የሀገርን እድገት ለማስቀጠል በሥነምግባር የታነፀ ወጣት ማፍራት ወሳኝ መሆኑን የሀረሪ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአለም ፀረ-ሙስና ቀን በአገርዓቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ግዜ "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!'' በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አዳል ሙላቱ እንደገለፁት ሙስና የሀገር እድገትን ከሚያቀጭጩ ጉዳዮች ዋንኛው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች ሙስናን በመጠየፍና በመከላከል ለሀገር እድገት መስራት እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡
ኮሚሽነሩ አክለውም ሙስና የልማት ስራዎች እንዳይስፋፉ የሚያደርግ መሆኑን ገለፀው፥ በተለይም ስራ አጥነት እንዲስፋፋ አስተዋጽኦው የጎላ በመሆኑ ሁሉም ሊረባረብበት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የወጣቶች ህልም እውን እንዲሆን ለወጣቱ ግንዛቤ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሥነምግባር ያለው ወጣት በመፍጠር ወጣቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመከላከል ሁሉም በቅንጅት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የሀረሪ ክልል ወጣቶች ሊግ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢልያስ በበኩላቸው ወጣቱ ነገ የሚረከበውን ሀገር ዛሬ መገንባት እንደሚገባ ገልፀው፥ በሥነምግባር በመታነጽ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
ብልሹ አሰራርን ማስወገድና ሕግ እንዲከበር ማድረግ የወጣቶች ተሳትፎ የሚፈልግ ጉዳይ ስለሆ፥ በዚህ ረገድ ተሳትፎአቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ሙስናንና መልካም ሥነምግባርን የሚመለከት ሰነድ ቀርቦ ውይይት መደረጉን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ከ25 ቢሊየን ብር በላይ የግብር ታክስ ጉዳት ያደረሰው ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ
******************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከ25 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ የግብር ታክስ ጉዳት አድርሷል ተብሎ ክስ የቀረበበት በረከት አለኸኝ በ10 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ወሰነ።
የፍትህ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ተከሳሹ ላይ በነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በሀሰተኛ ሰነድ የባንክ ሒሳብ መክፈት፣ በህገወጥ መንገድ ንግድ ፍቃድ ማውጣትና ማደስ፣ የታክስ አዋጁን መተላለፍ፣ ሀሰተኛ ሰነዶችን መጠቀም፣ የገቢ ደረሰኞችን አትሞ ለተለያዩ ነጋዴዎች ማሰራጨት የሚል ተደራራቢ 7 ክሶች በዝርዝር ማቅረቡ ይታወሳል።
በተለይም በመስከረም 24 ቀን 2011 ዓ.ም እና በመስከረም 22 ቀን 2012 ዓ.ም ፍቃድ በማሳደስ የተመዘገበዉ በአስመጪነት ንግድ ስራ ዘርፍ ሆኖ ሳለ ምንም አይነት እቃ ከዉጭ ሀገር ሳያስገባ እና የሀገር ዉስጥ የዕቃ ግዥ ሳይፈጽም ከወሰደው የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ደረሰኞችን በማተም ለ339 ግብር ከፋዮች 1 ሺህ 663 ደረሰኞችን በማሰራጨት በ15 የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ 25 ቢሊየን 989 ሚሊየን 943 ሺህ 223 ብር ከ83 ሳንቲም ጉዳት ደርሷል በማለት ዐቃቤ ሕግ ካቀረባቸው ክሶች መካከል ጠቅሶ ነበር።
ዐቃቤ ህግ በክስ ዝርዝሩ ላይ 30 ቢሊየን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል በማለት ያቀረበው ዝርዝር ክስ ለተከሳሽ ከደረሰው በኋላ ግለሰቡ የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ህግ 13 የሰው ምስክሮችን እና 23 ገላጭና አስረጂ የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።
ፍርድ ቤቱ የተሰሙ የሰው ምስክሮችን ቃልና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ ብይን ሰጥቶም ነበር።
