ-ሙስና ትግል የተገኘው ውጤት ዘላቂ እንዲሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
******************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በለውጡ ሂደት በፀረ-ሙስና ትግል የተገኘው ውጤት ዘላቂ እንዲሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 21ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ ከተማ አቀፍ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።
እለቱም ''ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገ ስብዕና ይገነባል!'' በሚል መሪ ሀሳብ የተከበረ ሲሆን፥ የመዲናዋ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ ወጣቶችና የተለያዩ ማህበራት ተሳትፈዋል።
በሀገር፣ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሙስና ያለበት ደረጃ ላይ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ሙስናን በመከላከሉ ረገድ የተዘረጉ አሰራሮች አወንታዊ ውጤት እያመጡ መሆኑን ተናግረዋል።
ለአብነትም ህዝቡን በማሳተፍ በተከናወኑ ተግባራት ሕግ የተላለፉ በርካታ ሰዎችን ተጠያቂ ማድረግ መቻሉን ጠቁመው፥ ፕሮጀክቶች ላይ ውጤታማ አፈጻጸም መታየቱ ከስራዎች ውጤቶች መካከል ነው ብለዋል።
በትምህርት እንዲሁም በሃይማኖት ተቋማት በኩል ሙስናን በተመለከተ ትውልድ የማነጹ ስራ ከፍተኛ ርብርብ ይጠይቃል ነው ያሉት።
የሙስና ወንጀልን መከላከል ለመንግስት አካል ብቻ የሚተው አይደለም ያሉት ከንቲባዋ፥ በለውጡ ሂደት በፀረ-ሙስና ትግል የተገኘው ውጤት ዘላቂ እንዲሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ፤ ኮሚሽኑ ተቋቁሞ ወደ ስራ ከገባበት 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሙስናን ለመከላከል የሚረዱ ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
የዜጎችን ግንዛቤ ማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰው፥ የተቋማትን የሙስና ተጋላጭነት በተመለከተ ጥናቶች መካሄዳቸውን አስረድተዋል።
በጥናቱ መሰረት ከተቋማት ጋር ውይይት በማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ማመላከቱን ገልጸው፥ በዚህም ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል።
ኮሚሽኑ ሙስናን ለመከላከል የሚረዱ ህግና መመሪያዎች ከማውጣት ጀምሮ የተቋማት አቅም ግንባታ ስልጠናዎችም ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑን አብራርተዋል።
ከውይይት ተሳታፊዎች መካከል አቶ ንጉሴ ደግፌ፤ የሙስና ወንጀልን ከመሰረቱ ለመግታት የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
እኔ እንደ ዜጋ ሃላፊነቴን እውጣለሁ የሚለው አስተሳሰብ ሊጎለብት ይገባል ሲሉም ነው የገለጹት።
ሌላኛው ተሳታፊ ኑሪ መሀመድ፤ አገልግሎትን በሙስና ሳይሆን በህጋዊ መንገድ ብቻ ማግኘት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ለዜጎች የማስገንዘቡ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በከተማ ደረጃ በፀረ-ሙስና ትግሉ እስከ ብሎክ ድረስ በመወረድ የዜጎችን ግንዛቤ የማስፋቱ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
አባገዳ ታከለ ጨመዳ በበኩላቸው በመዲናዋ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎች ስኬት የሚያበረታቱ መሆናቸውን አንስተው፥ በስኬት ሊቀጥሉ የሚችሉት ሙስናን መከላከል ሲቻል በመሆኑ ሁላችንም ወንጀሉን መከላከልና መታገል ይጠበቅብናል ብለዋል።
በበዓሉ አከባበር ላይ ኮሚሽኑ ለሚያከናውናቸው የፀረ-ሙስና ትግል አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና መሰጠቱን ኢዜአ ዘግቧል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

የሀሰት የወንጀል ምርመራ መዝገብ አደራጅተው ከባለሃብት ገንዘብ ተቀብለዋል የተባሉ ፖሊሶች ተከሰሱ
******************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሀሰተኛ የወንጀል ምርመራ መዝገብ በማደራጀት አንድን ባለሃብት በማስፈራራት ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ተቀብለዋል የተባሉ አራት በአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እና ሁለት ግለሰቦች ላይ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ።
ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
በፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ክስ ያቀረበባቸው ተከሳሾች 1ኛ በግል ስራ የሚተዳደረው መኩሪያ ማሞ ወይም (መስፍን ማሞ)፣ 2ኛ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የቂሊንጦ ፖሊስ ጣቢያ የክትትል ቲም ሀላፊ ኢንስፔክተር ዘለቀ ጥላሁን፣ 3ኛ በፖሊስ ጣቢያው የወንጀል መርማሪ ረዳት ኢንስፔክተር ዘውዴ አሰግደው፣ 4ኛ በፖሊስ ጣቢያው የወንጀል መርማሪ ዋ/ሳጅን መለሰ ማርቆስ፣ 5ኛ በፖሊስ ጣቢያው የክትትል አባል ምክትል/ሳጅን አጅቦ ተፈሪ እና 6ኛ በግል ስራ የሚተዳደረው ተገኔ ሀ/ማርያም ወልዴ ናቸው።
ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ)፣ አንቀጽ 33 እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና ንዑስ ቁጥር (2) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ጠቅሶ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።
በዚህም ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተከሳሾች የመንግስት ስራ ላይ በመስራት ላይ እያሉ ከ1ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች ጋር በመመሳጠር የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም በሌላ ሰው ጥቅም ላይ ጉዳት እንዲደርስ ለማድረግ በማሰብ የግል ተበዳይ የሆነው ባለሃብት ግለሰብ ላይ 1ኛ ተከሳሽ ሀሰተኛ የወንጀል ጥቆማ አቅራቢ ሆኖ ፖሊስ ጣቢያ ቀርቦ ጥቆማ ያቀረበ በማስመሰል ከ2ኛ እስከ 5ኛ የተጠቀሱ ተከሳሾች ከህጋዊ አሰራር ውጭ የምርመራ መዝገብ እንዲደራጅ አድርገው እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል
በዚህም ግለሰቡን አስረው “የወንጀል ምርመራው እንዲቋረጥልህ ገንዘብ መክፈል አለብህ” በማለት አስፈራርተው የግል ተበዳዩ ለጊዜው ባልተያዘ ምስጋና ዓለሙ በተባለ ግለሰብ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ የሂሳብ ቁጥር በነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም 180 ሺህ ብር፣ በመስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም 300 ሺህ ብር ገቢ እንዲያደርግላቸው ማስገደዳቸው በክሱ ዝርዝር ላይ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም ለጊዜው ባልተያዘ ለማ ባጃ በተባለ ግለሰብ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ ሂሳብ በመስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም 200 ሺህ ብር ገቢ ያስደረጉ በመሆኑን በክሱ ዝርዝር ላይ የተገለጸ ሲሆን፤ በጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ደግሞ በ3ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች አማካኝ የግል ተበዳዩን ከህግ አግባብ ውጭ በጣቢያው አስረው ካቆዩ በኋላ በ4ኛ ተከሳሽ ስም ከአዋሽ ባንክ በተከፈተ ሂሳብ 200 ሺህ ገቢ ያስደረጉ መሆኑ በክሱ መገለፁን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
በ6ኛ ተከሳሽ ስም ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ 300 ሺህ ብር ገቢ ካስደረጉ በኋላ ከዚሁ ገንዘብ ላይ በ4ኛ ተከሳሽ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ 200 ሺህ ብር ማስተላለፋቸው ተጠቅሷል።
ከዚሁ ገንዘብ ላይ ደግሞ ለ3ኛ ተከሳሽ እና ለ2ኛ ተከሳሾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳባቸው ለእያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር የተላለፈላቸው መሆኑ በክሱ ተዘርዝሯል።
ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱ የሚያስገኘውን አጠቃላይ ውጤት በመቀበል በሀሰተኛ የምርመራ የወንጀል መዝገብ በማደራጀት ግለሰቡን ከህግ ውጪ በማሰር በአጠቃላይ ከግል ተበዳዩ 1 ሚሊዮን 180 ሺህ ብር በመቀበል ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ መሆኑ ተጠቅሶ በልዩ እና ዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል በመፈጸም ክስ ቀርቦባቸዋል።