በዚህም ፍርድ ቤቱ በአንደኛና በሁለተኛ ክሶች ላይ ማለትም ሰለሞን ሙሉ ከውል በሚል የፈጠራ ስም በወጣ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያና ሀሰተኛ ውክልና መሰረት የንግድ ፍቃድ በማውጣትና በማሳደስ የተፈጸመ የወንጀል ድርጊት ተብሎ የቀረበውን ክስ በሚመለከት፣ ንግድ ፍቃድ መውጣቱንና መታደሱን እንጂ ሰለሞን ሙሉ ከውን በተባለው ሰው ወይም በተወካይ ንግድ ቢሮ ቀርቦ ንግድ ፍቃዱን ማን አወጣ ማን አሳደሰ የሚለው አሳማኝ ማረጋገጫ ያልቀረበ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አብራርቷል።
በተጨማሪም ከምስክሮች ቃል አሰጣጥ አንጻር በሰነዶች ማረጋጋጫ ተቋም አንድ ሰው በአካል ሳይቀርብ የጣት አሻራ ሳይሰጥና ሳይፈርም ውክልና እንደማይሰጥ መረዳቱን በመጥቀስ ሰለሞን ሙሉ ከውን በሚባል ሰው አሻራ ሰጥቶ ፈርሞ፣ በአካል ቀርቦ ውክልና የሰጠና ንግድ ፍቃድም ያወጣና ያሳደሰ መሆኑን ግምት መያዙን በማብራራት ከ1ኛ እና ከ2ኛ ክስ ነጻ ብሎታል።
ፍርድ ቤቱ 3ኛ እና 4ኛ ክስን በሚመለከት በ2010 እና በ2011 ዓ.ም ከውጭ ሀገር እቃ ሳያስገባና ምንም አይነት ሽያጭ ሳያከናውን ሀሰተኛ የተጭበረበሩ ሰነዶችን የዓመታዊ የግብር ሪፖርትን ለግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ማስገባቱ መረጋገጡን በመጥቀስ 3ኛ ክስ ከ4ኛ ክስ ጋር ተጠቃሎ ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቷል።
በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ለ339 ግብር ከፋዮች 1 ሺህ 663 የገቢ ደረሰኞችን አትሞ በማሰራጨት የንግድ ትርፍና የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በ15 የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ 25 ቢሊየን 989 ሚሊየን 943 ሺህ 223 ብር ከ83 ሳንቲም ጉዳት መድረሱን በማስረጃ መረጋገጡን ገልጾ፣ 5ኛ ክስን ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቷል።
6ኛ ክስን በሚመለከት ደግሞ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በተከራየው ሱቅ ውስጥ ህገወጥ እውቅና የሌለው የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያና ኮምፒዩተሮች በገቢዎች ሰራተኞች ተገኝቷል ተብሎ የቀረበው ክስን በሚመለከት የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያው ከጁፒተር ንግድ ስራዎች ድርጅት የተገዛና የተገጠመ መሆኑን መረጋገጡን ችሎቱ ጠቅሶ እውቅና የሌለው ህገወጥ መሳሪያ ተገኝቷል በሚል በዐቃቤ ሕግ የቀረበው ክስን በሚመለከት ግን ማስረጃ አለመቅረቡን ገልጾ፥ ተከሳሹን በ6ኛ ክስ ነጻ ነው ብሎታል።
7ኛ ክስን በሚመለከት የታክስ አስተዳደር አዋጅን በመተላለፍ ግብይት ሳይኖር ህገወጥ ደረሰኝ መጠቀም የሚለው ክስ ከ5ኛ ክስ ዝርዝር ጋር በተመሳሳይ በሀሳብ መደራረብ ያለው መሆኑን ጠቅሶ፤ ፍርድ ቤቱ 7ኛ ክስን በሚመለከት ነጻ በማለት ብይን ሰጥቷል።
ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያቀረበውን የመከላከያ ማስረጃ መርምሮና ከዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ጋር አመዛዝኖ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን ማረጋገጡን ጠቅሶ በሙሉ ጥፋተኛ መባሉን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ቅጣት አስተያየት መርምሮ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ተከሳሹ ያቀረበውን 5 የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በእርከን 29 መሰረት በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ3 ሚሊየን 8 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኗል።

በለውጡ ሂደት በፀረ-ሙስና ትግል የተገኘው ውጤት ዘላቂ እንዲሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
******************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በለውጡ ሂደት በፀረ-ሙስና ትግል የተገኘው ውጤት ዘላቂ እንዲሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 21ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ ከተማ አቀፍ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።
እለቱም ''ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገ ስብዕና ይገነባል!'' በሚል መሪ ሀሳብ የተከበረ ሲሆን፥ የመዲናዋ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ ወጣቶችና የተለያዩ ማህበራት ተሳትፈዋል።
በሀገር፣ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሙስና ያለበት ደረጃ ላይ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ሙስናን በመከላከሉ ረገድ የተዘረጉ አሰራሮች አወንታዊ ውጤት እያመጡ መሆኑን ተናግረዋል።
ለአብነትም ህዝቡን በማሳተፍ በተከናወኑ ተግባራት ሕግ የተላለፉ በርካታ ሰዎችን ተጠያቂ ማድረግ መቻሉን ጠቁመው፥ ፕሮጀክቶች ላይ ውጤታማ አፈጻጸም መታየቱ ከስራዎች ውጤቶች መካከል ነው ብለዋል።
በትምህርት እንዲሁም በሃይማኖት ተቋማት በኩል ሙስናን በተመለከተ ትውልድ የማነጹ ስራ ከፍተኛ ርብርብ ይጠይቃል ነው ያሉት።
የሙስና ወንጀልን መከላከል ለመንግስት አካል ብቻ የሚተው አይደለም ያሉት ከንቲባዋ፥ በለውጡ ሂደት በፀረ-ሙስና ትግል የተገኘው ውጤት ዘላቂ እንዲሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ፤ ኮሚሽኑ ተቋቁሞ ወደ ስራ ከገባበት 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሙስናን ለመከላከል የሚረዱ ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
የዜጎችን ግንዛቤ ማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰው፥ የተቋማትን የሙስና ተጋላጭነት በተመለከተ ጥናቶች መካሄዳቸውን አስረድተዋል።
በጥናቱ መሰረት ከተቋማት ጋር ውይይት በማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ማመላከቱን ገልጸው፥ በዚህም ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል።
ኮሚሽኑ ሙስናን ለመከላከል የሚረዱ ህግና መመሪያዎች ከማውጣት ጀምሮ የተቋማት አቅም ግንባታ ስልጠናዎችም ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑን አብራርተዋል።
ከውይይት ተሳታፊዎች መካከል አቶ ንጉሴ ደግፌ፤ የሙስና ወንጀልን ከመሰረቱ ለመግታት የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
እኔ እንደ ዜጋ ሃላፊነቴን እውጣለሁ የሚለው አስተሳሰብ ሊጎለብት ይገባል ሲሉም ነው የገለጹት።
ሌላኛው ተሳታፊ ኑሪ መሀመድ፤ አገልግሎትን በሙስና ሳይሆን በህጋዊ መንገድ ብቻ ማግኘት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ለዜጎች የማስገንዘቡ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በከተማ ደረጃ በፀረ-ሙስና ትግሉ እስከ ብሎክ ድረስ በመወረድ የዜጎችን ግንዛቤ የማስፋቱ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
አባገዳ ታከለ ጨመዳ በበኩላቸው በመዲናዋ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎች ስኬት የሚያበረታቱ መሆናቸውን አንስተው፥ በስኬት ሊቀጥሉ የሚችሉት ሙስናን መከላከል ሲቻል በመሆኑ ሁላችንም ወንጀሉን መከላከልና መታገል ይጠበቅብናል ብለዋል።
በበዓሉ አከባበር ላይ ኮሚሽኑ ለሚያከናውናቸው የፀረ-ሙስና ትግል አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና መሰጠቱን ኢዜአ ዘግቧል።

የሀሰት የወንጀል ምርመራ መዝገብ አደራጅተው ከባለሃብት ገንዘብ ተቀብለዋል የተባሉ ፖሊሶች ተከሰሱ
******************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሀሰተኛ የወንጀል ምርመራ መዝገብ በማደራጀት አንድን ባለሃብት በማስፈራራት ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ተቀብለዋል የተባሉ አራት በአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እና ሁለት ግለሰቦች ላይ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ።
ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
በፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ክስ ያቀረበባቸው ተከሳሾች 1ኛ በግል ስራ የሚተዳደረው መኩሪያ ማሞ ወይም (መስፍን ማሞ)፣ 2ኛ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የቂሊንጦ ፖሊስ ጣቢያ የክትትል ቲም ሀላፊ ኢንስፔክተር ዘለቀ ጥላሁን፣ 3ኛ በፖሊስ ጣቢያው የወንጀል መርማሪ ረዳት ኢንስፔክተር ዘውዴ አሰግደው፣ 4ኛ በፖሊስ ጣቢያው የወንጀል መርማሪ ዋ/ሳጅን መለሰ ማርቆስ፣ 5ኛ በፖሊስ ጣቢያው የክትትል አባል ምክትል/ሳጅን አጅቦ ተፈሪ እና 6ኛ በግል ስራ የሚተዳደረው ተገኔ ሀ/ማርያም ወልዴ ናቸው።
ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ)፣ አንቀጽ 33 እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና ንዑስ ቁጥር (2) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ጠቅሶ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።
በዚህም ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተከሳሾች የመንግስት ስራ ላይ በመስራት ላይ እያሉ ከ1ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች ጋር በመመሳጠር የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም በሌላ ሰው ጥቅም ላይ ጉዳት እንዲደርስ ለማድረግ በማሰብ የግል ተበዳይ የሆነው ባለሃብት ግለሰብ ላይ 1ኛ ተከሳሽ ሀሰተኛ የወንጀል ጥቆማ አቅራቢ ሆኖ ፖሊስ ጣቢያ ቀርቦ ጥቆማ ያቀረበ በማስመሰል ከ2ኛ እስከ 5ኛ የተጠቀሱ ተከሳሾች ከህጋዊ አሰራር ውጭ የምርመራ መዝገብ እንዲደራጅ አድርገው እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል
በዚህም ግለሰቡን አስረው “የወንጀል ምርመራው እንዲቋረጥልህ ገንዘብ መክፈል አለብህ” በማለት አስፈራርተው የግል ተበዳዩ ለጊዜው ባልተያዘ ምስጋና ዓለሙ በተባለ ግለሰብ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ የሂሳብ ቁጥር በነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም 180 ሺህ ብር፣ በመስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም 300 ሺህ ብር ገቢ እንዲያደርግላቸው ማስገደዳቸው በክሱ ዝርዝር ላይ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም ለጊዜው ባልተያዘ ለማ ባጃ በተባለ ግለሰብ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ ሂሳብ በመስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም 200 ሺህ ብር ገቢ ያስደረጉ በመሆኑን በክሱ ዝርዝር ላይ የተገለጸ ሲሆን፤ በጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ደግሞ በ3ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች አማካኝ የግል ተበዳዩን ከህግ አግባብ ውጭ በጣቢያው አስረው ካቆዩ በኋላ በ4ኛ ተከሳሽ ስም ከአዋሽ ባንክ በተከፈተ ሂሳብ 200 ሺህ ገቢ ያስደረጉ መሆኑ በክሱ መገለፁን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
በ6ኛ ተከሳሽ ስም ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ 300 ሺህ ብር ገቢ ካስደረጉ በኋላ ከዚሁ ገንዘብ ላይ በ4ኛ ተከሳሽ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ 200 ሺህ ብር ማስተላለፋቸው ተጠቅሷል።
ከዚሁ ገንዘብ ላይ ደግሞ ለ3ኛ ተከሳሽ እና ለ2ኛ ተከሳሾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳባቸው ለእያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር የተላለፈላቸው መሆኑ በክሱ ተዘርዝሯል።
ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱ የሚያስገኘውን አጠቃላይ ውጤት በመቀበል በሀሰተኛ የምርመራ የወንጀል መዝገብ በማደራጀት ግለሰቡን ከህግ ውጪ በማሰር በአጠቃላይ ከግል ተበዳዩ 1 ሚሊዮን 180 ሺህ ብር በመቀበል ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ መሆኑ ተጠቅሶ በልዩ እና ዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል በመፈጸም ክስ ቀርቦባቸዋል።
ዐቃቤ ሕግ ከክሱ ጋር የሰውና የሰነድ ማስረጃ ዝርዝር አያይዞ ያቀረበ ሲሆን ተከሳሾቹ ችሎት ቀርበው የክሱ ዝርዝር እንዲደርሳቸው ከተደረገ በኋላ የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅ ፍርድ ቤቱ ለታህሳስ 4 ቀን 2017 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።