ዐቃቤ ሕግ ከክሱ ጋር የሰውና የሰነድ ማስረጃ ዝርዝር አያይዞ ያቀረበ ሲሆን ተከሳሾቹ ችሎት ቀርበው የክሱ ዝርዝር እንዲደርሳቸው ከተደረገ በኋላ የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅ ፍርድ ቤቱ ለታህሳስ 4 ቀን 2017 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በየአማራ ክልል ግብርና ቢሮ "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፤ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ መልዕክት የፀረ-ሙስና ቀንን አከበሩ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፤ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ መልዕክት የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የቢሮ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በዛሬው እለት በፓናል ውይይት አክብረዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) የፀረ-ሙስና ቀን ስናከብር መሪ ቃሉን በዕለቱ ከማሰብ ባለፈ የሙስናን አስከፊነትና በሀገራችን ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እያስከተለ ያለውን ከፍተኛ ጉዳት በመረዳት በፀረ-ሙስና ትግሉ ባለቤትና ቁርጠኛ ሁነን በኃላፊነት ስሜት ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ለመታገል ቃል የምንገባበት ቀን ነው ብለዋል፡፡
የቢሮው ኃላፊ አክለውም ሙስናን ለመከላከል አሰራር በመዘርጋት፣ የአመለካከት ግንባታ በማድረግና በማስረጃ ላይ ተመስርቶ ተጠያቂነት ማስፈን ያስፈልጋል ብለዋል።
የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምሳሉ ጎባው የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡ ሲሆን፥ የሙስና ምንነት፣ መሰረታዊ መንስኤዎችና አባባሽ ምክንያቶች እንዲሁም ሙስና የሚያስከትላቸው ጉዳቶች፣ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ዋና ዋና ገፅታዎችና ሙስናን ለመከላከል የመንግስት ሠራተኞች የሚና በሚሉ ጉዳዮችን በዝርዝር አቅርበዋል።
በመነሻ ጽሑፉ ዘርዘር ያሉ ሀሳቦች የተብራሩ ሲሆን፥ ከመነሻ ጽሑፉ በመነሳትም ከተሳታፊዎች አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው ከመድረክ ማጠቃለያ ተሰጦ ፕሮግራሙ የተጠናቀቀ መሆኑን ከቢሮው ድህረ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በሙስና ሊመዘበር የነበረ ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ሀብት ማዳኑን የሰሜን ወሎ ዞን አስታወቀ
*****
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙሰና ትግል፣ የነገ ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ መልዕክት በሰሜን ወሎ ዞን አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በፓናል ውይይት ተከብሯል።
ዞኑ ሙስናንና ብልሹ አሠራሮችን በመታገል የመንግሥትን እና የሕዝብን ሃብት መታደጉን የሰሜን ወሎ ዞን የሥነምግባር መከታተያ ክፍል መኮንን ደሳለኝ ማዕረጉ ገልጸዋል።
በ2016 በጀት ዓመት በሙስና ክትትል እና ርምጃ ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን መቻሉን ገልፀው፥ በላሊበላ፣ ሀራ፣ መርሳ፣ መቄት እና ሌሎች የወረዳ ከተሞች ላይ ያለአግባብ ተላልፎ የነበረን 74 ሺህ 300 ካሬ መሬት ማስመለስ ተችሏል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ 529 የሙስና ጥቆማ ደርሰው 312 አሥተዳደራዊ ርምጃ መውሰዱንም አስረድተዋል። ለሕግ ከቀረቡት 114 ጉዳዮች ውስጥ 65 የሚሆኑት በመጣራት ላይ ናቸው ነው ያሉት።
ከሲቪል ሰርቪስ አኳያ ምልመላ፣ መረጣ እና ደረጃ ዕድገት ላይ ብልሹ አሠራር እንዳይኖር ክትትል እየተደረገ መኾኑንም ገልጸዋል።
ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እና ሌሎች ሰነዶች በአግባቡ አንዲፈተሹ የተቋማት ትብብር አስፈላጊ መኾኑም መጠቆሙን አሚኮ ዘግቧል።
የመልካም አሥተዳደር እና የሕዝብ የቅሬታ ምንጭ የኾነውን ሙስናን በመፀየፍ እና በመታገል የሁሉም ሴክተር ሠራተኞች ኀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ከ132 ሚሊየን ብር በላይ በታክስ ማጭበርበር የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከ132 ሚሊየን ብር በላይ በታክስ ማጭበርበርና መሰወር የተጠረጠሩ 3 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አብዱሰላም መሃመድ÷ሕግን ለማስከበር በተሰራው ሥራ በታክስ ማጭበርበርና መሰወር ወንጀል የተጠረጠሩ 3 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡
የታክስ ማጭበርበርና መሰወር ወንጀል መፈፀማቸው በኦዲት የተደረሰባቸው ግለሰቦች በወንጀል ምርመራ በኩል የወንጀል ምርመራ ተደርጐባቸው እንዲከሰሱ የተላለፈ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በታክስ አስተዳደር አዋጅ ሕግ መሰረት የተጭበረበረና ሀሰተኛ ግብይት የተፈጸመባቸው ሂሳባቸው ውድቅ ተደርጎ እንደገና እየተሰራ መሆኑንና በቀጣይ በሕግ የሚጠየቁበት ሂደት መኖሩ ተጠቁሟል፡፡
ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል 132 ሚሊየን 443 ሺህ 47 ብር በተቋሙና በመንግስት ገቢ ላይ ጉዳት ማድረሱንም የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ሀሰተኛ ሰነዶችን ለግለሰቦች ሲያከፋፍል የነበረ የጥበቃ ሠራተኛ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ግለሰቡ ህገ-ወጥ ተግባሩን የሚፈፅመው በሚያርፍበት የጥበቃ ቤት ውስጥ መሆኑ ታውቋል።
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ለቡ አካባቢ ነው። ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ለግለሰቦች እንደሚያሠራጭ መረጃ የደረሰው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጥቆማውን መነሻ በማድረግ ተጠርጣሪውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል።
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ የፍርድቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ወረዳ1 ለቡ አካባቢ ከሚገኝ እና ጥበቃ እንዲሠራ በተረከበው ጅምር ቤት ውስጥ ብርበራ በሚደርገበት ወቅት 93 ሀሰተኛ የቤት ካርታ፣ 13 ክብ ማህተም፣ 91ሀሰተኛ የቀበሌ መታወቂያዎች፣ 2 የኃላፊ ቲተር የተያዘ መሆኑን የንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
የህገ-ወጦች የወንጀል አፈፃፀም ስልት ምንም እንኳን ድብቅና የተወሳሰበ ቢሆንም ከህዝብ ዓይን የሚሰወር እንደሌለ ያስታወቀው ፖሊስ ሁለተኛ ተጠርጣሪን ለመያዝ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ገልጿል።
የህገ-ወጥ ሰነዶች መበራከት የሚያስከትለውን ሀገራዊ ጉዳት በመገንዘብ ሀሰተኛ ሰነዶችን የሚያዘጋጁ እና የሚጠቀሙ ግለሰቦችን በመለየት መረጃ በመስጠትና በህግ እንዲጠየቁ በማድረግ ረገድ ህብረተሰቡ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።

ሌብነት የልማት፣ የእኩልነትና የፈትሃዊነት ጠላት ነው - አቶ መልካሙ ጌትነት
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ 21ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ መልዕክት ከተለያዩ ተቋማት ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር አክብረዋል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መልካሙ ጌትነት መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ ሌብነት ከባህላችንም ሆነ ከእሴታችን ያፈነገጠ፣ በህግም ሆነ በፈጣሪ ያልተቀደ፣ በየትኛውም አሰራር ብንመዝነው ቀይ መስመር የሆነ ተግባር ነው ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት ሙስና በብሔር፣ በዘር፣ በሀይማኖትና በፖለቲካ ሰበብ በመደራጀት የዘረፋ ወንጀል እየተፈፀመ ነው ያሉት አቶ መልካሙ፥ ሌብነት የልማት፣ የእኩልነትና የፍትሃዊነት ጠላት በመሆኑ ሁሉም አካል ያለርህራሄ አምርሮ ሊታገለው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የአብክመ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ባለሙያ አቶ ዘላለም ንጉሴ የውይይት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፥ በሥነምግባር ግንባታና ግብረገብ ምንነት፣ በሥነምግባር ጥሰትና ብልሹ አሰራሮች ዙሪያ፣ የሙስና ወንጀል ውስብስብነት፣ የሥነምግባርና ሙስና መፍተሔዎችና ለውጦች፣ የመንግስት ሰራተኞችና የአመራሩ ሚና በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ አድርገው አቅርበዋል።
ተሳታፊዎችም በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተው፥ በአመራሮች ምላሽና ማብራሪያ መሰጠቱን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።